የአገራቸውን አጠቃላይ ሁኔታ እና መጪው ጊዜ ምን እንደሚመስል፤ የአገራቸውን የወደፊት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ፣ … ሁኔታ እንዲሁም አሜሪካ በቀጣይ ዓመታት የምትከተለውን የአጭርና የረጅም ጊዜ የውጪ ፖሊሲ ዕቅድ በተመለከተ ለሁለተኛ ጊዜ ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ማክሰኞ ምሽት ለምክርቤቱ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ኦባማ በርካታ ጉዳዮችን ዳስሰዋል፡፡ አፍሪካና ቻይናም የንግግራቸውን ሙሉ ቀልብ የሳቡ ነበሩ ባይባልም ሳይጠቀሱ አልታለፉም፡፡ በተለይ ስለአፍሪካ እንዲህ ብለዋል፤- ‹‹… የተለያዩ አፍቃሪ የአልቃይዳ ወኪሎችና አክራሪዎች ከአረብ ምድር እስከ አፍሪካ ብቅ እያሉ መጥተዋል፤ እነዚህ ቡድኖች ሊያመጡ የሚችሉት አደጋ እንደዚያው እያደገ መጥቷል፡፡ ይህንን አደጋ ለመቋቋምም በአስር ሺዎች የሚጠጉ ልጆቻችንን በመላክም ሆነ አገራትን መቆጣጠር አያስፈልገንም፡፡ ይልቁንም … [Read more...] about በአልቃይዳ ሰበብ ቻይናን መቆጣጠር
News
ዜና
ከእሁድ እስከ እሁድ
“ኢትዮጵያን ቀስ ብለን ስሟን እንቀይራለን” Ethio Muslims Interfaith Dialogue for Justice በሚል ስያሜ በሚታወቀው የፓልቶክ ክፍል ውስጥ "አቡ ሃይደር" በሚል ቅጽል ስም የሚታወቁት ተናጋሪን በመጥቀስና ንግግራቸውን በቀጥታ በማሰማት የሙስሊሞች እንቅሰቃሴ የመጨረሻ ዓላማ ኢትዮጵያን የሙስሊም መንግስት ማድግ እንደሆነ በEthio Christians and Muslims discussion 4 solution የፓልቶክ ክፍል "ዘ ቤስት ሶሉሺን" በሚል የቅጽል መጠሪያ የሚታወቁት ተናጋሪ አስታወቁ። የአቡሃይደርን ንግግር በተደጋጋሚ በድምጽ ማስረጃነት ሲቀርብ ኢትዮጵያን የእስላማዊ መንግስት ከማድረግ ባሻገር አስፈላጊ ከሆነ መጠሪያ ስሟን እንደሚቀይሩ ሲናገሩ ተደምጧል። "አገሪቱ የእኛ ናት። ካፊሮች አገሪቱ የኛ ናት የሚል የታሪክ ምስክር ያላቸውም" ሲሉ የተናገሩትን … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
“የሰከነው ትግል” በጋንዲ ምድር ተዘራ
“መጪው ጊዜ በእጃችሁ ነው” የንግግሩ መግቢያ ነበር። “በጨለማ ውስጥ ነን። ከፍተኛ በደል እየተፈጸመብን ነው። ለመረጃ ሩቅ የሆኑ ሰዎች፣ የስልጣኔ ጮራ ያልበራላቸው ሰዎች፣ የመማር ዕድል ያላቸኙ ሰዎች፣ ግፍ እየተፈጸማባቸው ነው። መብታቸውና ሰብዓዊ ክብራቸው ተረግጧል። በጉልበት መሬታቸው እየተነጠቀ በልማት ስም እየተሸጠ ነው። ይህ ሁሉ የሚደረገው በህንድ ህዝብና መንግሥት ስም ነው። ይህ አሳዛኝ ተግባር በስማችሁ እየተከናወነ ነው። በናንተ ስም። ተቃወሙ። ታገሉ። አግዙን። ለዚህ ነው መጪው ጊዜ በእጃችሁ ነው የምለው” ይህ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ንግግርና የትግል ጥሪ የቀረበው ህንድ ታዋቂው በሆነው ጃዋሃርላል ኔህሩ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፊትለፊት ነበር። “ትግል አርቆ ማሰብ ይጠይቃል፤ እቅድ ይፈልጋል። ትግል ህዝብን ማስተባበርና የረዥም ጊዜ … [Read more...] about “የሰከነው ትግል” በጋንዲ ምድር ተዘራ
እስላማዊ መንግሥት በኢትዮጵያ?
መለስ የሚሌኒየም ንግሥ እለት ተገኝተው ዘፈን ምረጡ ሲባሉ “የሱዳን ዘፈን ይሁንልኝ” ብለው ከባለቤታቸው ጋር የተምነሸነሹበት የሚሌኒየም አዳራሽ በአቶ አሊ አብዶ የከንቲባነት ዘመን ለመስጊድ ማሰሪያ ተጠይቆ እንደነበር ፣ አቶ አሊም ቦታውን ለተጠየቀው ዓላማ እንዲውል መፍቀዳቸውንና ውሳኔው ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ኢህአዴግ ዘንድ መረጃው ደርሶ መታገዱን ውስጥ አዋቂዎች ያስታውሳሉ። ከምርጫ 97 በኋላ ደግሞ መላ ሰውነታቸውን የተሸፋፈኑ ሙስሊሞች እየበዙ በመሆኑ ጉዳዩ ሥር ሳይሰድ፣ ከጀርባው እነማን እንዳሉበት ክትትል እንዲደረግ በታዘዘው መስረት የብሔራዊ የመረጃና የደህንነት አገልግሎት አስገራሚ ሪፖርት አቅርቦ እንደነበር እነዚሁ ክፍሎች ይናገራሉ። በክትትሉ የተገኘው መረጃና የመጨረሻ ድምዳሜ ተሸፋፍነው የሚለብሱት እህቶች አብዛኞቹ ሴተኛ አዳሪዎችና የገንዘብ ችግር ያለባቸው የሌላ ሃይማኖት … [Read more...] about እስላማዊ መንግሥት በኢትዮጵያ?
Indian investors are forcing Ethiopians off their land
Ethiopia's leasing of 600,000 hectares (1.5 acres) of prime farmland to Indian companies has led to intimidation, repression, detentions, rapes, beatings, environmental destruction, and the imprisonment of journalists and political objectors, according to a new report. Research by the US-based Oakland Institute suggests many thousands of Ethiopians are in the process of being relocated or have fled to neighbouring countries after their traditional land has been handed to foreign investors … [Read more...] about Indian investors are forcing Ethiopians off their land
የጎልጉል ቅምሻ
ሐላል ምግብ ውስጥ የአሳማ፤ በርገር ሥጋ ውስጥ ደግሞ የፈረስ ዲኤንኤ ተገኘ በእንግሊዝ አገር ለእስረኞች ሐላል ምግቦችን የሚያቀርቡ ድርጅቶች (ቸርቻሪዎች) በሚያቀርቡት ሥጋም ሆነ የጣፋጭ ምግብ ውጤቶች ውስጥ የአሳማ ሥጋ (ዲኤንኤ) እንደሚገኝ ከታወቀ ወዲህ በርካታዎቹ ለእስርቤቶቹ ምግብ ማቅረባቸውን እንዲቋረጥ የፍትህ ሚ/ር አዝዟል፡፡ በበርካታ አገራት የፈጣን ምግብ አቅራቢ እንደሆነ የሚታወቅ በርገር ኪንግ በሚሸጠው የበርገር ሥጋ ውስጥ የፈረስ ዲኤንኤ እንደሚገኝ ባለፈው ሐሙስ አምኗል፡፡ የአሳማ ሥጋ መገኘቱ ከታወቀ ወዲህ በርካታ ሙስሊም እስረኞች ተቃውሟቸውን እየገለጹ ሲሆን የፍትህ ሚ/ር በአቅራቢዎቹ ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ቃል ሰጥቷል፡፡ በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ሐዘን የተሰማቸው ሙስሊም አስተያየት ሰጪዎች ጉዳዩ ሆን ተብሎ የተደረገ ጉዳይ በመሆኑ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በሙሉ በአንድ … [Read more...] about የጎልጉል ቅምሻ
ከእሁድ እስከ እሁድ
ማክሰኞ ኢቲቪ ድግስ አለበት “ክርስቲያኖችም ሙስሊሞችም ልባችሁን ጠብቁ” “እስላማዊ መንግስት በኢትዮጵያ” የማስታወቂያው ፍንጣሪ ሃረግ ነው። በአብዛኛው የማህበራዊ ድረገጾች አስቀድመው የሚያስተላልፉት መልዕክት ደግሞ “ክርስቲያኑም ሙስሊሙም ልባችሁን ጠብቁ የሚል” ነው። ኢቲቪ ድግስ አለኝ ሲል ለማክሰኞ ቀጠሮ የያዘለት ዘጋቢ ፊልም አክራሪነት ላይ የሚያጠነጥን እንደሆነ ቀደም ብሎ የተሰራጨው ማስታወቂያ ያስረዳል። ከኢህአዴግ አፈጣጠርና የፕሮፓጋንዳ ልምዱ በመነሳት ለማክሰኞ በቀጠሮ የተዘጋጀውን ዘጋቢ ፊልም “አኬልዳማ ቁጥር ሁለት” በሚል ብዙዎች ሰይመውታል። አንዳንዶች ደግሞ “አዳዲስ ሆዳሞችን እንተዋወቃለን” ሲሉ ፊልሙ በደህንነት ሃይሎች የተቀነባበረ እንደሆነ መረጃ እንዳላቸው ይገልጻሉ። “የውሸት አባት ኢህአዴግና ወዲ ስምዖን የቆመሩት ቁማር” ሲሉ የሚገልጹትም ጥቂት … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
የሚድሮክ ልዑክ ለአባዱላ ያቀረቡት ጥያቄ
የሚድሮክ ኢትዮጵያ የበላይ አመራሮች አባዱላ ገመዳን ለማነጋገር ቀጠሮ አስይዘው የተወሰኑ ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ጠይቀው እንደነበር የጎልጉል ምንጮች አስታወቁ። በኦሮሚያ የሚገኙ የሼኽ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ንብረት የተባሉ ድርጅቶች ላይ የተደረጉ የሂሳብ ምርመራዎችና ግብር ታሪፍ የተሰራባቸው ሰነዶች ዝርፊያ ምርመራ ተድበስብሶ እንዲታፈን መደረጉ እስካሁን ምላሽ ያላገኘ ጉዳይ እንደሆነ ተጠቆመ። አባዱላ ገመዳ የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ወቅት ሚድሮክ የሰየማቸውና በዶ/ር አረጋ የሚመራ ልዑክ ቢሯቸው የተገኘው በወቅቱ የሼክ መሀመድ ድርጅቶች ላይ ክልሉ ግብር እንዲከፍሉ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ነበር። የክልሉ ካቢኔ ግብር መክፈል የሚገባቸው ባለሃብቶች በሙሉ ሊከፍሉ የሚገባቸውን ውዝፍ እዳ ገቢ እንዲያደርጉ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ክልሉ ውስጥ … [Read more...] about የሚድሮክ ልዑክ ለአባዱላ ያቀረቡት ጥያቄ
“የመበስበሱ በሽታ ሁሉም ዘንድ ነው”
የአቶ በረከት ስምዖንና የአቶ ስብሃት ነጋ የደፈጣ ውጊያ ገሃድ መውጣቱን የሚያመላክት መረጃ ይፋ መሆኑን ተከትሎ በህወሃት መንደር ውስጥ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሯል። ጉዳዩን የሚከታተሉ እንደሚሉት ልዩነቱን ለማርገብ በከፍተኛ ደረጃ ጥረት ቢደረግም ሊሳካ አልቻለም። ከፍተኛ ስልጣን የያዙትንና አቶ መለስ ለመተካካት ያዘጋጇቸውን አዳዲስ አመራሮች፣ በቅርቡ ደንብና ህግ በመጣስ ሹመት የሰጡዋቸውን ጨምሮ የሰራዊቱን አዛዦችና ደህንነቱን ከጎናቸው ያሳተፉት ክፍሎች የተፈጠረው ልዩነት እልባት ማግኘት ይገባዋል የሚል አቋም መያዛቸውን የሚጠቁሙ ክፍሎች እነማን ተለይተው እንደሚመቱ ለመገመት አስቸጋሪ መሆኑንን ይገልጻሉ። “ፓርቲያችን ከእንጥሉ በስብሷል” በማለት ከዛሬ አስራአንድ ዓመት በፊት በአገር ክህደት ሊያስወግዷቸው የተነሱትን ጓዶቻቸውን የረቱት መለስ የተጠቀሙበት ዋንኛ ስልት አባይ ጸሃዬን … [Read more...] about “የመበስበሱ በሽታ ሁሉም ዘንድ ነው”
የጎልጉል ቅምሻ
“የድመት ጸጉር የመብላት ሱሰኛ ነኝ” የሱሰኛነት ነገር ሲነሳ ሰሞኑን ከወደ ሚሽጋን ጠቅላይግዛት የተሰማው ጉድ የሚያሰኝ ነው፡፡ የ43ዓመቷ ሊሳ በቀን ሦስት ሩብ መጠን ያለው የድመት ጸጉርጥቅል እንደምትበላ ተናግራለች፡፡ “የድመት ጸጉር የመብላት ሱሰኛ ነኝ” በማለት የምትናገረው ይህች ግለሰብ ሱሰኝነቱ የጀመራት የዛሬ 15ዓመት እነደሆነና እስካሁ 3200 ጥቅርል እንደበላች ታስረዳለች፡፡ ጥቅልሉን ከወለል፣ ከሶፋ፣ … እንደምታዘጋጅ ገልጻ በጣም አሪፍ የሆነው ግን በቀጥታ ከድመቷ የምታገኘው እንደሆነ ተናግራለች፡፡ ማርገዝ --› መጠጣት --› ጽንሱ ማበላሸት --› ዳረጎት ማግኘት ከደቡብ አፍሪካ አስደንጋጭ ነገር ከተሰማ ጥቂት ቀናት ቢያልፉም የዜናው አስደንጋጭነት ግን እስካሁንም እውን ነው፡፡ ከመንግሥት የሚገኝ ጥቂት ዳረጎት ተጠቃሚ ለመሆን እርጉዞች ልጆቻቸውን በሽተኛ ሆነው … [Read more...] about የጎልጉል ቅምሻ