ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፩” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አንድ ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡
መልስ
ሲጠሩ የኖሩ – በዶክቶር ማዕረግ
የውጪ ጉዳይን – የመሩልን በወግ
በጥሩ ስራቸው – የሚነሱ ሁሌ
ስማቸው ምናሴ – አባታቸው ኃይሌ
ተብለው ሚጠሩ ባለስልጣን ናቸው
ምስላቸው ተለቆ – ሳምንት ያየናቸው
ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፪” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡
እኚህ ሰው ማናቸው – ፪?
ከግርማ ሞገስ ጋር – ውበት ተጨምሮ
እኝህ ምናያቸው – ቁመናቸው አምሮ
ስራ ታሪካቸው – ከኢትዮጵያ ጋራ
የሚተሳሰረው – ስማቸው ሲጠራ
ምን አበርክተው ነው? – ንገሩኝ ማናቸው
የሰሩትን ሁሉ – እስከ ማዕረጋቸው።
Bombu says
አወይ የኛ ጉዳት የ አሁኑ ትውልድ
የኢትዮጵያን ታሪክ ምነም እንክዋን ብንወድ
ወደ ሁዋላ ሂዱ እስቲ ስው ጥቀሱ
አገር ወዳድ ጀግኖች ስማቸውን አንሱ
የሚለን ከመጣ በፎቶ አስደግፎ
ቢቻል በዝምታ በቀልድ አሳልፎ
አልያም በሮ መጥፋት እንዳሞራ ከንፎ
ሁሉም ይሞከራል የስበብ አይነቱ
አላውቅም ከማለት ከማፈር በከንቱ
ሥለዚህ እባክህ አያ ወለላዬ
ላንተ ላይሆን ደስታ የኔ መከራዬ
ተጋግዘን እንድናውቅ የማናውቀውን
እንደተለመደው መርጫ እንኩዋን ሰጠን
welelaye says
ሰው ጠይቆ ማግኘት – ፋይል ማገላበጥ
ይሻላል ብዬ ነው – ሰዎች ከማስመረጥ
አለዛ ነገሩ – ከበዛበት ምርጫ
ኩስታሬው ጠፍቶ – ይሆናል አልጫ
Netsanet says
Betam Konjie Ethiopiawi nachew. Ethiopian ke akoru talalak ye Ethiopia Lijoch andu endeneberu alteraterm. Wolelaye, tebareki Ethiopia yeneman Enat endeneberech eyastawo/shin/ken new. Egziabher Yibarki/sh/h. “Talak Nebern, Degmom Enhonalen,” Yilual Artistu, Temesgen G/E. His look is truly graceful Ethiopian gentleman !
Gamachis Oromiya says
Dr. Minase Haile . He was the worest Neftegna of all the time !!!!
arsemawit says
but he is not as worest as you can be!!!!!!
aradaw says
Can you please explain the purpose of this ? Why are you doing this ?