• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከእሁድ እስከ እሁድ

April 15, 2013 01:03 am by Editor 2 Comments

መለስ “ከዋሸኸን ትሞታለህ”
መለስ ሀዋሳን ክልል ለማድረግ ቃል ገብተው ነበር

የሲዳማ አገር ሽማግሌዎች አቶ መለስ እድሜያቸው አጭር እንደሚሆንና እንደሚቀሰፉ ነግረዋቸው እንደነበር ተሰማ። በክልሉ የአገር ሽማግሌ ከሚባሉት መካከል አንዱን በማነጋገር በተለይ ለጎልጉል የተላከው መረጃ እንደጠቀሰው መለስ እድሜያቸው ሊያጥርና በድንገት ሊቀሰፉ የሚችሉት የሲዳማን ባህላዊ ልብስ ለብሰው ከዋሹ ነበር።

እንደመረጃው መለስ በ1997 ዓ ም ምርጫ ውጥረት ውስጥ በነበሩበት ወቅት አራት ተከታታይ ቀናት ሃዋሳ የብሄር ብሄረሰቦች አዳራሽ ውስጥ የብሄረሰቡን ተወላጆች ሰብስበው አነጋግረው ነበር። “አዲስ አበባ ያለው ድንኳናችን ፈርሷል። እዚህም ከፈረሰ በቃን ማለት ነው” በማለት የአገር ሽማግሌዎችን በተማጸኑበት ንግግራቸው መለስ አስቀድሞ ተቃውሞ ገጥሟቸው ነበር።

ስብሰባው አዳራሽ ውስጥ ሙሉ ልብስ ለብሰው መድረክ ላይ ተቀምጠው የነበሩትን መለስ “ማን እዛ ላይ አወጣህ? አውርደንሃል” በማለት ሽማግሌዎች ሲናገሩ በወቅቱ የጸጥታ ሃይሎችና የአቶ መለስ ጠባቂዎች ተደናግረው ነበር። ሽማግሌዎቹ አቶ መለስን ከመድረክ አውርደው “አስቀድመህ ያገራችንን የባህል ልብስ ለብሰህ ነው መድረክ ላይ የምትወጣው” በማለት ከመድረክ አውርደው ጓዳ በማስገባት “ሴማ” የሚባለውን የባህል ቡሉኮ አለበሱዋቸው።

“ይህንን የሚለብስ እውነት የሚናገር ብቻ ነው” በማለት አቶ መለስ መዋሸት እንደማይገባቸው ሽማግሌዎቹ አሳስበው እንደነበር የጠቆመው መረጃ፣ “ይህንን የሚለብስ መሪ የሆነ፣ እውነት የሚናገር ብቻ ነው። የሚዋሽ ይሞታል። እድሜው ያጥራል። ይቀሰፋል” በማለት በሲዳምኛ ደጋግመው መናገራቸውንና አቶ መለስም የተባሉትን ለማድረግ ተስማምተው እንደነበር አመልክቷል።

በዚሁ መሰረት አቶ መለስ በ1997 ምርጫ ተከትሎ ካጋጠማቸው ቀውስ ለመውጣት ሃዋሳን ከሌሎች የደቡብ አካል በመነጠል ራስዋን የቻለች ክልል ለማድረግ ለቀረበላቸው ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ ሰጥተው ነበር። ሃዋሳን ክልል ማድረግ አስቀድመው ቃል በመግባት በወቅቱ ከሲዳማ ህዝብ ማግኘት የፈለጉትን ድጋፍ ለማግኘት እንደተጠቀሙበት መረጃው ያስታውሳል።

አሁን በስደት የሚገኝና በወቅቱ ስብሰባው ላይ ተገኝቶ እንደነበር የገለጸ ለጎልጉል እንደተናገረው ቢችልም አቶ መለስ የገቡትን ቃል ለማስፈጸም የተመረጡትን 20 ሽማግሌዎች አዲስ አበባ ትልቅ ሆቴል በማስቀመጥ ገንዘብ በመስጠትና መሬት በማደል በሲዳማ ቅንጅት እንዲመረጥ የቀሰቀሱ ሰዎችንና ዋና አስተባባሪዎች ላይ የቂም ርምጃ እንዲወሰድ አድርገዋል።

ጉዳዩ አፈታሪክና ወይም ተረት ቢመስልም የሲዳማ አባቶች መለስ በፈጸሙት ክህደት እንደረገሟቸውና ሞቱ ተብሎ የሚታመነውም በዚሁ ርግማን እንደሆነ ያመለከተው መረጃ የሲዳማ ህዝብ አሁን እየደረሰበት ያለው በደልና ግፍ እያየለ በመሄዱ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ “ሲአን” ራሱን ከምርጫ ማግለሉ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍ እንዳለው አመልክቷል። ድርጅቱ ዋና ጸሃፊ አቶ ለገሰ ላንቃሞ ከኢሳት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ  ከ787 በላይ አባሎቻቸው በመታሰራቸውና ባለፈው ሳምንት በዳሌ ወረዳ እጩ ተወዳዳሪው ተሾመ ካሰና የሚባል ሰው ተገድሎ በመገኘቱ እንዲሁም የሲአን አባላትን ማዋከብ፣ ከስራ ማፈናቀል እና ተማሪዎችን ማባረሩ በመቀጠሉ ድርጅቱ ራሱን ለማግለል መወሰኑን ዋና ጸሀፊው ተናግረዋል።

የፌዴራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው ተሰማርተው በድርጅቱ አባሎች ላይ ወከባ እየፈጸሙ መሆኑን ዋና ጸሀፊው ተናግረዋል። መንግስት ከምርጫው እንዳይወጡ ለምኗቸው እንደነበር ዋና ጸሀፊው መግለጻቸውን ኢሳት ዘግቧል።

አንደበት

“ዛሬ ውድ ሀገራችን ደብዘዋ ጠፍቶ፣ ሕዝቧ ምስቅልቅሉ ወጥቶ ፣ሥነልቡናው እየተሰለበ፣ዓይኑ እያየና ጆሮው እየሰማ፣ ባህሉ እየተንቋሸሸና እየተጓደፈ፣ ታሪኩ እየተደለዘና ቅርሱ እየተመዘበረበት የውሻ ሞት እየሞተ ነው። በእንደዚህ ያለ የመከራ ጊዜና ወቅት አንገቱን ደፍቶ፣ያልከፋው መስሎ ሆደሰፊ በመሆንና ሳይቸኩል ፈጣሪውን ለምህረት እየተማፀነ ራሱን ሳያጋልጥ ለትግል የሚሰናዳ ታላቅ ሕዝብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ነው።  http://www.ethiotube.net/video/19536/Professor-Asrat-Woldeyes  ፕ/ር አስራት ወልደየስ በመዐህድ የወጣቶች ስብሰባ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ።

ግንቦት 7 የህቡዕ ሃይል ተደራጅቷል አለ
(ፎቶ: Abbay Media)

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የዘር ፖለቲካና አገሪቱ እየተጓዘችበት ያለው አደገኛ አቅጣጫ  ያሳሰባቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ራሳቸውን በህቡዕ በማደራጀት በቅርቡ ከሌሎች ለለውጥ ከሚታገሉ ሃይሎች ጋር በመሆን ወደ ተግባር እንቅስቃሴ ለመሸጋገር በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ግንቦት 7  አስታወቀ። ንቅናቄው በድረ ገጹ እንዳስታወቀው በህቡዕ የተደራጀው ቡድን ስያሜና ኣላማ “ኢትዮጵያን አድን” የሚል ነው።

በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኙ የህዋሱን መሪ እንዳነጋገረ፣ ነገር ግን ለደህንነት ሲባል ስማቸውንና ድምጻቸውን ይፋ ከማድረግ መቆጠቡን የጠየቀው የንቅናቄው ዜና ቡድኑ ከአራት ዓመት በፊት እንደተቋቋመ አስታውቋል። በ“አገርህን አድን” ቡድን ስር በመደራጀት ላይ የሚገኘዉ ሠራዊት አላማ የሠራዊቱን መብትና ነጻነት አስጠብቆ ወደ ሠፈሩ መመለስ ሳይሆን የቡድኑ ተቀዳሚ አላማ ለህዝብ በገባዉ ቃል መሠረት ኢትጵያንና ህዝቧን ከወያኔ ዘረኝነትና ከፋፍለህ ግዛዉ ፖሊሲ ማዳን መሆኑንን የቡድኑ ቃል አቀባይ በመጥቀስ አመልክቷል። የንቅናቄው ድረገጽ  አፕሪል 13/2013 ይፋ ያደረገው ዜና  “በአሁኑ ወቅት አያሌ ኢትዮጵያዉያን ወያኔን ለመታገል መሳሪያ ካነሱ ወገኖች ጋር በየቀኑ እየተቀላቀሉ ስለሆነ የኛም አላማ የትግል ስልትና የተለየ የትግል ቦታ ሳንመርጥ ወያኔን ያዋጣናል ባልነዉ ስልትና ይመቸናል ባልነዉ ቦታ ሁሉ እስከእለተ ሞቱ እንታገለዋለን” በማለት ከፍተኛ መኮንን የተባሉት የቡድኑ ቃል አቀባይ መናገራቸውን አመልክቷል። ግንቦት 7 በተለያዩ ጊዚያት ተመሳሳይ ወታደራዊ ዜናዎች ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

ኳታር ወደ ኢትዮጵያ ኢሳያስ ወደ ኳታር

የኳታር መንግስት በአሚር ሼኽ ሐሚድ ቢን ካሃሊፍ አልታሃኒ የሚመራ የልዑካን ቡድን በመያዝ ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያን ጎብኝተው ነበር። በዚሁ ጉብኝት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች መምከሩና በጋራ ለመስራት መስማማታቸው በተለያዩ መገናኛዎች ተዘግቧል።

በተመሳሳይ ሳምንት የኤርትራው ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ኳታር አምርተው ነበር። የኳታር የዜና ምንጮች እንደዘገቡት ኳታር በፕሬዚዳንት ኢሳያስ የሚመራውን የኤርትራ ልዑክ በክብር ተቀብላ አነጋግራለች። ኢትዮጵያ በሶማሊያ የሚንቀሳቀሱ አሸባሪ ሃይሎችን ትረዳለች በሚል በተደጋጋሚ ክስ ስትሰነዝርባት ከነበረችው ኳታር ጋር በግልጽ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመስራት አዲስ ስምምነት ማድረጋቸውን የተለያዩ ሪፖርቶች ይፋ አድርገዋል። ሪፖርተር ያነጋገራቸው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ በይፋ ባይናገሩም ኳታር ወዳጇ የሆነችውን ኤርትራንና ኢትዮጵያን ለማስማማት ውስጥ ውስጡን እየሰራች እንደሆነ ከወዲሁ እየተነገረ ነው።

ኳታር ከኤርትራ መንግስት ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላት በመጥቀስ ሲከሳት የነበረው ኢህአዴግ ይፋ ባያደርገውም በተመሳሳይ ሳምንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ኳታር ማምራታቸው ኳታር ሁለቱን አገሮች ለማሸማገል እየተንቀሳቀሰች ለመሆኑ አመላካች እንደሆነ ተደርጎ ተወስዷል። ኤርትራን በከፍተኛ ደረጃ በመደገፍ የምትታወቀው ኳታር በሶማሊያ የተፈጠረውን ሰላምና መልሶ ግንባታ ለማገዝ ፈቃደኛ መሆኗን ኢትዮጵያ አስታውቃለች። ኢትዮጵያ በኳታር ላይ ክስ ከማቅረብ አልፋ ኤምባሲዋን ዘግታ እንደነበር ይታወሳል።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. አ.በ. says

    April 15, 2013 05:02 am at 5:02 am

    ደግሞ ለኳታር ምን ለሸጡብን ይሀን? አቤት የኛ ዕዳ!

    Reply
  2. korktu says

    April 15, 2013 02:55 pm at 2:55 pm

    More lands to quatar as usual to buy love at the expense of the poor Ethiopian peasants. Woyane leaves no stone unturned to extend lease of iron hand rule. What a misfortune it is for Ethiopians to have such vampires ,termites and vagrants .

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule