“ሊገባኝ አልቻለም” ሲሉ ይጀምራሉ። በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የጅምላ ጭፍጨፋ ረፍት እንደነሳቸው ያስረዳሉ። አገሪቱ በደም እየታጠበችና በቂም እየነፈረች ጥቅም ህሊናና አእምሯቸውን ስለዘጋባቸው “ዜጎች” ማሰብ ለበሽታ አጋልጧቸዋል፤ ያነባሉ። ግራ በመጋባት “ህወሃቶች – ምንድነው የሚፈልጉት? ደም አይጠግቡም?” በማለት ይጠይቁና አጭሩን መልዕክት “ከርስ እንደዚህ እውር ያደርጋል?” የሚል ጥያቄ ጠይቀው ይሰናበታሉ።
“በጥልቅ ስንታደስ የጥፋት ሃይሎች ጊዚያዊ መነቃቃት ይከስማል” ሲል የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት በህዳሴ ጋዜጣ ላይ ያሰፈረውን አመልክተው፣ “በፍጥነት ወደ ጥልቁ ብትገቡ ለአገሪቱ ዘላለማዊ መነቃቃት ይሆን ነበር” የሚል ርዕስ በመስጠት ከላይ በመግቢያ የተገለጸውን የጠቆሙት የሃዋሳ ነዋሪ መሆናቸውን የጠቆሙ ደንበኛችን ናቸው።
ብዙዎች እንደሚስማሙት ራሱን “የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ” እያለ የሚጠራው ተገንጣዩ ቡድን በበላይነት በሚገዛት ኢትዮጵያ ያልተሰራ የግፍ አይነት የለም። ደም ከየአይነቱ በብሔር፣ በጾታ፣ በዕድሜ፣ ተግቷል፤ ፈሷል። ክፋቱና አረመኔነቱ ገሃድ የሚወጣበት ቀን በዙዎች በናፍቆት የሚጠበቁት ነው። የመገናኛ ዘዴዎችን ጠርቅሞ ዜጎችን በተወለዱበት ቀዬያቸው ድረስ ዘልቆ በመግባት በጅምላ እየጨፈጨፈ ያለውን ጨካኝ አገዛዝ አንዳንድ መገናኛዎች “መንግስት” እያሉ ፈጽሞ በማይገባው ስም ቢጠሩትም፣ ለዚያ ወግ የማይበቃ “ወሮ በላ፣ የሽብር ሁሉ ቁንጮ፣ የጭካኔ ማማ” መሆኑንን ዜጎች በብሶት እየገለጹት ነው። ዘወትር ደም ውስጥ የሚርመጠመጥና ከፍጥረት እስከ እርጅና ደም ቀለቡ እንደሆነ በግርምት የሚናገሩ ቁጥር አይገልጻቸውም።
ልጅዋን ገድለው፣ “የልጅሽ አስከሬን ላይ ተቀመጪ” በማለት መገረፏን የሰሙ፣ እጃቸው በሰነሰለት ታስሮ ማጎሪያ ቤት ያሉ ወገኖች በእሳት ሲቃጠሉ ለተመለከቱና ዜናውን ለተከታተሉ፣ “ሊያመለጡ ሲሉ ነው” በሚል ታፔላ በ“ህግ ከለላ” ስር ያሉ ወገኖች በጥይት ሲረሸኑ፣ … ነፍስ ያወቁ፣ አዛውንት እናትና አባቶች፣ ህጻናቶች በጥይት መደብደባቸው መሻሻል አሳይቶ አራስ ስትገደልና አራስ ልጇ በገዳዮች ሲወሰድ መስማት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ የሚገለጸው በከፍተኛ ምሬት ነው።
የግፉ ልክ መረን እየለቀቀ በሄደ ቁጥር፣ የንጹሃን ደም ሲግል፣ የንጹሃን ነፍስ ሙግት ሲያይል፣ ዋ!! ለናንተ ግፈኞች የሚሉ ሲበዙ፣ የብሄር ከፋፍለህ ግዛ ቁማር ሲነጥፍ፣ ትምክህት ቅጥ ሲያሳጣ፣ ጠብ መንጃ አንጎልን ሲዘጋ፣ ሁሉም ቀባሪ፣ ሁሉም አልቃሽ፣ ሁሉም ሃዘንተኛ፣ ሁሉም ጧሪ መከታውን ሲነጠቅ የሚፈሰው እምባና ሲቃ … ሁሉም ባንድ ተዳምሮ ወዴት ያመራ ይሆን? የሁሉም ኢትዮጵያዊ ስጋት ነው።
ኦሮሚያና አማራ ክልል ላይ የራሱን የሞግዚት አስተዳደር አፍርሶ ነፍስ እየበላ ያለው ህወሃት፣ ኦጋዴን፣ አፋር፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ደቡብ ክልል … መዋዕለ ሕጻናት፣ የመጀመሪያ ደረጃ ፣ ሁለተኛ ደረጃና ኮሌጅ ብሎም ዩኒቨርስቲ፣ ራሱ ስራአጥ አድርጎ የፈጠራቸውንና “ቦዘኔ” የሚላቸውን፣ … ሁሉንም አይነት ህዝብ በጅምላ ስለመጨፍጨፉና ስለመጨረሱ ደጋፊዎቹም ጭምር እንደማይክዱ የሚታወቅ ነው።
አሁን መገኛኛዎችን ጠርቅሞ አማራ ክልል እየተፈጸመ ያለው የጅምላ ጭፍጨፋ፣ የጅምላ እስርና ስቃይ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ባሳዘነበት ወቅት ሃርሞኒ ሆቴል ውስኪ እየተራጩ “እንቁጣጣሽን” ያሳለፉት ከሰው በታቾችና አሽከሮቻቸው ከታሪክና ከፍርድ እንደማያመልጡ ናቸው። በተለይም ጳግሜ 5 ቀን በኮንሶ ሶስት መንደሮች ሲጋዩ፣ ህዝብ መግቢያ አጥቶ ሲርበደብድ፣ ህጻናትና አዛውንቶች መግቢያ አጥተው ሲሸበሩ፣ ትዕዛዝ ሰጪዎቹ በአል ላይ ነበሩ። ፌሽታ ላይ ተጥደው ነበር። ሰው እንደጧፍ በተኛበት ሲነድ አስረሽ ምቺው ነበር።
በኮንሶ ህዝብ ላነሳው የራስን በራስ ማስተዳደር ጥያቄ፣ ምላሹ አስከፊና ህዝቡን ሙሉ በሙሉ ከምድረ ገጽ የማጥፋት እንደሆነ እየተነገረ ነው። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እንደሚሉት ጉዳዩ “ወረራ” ነበር። የሟቾችና የተጎጂዎችን ብዛትና የጉዳቱ መጠን ስለሚቀያየር አሃዙን በመተው ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ የላኩልንን ሙሉ ሃሳብ ከዚህ በታች ቀርቧል።
“እኔ እስከማውቀው ድረስ የመንግስት ኃላፊነት ህግን ማስከበር፣ ሰላምን ማስፈን እንዲሁም ግጭት ሲፈጠር እንደ ገለልተኛ ሆኖ ለየትኛውም ወገን ሳያዳላ የማረጋጋት ሥራን መስራት ነው። አሁን አሁን በኢትዮጵያ እየሆነ ያለው ግን ከዚህ የተቃረነ መሆኑ ባያጠያይቅም በኮንሶ ምድር ከጳጉሜ 5 ጀምሮ እስካሁኑ ደቂቃና ሰከንድ ድረስ እየሆነ ያለው ግን እጅግ የሚዘገንን ከአንድ መንግስት ቀርቶ በሀገር ጠላት ላይ እንኳን ለመፈፀም የሚከብድ የአንድን ብሔር ዘር ማጥፋትን ኢላማ ያደረገ ዘመቻ በፈደራል ፖሊስና በደቡብ ክልል ልዩ ሃይል ቅንጅት በኮንሶ ህዝብ ላይ እየተካሔደ ይገኛል።
“እንደሚታወቀው የኮንሶ ህዝብ ከሰገን ዞን ወጥቶ ራሱን በራስ ማስተዳደር ይችል ዘንድ ራሱን ችሎ በዞን ለመደራጀት ከዓመት በፊት ኮሚቴ አዋቅሮ ደረጃ በደረጃ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የኢህአዴግ እህት ድርጅቶችና ለውጭ ኤምባሲዎች ጭምር ማሳወቁ ይታወቃል።
“ይህ ጥያቄ ከዓመት በፊት ቀርቦለት የቃል መልስ ለመስጠት እንኳን ዓመት ሙሉ የፈጀበት የደቡብ ክልል መጀመሪያውኑ ጥያቄውን ተቀብሎ በህገ መንግስቱ መሰረት ከመመለስ ይልቅ ጥያቄውን በጉልበት እንደሚቀለብስ በተደጋጋሚ እየዛተ “ኮንሶ የሲኒ ውስጥ ማዕበል ነው፤ በአንድ ዘር ማጥፋት ይቻላል” ምናምን በማለት ለዓመታት ያቀደውን እቅድ አሁን ተግባር ላይ በማዋል ላይ ይገኛል።
“ዕቅዳቸውን ከግብ ለማድረስም በመጀመሪያ ከፌዴራል መንግስት ፍቃድ በማግኘት ጳጉሜ 5 ቀን 2008 አንድ የሰገን ዞን ተላላኪ አቶ ከተማ ካሽለ ከአጋሮቹ በምሥጢር የሰማውን የደቡብ ክልል የኮንሶ ብሔርን ከምድረ ገፅ የመገርሰስ ጥማት የፈደራል መንግስት መፍቀዱ ብቻ ሳይሆን አጋርነቱን እንደገለፀላቸው በመተማመን ሀላኮ (ታራ ማንጋሻ) የሚባል መንደር ማምሻውን ሄዶ እናቃጥላችሁሃለን፣ እንጨርሳችኋለን፣ በታቀደው መሰረት ዘራችሁን ከምድር ላይ እናጠፋለን በማለት ከደነፋ በኋላ ወዲያው ተሰወረ። ይህን የሰማው ሰላማዊ ህዝብ ውሸቱን ነው በማለት ተዘናግቶ እንዳለውም ምሽት ላይ ከሻላሎ በኩል ኮንሶን በከዱ ከሃዲዎች አማካኝነት መተረየስ ተጥምዶ ተኩስ ተከፈተባቸው። የሀላኮ ህዝብም ተደናግጦ ልጆችን ወደ ኋላ እያሸሹ መከላከል ጀመሩ ጠብ ጫሪዎቹም ከህዝቡ ጋር እስከ ሌሊቱ 8፡00 ተዋጉ በዚህ ሁሉ ግን ህይወት ሳይጠፋ ህዝቡ 3 ቀበሌዎችን አልፎ ቢያባርራቸውም ከ3 ቤት ቃጠሎ ውጪ ምንም ጉዳት በንብረትም ሆነ በሰው አካል ላይ ሳይደርሱ ወደ ቤታቸው ተመለሱ።
“በ01/01/2009 የመጀመሪያ ንድፋቸውን ያሳኩት የሰገን ዞንና የደቡብ ክልል አመራሮች ኮንሶ ጦርነት ቀስቅሷል በማለት በርካታ ልዩ ሃይልና የፌዴራል ፖሊሶችን ወደ ሰገን ዞን አስገቡ። ከዚያም ማታ ላይ ወደ ሻላሎ ስራዊቱን አስገብተው የኮንሶ ገሃዲ የሻላሎ ነዋሪዎች በሻላሎ ውስጥ ያሉትንና የኮንሶ ጥያቄን የሚደግፉትን ቤቶች በፌዴራልና ልዩ ኃይል ታግዘው ሙሉ በሙሉ አቃጠሉ።
“ምሽት ላይ ቤቱን ካስቃጠሉ በኋላ ሰራዊቱ ወደ ሰገን ከተማ ሲመለስ ገሃዲዎቹ ብቻቸውን አቅም እንደለላቸው ቢያውቁም በታዘዙት መሰረት በሀላኮ መንደር ላይ ዳግም ተኩስ ከፈቱ። ህዝቡም ተነስቶ ገጠማቸውና በምሽቱ እንደገና ብዙ ቤቶች ተቃጠሉ።
“በ02/01/09፤ በዚህ ዕለት የሰገን ዞንና የደቡብ ክልል ኮንሶን ለማጥፋት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንደደረሱ በመተማመን የዞኑን የበላይ አመራሮች ወደ ሀዌሳ ሲያስኮበልሉ የበታች አመራሮችን በምስጢር ቤተሰቦቻቸውን እንዲያስጠነቅቁ መልዕክት አስተላለፉና ቁጥሩን ለመገመት የሚከብድ አጋዚን በመንገድ ላይ ሌላው ህዝብ አይቶ ይሸበራል በማለት መሰለኝ ወታደሩን በሶስት አቅጣጫ ከፋፍለው ግማሹን በፕለን በጅንካ፣ ግማሹን በአርባምንጭ እንዲሁም ግማሹን በያቭሎ በኩል በማስገባት አይሎታን ከበቧት። ከሰዓት በኋላ ከተማ ገለቦ የሚባል የሰገን ዞን አመራር (አሁን አርባምንጭ ኤፍ ኤም ላይ መረጃ እንዲያቀባብል በዞኑ የተቀመጠ) ወደ እፋዮ መንደር ለቤተሰቦቹ ስልክ ደውሎ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋው ዛሬ ማታ ስለምከናወን ሸሽታችሁ አሁኑኑ አካባቢውን ልቀቁ ሲላቸው ዕለቱ የሙስሊም በዓል የሚከበርበት ስለነበር ደግሞ በዓል ባይሆንም መንግስት የገዛ ህዝቡ ላይ እንዲህ ዓይነት Genocide ያውጃል ብሎ ስለማያስብ ውሸቱን ነው ብለው ዝም አሉ።
“ይህን ተከትሎ ነው እንግዲህ ማታ በሞያለ በኩል የገባው የአጋዚ ሃይል በብርብርና ሻራንካ በኩል ገብቶ በጋማ ዳራ ከፍብሎ አንተና ያለበት አካባቢ ህዝቡን ከበው በከባድ መሳሪያ ታግዘው የውትድርና ብቃታቸውን ለማሳየት በቁም ህብረተሰቡ ላይ ተኩስ የከፈቱት። ህዝቡ ፌዴራል ሊያገላግላል እንጅ አይፈጀንም የሚል እምነት ስለነበራቸው ተኩስ አቁመው ቢያፈገፍጉም የአጋዚ የጥይት እሩምታን የሚያቆም አልተገኘም እንዲሁም ወዲያው 6 ሰው ገድለው ሬሳ እንኳን ለመውሰድ በከባድ መሳሪያ የታገዘው የአጋዚ ሃይል ፋታ ስላልሰጣቸው የአንዱን ሬሳ ብቻ እንደምንም ወስደው ካልጠበቁት ጥቃት ሰው ህይወቱን ለማትረፍ እየፈረጠጠ ስለነበር ከዚያ በኋላ የሞቱ ሰዎች ስንት እንደሆኑ እንኳን ከፈጣሪ በቀር ማንም በማያውቀው ሁኔታ ለሊቱን ሙሉ ህዝቡን እየጨፈጨፉ አደሩ።
“03/01/2009፤ ይህ በእንዲህ እንዳለ በሀላኮ በኩል ምንም ተኩስ ሳይሰማ በሰላም ያደረ ህዝብ ጠዋት በማለዳ ከየት በኩል እንደመጡ እንኳን ህዝቡ ሳያውቅ በአርባምንጭ በኩል የገባው የአጋዚ ሃይል የሀላኮን መንደር ከብቦ የጥይት እሩምታ ሲለቁባቸው ከእንቅልፍ ገና በደንብ ያልነቃው ህዝብ ፈዴራሎች ስለሆኑ አይነኩንም ብለው ሲሸሹ አከታትለው በማጥቃት ህዝቡን አሳድደው ከኋላ ባስከተሉት ልዩ ሀይል ቤቶቻቸውን እያቃጠሉ እነሱ ከፊት እያሳደዱ ብታምኑም ባታምኑም አሁን የሀላኮና የጎጫ መንደሮችን ሙሉ በሙሉ አመድ አድርገው መሮጥ ያልቻሉ ህፃናትና አዛውንቶች ጨፍጭፈው ጨርሰዋል ከዛን ወደ ሉልቱ ቀበሌ በመጓዝ ላይ ይገኛሉ።
“አሁን ህዝቡ እንዳለ ሸሽቶ ስለሆነ ከዚህ ድርጊት የሚመልሳቸው ማንም የለም። ከኮንሶ ያለው ህዝብ እንኳን መጥቶ እንዳይከላከል ተዋጊው አጋዚ ከመሆኑ ባሻገር በጅንካ በኩል የገባው ሃይል ከተማውን ከብቦ መንገድ ዘግቷል።
“እንግዲህ ከተጠየቀ ዓመታትን ያስቆጠረው የኮንሶ ህዝብ ሰላማዊ ዴሞክራሲያዊና ህገ መንግስታዊ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ በፅሑፍ ከቀረበ ከዓመት በላይ ዕድሜ ቢሆነውም ዛሬ መልሱ የ ኮንሶን ዘር ከምድረ ገፅ የማጥፋት ዘመቻን በደቡብ ክልልና በአጋዚ ቅንጅት ሆኗል። የሚገርመው ISIS እንኳን ለማጥፋት ዘመቻ ሲደረግ ልክ አለው፤ ዛሬ ግን የኮንሶን ህዝብ በሀገር ጠላት ላይ እንኳን በማይፈፀም የዘር ማጥፋት ዘመቻ ህዝቡን የሚታደግ ከፈጣሪ በቀር ያለ አይመስልም።
“በመጨረሻም ቤተሰቦቼን የጨረሱ አርመኔዎች እኔንም ይምሩኛል የምልበት እምነት የለኝም ከዚህ በኋላ የምኖረው ህይወት የራሴ አይደለም እኔም ዛሬ ሞቻልለሁ። ቢሆንም ግን ይህን በእንባ እየታጠብኩ የፃፍኩትን የምታነቡ ወገኖች ሁሉ በፀሎት ከጎናችን በመሆንና ይህን ግፍ ለዓለም ሚዲያዎች በማሳወቅ እንድትረዱን በነበረኝ ኢትዮጵያዊ ወንድምነት እማፀናችኋለሁ።”
እኛም ወገኖቻችን በሙሉ መልዕክቱ እንዲደርሳቸው አቅርበናል፤ የህወሃት መርዝ ሁላችንንም እየጎዳ ነውና ህወሃት ከፈጠረልን ትናንሽ የዘር ሳጥኖች ወጥተን በመጀመሪያ ሰው እንሁን፡፡ የዚያን ጊዜ የማንኛውም ሰው ስቃና ሃዘን፣ ግፍና መከራ፤ ሞት ይሰማናል፤ የራሳችን አድርገን እንወስደዋለን፡፡ እኛንም ያመናል፤ ያደማናል፤ ይገድለናል፡፡ በመጀመሪያ ሰው ከመሆን አንሰን ዘር፣ ጎሣ፣ ብሔር፣ … የምንሆን ግን አሁንም ከህወሃት ልክፍት አልወጣንምና የሌላው ስቃይ “የኔ” የምንለውን እስከሚያጠቃ ድረስ አይሰማንም፡፡ ህወሃትም ይህንን እንደ ጥሩ ምግብ እየተመገበ ይፋፋል፤ ይሰባል፤ በሥልጣን ይቆያል፡፡ መፍትሄው ቀላል ነው፤ መርዙ መከፋፈል ከሆነ ማርከሻው ሁሉንም እንደሰው የሚያከብር ኅብረት ነው!! (የፊት ፎቶ: Oakland Institute)
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Lusif says
That guy is absolutely right. No honest citizen can easily imagine and understand what the government is really up to. In every corner of the country is killings, burning down of villages and market places. Such atrocities are perpetrated in the name of peace and stability, to root out the antidevelopments elements, the Shabia Puppets, arch enemy Egiptian messengers.
One sensible question one can ask is, at whose watch all those elements happened to be in the country? Do we have a government that can fairly play out it responsibility, execute its duty according to the rule of law? The question must not be directed to the government only. We need to ask ourselves too. Do we consciously set up a responsible government? Do we have widely focused, discussed and agreed upon constitution? Who controls the government? The integrity of our political officials and parliament members is well and sound? Do those parliament members represent their constituents and try to help? Where is their voice at this trouble time of need? If the answers to those question are no, no. We need to learn from our mistakes. We have been misled is not enough. Those politician will definitely keep misleading us as long as we stay ignorant and willing to accept and tolerate or deny.
I agree we all are human beings. We need each other more than anything else. We have been victimized and killed piece by peace. That was our sordid weakness. Let us come together as human beings stand up face to face with our adversaries. Anybody can die anytime. A United force barely dies. ” instead of diying as a subhuman eating and kneeling, die as a human starving and standing”