• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

መለኮታዊ ጥያቄ

September 26, 2016 11:34 pm by Editor Leave a Comment

“ኤርምያስ ሆይ ምን ታያለህ” (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 1፡11)፡፡

እ.አ.አ 1519 ቤተሰቦች ልጆቻቸውን አሥርቱን ትእዛዛትና (አቡነ ዘሰማያት) በጥልቀት እንዲያጠኑ በማስተማራቸው (በርካታ ክርስቲያኖች በአውሮጳ) በእሳት ተቃጥለው ተገድለዋል፡፡ እ.አ.አ በ1536 ቲንደል የሚባል የእግዚአብሔር ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ከላቲን ወደ እንግሊዘኛ በመተርጎሙ በእንጨት ላይ ታስሮ በእሳት ተቃጥሎ ተገድሎአል፡፡ ጆን ዊኪሊፍ መጽሐፍ ቅዱስን ከላቲን በመተርጎሙ ተወግዞአል፤ ከሞተ ከ44 ዓመት በኋላ አጥንቱ ወጥቶ እንዲቃጠል ተድርጎአል፡፡

እንዲህ ዓይነት እኩይ ድርጊት እንዲከናወን ያደረጉት የቤተ ክርስቲያን ጳጳሳትና ጨካኝ የሆኑ በዘመኑ የነበሩ የፖለቲካ ሰዎች አማካኝነት እንደሆነ ታሪክ ምስክር ነው፡፡

ከላይ የተመለከትነው እግዚአብሔር ነቢዩ ኤርምያስን የጠየቀበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው፡፡

አስተውሉ! ምንጊዜም፣ እግዚአብሔር ከመጠየቅ ወደ ኋላ ብሎ አያውቅም፡፡

ለመሆኑ እግዚአብሔር ለምን ይጠይቃል? የሰዎችን የልብ ዝንባሌ ለማወቅ ፈልጎ ይጠይቃል፡፡ ሆኖም እግዚአብሔር የሚጠይቀው ነገሩን ስለማያውቅ ሳይሆን መለኮታዊ መሥፈርትን ለማሳወቅ ይጠይቃል፡፡

እግዚአብሔር አዳምን “ወዴት ነህ? (ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 3፡8) ሲል ጠይቆት ነበር፡፡ ቀደም ሲል እንደተመለከትነው ነቢዩ ኤርምያስን፣ “ምን ታያለህ? (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 1፡11) ሲል ጠይቆታል፡፡ ሙሴን ደግሞ፣ “በእጅህ ያለው ምንድነው? (ኦሪት ዘጸአት ምዕራፍ 4፡2) ሲል ጠይቆታል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ሰዎች ስለ እርሱ ምን እንደሚሉ ጠይቆአቸው ነበር (የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 16፡13)፡፡

እግዚአብሔር ዛሬም ይጠይቃል!

እግዚአብሔር ለምን ይጠይቃል? ፍርድ ሲዛባ፣ አንዱ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ሲነሳ፣ ብርቱ ነኝ የሚል ደካማውን ሲገዛ፣ ጥቂቱ ብዙሃኑን ሲገዛ፣ በመንግሥታት መካከል ያለው ጥላቻ፣ ሽኩቻ፣ ይበልጥ እየሰፋና እያደገ ሲሄድ፣ ፍትሕ ጠፍቶ ማህበረሰብ ሲንከራተት፣ ሽብርተኝት ዓለምን ሲያናውጥ፣ ዓለም በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋ ስትጨነቅ፣ ዜጎች ምግብና መጠለያ አጥተው ሲንከራተቱ፣ መልካም አስተዳደር ሲጠፋ፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት በሙስና ሲጨማለቁ፣ እርግማን ከመጠን በላይ በዝቶ፣ የአየር መዛባት፣ በድርቅ ምክንያት በርካታዎች በረሃብ አለንጋ ሲረግፉ፣ ሲገረፉ፣ የአገዛዝ ቀንበር በሰዎች ላይ ሲከብድ፣ ስደት ከመቼውም ጊዜ በላይ በዝቶ፣ ትውልድ ሲጠፋ፣ የሰዎች ደም በየቦታው በከንቱ ሲፈስ፣ ለጋ ወጣቶች ከወላጆቻቸው ዘንድ ተሰድደው የዓሳ ቀለብ ሲሆኑ፣ በክፉ ሰዎች እጅ ወድቀው አንገታቸው ሲቀላ፣ በጥይት ተደብድበው ሲሞቱ፣ መጠለያና መጠጊያ አጥተው ሲንከራተቱ፣ በባዕድ አገራት በወህኒ ሲጣሉ፣ አገርና ወገን እንደሌላቸው ተቆጥረው በዓለም ላይ ተበትነው ሲንከራተቱ፣ የክፉ ሰዎች መጫወቻ፣ መሰደቢያ፣ መዘበቻና መዘባበቻ ሲሆኑ፣ጨካኝና አምባገነን መሪዎች ሕዝቦቻቸውን ሲያስጨንቁ፣ ሲያንገላቱ፣ ሲያስሩ፣ የዜግነት መብት ሲያሳጡ፣ አሁንም፣ ሁሌም እግዚአብሔር ይጠይቃል!!

እግዚአብሔር ዛሬም እንደ ቀድሞ ይጠይቃል!

“ምን ታያለህ”!!?

እውነቱን ለመናገር ጥያቄው ዛሬ ለእኔ ቢቀርብ፣ ምላሼ የሚከተለውን ይመስላል፡፡

እኔ የማየውና የምሰማው፣ የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የኮንሶ፣ የጋምቤላ፣ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ደም በከንቱ በየቦታው ሲፈስ፣ ወጣቶች ከየመንገዱና ከየቤቱ ታፍሰው በየወህኒ ቤት ሲታጎሩ፣ የጎንደርና የባሕር ዳር ልጆች ደም ሲፈስ፣ የወለጋ ልጆች ደም ሲፈስ፣ ልጆች ወላጅ አልባ ሲሆኑ፣ ወላጆች ጧሪ አጥተው ሲጨነቁ፣ በልቅሶ ብዛት ዓይናቸው ደክሞ ከሰውነት ተራ ወጥተው ሲጨነቁ፣ ባሕር ዳር ላይ የፈሰሰው የጨቅላ ወጣቶች ደም፣ በአወዳይ ላይ የፈሰሰው ንጹሕ ደም፤ በደምቢዶሎ የፈሰሰው የወጣቶች ደም፣ በነቀምቴ የፈሰሰው ንጹሕ ደም፣ ያለ ምንም ወንጀላቸው ሞት የተፈረደባቸው፣ በጨካኙ የወያኔ መንግሥት ዛቻ፣ ማስፈራሪያና ክትትል ምክንያት አገር የለቀቁ፣ ለስደት የተዳረጉ፣ ሰዎች ከሞቀ ቤታቸው ተፈናቅለው በመንከራተት ላይ የሚገኙትን ዜጎች፣ አጋዚ ተብሎ የሚጠራው የወያኔ ቀኝ እጅ ቅጥረኛና ነፍሰ ገዳይ ቡድን ብዙዎችን ሲገድል፣ ሲያፈናቅል፣ ሲያሳድድ …. አያለሁ፤ እያየሁ ነው፡፡

እናንተስ ምን እያያችሁ ይሆን? ምን እየሰማችሁ ነው?

እግዚብሔር ዛሬም ይጠይቃል!

ነገር ግን ሕዝቦች ሆይ! ታላቅ ተስፋ አለን፡፡ እግዚአብሔር እንደ መዥገር በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተጣበቁትን ወያኔዎች እስከ ወዲያኛው ያራግፍልናል፤ ይበትንልናል፡፡ ወያኔ ከተወገደ በኋላ ሥጋት፣ ጥላቻ፣ መለያየት፣ መገፋፋት፣ በብሔረሰቦች መካከል ያለው ሽኩቻ፣ ልዩነት፣ ዘረኝነት፣ ብሔርተኝነት፣ ጎጠኝነት የማይኖርባት ኢትዮጵያ ትኖረናለች፡፡ ሕዝቦች በመቻቻል፣ በመፈቃቀድ፣ በመከባበር፣ ፍትሐዊ የሆነ የሀብት ክፍፍል ኖሮአቸው፣ በመተባበር ላይ የተመሠረተ አንዲት ኢትዮጵያ ትኖረናለች፡፡

እውነተኛ የሆነ ዲሞክራሲ፣ ቅጥረኛ ያልሆነ የምርጫ ኮሚሽንና ሕዝብን የሚፈራና የሚያከብር የአገር መሪ ይኖረናል፡፡ መልካም አስተዳደር የሰፈነበት፣ ሙስና የማይኖርበት፣ ጥቂቱ ብዙሃኑን የማይገዛበት ሥርዓት ይመጣል!

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እኩይ የሆኑ የኢትዮጵያ ጠላቶችን እስከ ወዲያኛው ሲያራግፋቸው ወያኔዎች ከተጠያቂነት ማምለጥ አይችሉም፡፡

የአቤል ደም ከምድር ወደ እግዚአብሔር እንደ ጮኸ ሁሉ፣ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የኮንሶ፣ የጋምቤላ፣ የሶማሌና የሌሎችም ብሔረሰቦች ደም ወደ እግዚአብሔር በመጮኽ ላይ ይገኛል፡፡ እግዚአብሔር ሆይ ፍረድልን ይላሉ፡፡ ሰው የሚዘራው ያንኑ ያጭዳል፡፡ ስለዚህ ወያኔዎች ሞት ዘርተዋል፤ ሞት ያጭዳሉ፡፡ ክፉ ዘርተዋል፤ ክፉ ያጭዳሉ፡፡ ንጹሐንን በወህኒ አጉረዋል፤ እነርሱም አንድ ቀን በወህኒ ይታጎራሉ፡፡

እግዚአብሔር ዛሬም፣ ነገም፣ ሁሌም፣ … ይጠይቃል!!

ደጉ ዘመን ከአዲስ አበባ – ኢትዮጵያ

E-mail: deguzemen@gmail.com

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions, Social Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am
  • የኤሊያስ መሠረትን ፌክ መረጃ ማን ያጋልጥ? February 19, 2025 06:00 pm
  • አዘርባጃን፡ የሻዕቢያን ሸምቀቆ ማጥበቂያ?! February 19, 2025 12:29 am
  • የአሜሪካ ድምፅ/ቪኦኤ ይዘጋ ተባለ  February 12, 2025 03:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule