የላሊበላ ቅርስ አደጋ ላይ ነው ታሪካዊና የኢትዮጵያ የጥንት የስልጣኔ አሻራ ምስክር የሆኑት ውድ የላሊበላ ውቅር አቢያተክርስቲያናትና ቅርሶች በመፈራረስ ላይ መሆናቸው በተደጋጋሚ መጠቀሱ ይታወቃል። መንግስትም በተደጋጋሚ ቅርሶቹን ለማደስ እንደሚሰራ ማስታወቁም አይዘነጋም። በሳምንቱ መጨረሻ በስፍራው የተገኙ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት “ስጋት አለን። ቅርሶቹ በመፈራረስ ላይ ናቸው” ሲሉ በመንግስት ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በተደጋጋሚ የላሊበላ ውቅር አቢያተ ክርስቲያናትና ውድ ቅርሶች የመፍረስ አደጋ እንደከበባቸው ቢገለጽም ምላሽ አለማግኘቱ አነጋጋሪ ሆኗል። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነና የመንግስት ቴሌቪዥን ይፋ እንዳደረገው ታሪካዊዎቹ የኢትዮጵያ ልዩ መገለጫዎች የሚፈለጉት ለቱሪዝም ገቢ ብቻ ነው። በዓመት እስከ 40 ሺህ የሚደርሱ ቱሪስቶች ይጎበኟቸዋል። ከመቶ ሃያ ሚሊዮን ብር በላይ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
News
ዜና
“በህወሓት ተወርረናል!” ደቡብ ሱዳኖች
አዲሷ አገር ደቡብ ሱዳን እንደ መንግሥት ተመቻችታ አልቆመችም። የፋይናንስ ስርዓቱም የተረጋጋ አይደለም። የገቢና ወጪ ቁጥጥሩ ክፍተት ያለበት በመሆኑ ለሙስና የተጋለጠ ነው። የጁባ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ የአገሪቱ ሃብት በግለሰቦች እጅ ነው። በተለያዩ መስኮችም የባለሙያና የአቅም ችግር አገሪቱ ምስጢርና የኔ የምትለው አስተዳደር እንዳይኖራት አድርጓታል የሚሉ በርከቶች ናቸው። ይህንኑ ክፍተት ለመሙላት በሚል ኢህአዴግ ደቡብ ሱዳንን ከተወዳጀ ጀምሮ ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል። የመከላከያ መኮንኖችን አሰልጥኗል፤ የፖሊስ ኃይሉን አደራጅቷል። በአማካሪነት በተለያዩ ዘርፎች የራሱን ሰዎች ጠቅጥቆ አሁንም ይህንኑ ድጋፉን አጠናክሮ ቀጥሏል። የተመሰረተው ግንኙነት ወደፊትም እንዲሁ በቀላሉ ንፋስ የሚገባው አይመስልም። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንደሚሉት ኢህአዴግ በህወሃት አማካይነት ደቡብ … [Read more...] about “በህወሓት ተወርረናል!” ደቡብ ሱዳኖች
እስራኤል ተጨማሪ ታዳጊዎች ለቀቀች
በእስራኤል አገር ታስረው ከሚገኙት ታዳጊዎች መካከል አራቱ መፈታታቸውን አቶ ሳሙኤል አለባቸው የኢትዮጵያ እናድን አንድነት ማህበር በእስራኤል ሊቀመንበር በተለይ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ አስታውቀዋል። አሁንም እስር ላይ የሚገኙት ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ አስር ታዳጊዎችን ለማስፈታት አስፈላጊው ሁሉ እየተደረገ መሆኑንንም አስታውቀዋል። አቶ ሳሙኤል በጽሁፍ በላኩት መልዕክት እንዳስታወቁት ከጎንደር አስኮብላዮች ወደ ሲና በረሃ በመውሰድ ለከፍተኛ እንግልትና ህሊናን የሚፈታተን ስቃይ ከዳረጓቸው ታዳጊዎች መካከል እስራኤል መድረስ የቻሉት እዚያ ሲደርሱ የገጠማቸው እስር ነበር። በተለይም እድሜያቸው ከአስራስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ ከታወቀ በኋላ እርሳቸው የሚመሩት ድርጅትና የወገኖቻቸው ስቃይ እረፍት የነሳቸው አገር ወዳዶች ባደረጉት ትብብር … [Read more...] about እስራኤል ተጨማሪ ታዳጊዎች ለቀቀች
“በፍቅርና በመተሳሰብ የምንኖርባት ኢትዮጵያ ትናፍቀኛለች”
የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ከአንዷለም አራጌ ጋር ተገናኙ "ከእስረኞች ሁሉ ህገ-መንግስታዊ መብቴ ተጥሶ ዘመድ አዝማድ እና ጓደኛ እንዳይጠይቀኝ የተደረኩት እኔ ነኝ" አንዷለም አራጌ የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የነበረውንና በሽብርተኝነት ሰበብ ለእስር ተዳርጎ የሚገኘውን ወጣቱን ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌን ከአንድነት ከፍተኛ አመራሮችና አባላት የተውጣጡ ሰዎች ጠይቀውት መመለሳቸውን የሕዝብ ግንኙነት መረጃ ይጠቁማል፡፡ በዋናው መጠየቂያ በር አትገቡም ከተባለ በኋላ ወደ ማረሚያ ቤቱ አስተዳዳሪ የቀረቡት ጠያቂዎቹ ስም ዝርዝራቸው ከተመዘገበ በሁዋላ ሊፈቀድላቸው የቻለ ሲሆን ከወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ ጋር የማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎች አጠገብ ቢኖሩም ውይይት አካሂደዋል፡፡ ከአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ … [Read more...] about “በፍቅርና በመተሳሰብ የምንኖርባት ኢትዮጵያ ትናፍቀኛለች”
የጎልጉል ቅምሻ
ጋብቻ በጠብመንጃ ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ እየተካሄደ ያለው የ“ጠብመንጃ ጋብቻ” አሁን በከፍተኛ ቁጥር ቀጥሎ እንዳለ ሰሞኑን ተሰምቷል፡፡ በላስቬጋስ የሚካሄደው ይኸው የጋብቻ ሥነስርዓት በቅርቡ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤት በተተከፈተ ተኩስ ህጻናት ከሞቱ በኋላ ይቋረጣል ተብሎ ቢጠበቅም ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ከተለያየ የዓለማችን ክፍል በመምጣት 500ዶላር አካባቢ በሚከፈልበትና በጠብመንጃ ሱቅ ውስጥ በሚካሄደው በዚህ ሥነስርዓት ሙሽሮች የተለያዩ ጠብመንጃዎች፣ ዑዚ መትረየስ፣ ኤኬ47፣ ወዘተ (ታንክ ሲቀር) የጦር መሣሪያዎችን በመያዝ ቃለመሃላቸውን ከፈጸሙ በኋላ ለእነርሱ ብቻ በተዘጋጀ ቦታ ላይ የዒላማ ተኩስ በማድረግ ጋብቻቸውን በተኩስ ያደምቁታል፡፡ ወ/ሮ የመከላከያ ሚ/ር ከተመሠረተ ጀምሮ ከወንዶች በስተቀር እንስት ሚኒስትር ያላየው የአሜሪካው የመከላከያ ሚ/ር (ፔንታጎን) … [Read more...] about የጎልጉል ቅምሻ
ኢህአዴግ የውጭ ምንዛሪ አሰሳ ሊያካሂድ ነው
ኢህአዴግ የተጭበረበረ የውጪ ምንዛሪ በማተምና በማሰራጨት ስራ የተሰማሩ እንዳሉ ከበቂ በላይ መረጃ ቢኖረውም ርምጃ እንደማይወስድ መደመጥ ከጀመረ ቆይቷል። በስራ ሽፋን የተጭበረበረ ዶላር የሚያትሙ የውጪ አገር ሰዎችን አስገብተው የሚሰሩት ለራሱ ለህወሃት የቀረቡ ሰዎች ዝርፊያ ስለማካሄዳቸው ፖሊስ ተደጋጋሚ መረጃ ቢደርሰውም ርምጃ ሲወስድ አይታይም በሚል የሚወቅሱት ጥቂት አይደሉም። ቀደም ሲል የተጭበረበረ ዶላር የሚያስገቡ እንደነበሩ የሚገልጹት የጎልጉል የፖሊስ ምንጮች እነዚሁ ክፍሎች አቅማቸውን በማሳደግ የሐሰት (ፎርጂድ) ዶላር አገር ውስጥ ማተም ከጀመሩ ቆይተዋል። ከሩቅ ምስራቅና “ከትንሿ ታላቅ አገር” ህገወጥ ብር አታሚዎችን ከማሽን ጋር በማስገባት የአዲስ አበባን ሃብታሞች ሙጥጥ አድርገው ዘርፈው አድራሻ የቀየሩ አሉ። በዚህ ስራ ውስጥ ተሳታፊ ከሆኑት መካከል የህትመት ሰዎችም … [Read more...] about ኢህአዴግ የውጭ ምንዛሪ አሰሳ ሊያካሂድ ነው
ከእሁድ እስከ እሁድ
ኢሳያስ “ተላላኪ” ሲሉ ህወሃትን ዘለፉ በፈረንጅ የዘመን አቆጣጠር አዲስ ዓመት የተቀበለችውን ኤርትራን የሚመሩት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሰሞኑን ባገራቸው ቴሌቪዥን በትግርኛና በአረብኛ ተሳድበዋል። የአዲስ አበባው መንግስት የሚሉትን ህወሃት፣ “ተላላኪ” ሲሉ ዘልፈውታል። ስርዓቱ በአሜሪካ ጠንካራ እንክብካቤ እድሜውን ቢያራዝምም ተቃውሞ የሚመሰረተው ውስጥ ባለው ሁኔታ እንደሆነ ያመለከቱት አቶ ኢሳያስ፣ “የራሱን ጥቅም ብቻ በሚያስቀድመውና አገሪቱን በሚያስተዳድረው ጠባብ ቡድን፣ እንዲሁም በተቀጥላነት በሚያገለግላቸው የውጪ ሃይሎች…” አማካይነት ማዕቀብ እንደተጣለባቸው ተናግረዋል። ጠ/ሚ ቢቀያየር ትርጉም እንደሌለው ያመለከቱት ኢሳያስ፣ በሃይል የተያዘባቸው መሬት እስካልተለቀቀ ድረስ እንደማይደራደሩ አስታውቀዋል። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላስተላለፉት የእንደራደር ጥያቄ “የጉዳዩን … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
በኬንያ ስደተኞች ከተማ ልቀቁ ተባሉ
ወቅቱ 2003 አጋማሽ ላይ ነው። ሁለት የኢህአዴግ ሰዎች ድንበር አቋርጠው ናይሮቢ ይገባሉ። በናይሮቢ አድርገው ወደ ሌላ አገር ለመኮብለል ጊዜያዊ ማረፊያ መጠነኛ ሆቴል ይከራዩና ለሁለት አንድ ላይ ያርፋሉ። አንደኛው ከሰዎች ጋር ቀጠሮ እንዳለው አስታውቆ ወደ ጉዳዩ ይሄዳል። ቀጠሮው ቦታ ቆይቶ ለጓደኛው ስልክ ሲደውል “እንዳትመጣ፣ ጓደኛህን ከተኛበት ገብተው የማይታወቁ ሰዎች ወስደውታል” የሚል መልዕክት ይደርሰዋል። ከዚያን ቀን ጀምሮ ስለጓደኛው ሰምቶ አያውቅም። እሱም አገር ቀይሮ በስደት በመንከራተት ላይ ይገኛል። ኬንያ ሶስት ዓይነት ስደተኞች አሉ። በኢኮኖሚ ድቀት የዕለት ጉርስ ፍለጋ የሚሰደዱ፣ በፖለቲካ ሳቢያ ኢህአዴግን ሽሽት አገር ለቀው የወጡ፣ በኢህአዴግ ልዩ ተልኮ ስደተኛ መስለው ኬንያ የሚኖሩ፤ ከናይሮቢ በስልክ ለጎልጉል መረጃ የሰጡት ወገኖች እንደደሚሉት በየጊዜው እየታፈኑ … [Read more...] about በኬንያ ስደተኞች ከተማ ልቀቁ ተባሉ
ቴሌን ደህና ሰንብት?
የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ስሙን ቀይሮ “ኢትዮቴሌኮም” በሚል ከተሰየመ በኋላ አስተዳደሩን ለፈረንሳዩ ፍራንስ ቴሌኮም ማስረከቡን ተከትሎ ኢህአዴግ ለወደፊቱ ያቀደውን እቅድ ይፋ የሚያደርጉ መረጃዎች ለንባብ በቅተዋል። በዛሬው እለት የመገናኛና የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል “ቴሌ ከዚህ በኋላ ለውጪ ካምፓኒ አይሰጥም። በአገር ውስጥ ባለሙያዎች ይቀጥላል” ሲሉ የማሳረጊያ ንግግር አሰምተዋል። የሚኒስትሩን ንግግር ያደመጡ “ቴሌን ህወሃት ጠቀለለው” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ “አዲሱ ቴሌና ኢንሳ” በሚል ርዕስ ከወራት በፊት ለንባብ ባበቃው ጥናታዊ ጽሁፍ እንዳስታወቀው ቀደም ሲል “አዲሱ ቴሌ” በሚል አሮጌው ቴሌን የሚረከቡ የህወሃት ሰዎች የበዙበት፣ ለማዛነቂያ ከተለያዩ ብሄሮች በጣም ጥቂት ተተኪዎችን በማካተት ስልጠና … [Read more...] about ቴሌን ደህና ሰንብት?
ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም “በኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኛ የለም”
አስመራ ለመሄድና ለመደራደር ፈቃደኛ ከሆኑ የመድረክ ተወካዮች እርሳቸው ቢሮ ድረስ በመሄድ እንዲደራደሩ እንዲፈቅዱ ተጠይቀዋል። በኢትዮጵያ ያለውን እስርና እንግልት፣እንዲሁም “የውንጀላ” ቅንብር ከንጹህ ህሊና እንዲመረምሩ በትህትና የልመና ያህል ቀርቦላቸዋል። በምትሰጠዋ አጭር የመናገሪያ ደቂቃ መነጋገሪያ የሚሆኑ ጥያቄዎች ተሰንዝረዋል። የእያንዳንዱን ቤት የሚያንኳኳ ሰብአዊነትን የሚፈታተን ጥያቄዎች በማንሳት አቶ ግርማ ሰይፉ ተሳክቶላቸዋል። በትህትና ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች በተለይም ዶ/ር ደብረጽዮንን በተደጋጋሚ ሲስቁ እንድንመለከት ከመጋበዙ በላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ነጻነት የተሞላው መልስ አልተሰጠባቸውም። አቶ ሃይለማርያም ቀሪዋን ሁለት ዓመት ለመጨረስ ውለታ አስቀማጭ በመሰሉበት የፓርላማ ውሏቸው ፖለቲካ ውሸትና ክህደት የሚበዛበት የአይነ ደረቆች ጨዋታ ነው ቢባልም፣ እሳቸው ግን … [Read more...] about ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም “በኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኛ የለም”