• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የዛፍ ላይ እንቅልፍ!” ስደት

August 25, 2016 01:33 am by Editor Leave a Comment

የመረጃ መረቡ ከሃገር ቤት በሚሰማው የህዝብ እንቢተኝነት አመጽ ተጨናንቆ እኛንም አጨናንቆን ከርሟል። በዚህ የመረጃ ቅብብሎሽ መካከል ወደ ምሥራቅ ሳውዲ ለስራ ጉዳይ አቅንቸ ነበር። ርያድ፤ ደማም፡ ጁቤል፤ ሃፍር አልበጠንን ለአንድ ሳምንት ሳካልል ከሃገር ቤት ከሚሰማው መረጃ  እኩል በሳውዲ ዙሪያ ያሉ በርካታ ወገኖቸ የተለያዩ መረጃዎች በስልክ አድርሰውኛል። በተዘዋዎርኩባቸው ከተሞች ያገኘኋቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቸም የሚያመውን የስደት ህመም ሳይደምቁ አጫውተውኛል። ሁሉም አሳሳቢ ናቸው፣ ሁሉም ቢያንስ መፍትሔ ይሻሉና ዝም የማይባለውን የወገንን ድረሱልኝ ጥሪ አሳውቃችኋላሁ!

ዛሬም በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች የተበተኑ ችግር የገጠማቸው ዜጎች መብት አስከባሪ አጥተው ሲንከራተቱ፣ ሲንገላቱና የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ ነው! በአንጻሩ አዲስ ኮንትራት ውል ከሳውዲ አረቢያ ጋር ለመስማማት ደጋግሞ ሞክሮ ያልተሳካለት የኢህአዴግ መንግስት ኮንትራት ውሉን ለማሳካት እየተሯሯጠ መሆኑን ከሪያድ ኢምባሲ ሁነኛ መረጃ ደርሶኛል። ይህ እየተሰራ ባለበት በሳውዲ በባህር መጥተው ለከፍተኛ አደጋ የተጋለጡትን መከራ መስማት ይከብዳል፣ ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ኃይማኖት ከየመን በየመን በኩል በሚደረገው በሳውዲ መዳረሻ በመንገዱ ያለውን አሰቃቂ ሁኔታ እፍታ እፍታውን ደጋግሞ ገልጾታልና ደግሜ አላሰለቻችሁም! ብቻ መከረኞቸን መታደግ ሳይቻለን በመቀረቱ አልመች ብሏቸው እንጀራ ፈልገው በየመን የሚጎርፉት ዜጎች “መከራውን እያወቁት መርጠው የመጡት ነው! ይበላቸው!” የሚል ሰብዕና የጎደለው የጨካኝ ምክንያት እየሰጠን ለመርዳት ከመደገፍ መሸሽን መርጫችን አድርገናል! … ያሳዝናል!

የባህርተኞቹ ጉዳይ ይሁን ቢባል፣ ህጋዊ በተባለው በኮንትራት ስራ ሳይደራጁ “በተደራጁት” ኤጀንሲዎች መጥተው በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች የተበተኑት እህቶች ጉዳይ አሳሳቢ ከሆነ ከራርሟል። በኮንትራት በሚሰሩባቸው የአረብ ቤቶች በስራ ጫና፣ በሚደርስባቸው በደል፣ በሕመምና በጭንቀት፣ ብሎም “የተሻለ እናገኛለን” ብለው ከአሰሪዎች የጠፉና “የተሻለ ስራ እናስገባለን!” በሚሉ ሆድ አደር ደላሎች የተፈናቀሉ አብዛኛው እህቶች ቁጥር እጅግ በጣም ከፍተኛ እንደሆነ ይነገራል! አንድ በኩባንያው ስራዬ በኩል በቅርብ የማውቀው ለፖስፖርት ጽ/ቤት መረጃ ቅርብ የሆነ ሳውዲ ከፍተኛ ኃላፊ በኮንትራት መጥተው ከአሰሪዎቻቸው የጠፉ “ሁሩብ” ተብለው የተመዘገቡ ኢትዮጵያን ቁጥር ወደ 60 እና 70 ሽህ እንደሚገመት አጫውቶኛል። ለእኒህ ከአሰሪዎቻቸው የጠፉ  ወገኖች መካከል በጠፉበት ሆነው ኑሮን በስደት ሲገፉ ጥቂት የማይባሉ “ህገወጥ” መሆናቸው ሳያስፈራቸው ቤት ይዘው፣ ትዳር መስርተው፣ ልጅ ወልደው የሚገኙት ቁጥር ቀላል አይደለም ።

“የዛፍ ላይ እንቅልፍ!” ስደት

አደጋው የደላ ቤት ይዘው፡ ትዳር መስርተው፤ ቀን መዳር መኳሉ ልጅ መውለዱ አይደለም። የሞቀው ሲበርድ፤ አፍላው አልፎ፤ የእውነቱ ኑሮ ሲጀመር ኑሮን በሃላፊነነት የመግፋቱ ክብደት የመጣ ጊዜ ነው ፍተናው! ሞልቶ የማይሞላው “የዛፍ ላይ እንቅልፍ” callየስደቱን ኑሮ እንዳሰቡት አልሰምር ሲል ደግሞ ከላጤዎች ይልቅ ቤተሰብ መስርተውና በስደቱ  የልጅ ፍሬ በረከት ለታደሉት መከራው የከፋ ይሆናል። በስቃይ፣ መከራው፣ በእምነት ክህደት፣ ውስብሰቡ ህይወት ያመጧልቸው የስደት ፍሬ ልጆቻቸው ደግሞ የመከራው ገፈት ቀማሽ ይሆናሉ! ነገሮች ይወሳቡባቸዋል! … ታዲያ  “የመጣ ይምጣ ወደ ሃገር እንግባ፣ የስደቱን ኑሮ ይብቃን!” ብለው ወደ ሐገር መግባት የፈለጉ ቀን ለከፋ ስቅየት ይዳረጋሉ …!

በተለይም ከአስሪዎቻቸው ጠፍተው ከርመዋልና ጠፉ ወይም “ሁሩብ” ተብለው በፓስፖርት መ/ቤት የሚፈለጉት ወደ ሐገር ለመግባት ሲፈልጉ ጣጣው የከፋ ሆኗል። በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች ወደ ሃገር ለመግባት ፈልገው የሚይዛቸው እና የሚሸኛቸው አካል አጥተው ወደ እስር ቤት አስገብተን ወደ ሃገር እንልካለን በሚሉ የራሳችን ዜጎች ደላሎች ከፍተኛ ገንዘብ ከስክሰው እስር ቤት ከገቡ በኋላ ለወራት በእስር ቤት እየማቀቁ ያሉት ቁጥር ቀላል አይደለም። ከዚ በታጓዳኝ ለደላላ የሚሰጥ ገንዘብ የሌላቸው ይዞ በእስር ቤት በኩል ወደ ሃገር ቤት የሚልካቸው ፖሊስ አጥተው የሚንክተቱ ቁጥር እጅግ ከፍ ያለ መሆኑን ተመለክቻለሁ። በሌላ በኩል ከአሰሪዎቻቸው ሳይጠፉ “ኑሮው በቃኝ” ያሉ ጊዘ ወደ ሃገር ለመግባት ፈልገው ፈቃድ ከአሰሪዎቻቸው የማይሰጣቸው፤ የመውጫ ቪዛ ለማስመታት ከፍተኛ ገንዘብ በመጠየቃቸው እጃቸው ለፖሊ ሰጥተው መያዙ የቀናቸው እስር ቤት ከገቡ በኋላ በወህኒ መጉላላት እ ደሚደርስባቸው መረጃዎች ደርሰውኛል። ወደ ሃገር ቤት ለመግባት ፈልገው የተያዙት እና ሳይፈልጉ በቤት ለቤት ሰበራ ፍተሻ ተይዘው እስር ቤት የተወረዎሩት ከወራት በኋላ እንኳ ወደ ሀገረቸው ለመግባት የከፋ  እንግልት እንደሚደርስባቸው በዝርዝር አጫውተውኛል!

በከፋ አደጋ ላይ ስለመሆናቸው የገለጹልኝ ህጻናትን የያዙ እናቶች ወደ ሀገር ለመግባት ቢፈልጉም ከነገ ዛሬ እየተባሉ ለወራት በወህኒ ሲቆዩ በስቃይ ላይ መሆኑን አጫውተውኛል። ወ ደ ሃገር ቤት እንግባ ብለው እጃቸው የሰጡ በማናቸውም መንገድ ወደ እስር ቤት የገቡ የኮንትራት ሰራተኞች በተደጋጋሚ ባደረሱኝ  መረጃ ህጻናት ፤ ነፍሰ ጥሩዎችና አቅመ ደካማ የአእምሮ ህመምተኞች የሚቀይሩት የረባ ልብስ፤ ምግብና ንጹህ መጠጥ በበቂ ሁኔታ እንደማያገኙ ገልጸውልኛል። ነፍሰ ጥሩዎችና የአእምሮ መታዎክ የደረሰባቸው እህቶች መኖራቸውን ከእስር ቤት መረጃ ያቀበሉኝ እኒህ ወገኖች ሌላው ቀርቶ የጅዳ ቆንስልና የሪያድ ኢንባሲ ተወካዮች ልባቸው ለህጻናቱ ራርቶ ወተትና መጸዳጃ እንዲያገኙ እንደማያደርጉ ጠቁመው የተገፊ ድምጻቸውን እንዳሰማ አደራ ብለውኛል! ሙሉና ዘርዘር ያለውን በድምጽና ምስል የተላከልኝን ጠልቆ የሚያመውን የድረሱልኝ መልዕክት መረጃ ዛሬ አላቀርበውም ፤ ብቻ ድምጻቸው ይሰማ ዘንድ እነሆ ደረሰብን የሚሉትን መረጃው እንዲህ አቀብላቸኋለሁ!

ቸር ያሰማን!

ነቢዩ ሲራክ
ነሐሴ 18 ቀን 2008 ዓም

Filed Under: Opinions, Social Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule