የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ አብርሐም ታሪክ ሰሩ። ከፋሽስት ወያኔ ነፍሰ በላዎች ፊት ለፊት እውነትን ተጋፍጠዋል። ጳጳሱ የደመራ በዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር ህዝባዊ ብሶቱን አስተጋብተዋል። እንዲህም አሉ…
“ችግር የሚፈጠር በመሪ እንጅ በተመሪ አይደለም፤ የህዝቡ ጥያቄ መመለስ አለበት፤ ወታደር ከዚህ በኋላ የሰላምን ምላጭ እንጅ የመሳሪያን ምላጭ መሳብህን አቁም፤ በየሀገሩ በስደት ያለው ወገናችን መመለስ አለበት፤ እኛ አባቶች የምናገረውን በተገቢው መልኩ ለህዝብ የማታቀርቡ የመንግስት ሚድያ ካላስተካከላችሁ ከዚህ በኋላ አደባባዩ አትገቡም፤ ያለ በደላቸው የታሰሩት ወንድሞቻችን መፈታት አለባቸው፤ ጠላትን እንዳላንበረከኩ አባቶቻችን፤ ዛሬ ለምን እርስ በእርስ ተከፋፈልን? መንግስት የተሸከምነው መሳሪያ ከክርስቶስ መስቀል አይበልጥም፤ ወታደሮችና ድንበር ጠባቂዎች ስለ እናንተ ቤተክርስቲያን ስለምትጸልዩ የሷ ልጆች ናችሁና ደም አታፍሱ” ብለዋል። ህዝብ ክርስቲያኑ አቡነ አብርሀም ይህንን ንግግር ሲያደርጉ በእልልታና በጭብጨባ ድጋፉን ገልጧል።
ባህር ዳር ላይ «የተከበረው» የደመራ በዓል ጸሎትና ሀዘን ታስቦ ውሏል። የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንቱ ወረብ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ የማኅበረ ቅዱሳንና የቅዱስ ያሬድ የበገና ተማሪዎችና መዘምራን ደግሞ ወቅቱን የተመለከተ መዝሙሮችን አቅርበዋል። በገና ደርዳሪውም፦
“ማዕበሉን አይቶ ልባችን አይፍራ፣
ሁሉን ቻዩ ጌታ አለ ከኛ ጋራ” ብሏል።
በመጨረሻም በየቤተክርስቲያኑ ይደረግ የነበረው የምህላና ጸሎት በጋራ መሀል ባህር ዳር ከተማ መስቀል አደባባይ ተስተጋብቷል። አባታችንን አቡነ አብርሀምን፣ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንቶቻችንን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን፣ የማኅበረ ቅዱሳንና የቅዱስ ያሬድ የበገና ተማሪዎችና መዘምራን ቃለ ህይወት ያሰማልን። ረጅም እድሜ ይስጥልን።
ሁሉም መርሀ ግብር ካለቀ በኋላ አቡነ አብርሐም መጀመሪያ «ሕዝቡ ወደቤቱ ሳይገባ እኔ አልንቀሳቀስም» በማለታቸው እዚያው መስቀል አደባባይ ከቀሩ በኋላ፤ በመጨረሻ ላይ የአማራ ፖሊስ ዩኒፎርም በለበሱ የትግራይ ወታደሮች ከታች በሚታየው መልኩ በፖሊስ መኪኖች ታጅበው እሳቸው ግን በእግራቸው ወደ ባዕታቸው ተመልሰዋል።
የአቡነ አብርሃምን ንግግር ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ
(ምንጭ: Achamyeleh Tamiru)
Leave a Reply