አቶ ኑሮ ውድነህ አምና የአዲስ ዘመን በዓልን አስመልክቶ ቤተሰባቸውን ለማስደሰት በማሰብ ያላቸውን ገንዘብ አሰባስበው ገበያ ይሄዱና የበግ ዋጋ ይጠይቃሉ። ሆኖም የበጎቹን ዋጋ ሲሰሙ የሚሮጡት የርቀት መጠን በሜትር እየተነገራቸው እንጂ መሸጫ ዋጋቸው አልመስል እስኪላቸው ድረስ አስደንጋጭ ይሆንባቸዋል።
አውጥተው አውርደው ግን ለቤተሰባቸው መጠነኛም ብትሆን በግ በመግዛት ሃሳባቸው ላይ ፀንተው ረከስ ባለ ዋጋ እጅግ ቀጫጫ የሆነች ግልገል በግ ተከራክረው ይገዛሉ። እናም ወደቤታቸው እየሄዱ እያለ በግ አራጅ ይመለከታሉ።
እሳቸውም ወጉ እንዳይቀርባቸው:
አቶ ኑሮ ውድነህ: ኮራ ጀነን ብለው “ስማ አንተ በግ አራጅ . . . እስኪ ና ወዲህ” ይሉታል።
በግ አራጅ: ወደ ሰውየው እየተጠጋ “አቤት?”
አቶ ኑሮ ውድነህ: በኩራት እንድ ሁለቴ ካገሱ በኋላ “ይህቺን በግ ስንት ትገፍልኛለህ?” ቢሉት
በግ አራጅ: ዞር ብሎ በጓን ተመልክቶ ሳቅና ስላቅ በተሞላበት ድምፅ “ቆዳዋን ነው ወይስ ቀልቧን?” ብሏቸው እርፍ!!
(ምንጭ: Mira Net ፌስቡክ)
Hus says
መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ.,…. ፓረረም…ተረረም…..ትርክ….ምርክህ..ሉሏእንግዲህ እዉነቱ ይነገረን ከለችሁ ቴዲ በዚህ ዘፈኑ በሳ ደረጀ ወርዷ… ልፓረረም …ተረረም