ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሴት ማናቸው? – ፰” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ስምንት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡
መልስ
በብዙ ትያትር – የመድረክ ዝግጅት
ዝናን ያተረፉ – ቀርበው በመታየት
«የአዛውንቶች ክበብ» – በተለይ ሲነሳ
እስከዛሬ ድረስ – ያላጡ ሙገሳ
አስካለ አመንሸዋ – ማለት እኚህ ናቸው
ከእድሜው በረከት – አሁንም ይስጣቸው።
ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፱” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡
ሥራቸው ካልቀረ – ወደፊት አስታዋሽ
ብዙዎች ሲሞቱ – ይረሳሉ ጭራሽ
አንዳንዶች ግን እንዲህ – በሙያቸው ብቃት
አይቀሩም ጨርሶ – ተሸፍነው በሞት
ከነዛ መካከል እኚህ – አንዱ ናቸው
በሉ ተጠየቁ – ንገሩኝ ማናቸው?
Tselot says
Wolelaye and Golgul,
I like to thank you much for this Section “Egnih Sew Man Nachew”. It is entertaining and teaching us (people like me) at the same time. I admit that I know better about many “Ferenjoch” History than my own people. This is same as “Hagerihn Iwok” and I thank you a lot for it. Please keep it up.
andnet berhane says
የቀድሞው የክብር ዘበኛ ጦር ጀነራል መንግስቱ ነዋይ ይባላሉ በስራው በተግባር የነበረ ብርቱ ዊስኪ ሻፓኝ ክትፎና ጮማ ይቅርብኝ በማለት ለህዝቡ የደማ ገርማሜ ወንድሙ ከጎኖ አቁሞ በደል እንዲቀር አነሳ ተቃውሞ የታህሳስ ግርግር ሲባል ተሰይሞ ሚኒስትር መሳፍንት ለቃቅሞ የሃገር ጉድፎች ጨረሰው አጋድሞ ይባል የነበረ በጊዜው በስውቅቱ መንግስት ግልበጣ ቅስቃሽ መሰረቱ እኝህ ናቸው ጀነራል መንግስቱ።
Amenen Gudaye says
He is Esatu Tesema.
Bombu says
ሰሞኑን ባገሬ የተሰማው ዜና
አስደንጋጭ ነበር የሚነሳ ጤና
የዛ ድንጋጤ ሳይበርድለኝ ገና
እኚ ሰው ማናቸው ገፅ ገባሁና
ትኩር ብዬ ሳይ ፎቶ በጥሞና
ወለላዬን ባላውቅ ጎልጉለን ባላነብ
ኢትዮጵያዊነትን እንድናውቅ በደንብ
የማልጠራጠር ይሕን አስመልክቶ
ትንሽ ግራ ገባኝ ሳየው ይሕን ፎቶ
ደሞ በየት በኩል እንዴትስ አድርጎ
ምን ጥሩ ሰራና ተጠቃሽ በበጎ
ፎቶው የሚለጠፍ ለሁሉም እንዲታይ
የወያኔ አለቃ አቦይ አባይ ፀሀይ
ብዬ ለመናደድ እፎይታም ሳላገኝ
ከዛ ከጨፍጋጋ እንቅልፌ ባነንኩኝ
እኚህ ኢትዮጵያዊ ለሐገር አሳቢ
አባይ ፀህይ ሌላ የራቀው ውቃቢ
እንዴትስ ብሎ ነው መመሳሰላቸው
አራምባና ቆቦ ለሐገር ሥራቸው
ብሎ ለሚከስኝ ለሚጠይቅ ካሣ
ብድር ከፋይ ያርገኝ ከእንቅልፌ ስነሣ›
ባሳ says
ፈጣኑ ግራኝ>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
አሁን ገባኝ
ባሳ says
ሁሌን እመኛለሁ ትጋትን ጭምሬ>
እንደምን አመሹ ወዳጄ መምሬ
Dubale Tariku says
I agree with Amenen.
He is Esatu Tesema