ዝናብ መች ይከፋል ቢዘንብ ምን አለ
መብረቅ ባያስከትል እያጉረመረመ
መዝነቡንስ ይዝነብ ማበስበሱን ቢተው
ቀን የጣለ አይደል ሌት የሚያዳልጠው።
★★★
ሌቱን ሲዘንብ አድሮ ቀኑን ብራ ዋለ
ለምን ይወቅሱታል ሰው መስራት ከቻለ
ሲጥልም አይጣል ነው ዶፉ ከወረደ
ማን አለብኝ ያለው ገደሉም ተናደ።
★★★
ዝናቡ ከመጣ “አህያ ማይችለው”
በጊዜ ‘ንጠለል ከወረደ አንዴ ነው
እዲህ ከሚፎክር መጣሁ ቀረሁ እያለ
ወርዶ ቢያሳርፈን እሱም እፎይ ባለ።
ተጻፈ 8/5/2014
በለው ! says
ተው ውረድ በለው!
**************
እንዲህ ዳምኖ የተንቀረዘዘው
ይወርዳል ሲባል ንፋስ እንዳይቀድመው
ቀስ ብሎ በጣለው ከቶ ሳያጋጨው
ሌቱን ዝነብና ቀኑን ብራ አድርገው
ቀን የጣለ እንደሆን የለ መጠለያው
ጎርፍ ሰው አይመርጥ ማጡም መከራ ነው
አንዱንም ሳንሰራ ቆፋፍረን ትተነው
አህያስ ቢሆን ዝናብ የማይፈራው
ሰማይ ሲጠቁር ወጨፎ አያቄው
ዱላ እንጂ ምክር አይገቤው
ቀስ እያልክ ተው ውረድ በለው!
ያጉረመረመ ንፋስ ውሽንፍር የበዛው
ቀን የጣለው ጨቅይቷል ገብቶ ሊመሰግ ነው።
አድኑኝ የለም አንዴ ከጣለ በኋላ
ተመልሶ እንዲዳምን የሚወጣው ፀሐይ ሌላ….
በለው!
gbz says
grum gtim new.
Solomon says
Ho Gerum