ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፯” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ሰባት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡
መልስ
አበበና ማሞ ሆኑ ባለቤቷ
ማራቶን ደንግጠሽ አቤን ብትቆጪ
ዕድሉ የኛው ነው የትም አታመልጪ
ብለው ያወደሱ – ሜክሲኮን ኦሎምፒክ
የኳስ ስም ሲነሳ – የሚታውሱ ሰርክ
ግጥም ያቀበሉ – ለብዙ ዘፋኞች
ዝናን ያተረፉ – በስፖርት ዓለም ሰዎች
አገር የሚሸበር – ድምጻቸው ሲሰማ
እኚህ ሰው ነበሩ – ስለሞን ተሰማ፡፡
ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፰” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡
ያን ንቁ ተፈጥሮ – እርጅና ተጭኖት
ቢያደበዝዘውም – ያላቸውን ውበት
እኝህ አዛውንቷ – ደርባባዋ እመቤት
ሆነው ቆይተዋል – የሕይወት መስተዋት
ሥራ አይሸፈንም – ቢርቅም ዘመኑ
እኚህ ሴት ማናቸው – እንደው ለመሆኑ
ፂዮን የመሲ ልጂ says
የጥበብ እመቤት – ቲያትርን መሥራች
ለጥበብ መሥፋፋትት – ትልቋ እመቤት
አንችን የማያቅሽ – እውን አለ ወይ
ፌትሽ ያሣየኛል – የጥበብ አደራ
በኛ በልጆችሽ ጥበብ – ከፍ እንድትል ስትሰጭን አደራ
እኛም ያንቺ ልጆች – አደራሽ ደርሶንል
ነገን ልናኮራሽ ይህው – ቃል ገብትናል::
በነገራችን ላይ ግጥም አልችልም ነገር ግን ለእኚህ አንጋፋ አርቲስት ያለኝን አክብሮት እና ፍቅር ለመግለፅ ነው:: የሀገር ፍቅር መሥራችዋ እና ተወዳጂዋ በይበልጥ በምናውቀው ሂሩት አባትዋ ማነው ዋና ተዋናይ አርቲሥት “አሥካለ አመንሸዋ” ይባላሉ! ክብር ለጥበብ መሥራች እናቶቻችን!!!!!