
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፪” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስራ ሁለት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡
የኚህ ሰው ማናቸው – አይነተኛ ተግባር
አይደለም ሙሉውን – ታሪክ ለመዘርዘር
ጥቆማውን አይቶ – አንባቢ እንዲፈልግ
ይረዳል ብለን ነው – መንገዱን ለመጥረግ
ተሰማ እሸቴንም – በዚህ አጭር ግጥም
ማንነታቸውን – ማስቀመጥ ባንችልም
በዜማ በቅኔ – አዋቂነታችው
ምንጊዜም ይነሳል – ይጠራል ስማቸው
ከሊቅ እስከ ደቂቅ – ከሹም እስከ ንጉስ
ያገኙ ሰው ናቸው – እጅግ ታላቅ ሞገስ፡፡
ላሁኑ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፫” ደግሞ ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ በሚቀጥለው መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡
ጥያቄ
በያንዳንዱ ጊዜ – በያንዳንዱ ዘመን
በቸገራት ጊዜ – ሀገርን የሚያድን
መነሳቱ አይቀርም – ድንገት አንድ ቆራጥ
ነፍሱን የሚገብር – ህይወቱን የሚሰጥ
እኚህም ታላቅ ሰው – የሰሩትም ሥራ
የምመሰክር ነኝ – ማንንም ሳልፈራ
ሆኖም ከዛ በፊት – እድሉን እንካችሁ
ማንነታቸውን – ንገሩኝ ጽፋችሁ።
Ene yemilew timkhtengoch meche yihon bedimocrasi ena belimat yemiyamnut lenegeru yeshabiya kitirenga silehonachihu alferdibchihum koy tebiku yanen kirchat teshekami alekachihun birihanun yizen sinasgebalachihu maninetachiun tiredalachihu ,
ከላይ የፃፍከው ሰው ሐጎስ የወያኔ
መድከምህ በከንቱ ያሳዝናል ለኔ
ወይ ጥያቄው አልገባሕ ወይ ከብዶሐል መልሱ
እንደው ዘራፌዋ በአሰሱ ገሰሱ
ባንተ አይፈረድም ያቅምህን ነውና
እንደው መዘባረቅ አወይ ድንቁርና
እንኩዋን ልትመልስ ጥያቄ ተረድትህ
ገና ፈራሃቸው ፎቶአቸውን አይትህ
አዎ ያስፈራሉ የኢትዮጵያ ጀግኖች
ጊዜ ለስጥው ቅል ድንጋይ ሰባሪውች
ምናልባት ከሆነ በግጥም መቅረቡ
ለስድ ስድ ንባብ ጠይቅ በአግባቡ
ትንሽ ታገሥና ዞር ዞር ብለህ
ብትመለስ ሽጋ ከራሥህ ጋር ታርቀህ
የምትሰማ ቢሆን ምክር ለአንዳፍታ
ውርደት ቀለብ ላይሆን ሐፍረትም በተርታ
ግጥሙ ላይሆንልህ ይቅር መዘባረቅ
ሐጎስ አባ ሆዱ ኢትዮጵያዊን ለቀቅ‹
ዘጠኝ ዓመት ጎንደር ተኝተው የከረሙት ኮሎኔል ታምራት ይገዙ
Col.Tamirat Yigezu.
Betekekel negerkew yehenen yezemen atela.
ጌታው አቶ ጉርሙ ሆነብን ባጭሩ
ሐሳቡ ይብራራ እንዲታይ ሚስጥሩ
ወጉን ስላገኘን እዚህ መታደሙ
ግልፅነት መልስ ነው ባየው አቶ ጉርሙ
ጉዳዩ አልገባንም ይብራራልን ትንሽ
በግምት ተነስተን ፀሐይ ጠልቃ ሳይመሽ
መልዕክቱ ምን ይሆን የዕርስዎ አስተያየት
ዳር ዳሩን አይሂዱ ሥጋ እንዳየ ድመት
ዘጠኝ ዓመትማ ሁሉም ሰው የተኛል
በናቱ መሐፅን በፍጥረት ይዋኛል
ጎንደር አፍርታለች ጀግኖች በየተራ
ለሁላችን መኩሪያ ታሪኳም የጋራ
መተኛት የሚሉት የቃል አመራረጥ
ማብራሪያው ካልመጣ ካልሆነ አንድ ወጥ
ትችት ያስከትላል ጥርጣሬ አብዝቶ
ፍራቻው ምን ይሆን ከአደባባይ ወጥቶ
ሥለዚህ ወገኔ ግድ የለም አይፍሩ
ግልፅነት ያዋጣል ቢሆንም ባጭሩ
እንደገና መለስ ብለው ከተቻለ
መልሱን ያብራሩልን ፍላጎቱ ካለ
እኝህ ሰው ማናቸው – ብለው ለጠየቁን፣
ለዕውቁ ገጣሚ – ለማስረዳት ሀቁን፣
በዚህ በምስሉ ላይ – የሚታዩት ጀግና፣
የፈጸሙት ገድል ብዙም አልተጠና።
ግና…
ብዙም ባይነገር – ዝክረ ታሪካቸው፣
በሞት ቢለዩንም – በአፍላ ዕድሜቸው፣
ሎረንዞ ታዘዘ – ይባላል ስማቸው።
ፋሽስት ኢጣሊያ -ኢትዮጵያን ለመውጋት፣
ዕቅድ ስታወጣ – ያለምንም ስጋት፣
ከተወለዱበት – ከኤርትራ አምልጠው፣
በጣም ተጠንቅቀው – በጅቡቲ ዞረው፣
ለአጼ ኃይለሥላሴ – ምስጢር ሊያቀብሉ፣
ሎረንዞ ታዘዘ (ወደ አዲስ አበባ) – ሌሊት ኮበለሉ።
ንጉሡ ዘንድ ቀርበው – ጉዳዩን ሲያስረዱ፣
በፈጸሙት ገድል – ስለተወደዱ፣
ሹመት ተሰጣቸው – አገር እንዲመሩ፣
ሕዝብ በቅንነት – እንዲያስተዳድሩ።
ስለዚ ለእኝህ ሰው
ይጻፍ ግድላቸው – ፍሰቱን ጠብቆ፣
ይውጣ አደባባይ – አይቅር ተደብቆ።
ማስታወሻ
በዚህ ታሪክ ውስጥ የተጠቀሰ ጊዜ ፋሽስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ዳግመኛ የወረረችበትን ከ1928 እስከ 1933 ዓ.ም ያለውን ጊዜ ያመለክታል።
Lorenzo
ይድረስ ለአስናቀ ደመናው ወገኔ
ሰላምታና አድናቆ ቢቀበሉኝ ከኔ
መልስ ማለት እንዲህ ሁሉንም አካቶ
የግጥምን ውበት በዛው አሳይቶ
መንደርደሪያውና ማረፊያው የሚታይ
ማብራሪያ ከሥሩ ሁሉም ተከታታይ
ቅደም ተከተሉ እንደተጠበቀ
መሠረቱን ሳይለቅ ባግባቡ ዘለቀ
ከላይ በቀረበው የተሳካ ሥራ
ስለ ተደስትኩኝ እኔም እንደ ተራ
በግጥም ወረዳ በዛ በጎዳናው
ይመላለስበት አስናቀ ደመናው
በማለት ላመስግን ለመልሱ ባለቤት
ታሪኩን ተረዳሁ የቃላትም ሥሌት
ከዚህ በተረፈ መልሱን አስመልክቶ
የዐምዱ ባለቤት አስተያየት ስጥቶ
ሎሬንዞ ታዘዘ ትክክል ከሆነ
አስናቀ ደመናው ወደፊት ታመነ
ወለላዬ ወዳጄ
No—12
የእኚህን አዛውንት ይህን ምስል አይቶ፤
አላውቅም የሚል ሰው ታሪክን ዘንግቶ፤
እዚህ ላይም አይጻፍ አይጫወት እግር ኳስ፤
መልሱን እስኪሰጥህ ይህን ሊቀ-መኳስ።
የኢትዮጵያ ውድ ልጅ ክቡር የቅኔ ሰው፤
የኳስ አባት ወላጅ ሕዝብ የሚያስታውሰው፤
የሚያስደንቅ ልጁ የጥቁሮች ጥበቃ፤
በስፖርት ፍቅር ብቻ አዕምሮው እንደነቃ፤
ታሪክ ፅፎ አለፈ አይደለም ውሸቴ፤
የነጋ ድረስ ልጅ አያቱ እሸቴ።
No 13—-
የራስ መስፍን ምክትል፤
ጉቦ አልወድም እንኳን ሳይል፤
እሱም ገባና በመዘዙ፤
ሌ/ኮረኔል ታምራት ይገዙ፤
ነብሱን ገበረ እንደ መስፍን፤
ሥልጣኑን በሞት ሊሸፍን።
Mengistu Newayn yimeslalu