
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፩” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስራ አንድ ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡
መልስ
ከምንጊዜም በላይ – ብዙ ሰው ተሳትፎ
ማንነታቸውን – እንዳሳየን ጽፎ
በጀግንነታቸው – መቼም ያልተረሱ
እኚህ ስው ነበሩ – ደጃዝማች ገረሱ
ላሁኑ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፪” ደግሞ ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ በሚቀጥለው መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡
ጥያቄ
ድጋሚ ተወልደው – በህይወት ቢኖሩ
የምንፈልጋቸው – ብዙዎች ነበሩ
ከነዛ መካከል – ከሚጠቀሱ አንዱ
እኚህ ስው ነበሩ – በሀገር ‘ሚወደዱ
ከታሪካቸው ጋር – ጠቅሳችሁ ንገሩኝ
ሰዉም ያስታውሳቸው – እኔም ደስ ይበለኝ፡፡
Alakachwemi
ፊት አውራሪው ሀብቴ
መጣብኝ ከፊቴ
ምን አሳወቀኝ እቴ
መለስ ነው በሞቴ
አጥንቱን ልቅበረው መቃብር ቆፍሬ
ጎበናን ተሸዋ አሉላን ተትግሬ (አሉላ ናቸው)
ታሪኬ ብዙ ተሰማ እሸቴ፣
ተደብቄአለሁ በገዛ ቤቴ።
The legendary nagadras Tesema Eshetie, father of an other legendary Yidnekachew Tesema.
ከስላምታ ጋር ምሥጋናም አብሮ
ለወለላዬ ከአሁን ጀምሮ
ሥራስ ማለትስ የ ወለላዬ
በ ፬ መስመር ተገላግዬ
ሌላው ሲደክም ሲውተረተር
የወለላዬ ሆነ ባጭር
ለመግጠምማ ለማሳካቱ
የወለላዬ ባናት ባናቱ
መልስ ማግኘቱ ደግ ሆኖ ሳለ
የማጠሩ ግን ሆድ አማለለ
ሥለናፈቀን የግጥም ጮማ
ሽንጠ ረጅሙ ይቅረብ በዜማ
……