አማርኛ ተናጋሪዎችን የማመናመን፣ የማደህየት፣ የማራቆትና ክልላቸውን እያሳነሱ የማጥፋት እቅድ በህወሃት መርሃግብር ውስጥ የተካተተ ዋና ተግባር እንደሆነ ተገለጸ። አማርኛ ቋንቋንም ማሽመድመድ የዚሁ እቅድ አካል መሆኑ ተዘግቧል።
አቶ ገ/መድህን አርአያ ከኢሳት ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በህወሃት ፕሮግራም ገጽ 18 አካባቢ “አማራ የትግራይና የኤርትራ ህዝብ ጠላት እንደሆነ ተመልክቷል” ብለዋል፡፡ አያይዘውም አማራ ማጥፋት የቅስቀሳው ዋና መሳሪያ ቢሆንም የትግራይ ህዝብ አልተቀበለም ብለዋል። ቅስቀሳውን አንቀበልም ያሉ “የትግራይ ሸዋ” ተብለው መገደላቸውን ይፋ አድርገዋል።
በተለይ የድርጊቱ ዋና አስተባባሪ በማለት የጠቀሷቸው አቶ መለስ ዜናዊ፣ አቶ ስብሃት፣ አቶ ስዩም መስፍን፣ አቶ አባይ ጸሐዬን የጠቀሱት አቶ ገ/መድህን፣ በ1972 በሰሜን ጎንደር የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን አጋልጠዋል። በወቅቱ የተካሄደው ጭፍጨፋ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደሆነም አመልክተዋል። “በሰላም እጃቸውን የሚሰጡ ወታደሮች እንኳ አማርኛ የሚናገሩ ከሆነ ይረሸኑ ነበር” ሲሉ እነ መለስ ያለቸውን በዘር ላይ የተመሰረተ ቆሻሻ አመለካከት አጋልጠዋል።
“ኢትዮጵያ የምትበተነው አማራ ሲጠፋ ነው” በሚለው የነመለስ ሃሳብ መተግበር የጀመረው ህወሃት አዲስ አበባ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑንን ያወሱት አቶ ገ/መድህን፣ ህወሃት ያሰማራቸው ከ350ሺህ በላይ ካድሬዎች ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ አማራዎች በተለያዩ ምክንያቶች እንዲጨፈጨፉ ማድረጋቸውን አመልክተዋል።
ብአዴንን “አማራን ለማጥፋት የተፈጠረ፣ ጸረ አማራ ድርጀት” ሲሉ የሰየሙት አቶ ገ/መድህን፣ አመራሮቹ የኤርትራና የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውን በርግጠኛነት ተናግረዋል። የትግራይ ህዝብ የተወከለው “በባንዳ ልጆችና የኤርትራ ተወላጆች ነው” ሲሉም ህዝቡ አደጋ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱን “የባሻ ወልዱ ልጅ ነው” በማለት የትግራይ ህዝብ በባንዳ ኤርትራዊ ልጅ እንደሚመራ ያመለከቱት አቶ ገ/መድህን፤ ብርሀነ ገብረክርስቶስ፣ ቴድሮስ ሃጎስ፣ ቴድሮስ አድሃኖም፣ በማለት በመዘርዘር የባንዳ ልጆች መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል።
“አማራው የሚኖርበትን መሬት በመውሰድ መሬቱን ያጠቡበታል፣ ከሌላው ክልል በማባረር የሚኖርበትን ክልል ያጠቡታል” ያሉት አቶ ገ/መድህን፣ ይህ የሚደረገው ከመጀመሪያው እንዲጠፋ የተወሰነበትን ህዝብ አጥብቦ በማፈን በችግር ለመግረፍና ለመቆጣጠር ተብሎ እንደሆነ ገልጸዋል።
ዘር የማጥራት የህወሃት የቀደመ ድርጅታዊ መዋቅር እንደሆነ በማመልከት መለስን የጠቀሱት አቶ ገ/መድህን፣ “አማራውን ዝም ካልነው አያስቀምጠንም” የሚለው የመለስ መፈክር አካል የሆነው የቤኒሻንጉል ክልል ርምጃ የህወሃት ቤት ስራ እንደሆነ አረጋግጠዋል። አማራውን ፋታ ማሳጣት፣ ማንገላታት፣ ስነልቦናውን መግፈፍ ህወሃት በፕሮግራም ደረጃ የያዘው እቅድ ስለሆነ ወደፊትም እንደሚቀጥል አቶ ገ/መድህን ተናግረዋል።
“ሞት መፍራት አያስፈልግም። የተቀደሰ ሞት መሞት ክብር ነው” ሲሉ በቃለ ምልልሳቸው መጨረሻ የተናገሩት የቀድሞው የህወሃት የፋይናንስ ሃላፊ ህዝቡ ተባብሮ ህወሃትን ማስወገድ ካልቻለ ማፈናቀሉና መሰደዱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስጠንቅቀዋል።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Truneh Yirga says
ሀገሬ ኢትዮጵያ ብሔሬ ኢትጵያዊ፦
ሀገሬ ኢትዮጵያ ዘሬ ኢትዮጵያዊ ነው፣ በዘርና በነገድ በቋንቋና በሃይማኖት መከፋፈልን አጥብቄ እቃዎማለሁ። ብዙም አልጽፍም በአገሬ ጉዳይ ዙሪያ ማንበብና ማዳመጥና በቻልኩት መጠን መርዳትን እመርጥ ነበር፣ በሰሞኑ ዜና ግን ልቤ እጅጉን ተጎዳ፤ ሰው በአገሩ እንዴት በማለት የውስጥ ሀዘንም ተሰማኝ፦
በሐገረ ኢትዮጵያ ጩኸት በረከተ….. ከደቡብ ጠርዝ እስከ ሰሜን ጫፍ ዋይታ በዛ፣ የሕጻናትና የዓረጋውያን ለቅሶ፤ የጎበዙ የሞት ጣርና የወይዛዝርቱ የልብ ስብራት፤ የናቶች ሐዘንና ትካዜ የአባቶች የድረሱልን ድምጽ ይሰማል።
ከሐረር እስከ ወለጋ፤ ከጎንደር ጫፍ እስከ አርሲና ጋሞጎፋ፤ ከወልቃይት ጸገዴ እስከ ጉራፋርዳ፤ ከሰቲት ሁመራ እስከ በደኖ አርባጉጉ፤ ከአብደራፊ መተማና ስናር እስከ ወሎና አፋር፣ ከአርማጭሆ የዋልድባ ገዳም እስከ ትልቁ የዓንዋር መስጊድ መርካቶ፦
ያጠላው የሞት ድባብ አሁንም በጋምቤላ አድርጎ በጉሙዝ ቤኔሻንጉል የብሔረ አማራን ማጋየት ቀጥሏል፤ እንደነርሱ አባባል አማራ አፈርድሜ እየበላ ነው። የዜጎቻችን በግፍ መጨፍጨፍ በዛ፦
አገር ፈረሰ፤ ድንበር ተቆረሰ፤ ሐይማኖት ተጣሰ፦የአማራ ሕዝብ መከራና ስቃይ ከልኩ አለፈ…እኖር ማለት፣ ሰላም ፈላጊ መሆንና ትግስት ማድረግ እንደ ፍርሃት ተቆጠረ፦
ወገኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ሀሳብህን አስማማና በአንድ ድምጽ በያለህበት ተናገር፤ የማንነታችን አሻራ የጥቁር ዘር ኩራት የሆነችውን ኢትዮጵያችንን ለማጥፋት ጨክኖ ከተነሳ ሀገር በቀል ጠላት ለመታደግ ሰዓቱ አሁን ነው፤ የወያኔን መሰሪ ደባ ለማስቆም ሳይመሽ እንሰባሰብና እንምከር፦ የወያኔ ዋናው ዓላማ ታላቋን ኢትዮጵያን አጥፍቶ ድንክየ አገሮች ለመፍጠር እንደሆነ በውስጥ አዋቂዎች በዐጽንኦት ይነገራል።
የማጥፋት ዘመቻው ያነጻጸረውም፦ ለኢትዮጵያ አንድነት ምሶሶ በሆነው ብሔረ አማራና የጋራ መግባቢያ በሆነው በአማርኛ ቋንቋችን እንዲሁም የአንድነታችን መሰረት በሆነው በሐይማኖታችን ላይ ነው።
የሁለቱን ታላላቅ እምነት ተከታዮች እስላምና ክርስቲያኑን፤ እንዲሁም የአገሪቱ አምድ የሆኑትን ብሔረ አማራንና ብሔረ ኦሮሞን ለማጣላት የተሞከረው አልተሳካላቸውም፤ ስለሆነም እነሱ እንደሚጠሯቸው በአናሳ ጎሳዎች ታላቁን የአማራ ሕዝብ ለማስመታት የተጀመረው ይህ ድፍረት በፍጥነት ካልቆመ ተዳፍኖ ተዳፍኖ የሚነሳውን እሳት ማብረድ እጅግ ይቸግራል፣ ለፓለቲካ ፍጆታ ሲባል ስም ከመጥራት ልቆጠብ ቢዳዳኝም አስተዋይ የሆኑ የትግራይ ተወላጆችና ሆዳም የወያኔ መናጆዎች በጥብቅ ሊያስቡበት ይገባል።
አገርና ሕዝቡን ወዳጅ፣ ልበ ሰፊና መንፈሰ ጽኑ የሆነውን የአማራ ነገድ ቅስሙን ለመስበርና ዘሩንም ለማጥፋት የሚደረገውን ሩጫ በአንድነት እንቃዎምና እናስቁም፣ ላማንኛችንም አይጥቅምምና ዘረኝነትን በየጎጣችን እንዋጋ፣ ሁላችን በመከባበር በጋራ የምንኖርባት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት በአንድነት ድምጻችንን እናሰማ፣ በምንችለው ሁሉ እንታገል…..
koster says
Amhara has several enemies at home and in foreign countries. Not only woynane ethnic fascists are enemies of Amhara but even Opposition politicians have open or hidden hatred on Amharas. Say no to woyane ethnic fascists, ethnic politics and state terrorism in Ethiopia. Excluding any one Group does not bring Lasting peace so all criminals face justice but an all Ethiopian anti-woyane ethnic Fascist force is needed to build a free and democratic Ethiopia where all live freely and democratically.
Girma says
I am Amhara and I am Ethiopian. I am not ashamed to reveal myself as Amhara. I bet the biggest enemy of Amhara and the Stupid elites of Amahara. Have you thought about what would happen to Amhara if for some unlikely reason Ethiopia no more exists? Do we have a plan B? what a stupid people on earth! Whether you accept it or not Ethiopia’s very existence conditional on “the very will of ALL Ethiopians to live together”. What would happen say 100 years from now with a democratcy flourishing all over Africa some of the Ethiopians decide to be independent?
By the way from what I have seen every one is trying to develop their own reagion except Amhara. Everyone wants their region to be a trade center, where their people prosper, Asphalt roads are being built even with a contribution from the people. But Amharas are Ethiopians, their region, their people are nothing for them. They don’t dare if south prospers and Amhara starves, because for them what matters is Ethiopia not Amhara.
Probably, a united Ethiopia requires a Strong Amhara! Unfortunately, Amhara is committing a suicide. Probabaly Amahara are the only people in this world who don’t give a dime shit about their people. I have been in the region for a holiday and I was devastated by their economic lives. Oromia may be is prospering, Tigray may be is prospering, but Amhara is dying.
As usual I can blame TPLF/EPRDF for that, I have heard people doing so. But I point my fingure on me and the so called Educated Ahmaras. The region is not business freindly because they are not educated about its benefits; the region is hostile to changes of any kind, because they are not told of the benefits. I was asking myself – do these people have elites of any kind. I guess the elites of Amahara are busy with protecting Ethiopia their brothers and sisters are dying.
I told myself – I am Amhara before I am Ethiopian. Ethiopia’s fate is on the hands of 80 million people, but Amhara’s fate is on our hands. Those people need elites who bring ideas of prosperity, positive change! I want to see a prosperous Amhara!
See the long term, TPLF will vanish, but the regional imbalance will prevail. One the trade hub is built in Oromia/AA/Tigray/debus, there is no way we can be economically powerful people. To make things even worse, even if we are poor people we don’t like to hear a smart idea from poor guys. Think of what would happen if Amhara is still poor and others prosper, no one will give ear to us!
Thanks – I am coming is an article about my observation and my vision for Amhara!
Enkokow says
Hi Girma , Can you please add on facebook ( Enkokow Gojje is my name) and we can talk what we can do