እንዳገኘ በልቶ እንዲህ ተነርቶ እንዲህ ሆዱ ሰፍቶ ቁርጡ ቀን ሲመጣ፥ ወያኔ ሲወገድ ገና መዋጮ አለ፥ ለልማታዊ ሆድ። … [Read more...] about … ለልማታዊ ሆድ
Literature
ጽፈኪን
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፩
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስር ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ (እንደተለመደው በየሳምንቱ መልሱን ተከታትለን ባለማቅረባችን ለአንባቢያን ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን::) መልስ እኔ ነኝ፣ እኔ ነኝ፣ - እኔ ነኝ ተዘራ የማስደስታችሁ - ከክራሬ ጋራ ብለው የዘፈኑ - በገዛ ስማቸው ድምጻዊ ተዘራ - ማለት እኚህ ናቸው ላሁኑ ደግሞ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፩” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ በሚቀጥለው … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፩
፸ ደረጃ
ሣልሳዊ ቴዎድሮስ ወይም "ቴዲ አፍሮ" በሰባ ደረጃ የተባለ(ች) ነጠላ ዘፈን ለቆልናል፡፡ "በሰባ ደረጃ"ን እኔ ስሰማው እልም ያለ የፍቅር ዘፈን ነው፡፡ ፍቅርን ልዩ በሆነ ቦታና ልዩ በሆነ ሥፍራ የሚያሳይ ዘፈን፡፡ በአማርኛ ዘፈን ባህል ውስጥ ቦታን ማስጎብኘት የተለመደ ነው፡፡ "የሐረር ልጅ ነች ወጣቷ/ጀጎል ነው ቤቷ" አይነት ዘፈን ሞልቶናል፡፡ አብዛኛው ያገራችን ዘፋኝ፣ ያስጎብኝነት ሚናም ደርቦ ሲጫወት ኖሯል፡፡ በዚህ ምክንያት ተፈቃሪዋ ሴት ሁሌም ከታሪካዊ ቦታ አጠገብ ለመወለድ ትገደዳለች፡፡ ቴዲ በዚህ ዜማው ባልተሄደበት መንገድ ሄዷል፡፡ ሲጀምር፣ እዚህ ግባ የማይባል፣ ለዓይን የማይሞላ ቦታ መረጠ፡፡ ብዙ ጊዜ፣ ታሪካዊ ቦታ ሲባል አክሱም፣ ላሊበላ፣ ፋሲል፣ ሶፍኡመር፣ ጀጎል እንላለን፡፡ ካሜራው በኒህ ቅርሶች ላይ አፍጥጦ ኖሯል፡፡ ታሪክ አክሱም ላይ ጀምሮ ጀጎል ላይ የተጠናቀቀ … [Read more...] about ፸ ደረጃ
የቅርብ ጊዜ አዳዲስ ስሞች
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየወጡ ያሉ ስሞች 1. ልማቱ ፈጠነ 2. ቦንድነህ አባይ 3. ሊግ ይበልጣል 4. አኬልዳማ ታዬ 5. ኑሮ ውድነህ 6. ፌደራል እርገጤ 7. ስልጣኑ በዛብህ 8. ኮንዶሚኒየም ለማ 9. ግምገማ ከበደ 10. ተሳለጭ ሃገሬ 11. መተካካት ተሻለ 12. ባድመ ይበቃል 13. አሰብ ተስፋዬ 14. ቻይና ፍቅሩ 15. መብራት ይታገሱ 16. ቴሌነሽ በዝብዝ 17. አክስዮን ሰብስቤ 18. ቫቱ በዛብህ 19. ግብሩ ጫንያለው 20. ህገመንግስት ጣሴ 21. ነጠፈ ብሩ 22. ፌስቡክ ተመስገን 23. ሀያልነሽ መንግስቴ 24. አምስትለአንድ አደራጀው 25. ግንቦት ሃያ ገብረማርያም (ምንጭ: Ethio-Sunshine ፌስቡክ) በአንባቢያን የተጨመሩ: Gulilat Kasahun የጨመሩት 1. ምርጫዬ ደረሰ 2. ደሞዝ ስሜነህ 3. … [Read more...] about የቅርብ ጊዜ አዳዲስ ስሞች
የግልና የመንግሥት ለቅሶ
(ሃዘንን በሳቅና በፈገግታ ካላሳለፉት መሪር ይሆናል) አቶ መለስ ያረፉ ሰሞን በየሰፈሩ ድንኳን ተጥሎ ነበር። በዚያው ሰሞን አንድ ሌላ ለቅሶ ሳሪስ አካባቢ አንድ ቤተሰብ ልጃቸው አርፋ ለቅሶ ተቀምጠው ነበር። በዚህ ጊዜ አንዷ በስህተት (የአቶ መለስ ድንኳን መስሏት) "ራዕያቸው"፤ "ራዕያቸው" እያለች እያለቀሰች ለቅሶ ቤት ስትገባ ልጃቸው ያረፈችባቸው አባት በንዴት "ይህ የግል ለቅሶ ነው የመንግስት ለቅሶ አይደለም የመንግስት ከፈለግሽ ወዲያ ተሻገሪ" ብለው አመነቃቅረው አባረሯት። (ከHayle Adam ፌስቡክ የተገኘ) … [Read more...] about የግልና የመንግሥት ለቅሶ
ክደራና ክየና
አንድ ብልጣብልጥ ባለተራ ፤ ከያኔ ነኝ የሚል ጽፎ በእሱ ቤት የማላውቅበት ፤ መከደሩን ለንብ ቀፎ በየሔደበት ያወራል ፤ ጸሐፊያንን ነቃቅፎ ጋዜጣ መጽሔት ድረ ገጽ ፤ ወደዛ! እያለ ተጸይፎ አታንብቡ አትስሟቸው ፤ ብሎ ያርቃል አንባቢ የጌቶቹ ጉድ እንዳይወጣ ፤ እንዳይገለጥ ሸባቢ እንዴት ምን ነካህ? ለሚሉት ፤ ተገርመው በጭፍን ትችቱ ችግር መኖሩ መች ጠፋን ? ይሄ ሀገር የሚሻው በብርቱ መፍትሔውን ቢነግሩን ነው ፤ ይላል ልሳኑን አስልቶ መፍትሔው እንዳልተጻፈ ፤ ከችግሮቹ ጋር ጎልቶ፡፡ ይሄው አይደሉ እነሱ? ማደናቆር መተጣጠፍ ምን እነግራለሁ ለእናንተ ፤ ታውቋቸው የለ ከወደአፍ? በዐይን የሚታየው በጉልህ ፤ የሚጨበጠው ተይዞ ካሳበቃቸው ጭራሽ የለም ፤ በቃ የለማ ማን አዞ? የማይታየው የሌለው ፤ ምናባዊውን ሕልም እንጀራ ብሉ ጠጡ ጥገቡ … [Read more...] about ክደራና ክየና
ጭቃና ውኃ
ጭቃ እያቦካ ጭቃ እየለወሰ ጭቃ እየጋገረ ጭቃ እየጎረሰ ያረፈደው አያ ከጭቃው ገበያ ያውና ብቅ አለ ከጭድ መሃል ወጣ በጨመለቅ እጁ ሊጨብጠኝ መጣ። 'መቼም ከጭቃ ነው ተፈጥሮ ስሪቴ' ብዬ እንዳልጨብጠው 'እምቢኝ!' አለኝ ቤቴ "ጭቃማ አይደለሁም! _ ነኝ እንጂ ውብ ሸክላ ታሽቶና ተቦክቶ በውቅ የተኮላ ይታጠብ በቅድሚያ አቅርብለት ውሃ ለጨቀየው ነፍሱ በነገር ቤት ዝሃ" ብሎ ይሞግተኛል ተላላው መንፈሴ ውሃውን ረስቼ ጭቃን በማንገሴ እነሆኝ በል እንካ አንተ ጭቃ ለዋሽ ኮዳዬን ዘቀዘቅኩ ለእድፍህ አባሽ። የመንፃት ቀንህን አታርቀው ጓዴ ውሃዬን ተጠቀም ላፍስልህ ላንዴ ከዚያም ልጨብጥህ ደርሳለሁ ዘመዴ ጭቃ እያቦካ ጭቃ እየለወሰ ጭቃ እየጋገረ ጭቃ እየጎረሰ ስንቱ ሰው መሰለህ ደግሞ የታደሰ ከመቡካት በኋላ ውበት የለበሰ። … [Read more...] about ጭቃና ውኃ
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሴት ማናቸው? – ፱” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ዘጠኝ ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ (እንደተለመደው በየሳምንቱ መልሱን ተከታትለን ባለማቅረባችን ለአንባቢያንና መልሱን አዘጋጅተው ልከው ላቆየንባቸው ወለላዬ ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን::) መልስ ትንሽም ቢሆኑ - ቁጥራቸው ባይበዛ የድሮ ዘፋኞች - ነበራቸው ለዛ ከነዛ መካከል - በድፍን ከተማ ታዋቂ ነበሩ - እሳቱ ተሰማ ምስጋና አቀርባለሁ - መልስ ለሰጣችሁ እሳቱን እወቁ - ደግሞ ሌሎቻችሁ ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲” ወለላዬ የሚከተለውን … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲
ትኩረት – ከውጪ ቋንቋዎች ለተወረሱ ቃላት
የሀገራችን ቋንቋዎች ከውጪ ቋንቋዎች በርካታ ቃላትን ወርሰዋል፡፡ ይህም ከብሉይ ዘመን ጀምሮ ይታይ የነበረ ክስተት ነው፡፡ የመወራረሱ አድማስ ስፋቱን የጨመረው ግን በአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በቀጣዮቹ አንድ መቶ ሀያ ዓመታት ውስጥ የታዩት ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ክስተቶች የሀገራችን ቋንቋዎችን ለውጪ ቋንቋዎች ተጽእኖ የበለጠ ክፍት እንዲሆኑ አድርገዋቸዋል፡፡ ታዲያ ከሶስት ሺህ ከሚልቁት የውጪ ቋንቋዎች መካከል ለሀገራችን ቋንቋዎች ብዙ ቃላትን ለማውረስ የበቁት አራቱ ብቻ ናቸው፡፡ እነርሱም ዐረብኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ጣሊያንኛና እንግሊዝኛ ናቸው፡፡ የቱርክ እና የጀርመን ቋንቋዎችም ጥቂት ቃላትን ለሀገራችን ቋንቋዎች አበርክተዋል፡፡ ***** ዐረብኛ በሀገራችን ቋንቋዎች ላይ ተጽእኖ ለመፍጠር የቻለው በዋናነት የእስልምና ሀይማኖት የአምልኮና … [Read more...] about ትኩረት – ከውጪ ቋንቋዎች ለተወረሱ ቃላት
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፱
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሴት ማናቸው? – ፰” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ስምንት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ በብዙ ትያትር - የመድረክ ዝግጅት ዝናን ያተረፉ - ቀርበው በመታየት «የአዛውንቶች ክበብ» - በተለይ ሲነሳ እስከዛሬ ድረስ - ያላጡ ሙገሳ አስካለ አመንሸዋ - ማለት እኚህ ናቸው ከእድሜው በረከት - አሁንም ይስጣቸው። ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፱” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፱










