ሰዎችን እንደ እህል በዘር ጆንያ እየሠፈረ በፈለገበት ሣጥን ውስጥ ማስገባት ዓላማው የሆነው የትግራይ ሕዝብ ነጻአውጪ ግምባር (ህወሃት)፤ በኦሮሞ ተቃውሞ #oromoprotest እና በአማራ ተጋድሎ #amhararesistance የተነሳው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ዕንቅልፍ ስለነሳው በተለይም ደግሞ የሁለቱ በኅብረት መቆም ኅልውናው ላይ አደጋ ስለጣለበት ሶማሊና አፋር ክልል መንጎዳጎድ ጀምሯል፡፡ ለኢትዮጵያ ቅንጣት ታህል ደንታ የሌለው ህወሃት የኦጋዴንን ሕዝብ እንዴት እንደፈጀ፣ ሴቶችን (ህጻናትንና ወንዶች ልጆችን ጨምሮ) እንደደፈረ፣ ለመከራና ለስቃይ እንደዳረገ የተረሳ መስሎት ሰሞኑን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ቅኝቱንም ሆነ ዜማውን የሶማሊ አድርጎታል፡፡ የህወሃትን ግፍ እንኳንስ የክልሉ ነዋሪዎች ሊረሱት ስዊድናውያኑ ማርቲን ሺብዬና ዩሃን ፐርሸን እስከ ሞት የሚረሱት አይደለም፡፡ “ዝም … [Read more...] about “ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”
Socio-Political
ማኅበራዊ-ሽከታ
የኮንትራት ሰራተኛዋ ኢትዮጵያዊት መጨረሻ!
* "አሰቃዩኝ" ስትል ፍልቅልቋን የ 6 ዓመት ብላቴና ለሚስን ቀጠፈቻት * ገዳይ ኢትዮጵያዊት ትናንት በሞት ተቀጣች * ዘምዘምም ለሚስም ልብ ይሰብራሉ ሁሉም ልብ ይሰብራል ይህን ሁለት ቀን ተረብሻለሁ፣ ምክንያቴ ብዙ ነው፣ ከምንም በላይ ከሪያድ የደረሰኝ መልዕክት ህመም ሆኖኛል ሰው ልምጣ ሲል እሷ "የመጨረሻ ቀናቶቸን የወላጆቸን አይን ሀገሬን ልይ እርዱኝ! ወደ ሀገሬ እንድገባ እርዱኝ!" የምትለው ታማሚ የኮንትራት ሰራተኛ እህት መልዕክት ጨካኙን ሰው ሆዴን አባባው። ማምሻውን ያነኑ ቪዲዮና ድምጽ ሳስተካክል ሌላ መረጃ እዚያው ሪያድ ደረሰኝና ቅስሜ ሰብር ብሎ አመሸ ... ኢትዮጵያዊቷ ሌላ የቤት ሰራተኛ በሞት መቀጣቷን ሰማሁ! እናም ወደ መረጃው አቀናሁ ... ድርጊቱ ሲፈጸምና መረጃው ሲናኝ ተከታትዬ መረጃ አቅርቤበት ነበርና ያንኑ ጊዜ እያስታዎስኩ የፍርድ ውሳኔውን ዜና ገለባብጨ … [Read more...] about የኮንትራት ሰራተኛዋ ኢትዮጵያዊት መጨረሻ!
መለኮታዊ ጥያቄ
"ኤርምያስ ሆይ ምን ታያለህ" (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 1፡11)፡፡ እ.አ.አ 1519 ቤተሰቦች ልጆቻቸውን አሥርቱን ትእዛዛትና (አቡነ ዘሰማያት) በጥልቀት እንዲያጠኑ በማስተማራቸው (በርካታ ክርስቲያኖች በአውሮጳ) በእሳት ተቃጥለው ተገድለዋል፡፡ እ.አ.አ በ1536 ቲንደል የሚባል የእግዚአብሔር ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ከላቲን ወደ እንግሊዘኛ በመተርጎሙ በእንጨት ላይ ታስሮ በእሳት ተቃጥሎ ተገድሎአል፡፡ ጆን ዊኪሊፍ መጽሐፍ ቅዱስን ከላቲን በመተርጎሙ ተወግዞአል፤ ከሞተ ከ44 ዓመት በኋላ አጥንቱ ወጥቶ እንዲቃጠል ተድርጎአል፡፡ እንዲህ ዓይነት እኩይ ድርጊት እንዲከናወን ያደረጉት የቤተ ክርስቲያን ጳጳሳትና ጨካኝ የሆኑ በዘመኑ የነበሩ የፖለቲካ ሰዎች አማካኝነት እንደሆነ ታሪክ ምስክር ነው፡፡ ከላይ የተመለከትነው እግዚአብሔር ነቢዩ ኤርምያስን የጠየቀበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል … [Read more...] about መለኮታዊ ጥያቄ
“ችግር የሚፈጠር በመሪ እንጂ በተመሪ አይደለም”
የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ አብርሐም ታሪክ ሰሩ። ከፋሽስት ወያኔ ነፍሰ በላዎች ፊት ለፊት እውነትን ተጋፍጠዋል። ጳጳሱ የደመራ በዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር ህዝባዊ ብሶቱን አስተጋብተዋል። እንዲህም አሉ... "ችግር የሚፈጠር በመሪ እንጅ በተመሪ አይደለም፤ የህዝቡ ጥያቄ መመለስ አለበት፤ ወታደር ከዚህ በኋላ የሰላምን ምላጭ እንጅ የመሳሪያን ምላጭ መሳብህን አቁም፤ በየሀገሩ በስደት ያለው ወገናችን መመለስ አለበት፤ እኛ አባቶች የምናገረውን በተገቢው መልኩ ለህዝብ የማታቀርቡ የመንግስት ሚድያ ካላስተካከላችሁ ከዚህ በኋላ አደባባዩ አትገቡም፤ ያለ በደላቸው የታሰሩት ወንድሞቻችን መፈታት አለባቸው፤ ጠላትን እንዳላንበረከኩ አባቶቻችን፤ ዛሬ ለምን እርስ በእርስ ተከፋፈልን? መንግስት የተሸከምነው መሳሪያ ከክርስቶስ መስቀል አይበልጥም፤ ወታደሮችና ድንበር ጠባቂዎች ስለ እናንተ … [Read more...] about “ችግር የሚፈጠር በመሪ እንጂ በተመሪ አይደለም”
ግፍና ጎርፍ
ሰሚ ካጡ የሶማሌ ተረቶች አንዱ እንዲህ ይላል፡፡ አንድ ሰው የጠፋች የአካባቢውን ግመል ፍለጋ ጫካ ይገባል፡፡ ከብዙ መከራ በኋላ ያቺን ግመል አግኝቶ ከተማ ገባና ግመሏን ለባለቤቱ ሳይመልስ ሐሳቡን ቀይሮ ራሱ ያልባትና ይጋልባት ጀመር፡፡ ግመሏን ከአውሬ ለማዳን ጫካ ገብቶ የነበረው ሰውዬ እርሱ ራሱ ግመሏን መውሰዱ ብዙዎችን አስገረማቸው፡፡ ትንሽ ቆየና ከዚያች ከአንዷ ግመል ወተት እያለበ በግመሏ ላይ ተቀምጦ እየዞረ ለአካባቢው ሰው ወተት መሸጥ ጀመረ፡፡ ነገር ግን የግመሏ ወተት በአንድ ጊዜ ሀብታም ሊያደርገው አልቻለምና ሌላ ነገር አሰበ፡፡ በወተቱ ውስጥ ውኃ እየጨመረ ቀላቅሎ መሸጥ፡፡ ‹‹ሰውም ምነው የሰውየው አመሉም ወተቱም ተቀየረሳ›› እያለ ዝም ብሎ ይገዛ ጀመር፡፡ (ይገዛ የሚለው ቃል ጠብቆ እንዳይነበብ አሳስባለሁ) ሰውዬውም በግመል ወተቱ ላይ ውኃን እያበዛው፤ የግመሉም ቁጥር … [Read more...] about ግፍና ጎርፍ
የተወጠረችው አዲስ አበባ ታስፈራለች – ብሶት ይንፈቀፈቅባታል!!
እድሜው አርባዎቹን ስለመሻገሩ ገጹ ይናገራል። በተፈጥሮ ያለው እርጋታ አዲስ አበባ ካጋጠመው ትንግርት ጋር ተዳምሮ አፍዞታል። ፊቱን ፈገግ የሚያደርገው ስለ አዲስ አበባ አራዳዎች ሲናገር በቻ ነው። ጨዋታውን የጀመረው በጫማ አሳማሪዎች ነበር። ጫማ አሳማሪዎች ደረጀ ወጥቶላቸዋል። “የታቀፉና ያልታቀፉ” ሁሉንም ገጠመኞቹን ሲያስረዳ “አዲስ አበባ እንደ ወበቅ ነች” ይላል። የወበቅ ጭንቀት የሚለቀው በደንብ ሲዘንብና አየሩን አፍኖ የያዘው ደመና ሲገፈፍ ነው። ወበቅ ለሱ በሽታ ነው። ነዋሪነቱ አውሮጳ ሲሆን አዲስ አበባ የከረመበት ምክንያት ቤት ቢጤ ስላለው እሱኑ ሸጦ ለአንዴና ላልተወሰነ ጊዜ የሚወዳትን “ወበቃም” ከተማ ለመለየት ነው። ቦሌ ፒኮክ ቁጭ ብለን ስናውጋ ቀድሞ አደራ ያለኝ ፊቱ ማስታወሻ አውጥቼ የሚነግረኝን እንዳልጽፍ ነው። ለወትሮም ቢሆን ስለማላደረርገው ተስማማሁና አወጋን። … [Read more...] about የተወጠረችው አዲስ አበባ ታስፈራለች – ብሶት ይንፈቀፈቅባታል!!
“ህወሃቶች – ምንድነው የሚፈልጉት? ደም አይጠግቡም?”
“ሊገባኝ አልቻለም” ሲሉ ይጀምራሉ። በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የጅምላ ጭፍጨፋ ረፍት እንደነሳቸው ያስረዳሉ። አገሪቱ በደም እየታጠበችና በቂም እየነፈረች ጥቅም ህሊናና አእምሯቸውን ስለዘጋባቸው “ዜጎች” ማሰብ ለበሽታ አጋልጧቸዋል፤ ያነባሉ። ግራ በመጋባት “ህወሃቶች - ምንድነው የሚፈልጉት? ደም አይጠግቡም?” በማለት ይጠይቁና አጭሩን መልዕክት “ከርስ እንደዚህ እውር ያደርጋል?” የሚል ጥያቄ ጠይቀው ይሰናበታሉ። “በጥልቅ ስንታደስ የጥፋት ሃይሎች ጊዚያዊ መነቃቃት ይከስማል” ሲል የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት በህዳሴ ጋዜጣ ላይ ያሰፈረውን አመልክተው፣ “በፍጥነት ወደ ጥልቁ ብትገቡ ለአገሪቱ ዘላለማዊ መነቃቃት ይሆን ነበር” የሚል ርዕስ በመስጠት ከላይ በመግቢያ የተገለጸውን የጠቆሙት የሃዋሳ ነዋሪ መሆናቸውን የጠቆሙ ደንበኛችን ናቸው። ብዙዎች እንደሚስማሙት ራሱን … [Read more...] about “ህወሃቶች – ምንድነው የሚፈልጉት? ደም አይጠግቡም?”
የሰማዕታት ዝርዝር በከፊል
Partial list of Oromos that have been killed as a result of Excessive force by Ethiopian Government (TPLF's regime) armed forces during Peaceful demonstration on August 6,2016, Oromia, Ethiopia. (updated 4 September 2016) Nr Name Sex Age Zone Locality Killed by 1 Abbuu Muummee M 17 Arsii Ticho Agazi 2 Abdallaa Mohammed M - East Harageh Qobo Agazi 3 Abda Jiloo M 24 West Arsii Asasa Agazi 4 Abdaa Hasanoo M 31 West … [Read more...] about የሰማዕታት ዝርዝር በከፊል
“የዛፍ ላይ እንቅልፍ!” ስደት
የመረጃ መረቡ ከሃገር ቤት በሚሰማው የህዝብ እንቢተኝነት አመጽ ተጨናንቆ እኛንም አጨናንቆን ከርሟል። በዚህ የመረጃ ቅብብሎሽ መካከል ወደ ምሥራቅ ሳውዲ ለስራ ጉዳይ አቅንቸ ነበር። ርያድ፤ ደማም፡ ጁቤል፤ ሃፍር አልበጠንን ለአንድ ሳምንት ሳካልል ከሃገር ቤት ከሚሰማው መረጃ እኩል በሳውዲ ዙሪያ ያሉ በርካታ ወገኖቸ የተለያዩ መረጃዎች በስልክ አድርሰውኛል። በተዘዋዎርኩባቸው ከተሞች ያገኘኋቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቸም የሚያመውን የስደት ህመም ሳይደምቁ አጫውተውኛል። ሁሉም አሳሳቢ ናቸው፣ ሁሉም ቢያንስ መፍትሔ ይሻሉና ዝም የማይባለውን የወገንን ድረሱልኝ ጥሪ አሳውቃችኋላሁ! ዛሬም በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች የተበተኑ ችግር የገጠማቸው ዜጎች መብት አስከባሪ አጥተው ሲንከራተቱ፣ ሲንገላቱና የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ ነው! በአንጻሩ አዲስ ኮንትራት ውል ከሳውዲ አረቢያ ጋር ለመስማማት ደጋግሞ … [Read more...] about “የዛፍ ላይ እንቅልፍ!” ስደት
የበጎው ሰው፣ የጎልማሳው ህልፈት…!
በያዝነው ሳምንት ... በአብዛኛው የሀበሻ መገናኛ መንደር፣ በማህበራዊ ድህረ ገጽ ዋንኛ መድረክ በ Facebook መስኮት አንድ መሪር መርዶ ተሰምቷል! የትሁት ፣ አስተዋይና አርቆ አስተዋዩ በጎ ሰው ፣ የጎልማሳው የአቡኬ አሌክስ ህልፈት!!! የአቡኬ አሌክስ በድንገት መለየት ጥልቅ ሀዘናን ሁላችንም አንገብግቦናል! "ከሞቱ አሟሟቱ " እንዲሉ አቡኬ ባንድ ጀንበር ታይቶ በርቶ ፣ ባንዱ ጀንበር ሳይታሰብ ጠፍቶብናል! እናም በቅርብ ከሚያውቁት ፣ ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ ጓደኞች እኩል በስራው በዝና የምናውቀው በሀዘኑ አዝነን ከፍቶናል! የጎልማሳው በጎ ሰው አቡኬ አሌክስ መረጃዎች የቅርብ ተከታታይ የሆነችው ባለቤቴ በህልፈቱ ጥልቅ ሀዘን የተሰማቸው መካከል አንዷ ናት ፣ ስለአቡኬ ስትገልጽ እንዲህ ብላኛለች " አቡኬ ብሩህ አዕምሮ የነበረው ፣ ኢትዮጵያውያንን በዘር በሐይማኖታዊ ሳይለየን … [Read more...] about የበጎው ሰው፣ የጎልማሳው ህልፈት…!

![“ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”](https://www.goolgule.com/wp-content/uploads/2016/06/Slide15-e1466825122855-300x188.jpg)








