ከአዘጋጆቹ፤ የዘወትር የጋዜጣችን ተሳታፊና የጎልጉል ወዳጅ ወለላዬ “እኚህ ሰው ማናቸው?” በሚል ርዕስ በየሳምንቱ የታዋቂ ሰዎችን ፎቶ ከግጥም ጋር በመላክ ጥያቄ ለማቅረብና አንባቢያንን ለማሳተፍ ውሳኔ አድርገዋል፡፡ ለዚህ ከግጥምና ፎቶ ጋር ለሚቀርብ ዝግጅት አንባቢያን ጥያቄውን በግጥም በመመለስ እንዲሳተፉ እንፈልጋን፡፡ በሳምንቱ ቀጣዩን “እኚህ ሰው ማናቸው?” ስናትም መልሱን አብረን እናወጣለን፡፡ በዚህ መልክ ውይይቱ እንዲቀጥል ለማድረግ ያቀድን ሲሆን አንባቢያንም የእውቅ ሰዎች ፎቶዎችና ማንነታቸውን ብትልኩልን ለማስተናገድ የምንችል መሆናችንን እንገልጻለን፡፡ በተለይ የታዋቂ ሰዎች የልጅነት ፎቶዎች ቢሆን የበለጠ አስተማሪ ይሆናል ብለን እናስባለን፡፡ ለዛሬው የእኚህን ታዋቂ ሰው ፎቶ ከግጥም ጋር አቅርበናል፡፡ ምላሹን ከእናንተ እንጠብቃለን፡፡ ይህንን የዝግጅት ሃሳብ ላቀረቡትና በየሳምንቱ ግጥም ከፎቶ ጋር ለማቅረብ ቃል ለገቡልን የጎልጉል ወዳጅ ወለላዬ ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
እኚህ ሰው ማናቸው – ፩?
እስቲ መልስልኝ – እኝህ ሰው ማናቸው?
በምን ሀላፊነት – የት ይሰሩ ነበር?
በመቼው ዘመን ላይ – በማን አስተዳደር
በሕይወት አሉ ወይ – ክቡርነታቸው?
እባክህ አስረዳኝ – እስከ ታሪካቸው።
Zeg says
Wolelaley (-woch):
Ignih sew begizew beneberubet bota betam tawi / awaki balesiltan neberu. Bekedamawi Haile Sellassie gize keAto Ketam Yifru befit yewichi guday minister yeneberut Dr. Minassie Haile nachew. Ahun behiywot menorachewin iterateralehu, kalu degmo, Egziabher yakoyachew.
“Yihe degmo keyet yemeta adhari, neftegna, cherchasa shimagle naw” tilugnalachihu mechem, (atlugnim, sikelid naw)Lik kohunk andd ken yalachihubet imetalhu, misa tigbizugnalchihu, eshi?
Melkam ken / lelit.
Z
arsemawit says
Thank you for all.
Bombu says
ካለፈ በሁዋላ መልሱ ከተገኘ
አስተያየት መስጠት ልብ እንደተመኘ
እንዴት ያሰደስታል እንዴትስ ይመቻል
ራስን ማታለል ለካሥ ያስጎመጃል..
ከፎⶆአቸው ባላውቅ ቢርቀኝ ምሥላቸው
ሥማቸውን ባልይዝ ካለባበሳችው
ሥነምግባር ሳይቀር ወይም እውቀታቸው
መቼ ይረሳና ውለታቸው ላገር..
ታሪክ መዝግቦታል አይታለፍ ነገር
ኢትዮጵያዊ ኩራት ለአገር ውላታ
ተጠቃሽ ከጀግኖች ከአዋቂዎች ተርታ
ባንድ ላይ በመሆን ከ ከተማ ይፍሩ
በዓለም መድረክ ላይ አንድ ላይ ሲስሩ
ትርጉሙ ባይገባኝ ምናሴ ስማቸው
ነበሩ በርግጥም ደጀን ላገራቸው
በዛ ባስቸጋሪ በፈተና ጊዜ
ኢትዮጵያ እያለች ባዘን በተካዜ
ኤርትራ ዋይ ሰትል እንደከርሞ ጥጃ
በቻዋን ስትዳክር ጠፍቶባት መሄጃ
ምናሴ ከተማ መክረው ከንጉሱ
የኤርትራን ዋይታ ከላይዋ አነሱ