ድርቅ ጦር እያማዘዘ ነው የሟቾች ቁጥር ተደብቋል በምስራቅና በምዕራብ ሃረርጌ ድርቅ በመግባቱ አርሶ አደሮች ከብቶቻቸውን በርካሽ ዋጋ ለመሸጥ መገደዳቸውን ዶይች ቬለ ሬዲዮ የአሜሪካን የርዳታ ድርጅት USAIDን ጠቅሶ ዘገበ። የድርጅቱ የምግብ አቅርቦት ተንታኝ ብሬክ ስታበረር እንዳሉት በአካባቢው የተከሰተው ድርቅ በሶማሊና በኦሮሞ አርብቶ አደሮች መካከል ግጭት አስከትሏል። በተፈጠረው የውሃ ችግር ምክንያት ከብቶቻቸውን ውሃና ግጦሽ ፍለጋ ይዘው በሚሄዱ አርብቶ አደሮች መካከል የይገባኝልና ውሃና የግጦሹ ሳር ያልቃል በሚል ግጭት ተነስቷል። ተንታኙን የጠቀሰው ሬዲዮ በግጭቱ ስለደረሰው ቀውስ ያለው ነገር ባይኖርም ከተለያዩ ወገኖች የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሶማሊና ኦሮሞ አርብቶ አደሮች መካከል በተከሰተው ግጭት ከሰባ የማያንሱ ሰዎች ተገድለዋል። የበልግ ዝናብ በወቅቱ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
News
ዜና
“በፌዴራል ተደብድባችሁ ትባረራላችሁ!”
“አማራ መሆን ወንጀል ነው? የሌሎች ብሔረሰብ አባላት በፈለጉበት ክልልና ስፍራ ይኖራሉ። አማራ ክልል ውስጥ ሰፊ መሬት ወስደው የሚኖሩ አሉ፤ የሚነካቸው የለም። አማራው እየተመረጠ ለስደት፣ ለመከራ፣ ለእንግልት ይዳረጋል? እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል? ክልሉን እንመራለን፣ የአማራ ህዝብ ወኪል ነን የሚሉ የት ናቸው? ያሳዝናል፣ ለአማራው አልቅሱ፣ ለአማራው አንቡ፣ አማራው አለቀ …” ሲል በስልክ ለጎልጉል አስተያየቱን ሰጠ። መናገር አይችልም፤ ሲቃ ልሳኑንን አንቆ ይዞታል። ከዓመታት በፊት መተከል ዞን ፓዌ የተካሄደውን ያነሳል። 1984 – 85 ፓዌ መንደር አራት በሚባለው የገበያ ቦታ እየገበዩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች ያላሰቡት ደረሰባቸው። በድንገት ገበያው ታወከ። የቻሉትን በቀስት፣ ሌላውን በጥይት ለቀሙት። 56 ሰዎች በቅጽበት ተረሸኑ። ይህ ሁሉ ሲደረግ አገር የሚመሩት ባለስልጣኖች … [Read more...] about “በፌዴራል ተደብድባችሁ ትባረራላችሁ!”
የጎልጉል ቅምሻ
“ሐብቴ ቢያንስ 20ቢሊዮን ፓውንድ ነው” የዓለማችንን ባለጠጋዎች ዝርዝር በማውጣት የሚታወቀው ፎርብስ የተሰኘው መጽሔት የሳውዲ ንጉሥ አብዱላ ወንድም ልጅ የሆኑትን ልዑል አልዋሊድ ቢን ጣላል ያላቸውን ሃብት ዝቅ አድርጎ በመናገሩ ልዑሉ እጅግ ተቆጥተዋል፡፡ የሐብታቸው መጠን ቢያንስ 20ቢሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ እንደሚደርስ የተናገሩት ልዑል በደንብ ከተሰላ መጠኑ 29.6ቢሊዮን ፓውንድ እንደሚደርስ አስታውቀዋል፡፡ ሮልስ ሮይስን፣ ፌራሪን እና ላምበርጊኒስን ጨምሮ ከ200 መኪናዎች በላይ ያሏቸው የ57ዓመቱ ልዑል ጣላል፤ በአውሮጳ እጅግ ውድ የሆኑ ሆቴሎችን ባለቤት ከመሆናቸው አልፎ እጅግ ትልልቅ የሆኑ ሁለት መርከቦች እና የዓለም ትልቁ የግል አውሮፕላን ጀት ባለቤትም ናቸው፡፡ በለንደኑ ሳቮይ ሆቴል፣ በአፕል ኩባንያ፣ በሲቲግሩፕ እና ኒውስ ኮርፕ ያላቸው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ዋጋው ዝቅ … [Read more...] about የጎልጉል ቅምሻ
ኢህአዴግ አሣ አስጋሪዎችን ጨፈጨፈ
የመከላከያ ሰራዊት በድንገተኛ ከበባ ከገደላቸው ንጹሃን ዜጎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን የአቶ ኡሞት ኡዶል ግድያ አስመልክቶ የአሜሪካ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ግድያው ከተፈጸመ በኋላ የሰራዊቱ አባላት አስከሬን አደባባይ በማውጣት ለህዝብ እያሳዩ ደስታቸውን ሲገልጹ የተመለከቱ የጋምቤላ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ክፉኛ መበሳጨታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በጋምቤላ የደረቁን ወቅት ወይም በጋውን በወንዞች ዳር ውሃ ተንተርሶ መኖር የተለመደ ነው። ከቋሚ የመኖሪያ ቀዬ ወደ ወንዝ ዳርቻ በመሄድ አድኖ መመገብና አሳ አስግሮ ዕለትን ማሳለፍ የባህል ያህል ነው። በአገሬው ልምድ መሰረት ከቋሚ መኖሪያቸው ወደ ውሃ ዳር የሚሄዱት ወንዶች ሲሆኑ ጉዞውም የሚደረገው በቡድን ነው። በዚሁ መሰረት በጋምቤላ ክልል የጎክዲፓች ነዋሪዎች የደረቁን ወቅት ለማሳለፍ … [Read more...] about ኢህአዴግ አሣ አስጋሪዎችን ጨፈጨፈ
ከእሁድ እስከ እሁድ
“የሙስሊሙ እንቅስቃሴ ከመንግስት እጅ እየወጣ ነው …” የሙስሊሙ ጥያቄ ከመንግስት እጅ እየወጣ ስለመሆኑ የሚያመላክት ሁኔታ መታየቱን ኢሳት የካቲት 22 ቀን 2005 ዓ ም ዘገበ። ኢሳት እንዳለው የድምጻችን ይሰማ አስተባባሪዎች በነደፉት መርሐግብር መሰረት በአገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ተቃውሞዎች ተደርገዋል። በመቀሌ፣ በመቱ፣ በጅጅጋ፣ በአፋር፣ በጅማ፣ ወልቂጤ፣ ጎንደር፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ተቃውሞዎች ተነስተዋል። በአዲስ አበባ ሙስሊሙ ማህበረሰብ “መሪዎቻችን ይፈቱ ድምጻችን ይሰማ በቤታችን ሰላም ስጡን” የሚሉ መፈክሮችን ማሰማታቸውን ያስታወቀው ኢሳት አሁን ባለው ሁኔታ የሙስሊሙ ጥያቄ ከመንግስት እጅ እየወጣ ለመሆኑ አመላካች እንደሆነ ገልጿል። የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ለመከፋፈል መንግስት በእየለቱ የሚያሰራጨው ፕሮፓጋንዳ ሙስሊሙን በቁጭት እንዲነሳ እያደረገው … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
“በኤርትራ መፈንቅለ መንግስት ይገመታል!”
ኤርትራ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ሁኔታና ወቅታዊው የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ልዕልና መላላት ተከትሎ የፖለቲካ ጨዋታው ጦዟል። በበርካቶች ዘንድ ኢሳያስ እንዳበቃላቸው ተደርጎም እየተወሰደ ነው። ኤርትራ ውስጥ ለውጥ ከተካሄደ ምን ሊከሰት ይችላል የሚለው አጓጊ ጉዳይ የሁሉንም ትኩረት የሳበ አጀንዳ ሆኗል። ኢሳያስ ያሉበት የ"ፖለቲካ ኮማ" ድብታ ውስጥ የከተታቸውም ጥቂት አይደሉም። ኢሳያስን የደረሱበት የኮማ ጣጣ መቀመጫቸውን ኤርትራ ያደረጉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎችና ወታደሮቻቸው የመጨረሻ እድል ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል የጠራ መረጃ ባይሰጥም ሌላውና ዋናው የጡዘቱ አካል እንደሚሆን በርካቶች ይስማማሉ። በቅድሚያ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት የሚጠቁሙም አሉ። ግን ምን አይነት ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት መፍትሄ የሚያቀርቡ የሉም። ዙሪያው ዝግ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኤርትራ ውስጥ … [Read more...] about “በኤርትራ መፈንቅለ መንግስት ይገመታል!”
ከእሁድ እስከ እሁድ
“ጁነዲን ሳዶ ሳዑዲ ገብተዋል” የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩትና በቅርቡ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነታቸው የተነሱት አቶ ጁነዲን ሳዶ ወደ አረብ አገር ማምራታቸውን አውቃለሁ ሲሉ አንድ ጎልጉል ተከታታይ ተናግረዋል። ነዋሪነታቸው ሳዑዲ አረቢያ የሆነው እኚሁ ሰው ላቀረቡት ጥቆማ ማረጋገጫ አላቀረቡም። የሆነ ሆኖ አቶ ጁነዲን ኬንያ የፖለቲካ መጠየቃቸውን ኢትዮቻናል የሚባለው የመንግስት አንደበት የሆነው ጋዜጣ ይፋ አድርጓል። ኢትዮቻናልን በመጥቀስ ዜናውን በርካታ ሚዲያዎች የዘገቡት ሲሆን እስካሁን ድረስ ማስተባበያ አልቀረበም። አቶ ጁነዲን በትክክል ኬንያ የሚገኙ ከሆነ ኢህአዴግ ሊይዛቸው ስለሚችል ወደ ሌላ አገር ባስቸኳይ እንደሚያመሩ ከግምት በላይ አስተያየት ተሰጥቷል። ወደ አውሮፓና አሜሪካ ለማምራት አስቸጋሪ ሁኔታ ስለሚገጥማቸው ምን አልባትም የደንበኛችን ጥቆማ ትክክል … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
ጊዮን ሆቴል የተጠናቀቀው የኦህዴድ ድራማ!!
የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ወገኛ ድርጅት ነው። “ሲያደርጉ አይታ” እንደሚባለው እንደ ኤፈርት አይነት ታላቅ የንግድ ኢምፓየር ከፈተ። ስሙንም ቱምሳ ኢንዶውመንት አለው። ቱምሳ የድርጅት ቅርጽና መልክ ተበጅቶለት ስራ ጀመረ። በበረሃ ትግል ወቅት በነበረን ሃብት መሰረትነው ለማለት ቀዳሚዎቹ የኦህዴድ ምልምሎች ሳንቲም አዋጡና ወደ ተግባር ገቡ። ቱምሳ በስሩ ዲንሾ ትሬዲንግ፣ ዲንሾ ትራንስፖርት፣ አግሮ ኢንዱስትሪና የንግስ ድርጅቱ የጀርባ አጥንት የሆነውን ቢፍቱ ገነማ የሚባል የጫት ንግድ አቋቋመ። የትራንስፖርት ዘርፉን ይመሩ የነበሩት የአቶ ኩማ ደመቅሳ ወንድም እንክት አድርገው በሉትና ከሰረ። ዲንሾ ንግድ ማዳበሪያ እነግዳለሁ ብሎ ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ከንግድ ባንክ ተበደረና ታሪኩን በኪሳራ ደመደመው። ዲንሾ አግሮም ከእህት ኩባንያዎቹ እንደተማረው ኪሳራ ተከናንቦ መሬት … [Read more...] about ጊዮን ሆቴል የተጠናቀቀው የኦህዴድ ድራማ!!
ከእሁድ እስከ እሁድ
ቴዲ አፍሮ በስራው ተከብሮ ተሸለመ ታዋቂ የሚባሉት የኪነት ባለሙያዎች በአብዛኛው የህዝብ አንደበት ከመሆን ይልቅ "አጫፋሪነትን" መርጠዋል በሚል በሚዘለፉበት ወቅት ላይ ከየአቅጣጫው ምስጋና፣ ውዳሴና አድንቆት የሚዘንብበት ቴዲ አፍሮ በስራው ተከብሮ ተሸለመ። በካሊፎርኒያ ግዛት የሳን ሆዜ ከተማ (City of San Jose) በኢትዮጵያና በኤርትራ ወዳጆች ፎረም ስም ቴዲ አፍሮን የሸለመው ፌብሩዋሪ 15 ቀን 2013 ነው። የምስጋና ሽልማት /Commendation Award/ የተሰጠው ቴዲ አፍሮ ስለተሰጠው ሽልማት የቀረበው ምክንያት "ራሱን ለሰላምና ለመፈቃቀር አግልግሎት አሳልፎ ሰተ በጣም ተደናቂና ታዋቀቂ የሙዚቃ ሰው" በሚል ሙገሳ መሆኑን የቴዲ አፍሮ የፌስቡክ ገጽ ጠቁሞዋል። ቴዲ አፍሮ በኤርትራ አዲስ ትውልድ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያለው የጥበብ ሰው ነው። አርቆ በማስተዋልና ጊዜና … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
“ኢህአዴግ አንገቱን ታንቋል”
/ዜና ጎልጉል/ ኢህአዴግ ላይ ቀደም ሲል ሲቀርቡበት ከነበሩት ሪፖርቶች በተለየ ጥቅሞቹ ላይ ያነጣጠሩ አስደንጋጭ መረጃዎች እንደወጡበት ተሰማ። መረጃው የኢህአዴግን አንገት የማነቅ ያህል እንደሚቆጠርና ለተግባራዊነቱ የተንቀሳቀሱትን አካላት "የአስተዋይነት" ትግል ውጤት እንደሆነ ተጠቁሟል። ኢህአዴግ በህዝብ ስም በብድርና በርዳታ የሚያገኘውን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለፖለቲካ ስራ እንደሚያውለውና ለአፈና ተቋማቱ ማጠናከሪያ እንደሚጠቀምበት የተከሰሰበት ሪፖርት መጠናቀቁን የገለጹት የጎልጉል ታማኝ ምንጮች ናቸው። ምንጮቹ እንዳሉት ሪፖርቱ የቀረበለት የዓለም ባንክ በቅርቡ መረጃውን ተቀብሎ ርምጃ ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል። ኢህአዴግ ርምጃው ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ለማክሸፍ የተለመደውን ሩጫ መጀመሩ ተሰምቷል። በኢህአዴግ ላይ የቀረበው ሪፖርት የመፍትሄ ሃሳብም ያካተተ እንደሆነ የተናገሩት … [Read more...] about “ኢህአዴግ አንገቱን ታንቋል”