የምሁር መሃይም – ተባይ አላዋቂ፤
የመሃይም ኩፍስ – አስመሳይ አዋቂ፤
የጅብ ባለ ጊዜ – ታፋ መራጭ ከሽንጥ፤
ያንበሳ ልክስክስ – ልፋጭ የሚያላምጥ
የቁራ ዕርግብ መሳይ – ሠላምን አብሳሪ፤
የፈረስ አዝጋሚ – የግመል ሰጋሪ፤
ንጹህ ሰው ታሳሪ – በፈጠራ ወንጀል፤
ፍርደ ገምድል ዳኛ – ፈራጅ በቂም በቀል፤
የባዕድ ባለቤት – የነባር ባይተዋር፤
ሥልጡን ሥራ ፈቶ – ሞያ ቢስ ሲገብር፤
ልማድ ሆኖ ቀረ – አቀርቅሮ መኖር፤
በተወሇድንባት በጦብያ ምድር :: (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply