• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የኮንትራት ሰራተኛዋ ኢትዮጵያዊት መጨረሻ!

September 27, 2016 06:23 am by Editor Leave a Comment

* “አሰቃዩኝ” ስትል ፍልቅልቋን የ 6 ዓመት ብላቴና ለሚስን ቀጠፈቻት
* ገዳይ ኢትዮጵያዊት ትናንት በሞት ተቀጣች
* ዘምዘምም ለሚስም ልብ ይሰብራሉ ሁሉም ልብ ይሰብራል

ይህን ሁለት ቀን ተረብሻለሁ፣ ምክንያቴ ብዙ ነው፣ ከምንም በላይ ከሪያድ የደረሰኝ መልዕክት ህመም ሆኖኛል ሰው ልምጣ ሲል እሷ “የመጨረሻ ቀናቶቸን የወላጆቸን አይን ሀገሬን ልይ እርዱኝ! ወደ ሀገሬ እንድገባ እርዱኝ!” የምትለው ታማሚ የኮንትራት ሰራተኛ እህት መልዕክት ጨካኙን ሰው ሆዴን አባባው። ማምሻውን ያነኑ ቪዲዮና ድምጽ ሳስተካክል ሌላ መረጃ እዚያው ሪያድ ደረሰኝና ቅስሜ ሰብር ብሎ አመሸ … ኢትዮጵያዊቷ ሌላ የቤት ሰራተኛ በሞት መቀጣቷን ሰማሁ! እናም ወደ መረጃው አቀናሁ … ድርጊቱ ሲፈጸምና መረጃው ሲናኝ ተከታትዬ መረጃ አቅርቤበት ነበርና ያንኑ ጊዜ እያስታዎስኩ የፍርድ ውሳኔውን ዜና ገለባብጨ አነበብኩት!

“አተርፍ ባይ አጉዳይ”

ከሶስት አመት በፊት ለሚስ የተባለችውን የ6 ዓመት ታዳጊ ሳውዲ ብላቴና “በጭካኔ አንገቷን በማረድ ገድላለች!”  የተባለችው ኢትዮጵያዊቷ ዘምዘም አብደላ ሰኞ መስከረም 16 ቀን 2009 ዓም ሪያድ ላይ  በሞት ተቀጥታለች! የኢትዮጵያዊቷን የቤት ሰራተኛ ዘምዘም በሞት መቀጣትን መረጃ ይዘው የወጡት የሳውዲ ጋዜጦች በዘገባቸው ዝርዝር መረጃም አካትተዋል። የቀረበው መረጃ እንደሚያስረዳው ዘምዘም እአአ June 2013 ዓም ከሪያድ ሰሜናዊ ክፍል በ150 ኪሜትር ርቀት በምትገኘው Hota Bani Tamim በተባለች ትንሽ ከተማ ከሃገር ቤት በኮንትራት መጥታ በሳውዲ አሰሪዎች ጋር ትሰራ ነበር፤ ይሁን እንጅ ዘምዘም ከምትሰራባቸው አሰሪዎቿ ጋር ስምምነት አልነበራትም። ባንዱ ክፉ ቀን ዘምዘም “በደል ፈጽመውብኛል” ብላ በአሰሪዎች የደረሰባትን በደል ለመበቀል ታዳጊዋን ብላቴና ልጃቸውን የ6 ዓመቷን ለሚስን መግደሏን እአአ Dec. 2013 ዓም ሪያድ ላይ በዋለው ፍርድ ቤት ቀርባ የእምነት ክህደት ቃሏን መስጠቷ ተጠቁሟል። ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን በማጣራት እንድትገደል በወሰነው መሰረት በኢትዮጵያዊቷ ዘምዘም ላይ የሞት ቅጣቱ ትናንት ሰኞ ሪያድ ላይ መተግበሩ ታውቋል!contract-worker-kids saudi

በወቅቱ የብላቴናዋ የሚስን ግድያ በመላ ሳውዲ ከፍተኛ የዜና ሽፋን ተሰጥቶት የነበረ መሆኑ ይጠቀሳል። ሳውዲዋ ብላቴና የለሚስና ሌላ ኢስራ የተባለች የ11 አመት ሶርያዊት ታዳጊ ላይ ኢትዮጵያውያን በቤት ሰራተኞች ተፈጸመ የተባለውን አሰቃቂ ወንጀል ተከትሎ ሳውዲ ከኢትዮጵያ ሰራተኛ ማስመጣት ማገዷ ቀዳሚ ምክንያት ነበር። ይህንን ሳውዲ የምትኖሩ የምታስታውሱት አትኖሩም አልልም …

ቀጣዩ ህምም …

ይህ በእንዲህ እንዳለ በተመሳሰይ ግድያ የተወነጀሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን የኮንትራት ሰራተኞች በተለየያዩ የሳውዲ ወህኒ ቤቶች እንደሚገኙ መረጃዎች ያስረዳሉ። ምንም እንኳን የኢትዮጵያ የኢንባሲና ቆንስል ተወካዮች ክትትል ማድረግ ያለባቸው የዜጎች ጉዳይ በየፍርድ ቤቱ በእንጥልጥል ላይ ያለ ጉዳይ ቢሆንም የመንግስት ተወካዮች ክትትል እያደረጉ ስለመኖሩ መረጃው የለኝ። ያም ሆኖ ጉዳያቸው በሳውዲ መንግሥት ከፍተኛ የሸሪአ ፍርድ ቤት በኩል እየተጣራ ወንጀለኛ መሆናቸው ሲረጋገጥ ሳውዲ በምትመራበት የእስልምናው የሸሪአ ህግ መሰረት ተመሳሳይ የሞት ቅጣት ውሳኔ እንደሚተላለፍባቸው ይጠበቃል። ይህም ቀጣዩ ህመም ሆኖን ይዘልቃል።

ማነው ተጠያቂው?

ያለ ምንም ቅድመ ዝግጅት ዘንድሮ “ህጋዊ አልነበረም” በተባለው ሳውዲ ሰራተኛ ከኢትዮጵያ ማስገባት እገዳ ከመጣሏ አስቀድሞ በነበረው የስራ ስምሪት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የኮንትራት ሰራተኞች ወደ ሳውዲ መግባታቸው አይዘነጋም። እውነት ነው፣  በሰራተኛ ዝውውሩ የኤጀንሲ ባለቤቶች፣ ሰራተኛ አቅራቢ ደላሎች፣ እዚህም ሳውዲ ሆነው ከኤጀንሲ ጋር ተሻርከው በሰራተኛ ድለላ አቅርቦቱ የተሳተፉ በርካታ ለመንግስት ቅርብ የሆኑ የምናውቃቸውና የማናውቃቸው የብዙ ደላሎች ህይዎት ተቀይሯል፣ በአጭር ጊዜና በአንዲት ጀንበር የናጠጡ ሃብታም ባለንብረቶች ሆነዋል! በአንጻሩ የብዙ የድሃ ልጆች ያለ እድሜያቸው እድሜ እየቆለሉ መጥተው ያሉበት ሳይታወቅ የውሃ ሽታ ሆነዋል፣ ጠፍተዋል፣ ታመው ወደ ሃገር ተለከውም ሳይላኩም የወላጅ አንጀት ታጥፏል፣ የወላጅ ቤት ተዘግቷል፣ የእልፍ አዕላፍ ወላጅ እናቶች ቤት በሀዘን ተውጧል! በሀገር ደረጃም ስለመከበር መናቃችን ይህው ያለ ዝግጅት የተፈጸመው የስራ ስምሪት ለመሆኑ በድፍረት እነግራችኋለሁ፣ እንግዲህ ጥቅም፣ ጉዳት ትርፉን መዝኑት…!!!

ለሀገር፣ ለባህሉ፣ ለሐይማኖቱ፣ ለቋንቋውና ለስራ ጸባዩ እንግዳ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በኮንትራት መጡ ተብሎ አመት ሳይደፍን ራሳቸውን ሲያጠፉ፣ አብደው ባልተለመደ መልኩ በአደባባይ ሲዘዋወሩ ተመልክተን የመንግሰት ያለህ ብንል ሰሚ አልተገኘም። ከአማካሪ እጦትና ከጭንቀት ራሳቸውን መቆጣጠር ሲያቅታቸው እስከ ግድያ ወንጀል የሚፈጽሙ የሉም አይባልም። ታዝበናል፣ እነሱም መብት አስከባሪ ተከራካሪ ባያገኙም (ፈጸሙት የሚባለው ወንጀል ከፋ እንጅ) ወንጀል ለመፈጸማቸው ምክንያቱ  የደረሰባቸው በደል መሆኑን መናገራቸውንም እውነት ነው፣ ተደጋግሞ ይጠቀሳል!

ቁጥራቸው ቀላል የማይባል በስራ ብዛት ታመው፣ ተደፈርን፣ ተደበደብን፣ ግፍ ተፈጸመብን ብለው ወደ ኢንባሲና ቆንስል መስሪያ ቤቶች የሚመጡት መፍትሔና ሁነኛ ድጋፍ ባያገኙም ችግራቸውን በመናገራቸው እና ተከላትመውም ቢሆን በጉትጎታ ብዛት ወደ ሀገር መላክ መቻላቸው እድለኞች  ናቸው ማለት ይቻላል። ያሉበት ሳይታዎቅ፣ ሞቱ ዳኑ የሚባል መረጃ የማናገኝላቸው፣ አድራሻቸው የማይታወቅ  በርካታ ኢትዮጵያውያን አሁን ድረስ በየሳውዲው ተላልቅና ትናንሽ መንደሮች ይገኛሉ!

በቂ ዝግጅት ሳይደረግ “በቂ ዝግጅት ተደርጓል!” በማለት በግፍ ዜጎችን በሌለና ባልተፈረመ የሁለት ሀገራት ስምምነት ዜጋን ለሌላ ሀገር ለስራ የማቅረቡ እርምጃ ተጠያቂው ማነው? ስምምነት በሌለበት ሁኔታ በተራ “ሚሞረንደም” ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ዜጋን ወደ ሳውዲ መላክ ከአንድ መንግሰት ይጠበቅ ነበርን? አሁን በአረብ ሀገራት የምናየው የዜጎች እንግልት የዚህ ሁሉ በግዴለሽነት ሥራ ውጤት አይደለምን? “አይደለም?” የምትሉ ካላችሁ እማኝ፣ ዋቢው ሞልቶ ተርፏል፣ ዘርዘር አድርገን በመረጃ ማስረጃ መነጋገር እንችላለን!

አሁንም አልመሸም!

አሁንም መንግሥት ባለድርሻ አካላት ሳንመክርበት ባጸደቀው አዲስ የስራ ስምሪት ስምምነትን ዘንድሮ ከሳውዲ ጋር ለመፈራረም ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ  መሆኑን አውቃለሁ፣ ይህንን አዲስ ስምምነት መፈራረም ጋብ አድርጉና ከዚህ ቀደም በኮንትራት ስራ ስም የተበተበውን ዜጋ ሰብስቡት! አሁንም አልመሸም … በኮንትራት መጥተው ደመወዝ ሳይቀበሉ፣ በስራ ብዛት ታፍነው መውጫ መግቢያ የጠፋቸው፣ በስቃይ ላይ የሚገኙ ሞልተው ተርፈዋል … እነዚህን ወገኖች መታደግ ገጽታን መገንባት ነው … እነዚህን እህቶች ለችግር ጭንቀታቸው መድረስ ተበሳጭተው ወንጀል ከመፈጸም እንዲታቀቡ መርዳት ነው …  ከዚህ በተረፈ የተቸገሩትን ማዳን ከተፈለገ ይቻላል! የታመሙ፣  የደከሙትን ለመርዳት ልባችሁ ቀናኢ ከሆነ የተበተኑትንና በችግር ላይ ያሉትን ዜጎች ድምጽ ስምታችሁ ወደ ሀገራቸው መላክ ይቻላችኋል፤ ብቻ  ቅና  እዝነ ልቦና ይኑራችሁ!

ዘምዘምም ለሚስም ልብ ይሰብራሉ

ካለፈው ጥፋት ካልተማርን እያለቅስን መኖራችን ግድ ነው፣ የዘምምዘም ጭካኔ ቢሰቀጥጥም መጨረሻዋ ያሳዝናል። ከሀገር ቤት ስትመጣ ነፍሰ ገዳይ ሆና ለሚስን ለመግደል ደም ጠምቷት ነበርን? አይደለም! ዘምዘም ለፍርድ ቤት ሰጠችው ከተባለው የእምነት ክህደት ቃሏ እንኳ ብንነሳ ዘምዘም በአሰሪዎቿ አያያዝ ተማራ፣ ከአሰሪዎቿ ጋር ተጋጨታ፣ ሰይጣን አሳስቷት “አሰቃዩኝ” ስትል አቅሏን አጥታ ለበቀል መዳረጓ እውነት ነው … እናም ዘምዘም የምትወዳትን ፍልቅልቋን የ6 ዓመት ብላቴና ለሚስን ቀጠፈቻት! እሷም ሳታልም ሳታስበው አተርፍ ባይ አጉዳይ ሆና! እንደወጣች ቀረች፣ ትናንት የመጨረሻዋ ሆነና ገድላለችና ሰይፍ በአንገቷ ላይ አረፈና፣ ተገላለች! ዘምዘምም ለሚስም ልብ ይሰብራሉ! ሁሉም ልብ ይሰብራል 🙁

(ከዚህ ጋር የፍልቅል የብላቴናዋ  የለሚስንና የእኛዋን ዘምዘምን ፎቶ አያይዥዋለሁ)

እስኪ ቸር ያሰማን!

ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 17 ቀን 2009 ዓም

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Social Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule