
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሴት ማናቸው? – ፱” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ዘጠኝ ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ (እንደተለመደው በየሳምንቱ መልሱን ተከታትለን ባለማቅረባችን ለአንባቢያንና መልሱን አዘጋጅተው ልከው ላቆየንባቸው ወለላዬ ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን::)
መልስ
ትንሽም ቢሆኑ – ቁጥራቸው ባይበዛ
የድሮ ዘፋኞች – ነበራቸው ለዛ
ከነዛ መካከል – በድፍን ከተማ
ታዋቂ ነበሩ – እሳቱ ተሰማ
ምስጋና አቀርባለሁ – መልስ ለሰጣችሁ
እሳቱን እወቁ – ደግሞ ሌሎቻችሁ
ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡
ፍቅርና ችሎታን – አብረው ያጣመሩ
በሙያቸው ብቃት – ጥሩ ስም ያፈሩ
ህዝብ ያደነቃቸው – ትልቅ ሰው ነበሩ
ያወቀ እንዲያስታውስ – ሌላው እንዲያውቃቸው
መልሳችሁን ስጡ – እኚህ ስው ማናቸው።
This man is Tezera H/Mekael