• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከእሁድ እስከ እሁድ

April 8, 2013 03:14 am by Editor Leave a Comment

ሼኽ መሐመድ “ለቀቅ አድርጉን” አሉ
ከኢትዮጵያ “አንድም ሳንቲም” እንዳልወሰዱ ተናገሩ

ባለፈው ሳምንት ከፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የገዟቸውን የላይኛው አዋሽ አግሮ ኢንዱስትሪ፣ የጐጀብ እርሻ ልማትና የቡና ማደራጃና ማከማቻ ድርጅት የርክክብ ፊርማ በሆቴላቸው ሸራተን አዲስ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ውለታ በፈጸሙበት ወቀት “አንዳንድ የመገናኛ ብዙኅን እባካችሁ ለቀቅ አድርጉን እንሥራበት፡፡ አሁን ጊዜው የሥራ ነው እንጂ የአሉባልታ አይደለም፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናትንም አትጨቅጭቋቸው፡፡ ውጤቱን የሚያውቁት እነሱ ናቸው፡፡ ለእናንተ በሬ እንኳ ዝግ ነው፡፡ እባካችሁ በአገር ልማት ላይ እወቁበት፡፡ ነገር ፍለጋ፣ ቁስቆሳና አሉባልታ አያዋጣም፤ አገራችንን እንገንባ፤” በማለት ማሳሰቢያ አዘል መልዕክት ማስተላለፋቸውን ሪፖርተር ዘገበ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት በስነ ስርዓቱ ላይ የተለያዩ ሚዲያዎች እንዲገኙ በጋበዘው መሰረት ሪፖርተር ጋዜጣ ሸራተን ሆቴል የላካቸው ጋዜጠኞች “ሪፖርተር ከሚድሮክ ጋር ተስማምቶ እስከሚሠራ ድረስ ከእኛ ጋር እንዲሠራ አንፈቅድለትም፤” በማለት በሆቴሉ ጥበቃዎች አማካይነት እንዳስወጣቸው ሪፖርተር ዘግቧል። ባለሃብቱ በፊርማው ስነስርዓት ላይ “አንድም ሳንቲም አልወሰድንም። የምናለማው ከውጪ በምናስገባው ገንዘብ ነው” ማለታቸውንና፣ የኤጀንሲው ዳይሬክተርም አብዝተው እንዳመሰገኑዋቸው ሪፖርተር አስታውቋል። ሪፖርተር ሼኽ መሐመድን በተመለከተ እየተከታተለ ዜና የሚያቀርብ ብቸኛ ጋዜጣ መሆኑ ይታወቃል። ከዚሁ ጋር ተያያዥነት እንዳለው በሚነገርለት ኦፕሬሽን የጋዜጣው ባለንብረት አቶ አማረ አረጋዊ የግድያ ሙከራም እንደተደረገባቸው ይታወሳል። (ፎቶ: ሪፖርተር)

ቴዲ አፍሮ አይኑን በአይኑ አየ

ከሳምንት በፊት አፕሪል ዘፉል እየተባለ በሚቀለድበት ቀን፣ ቴዲ አፍሮ ከባለቤቱ አምለሰት ሙጬ ጋር ፍቺ ፈጸመ በሚል ወዳጆቹን ያስደነገጠ ዜና መዘገቡ ይታወሳል። ይህ ኢትዮጵያዊ ወግ የሌለው “ከርዳዳ” ቀልድ ላስደነገጣቸው ሁሉ ቴዲ አዲስ ዜና ይዞ ብቅ ብሏል።

ኢኤምኤፍ እንደዘገበው ቴዲ አፍሮ የወንድ ልጅ አባት ሆኗል። ቴዎድሮስ ካሳሁን ወንድ ልጅ ካገኘ ስሙን “ሚካኤል” ብሎ እንደሚጠራው አስቀድሞ በተናገረው መሰረት የባለቤቱ ውድ ስጦታ የሆነውን ወንድ ልጅ ሚካኤክ ቴዎድሮስ ካሳሁን ብሎ እንደጠራው ከዘገባው ለመረዳት ተችሏል። ቴድሮስም ሆነ ባለቤቱ ለወደፊት ስንት ልጅ የመውለድ እቅድ እንዳላቸው እስካሁን በይፋ አልተናገሩም። ዝግጅት ክፍላችን ለቴዲ አፍሮና ለባለቤቱ እንዲሁም ለአድናቂዎቻቸው በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ይላል። (ፎቶ: teddyafro.info/)

ከ106 በላይ ክስ ያለበት ተመስገን “እንታገል” አለ

የፍትህ ጋዜጣ ሲታገድ አዲስ ታይም የሚል መጽሔት ማሳተም ጀምሮ ነበር። ፍትህን የከረቸሟት አምባገነኖች አዲስ ታይምንም ጠረቀሟት። ለሶስተኛ ጊዜ ልዕልና ጋዜጣ ማሳተም የጀመረው ተመስገን ደሳለኝ አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ የማሳተም ህጋዊ መብቱ ተገፏል። አጋጣሚውን የኮነነው ተመስገን “ያለኝ አማራጭ ከሲቪክ ተቋማት ጋር በመተባበር፣ ከጫካ ትግል በመለስ ያሉትን የሰላማዊ ትግል አማራጮች በመጠቀም፣ አስገዳጅ ሁኔታ በመፍጠር መብታችንን እናስከብራለን” ማለቱን ኢሳት አስታውቋል።

“ዜና በጫወታ” በሚል ገጽ የሚጽፈው አቤ ቶኪቻ “እንኳን ልዕልና መለስም ተሰውተዋል” በማለት ልዕልና መሰዋትዋን በኢህአዴግ ቋንቋ በመግለጽ አምባገነኖቹን ተሳልቆባቸዋል።

“ልዕልናጋዜጣ ታግዳለች፤ እንደ “ፍትህ” እና አዲስ ታይምስ ሁሉ የስርዓቱ የአፈና ሰለባ ሆናለች፤ የሚገርመው ግን መታገዷ አይደለም፣ የታገደችበት መንገድ እንጂ፡፡ ከዚህ ቀደም ደጋግሜ እንደገለፅኩት አቶ መለስን የተኩት ሰዎች ከእርሱም የባሱ ጭፍን አምባገነኖች ናቸው፡፡ ማንንም አይፈሩም፡፡ እግዚአብሄርንም ቢሆን በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ካልተጠመቅህ አምላክ ሆነ እንድትቀጥል አንፈቅድልህም” እንደሚሉ ተመስገን ግርምቱን የጋዜጣዋን መታገድ አስመልክቶ ሰሞኑን በተለያዩ ድረገጸች ባሰራጨው ጽሁፍ አመልክቷል። (ፎቶ: አውራምባ ታይምስ)

አንደበት

“እኛ ከክልል ሶስት ውጪ ስለሚኖሩ አማሮች አያገባንም፡፡ ምክንያቱም በነፍጠኝነት ለወረራ የሄዱ ናቸው” አቶ ታምራት ላይኔ ስልጣን ዘመናቸው በርካታ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ተወላጆች በየአካባቢው ሞትና መፈናቀል እየደረሰባቸው ስለመሆኑ በተጠየቁበት ወቅት ከመለሱት፤

“ከኢትዮጵያ አስመራ፣ ኤርትራ የሄዱት ለአፈና ነው። ስለነሱ ጉዳይ አይመለከተንም” የአንድነት ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አቶ ስዬ አብርሃ የመከላከያ ሚኒስትር እያሉ ኤርትራ ስለተማረኩና በኤርትራ ስቃይ እየደረሰባቸው ስላሉ ወገኖች ተጠይቀው ከመለሱት፤

የቤኒሻንጉል ጉምዝ መሪ የተምታታ መግለጫ ሰጡ

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ፕሬዚዳንት አቶ አህመድ ናስር በህገወጥ መንገድ መፈናቀላቸውን የሚገልጹትን   አማርኛ ተናጋሪዎች አስመልክቶ አስተባበሉ። ባለስልጣኑ Ethiopian forum for political civility on current issues ከሚባለው የፓልቶክ ክፍል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተፈናቃዮቹ መኪና ተከራይተውና ንብረታቸውን ይዘው በፍላጎታቸው ወደ ክልላቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል። በግፍ ተፈናቅለናል የሚሉት አማርኛ ተናጋሪዎች እስካሁን መፍትሄ አላገኙም። ንብረታቸው ተዘርፏል። ለዓመታት ያፈሩት ሃብት መና ቀርቷል።

እርስ በርሱ የሚጋጭ ምላሽ ሲሰጡ የነበሩት አቶ አህመድ “ችግር ካለ ለመገምገም ከአማራ ክልላዊ መንግስት ጋር በጋራ ተቀምጠናል” በማለት የማጣራት ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል። “አንድ ክልል የመሬት እጥረት ካጋጠመው በሁለቱ ክልሎች በጋራ በሚደረግ ስምምነት ይከናወናል” በማለት የክልሎችን መብት አጉልተው አሳይተዋል። ለዓመታት በክልሉ የኖሩና ህጋዊ ሰነድ ያላቸውን ዜጎች አማርኛ ስለተናገሩ ብቻ ማፈናቀላቸው መዘዝ እንደሚያስከትል የተረዱት አቶ አህመድ፤ ብሄር ባይጠቅሱም በኢንቨስትመንት ስም ሰፋፊ መሬት ይዘው እየሰሩ ያሉ እንዳሉ ጠቁመዋል። ከብአዴን አባላት ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ እየተሰማ በመሆኑ ሁኔታውን ለማርገብ በፌደራል ደረጃ ሩጫ መጀመሩንና የተወሰኑ የወረዳ ባለስልጣናትን ለመቅጣት እንደታሰበ ለማወቅ ተችሏል።

“የመለስ ፋውንዴሽን” ተመሠረተ
ወ/ሮ አዜብ የቦርዱ ፕሬዚዳንት ሆነዋል

በሟቹ ጠ/ሚ/ር ስም የተቋቋመና “አቶ መለስ በማህበረ ኢኮኖሚ ዘርፍ ያበረከቷቸውን አስተዋፅኦዎችን ከመዘከር ባለፈ የእሳቸውን ራእይ አስቀጥሎ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ብሎም ለዓለም ብልፅግና የሚሰራ ፋውንዴሽን” መመሥረቱን ኢሬቴድ አስታወቀ፡፡

የፋውንዴሽኑን ምስረታ አስከትሎም በተደረገ ምርጫ ባለቤታቸው ወ/ሮ አዜብ የቦርዱ ፕሬዚዳንት፤ አቶ ካሳ ተክለብርሃን ምክትል ሆነው የተመረጡ ሲሆን ጄ/ል ሳሞራ ዩኑስ፣ ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም፣ አቶ ሱፊያን አህመድ፣ ወ/ሮ አስቴር ማሞ፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እና ሌሎች በድምሩ 13 አባላትን ያካተተ ቦርድ መመሥረቱን አብሮ ተዘግቧል፡፡ ከ13ቱ አባላት መካከል አራቱ የአቶ መለስ ቤተሰብ አባላት መሆናቸውን የዘገበው ዜና፤ ወ/ሮ አዜብ የቦርዱ የመጀመሪያ ፕሬዚዳንት ሆነዉ ከተመረጡት በኋላ ባደረጉት ንግግር “የተሰጠኝ ሃላፊነት ከባድ ቢሆንም ከኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በመሆን እወጣዋለሁ” ማለታቸውን ጨምሮ ገልጾዋል፡፡

የፋውንዴሽኑን መመሥረት አስመልክቶ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ እንዲሁም የካናዳው አምባሳደር ዴቪድ አሸር ድጋፋቸውን ገልጸዋል፡፡ በተለይም የካናዳው አምባሳደር “በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ስም የተቋቋመው ፋውንዴሽን ለምርምርና ለጥናት መሰረት የሚጥል ነው” ማለታቸውን በመለስ ስም የተከፈተ የፌስቡክ ገጽ ዘግቧል፡፡

ዜናውን አስመልክቶ አስተያየት የሰጡ አንባቢ “በርግጥ የአቶ መለስ ጉዳይ ከስማቸው ጀምሮ ከበረሃ እስከ መሪነት ድረስ የፈጸሙት ተግባራት እንዲሁም የ4ሺህ ብር ደመወዝተኛ በመሆን አገር የማስተዳደራቸው ጉዳይ በርካታ ምርምርና ጥናት የሚያሻው ነው” በማለት ስላቅ አዘል ምልከታቸውን ሰጥተዋል፡፡ (ፎቶ: የአቶ መለስ ሐውልት ጅጅጋ)

 

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am
  • የኤሊያስ መሠረትን ፌክ መረጃ ማን ያጋልጥ? February 19, 2025 06:00 pm
  • አዘርባጃን፡ የሻዕቢያን ሸምቀቆ ማጥበቂያ?! February 19, 2025 12:29 am
  • የአሜሪካ ድምፅ/ቪኦኤ ይዘጋ ተባለ  February 12, 2025 03:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule