ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፪” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ሁለት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡
መልስ
መውለድ አስተካክሎ እንደዚህ ነው እንጂ”
በማለት አዝማሪ የገጠመላቸው
ቢትወደድ መኮንን ማለት እኚህ ናቸው
እኚሁ ትልቅ ሰው ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ብዙ መጽሐፍትን የጻፉም ነበሩ።
ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፫” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡
እኚህ ሰው ማናቸው – ፫?
ለአንቱታ ማዕረግ – በምኑ ነው የሚያንስ
እንደሌላው ሁሉ – በመስጠት አክብሮት
አንቱታ ጨምረን – ይገባናል መጥራት
ለምሳሌ እኝህ ሰው – አሁን ምናያቸው
የጥበብ በረከት – አምላክ የሰጣቸው
አንቱ የሚባሉ – ባለሙያ ናቸው
እኔ አልናገርም – ንገሩኝ ማናቸው?
kashun grmamo says
on off the best artist ted father kashun
senu says
egnih sew Gazetegna kasshun´nachew !!
ye Teddy Afiro abat !
ye Tedros kassahun abat ::
Abu Ami says
የሳምንቱ ምርጥ የምርመራ ውጤት
በፓሊስ ፕሮግራም ያቀርባል በወቅቱ
ብራቮ ግርማሞ ይመስክር ብቃቱን
ቴዲን ተክቶዋል አሁን በሰዓቱ
ካሳሁን ግርማሞ ሞቢል ጋ ነው ቤቱ