• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፩

September 10, 2014 06:21 am by Editor 15 Comments

ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስር ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ (እንደተለመደው በየሳምንቱ መልሱን ተከታትለን ባለማቅረባችን ለአንባቢያን ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን::)who-is-he-10

መልስ

እኔ ነኝ፣ እኔ ነኝ፣ – እኔ ነኝ ተዘራ

የማስደስታችሁ – ከክራሬ ጋራ

ብለው የዘፈኑ – በገዛ ስማቸው

ድምጻዊ ተዘራ – ማለት እኚህ ናቸው


who is he 11ላሁኑ ደግሞ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፩” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ በሚቀጥለው መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡

ጥያቄ

ዝርዝሩ ሲወጣ – ጀግኖች ሲቆጠሩ

አንደኛው አንበሳ – እኚህ ሰው ነበሩ

እንዲህ የገነነው – ሲጠራ ስማቸው

በምን ምክንያት ነው – ንገሩኝ ማናቸው?

Filed Under: Who is This Person Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. dereje Mengesha says

    September 10, 2014 04:35 pm at 4:35 pm

    መድፍና ጠመንጃ ጥይት ሲጉዋረሱ
    አሳላፊ ነበር የማሩ ገረሱ።
    የተባለላቸው ደጃዝማች ገረሱ ዹኪ የሸዋ አርበኛ የነበሩ ናቸው።

    Reply
  2. Qaalluu says

    September 12, 2014 09:15 am at 9:15 am

    ከአዋሽ እስከ ጊቤ ጣሊያንና ባንዳን መቆሚያ መቀመጫ ያሳጣቸው። በቆራ፡ በዳዎ፡ በገፈርሳ፡ በጭቱ፡ በወሊሶ አካባቢ ጣሊያንና ባንዳን የረፈረፋ ጀግና አርበኛ ነው። ብዙ ሺህ የገበሬ ጦር ይዞ ከወራሪ የኢጣሊያ ፋሽት ጋር ሲታገል የቆቀ። ተፈሪ (ሀይለ ስላሴ) በእንግሊዞች ተጭኖ ፊንፍኔ (አዲስ አበባ) ሲገባ እንደ ሌሎች አርበኞች ሄዶ ያልሰገዳለት፡ ነገር ግን ሀይለ ስላሴ በዚህ ጉዳይ ደንግጦ አርባኛው ባለበት አመያ አካባቢ ግንዶ መንደር ላይ በእንግሊዞች ወተደር ታጂቦ ለአርበኛው ሰገዳለት። የመሻንገያ ሹመትም “ፊታውራሪ” አለው። ሽጉጡንም ሸለማው። ከዚያ በሁዋላ አርበኛው ወዳ ጂማና ኢሉ አባቦር የተሰባሰባውን የጠሊያንና ባንዳ ጦር ለመደምሰስ ጊቤን ተሸግሮ ቃላመሃለውን ፈጸመ።ከጊቤ እስክ ጎሬ ያለውን ጠላት ድምስሶ ምርኮኛውን ለዘመዶቹ ነጭ እንግሊዞች አስረክቦ። የጦር መሳሪያውን ለራሱ አደረገ። ከነጻነት በሁዋላ ቃል የተገባለት የጦር አባጋዝነት ሁሉ ተሰርዞ ፊታውራሪነት ወዳ ቀኛዝማችነት ወርዶ አርባኛው በአጼውና በጸሐፊ ትዕዛዜ እንደ ውሃ በቀጠነ ትዕዛዝ የቁም እስር ተፈረዳበት። ከቦታ ቦታ ከግዞትነት በማያንስ መልኩ ሹመት ተብዬው ስራ ተሰጠው።
    በሁዋላ ላይ ደግሞ ወደ ፊንፍኔ በመመለስ በሃይለ ስላሴ ነጭ ለባሾች እይታ ስር ሆኖ እስክ እለተ ሞቱ ድረስ በቁም እስርነት ኖረ።
    ይህ ጀግና አርበኛ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ደብሱ (Garasuu Dhukii Dhabsuu Akkee Lubee)የፈረሱ ስም ኣባ ቦራ ይባላል።
    ትውልድ ቦታው ካሮ (Kaarroo) የሚባል በወሊሲ አካባቢ ነው። መኖሪያ ቤቱን ሰርቶ የነበረው ጨፎ የሚባል ቦታ ሲሆን ከሞተም በሁዋላ በዚሁ ቦታ እራሱ ባሰራው ጨፎ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተቀበረ።
    ስለ ኢትዮጵያ አርበኞች ሲነሳ፡ ብዙ ጊዜ ንጉሱና ጀሌዎቹ የፈጸሙበት ግፍ ሲገልጹ በሚከተለው መልኩ ነበር
    “ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ፡ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ።” ይባል ነበር።

    Reply
  3. Bombu says

    September 14, 2014 10:42 pm at 10:42 pm

    የሰው ልጅ በሕይወት ያሳለፈው ኑሮ
    የውጣ ውረዱ በታሪክ ላይ ሰፍሮ
    ለሌሎች ምሣሌ እንዲሆን መማሪያ
    በፅሁፍ ይሰፍራል ለትውልድም መኩሪያ

    የዚሕ ዓይነቱ ዕድል የዚሕ አይነት ዕጣ
    ክብሩን ተሸካሚ ከልኩ ሳይወጣ
    ምንም ሳይቀነስ ኣልያም ሳይለጠጥ
    የክብር ሥራቸው ከጃችን ሳያመልጥ

    ከቶ አከራካሪ ወይም ግራ አጋቢ
    ያልሆኑት እኝህ ሰው በውጭም በግቢ
    ኮርተው ያኮሩንን ስዎች ስናነሳ
    ደጃዝማች ገርሱ የኢትዮጵያ አንበሳ

    ሞተው ላገራቸው በዱር በገደሉ
    የውጭ ወራሪውን መክቶ በግሉ
    በሌለ መሣሪያ ትጥቅ ሳይሙዋላ
    በአገር ፍቅር ስሜት በዕምነት በመላ
    የገበሬ ጦሩ ተዋጊ በፈረስ
    ኣደራጅቶ መርቶ ወራሪን መደምሰስ
    ያስተማረን መክፈል ላገር መሥዋዕትነት
    ማን እንደ ገረሱ ለኢትዮጵያ በሕይወት »

    Reply
  4. bombu says

    September 14, 2014 11:36 pm at 11:36 pm

    ገድላቸውን ሰምተን ፍቅር ላገራችው
    በታሪክ ተፅፎ እንዳነበብናችው
    ተረት በምሳሌ ከሰዎችም ሰምተን
    ጀግኖች የነሳሉ ጊዜ ሳይወሰን

    አድንቀን ተገርመን ስማቸው ሳይቀረን
    የትውልድ ቦታ የዕድሚያቸውን ዘመን
    ሁሉንም ጠንቅቀን ካወቅን በሁዋላ
    ፎቶዋቸውን ስናይ ሆነ የተሟላ

    ታሪክ ትርጉም ሲያገኝ ገፅታ ተላብሶ
    ከፊታችን ሲቆም ሕልውና ቀምሶ
    ትጥቁም እየታይ ከነጎፈሪያቸው
    ማሥባሉ አይቀርም ለካስ እኝህ ናቸው

    Reply
  5. Ras Ja says

    September 15, 2014 03:09 am at 3:09 am

    እኔም አላውቅም
    እናንተው ንገሩኝ
    ታሪኩን ሥራውን በደንብ አብራሩልኝ

    ብዙ ማላውቃቸው ጀግኖች ስላሉ
    ከነርሱ መካከል አንዱ ይሆናሉ

    Reply
  6. Amsayaw Atnafu says

    September 15, 2014 03:12 am at 3:12 am

    ግምባሩን ኮስኩሶ እንደንብ አስፈሪ
    ጠመንጃውን ታጥቆ ጠላት አሳፋሪ
    ግርማ ሞገሳቸው እጅጉን አስፈሪ
    ስማቸው ግን ጠፋኝ እኚህ ፊት አውራሪ

    Reply
  7. Gadafi Derbew says

    September 15, 2014 03:16 am at 3:16 am

    አልገዛም ብሎ ለፋሽስት ወራሪ
    ለህዝቡ የቆመ አገሩን አክባሪ
    ከሊማሊሞ ገደል እስከ አርማጭሆ ድንበር
    በዱር በገደሉ ጠላትን ሲያሸብር
    የጣልያኑ ዘማች የሰሜኑ አርበኛ
    የውብነህ ልጅ አሞራው በለኛ

    Reply
  8. Seid Ebrahim says

    September 15, 2014 03:17 am at 3:17 am

    ግራ ተጋብቶኛል ማን እንደሆነ እሱ
    እኔ አላወኩትም ይነገረኝ መልሱ

    Reply
  9. Etsub Abebe says

    September 15, 2014 03:21 am at 3:21 am

    የርሻ ሚኒስትሩን
    ደጅ አዝማች ታከለን
    ተክለ ሃዋሪያን
    ይመስላል ፎቶዋቸው
    እንደው ግምቴ ነው
    ካልሆኑ እርሳቸው
    እስቲ ጎበዝ መልስ እኝህ ሰው ማናቸው?

    Reply
  10. Melkamu Mehirete says

    September 15, 2014 03:22 am at 3:22 am

    ጀግናዉ በላይ ዘለቀ – የጎጃሙጀግና
    ስምህ ይወደሳል ዛሬምእንደገና!

    Reply
  11. Getamesay Bekele says

    September 15, 2014 03:24 am at 3:24 am

    ጅግና የወለደው የጅግና ልጅ
    መሸሽ የማያውቀው ይሞታታል እንጂ
    በላይ ዘለቀ ነው የኢትዮጵያ ልጅ

    Reply
  12. Yeab Habesha Abebe says

    September 15, 2014 03:27 am at 3:27 am

    ዝርዝሩ ሲወጣ ጀግኖች ሲቆጠሩ
    ይሄ ሰውየማ ባሻ ቅጣው እንዳይሆኑ

    Reply
  13. Ephrem Nurye says

    September 15, 2014 03:28 am at 3:28 am

    ያበላይ ዘለቀ የጭንጫው በርበሬ
    ጠላት ተሸበረ እየሠማ ወሬ
    የዱሩ ደጅ አዝማች የከተማው ደሃ፥
    ያበላይ ዘለቀ ታላቁ ዝሆን
    ጦር መጣልህ በሉት ይነሣ እንደሆን
    ምንጭ ከህዝብ

    Reply
  14. ገብረየሱስ says

    September 17, 2014 11:36 pm at 11:36 pm

    ኣትቀስቅስልኝ የት ኣገኘሁህና
    በነዚህ ሲነሳ ልቤ ይረበሻል ስራየም ይህ ነውና

    Reply
  15. ገብረየሱስ says

    September 18, 2014 03:30 pm at 3:30 pm

    ለካ ለዚህ ነበር እዳስታውሰው የቀሰቀስከኝ
    ጀግንነት ከምሬት ተደበላልቆብኝ
    እርር እያልኩኝ እምባየ እየተናነቀኝ
    ጀግንነቱ ከነብሴ ተዋህዶ ህያውነት ዘራልኝ
    ባንዳዎች በዙ እንጂ ወንድነቱም ቀሰቀሰኝ
    ለነጋሪ ብቆይም እግዝሔር ሃጥያቱን ይቅልልልኝ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule