እርሳስ በጓደኛው፤ በብዕር እስክሪፕቶ ባለው ገደብ የለሽ፤ ነጻነቱ ቀንቶ እንዳሻው ቢናገር፤ የልቡን አውጥቶ እንዲህ አልክ ብሎ፤ ያለውን አጥፍቶ የሚያስወግድበት፤ በላጲስ አንሥቶ ስለማይከላ፤ ሲናገር አፍ ከፍቶ ፡፡ እሱ ግን ዘለዓለም፤ በላጲሱ ጠፍቶ መኖሩ አስመርሮት፤ በእጅጉ ተከፍቶ እኔስ ለምን እንዴት? ማለት ጀመረና ጠየቀ አፋጠጠ፤ ተሰማው ፍነና ነጻነቱን ሊያውጅ፤ ተነሣ ይሄ ጀግና ከእንግዲህ በኋላ፤ አለ ቆፍጠን ብሎ የነበረውን ፍርሐት፤ ከልቡላይ ነቅሎ ከእንግዲህ ወዲህ፤ አለ አንሥቶ ክንዱን ባናቴ ያለው ላጲስ፤ ገደብ የለሽ ሥልጣን አብቅቷል ብያለሁ፤ ይሰማ አዋጀ የሚጸና ይሆናል፤ በትውልድ ልጅ ልጀ ከዚህች ቀን በኋላ፤ ማንም ያላወቀ በእውቀት ያለበቃ፤ ከንቱ ያልጠነቀቀ ዐሥሬ እየጻፈ፤ እየለቀለቀ ዐሥሬ የሚያጠፋ፤ መሀይም የወደቀ ውሸት … [Read more...] about እርሳስና ላጲስ
Literature
ጽፈኪን
የዝናብ ሀሳቦች
ዝናብ መች ይከፋል ቢዘንብ ምን አለ መብረቅ ባያስከትል እያጉረመረመ መዝነቡንስ ይዝነብ ማበስበሱን ቢተው ቀን የጣለ አይደል ሌት የሚያዳልጠው። ★★★ ሌቱን ሲዘንብ አድሮ ቀኑን ብራ ዋለ ለምን ይወቅሱታል ሰው መስራት ከቻለ ሲጥልም አይጣል ነው ዶፉ ከወረደ ማን አለብኝ ያለው ገደሉም ተናደ። ★★★ ዝናቡ ከመጣ "አህያ ማይችለው" በጊዜ 'ንጠለል ከወረደ አንዴ ነው እዲህ ከሚፎክር መጣሁ ቀረሁ እያለ ወርዶ ቢያሳርፈን እሱም እፎይ ባለ። ተጻፈ 8/5/2014 … [Read more...] about የዝናብ ሀሳቦች
“ትግሬ ትጠላለህ”
. . . ነፍሱን አይማርና! ያ! ቀጣፊ ከንቱ - የሂትለሩ ጉብልስ፣ አሳልፎ ሄደ፤ መሰሪ ትምህርቱን - ለበረከትና...ለነ አቶ ሽመልስ፤ እነሱም በተራ፣ ለታችኛው አሽከር ነጭ ውሸቱን ዘርተው፣ አጨዱት. . .፣ ከመሩት. . .፣ ማተብ-አልባ አድርገው፤ ከወያኔ ካድሬ፣ የውሸት ፋብሪካ፣ ተመርታ የወጣች፣ የዘረኞች ቋንቋ፣ “ትግሬ ትጠላለህ” የሚሏት ቃል አለች፤ ያገር ወዳዶችን ተቃውሞ ማስቆሚያ፣ በይሉኝታ ገመድ ሸብቦ ማሰሪያ. . .፣ ሆና ታገለግል ዘንዳ የተቃኘች፣ የጥላቻ ዜማ፣ ለጆሮ እምትቀፍ፣ ጩኸት የቁራዎች። . . . እዩትማ እንግዲህ፣ ወደ ውስጥ ሲሰምጥ፣ መብሰሉን ሲያቅተው፣ ሲላወስ እንደ ሊጥ፣ ራሱ በፈጠረው፣ ራሱን አስጨንቆ፣ ጭቃ ሲንከባለል፣ እኩዮቹን ክዶ፣ ራሱን አሳንሶ፣ ሚጢጢዋን ሲያክል፤ ስልጣኑ አስክሮት፣ የግፍ ሃብት ቆዝሮት፣ ንቀት አሳውሮት፣ … [Read more...] about “ትግሬ ትጠላለህ”
ወፍ፣ መብራትና እኛ!!
ይሄ የፓውዛ ግንድ - የመብራት ምሶሶ ያደምቀናል ስንል - ለጭለማው ደርሶ ለካ ጎጆ ሆኗል - የአዕዋፋት ማረፊያ የዕንቁላል መጣያ - የድካም መግፈፊያ፤ ወትሮም እንደዚህ ነው እያለ በሌለ- ላሰቡት ባልዋለ - በቆመ ህይወት ላይ ሲንደረደርበት - ብርቱ ዘሎት ሲሄድ - ሲያልፈው ነው የሚታይ!! (ፎቶ - አብርሃም አዳሙ) … [Read more...] about ወፍ፣ መብራትና እኛ!!
The Last Post-Cold War Socialist Federation
After the fall of the Berlin wall and the disintegration of the former USSR and Yugoslavia, it has widely been assumed that socialist federations have become a thing of the past. Ethiopia’s ethnic federal system however is essentially a socialist federal system based on the notion of the ‘right to self-determination of nationalities’ and a Marxist-Leninist organization of the state and party. This book assesses the Ethiopian ethnic federal system from the perspective of the principles of … [Read more...] about The Last Post-Cold War Socialist Federation
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፫
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፪” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስራ ሁለት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ የኚህ ሰው ማናቸው - አይነተኛ ተግባር አይደለም ሙሉውን - ታሪክ ለመዘርዘር ጥቆማውን አይቶ - አንባቢ እንዲፈልግ ይረዳል ብለን ነው - መንገዱን ለመጥረግ ተሰማ እሸቴንም - በዚህ አጭር ግጥም ማንነታቸውን - ማስቀመጥ ባንችልም በዜማ በቅኔ - አዋቂነታችው ምንጊዜም ይነሳል - ይጠራል ስማቸው ከሊቅ እስከ ደቂቅ - ከሹም እስከ ንጉስ ያገኙ ሰው ናቸው - እጅግ ታላቅ ሞገስ፡፡ ላሁኑ “እኚህ ሰው … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፫
“ክልክል ነው”
ማጨስ ክልክል ነው ማፍዋጨት ክልክል ነው መሽናት ክልክል ነው ግድግዳው በሙሉ ተሰርቶ በክልክል የቱ ነው ትክክል? ትንሽ ግድግዳና ትንሽ ኃይል ባደለኝ "መከልከል ክልክል ነው"፤ የሚል ትዕዛዝ አለኝ፡፡ (በእውቀቱ ስዩም፣ የ፣ሣት ዳር ሐሳቦች፣ 2000) … [Read more...] about “ክልክል ነው”
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፪
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፩” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስራ አንድ ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ ከምንጊዜም በላይ - ብዙ ሰው ተሳትፎ ማንነታቸውን - እንዳሳየን ጽፎ በጀግንነታቸው - መቼም ያልተረሱ እኚህ ስው ነበሩ - ደጃዝማች ገረሱ ላሁኑ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፪” ደግሞ ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ በሚቀጥለው መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡ ጥያቄ ድጋሚ ተወልደው - በህይወት ቢኖሩ የምንፈልጋቸው - ብዙዎች … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፪
ናፍቆት (በኑሬ)
ስጋዬ ሲበላኝ በጥርሴ ነከስኩት፤ ቆዳዬ ሲበላኝ በጥፍሬ ፎከትኩት፤ እፎይ አስታገስኩት፤ ፀጥ ረጭ አረ'ኩት። የውስጥ አጥንቴ ግን ሲበላኝ ነዝንዞ፣ ሲነክሰኝ ጠዝጥዞ፣ ምንም አላረ'ኩት፤ ምንም አላከኩት፤ ላልችል ችየ ቻልኩት። አልፎክተው ነገር ቆዳዬን መንቅሬ፣ አላኝከው ነገር ስጋዬን ሰርስሬ፣ ይሔው እስከዛሬ፣ አጥንቴ እየበላኝ፣ አለሁልሽ ፍቅሬ። ኑረዲን ዒሳ (ዒሻራ) 14/02/1995 ዓ.ም … [Read more...] about ናፍቆት (በኑሬ)
በግ አሳራጅና አራጅ
አቶ ኑሮ ውድነህ አምና የአዲስ ዘመን በዓልን አስመልክቶ ቤተሰባቸውን ለማስደሰት በማሰብ ያላቸውን ገንዘብ አሰባስበው ገበያ ይሄዱና የበግ ዋጋ ይጠይቃሉ። ሆኖም የበጎቹን ዋጋ ሲሰሙ የሚሮጡት የርቀት መጠን በሜትር እየተነገራቸው እንጂ መሸጫ ዋጋቸው አልመስል እስኪላቸው ድረስ አስደንጋጭ ይሆንባቸዋል። አውጥተው አውርደው ግን ለቤተሰባቸው መጠነኛም ብትሆን በግ በመግዛት ሃሳባቸው ላይ ፀንተው ረከስ ባለ ዋጋ እጅግ ቀጫጫ የሆነች ግልገል በግ ተከራክረው ይገዛሉ። እናም ወደቤታቸው እየሄዱ እያለ በግ አራጅ ይመለከታሉ። እሳቸውም ወጉ እንዳይቀርባቸው: አቶ ኑሮ ውድነህ: ኮራ ጀነን ብለው "ስማ አንተ በግ አራጅ . . . እስኪ ና ወዲህ" ይሉታል። በግ አራጅ: ወደ ሰውየው እየተጠጋ "አቤት?" አቶ ኑሮ ውድነህ: በኩራት እንድ ሁለቴ ካገሱ በኋላ "ይህቺን በግ ስንት ትገፍልኛለህ?" … [Read more...] about በግ አሳራጅና አራጅ










