ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፮” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ በተለይ በዚህኛው በርካታዎች በመሳተፋችሁና በግጥም ምላሽ በመስጠት ዝግጅቱን ላሳመራችሁ ሁሉ በድጋሚ ምስጋናችን ይድረሳችሁ – ቀጥሉበት:: የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ስድስት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡
መልስ
ኤርትራ በሚገኝ – የስዊድን ሚሽን
በኋላም ውጪ ሀገር – ብዙ የተማሩ
በዕውቀታቸውም – ለሀገር የሰሩ
በሹመት የቆዩ – ሆነው ነጋድራስ
ታሪክ ያረሳቸው – እስከዛሬ ድረስ
ገብረህይወት ባይከዳኝ – በሚል የጻፋችሁ
ስህተት የለውም – ልክ ነው መልሳችሁ።
ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፯” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ በብዙ ፍለጋ የተገኘው ፎቶ ይህ ወለላዬ የላኩት ብቻ ነው:: ምናልባት መልሱን ስንሰጥ የተሻለ ፎቶ ያላችሁ ትልኩልንና እናሻሽለዋለን:: የዛሬ ሳምንት መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡
መቼም አጋጣሚ – ሰውን ያስታውሳል
ላገሩ የሰራ – ምን ግዜም ይወሳል።
ድምጻቸው ሲሰማ – እኝህ የሚታዩት
ብዙ ሰው ነበረ – የሚያዝን ሚደሰት
አቤት አነጋገር – ያቀራረበ ለዛ
ዳሩ ምን ይሆናል – አለፉ እንደዋዛ
ሰላሳ አራት ዓመት – ምድሪቷን ከራቁ
እኝህ ሰው ማናቸው? – በሉ ተጠየቁ።
bombu says
እስከዛሬ ድረስ ሲቀርብልን ፎቶ
የተገኘ ነበር ሁሉንም አካቶ
ገጽታውም ቢሆን ከዛም አለባበስ
ጎልቶ ይታይ ነበር ምንም ሳይቀነስ
የዛሬው ማናቸው ጥይቄ ክብደቱ
ከፎቶው ጀመረ ጎበዝ በሉ በርቱ›
እንኩዋንስ ደብዝዞ ነጭ ጥቁር ሆኖ
በቀለማት ቢደምቅ ቢቀርበለን ገኖ
እኔ እንደሁ አምናለሁ ካለፈው ሙከራ
መልሱን ለማሳወቅ ያለውን መከራ
ሰበቡ ሰበቡ ወዴት ትሄጃለሽ
ጥያቄው ሲከብድሽ ሰበብ ታበዥያለሽ
መሆኑን አውቄ እውነቱን ልናገር
ጊዜ መግዛት ደጉ በዘዴ ሲሞከር›
Dereje Mengesha says
ለስፖርት የተስማማ
ሰለሞን ተሰማ
(Send u soon his Foto a better one)
andnet berhane says
የስፖርት ጋዜጠኛ የነበሩት አቶ ሰለሞን ተሰማ ይባላሉ፡ ባነጋገር ለዛ ጫወታን በማማሟቅ በጊዜው ከነበሩት ተደናቂ ጋዜጠኛ በታሪክ እማይረሳ ዘላለማዊ ትውስታ ትተው አልፈዋል፡ ስፖርት (የግርኳስ) በሬድዮ በሚሰሙበት ወቅት ሰፈርተኛው የውቅቱ ልጆች በስማቸው ብቻ በማድነቅ ቅዳሜና እሁድ እስኪደርስ ይናፍቁን ነበር