ስጋዬ ሲበላኝ በጥርሴ ነከስኩት፤
ቆዳዬ ሲበላኝ በጥፍሬ ፎከትኩት፤
እፎይ አስታገስኩት፤
ፀጥ ረጭ አረ’ኩት።
የውስጥ አጥንቴ ግን ሲበላኝ ነዝንዞ፣
ሲነክሰኝ ጠዝጥዞ፣
ምንም አላረ’ኩት፤
ምንም አላከኩት፤
ላልችል ችየ ቻልኩት።
አልፎክተው ነገር ቆዳዬን መንቅሬ፣
አላኝከው ነገር ስጋዬን ሰርስሬ፣
ይሔው እስከዛሬ፣
አጥንቴ እየበላኝ፣ አለሁልሽ ፍቅሬ።
ኑረዲን ዒሳ (ዒሻራ)
14/02/1995 ዓ.ም
Leave a Reply