ፍቅር ቁመት አይወስነውም የዓለማችን ረጅም ወጣት የከንፈር ወዳጅ የሆነው የ22ዓመቱ ብራዚላዊ ከፍቅረኛው ጋር ያለው ግንኙነት እጅግ አስደሳች እንደሆነ ገለጸ፡፡ ዕድሜዋ 17ዓመትና ቁመትዋ 6ጫማ ከ8ኢንች (2.1ሜትር) የምትረዝመው ኤሊሳኒ ሲልቫ ዕድገቷን የሚቆጣጠረው ዕጢ ላይ ባጋጠማት ችግር ምክንያት እንደዚህ ቁመቷ ሊረዝም እንደቻለና በሽታዋ ከታወቀ በኋላ ሐኪሞች ዕብጠቱን እንዳስወገዱት ተገልጾዋል፡፡ ወደፊት ሞዴሊስት ለመሆን የምታስበው የከንፈው ወዳጅዋ መልካም ስብዕና ያለውና ለእርሷም ድንቅ አመለካከት እንዳለው ገልጻለች፡፡ ሆኖም ችግሯን ከመግለጽ አልተቆጠበችም፤ “ያለኝ ዋና ችግር እጅ ለእጅ ተያይዘን ስንሄድ ትንሹን ወንድሜን ወይም ልጄን ይዤ የምሄድ ይመስለኛል” ብላለች፡፡ የዓመቱ ሰው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ታህሳስ 4፤ 1928ዓም (ጃኑዋሪ 6፤1936 አውሮጳውያኑ ቆጣጠር) … [Read more...] about የጎልጉል ቅምሻ
News
ዜና
ከእሁድ እስከ እሁድ
ጁነዲንና ኢህአዴግ ፊርማቸውን ቀደዱ ከሚኒስትርነታቸውና ከኦህዴድ ስራ አስፈጻሚነታቸው በግምገማ እንዲነሱ የተደረጉት አቶ ጁነዲን ሳዶ ያለ መከሰስ መብታቸው ተነስቶ ክስ እንደሚመሰረትባቸው ሰንደቅ ጋዜጣ መዘገቡ ይታወሳል። ሪፖርተር በእሁድ እትሙ ጁነዲን ሳዶ ያለመከሰስ መብታቸው ለማንሳት ፓርላማው በዝግጅት ላይ መሆኑን ይፋ የምክር ቤት ምንጮቹን ጠቅሶ አስታውቋል። ባለፈው ሐሙስ የዓመቱን ዘጠነኛ ስብሰባውን ያካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአምስት አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት ፕሮግራም ይዞ የነበረ ቢሆንም፣ በአራቱ ላይ ብቻ ተወያይቶ የቀረውን ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፎታል፡፡ ሪፖርተር እንዳለው “የአንድ የምክር ቤት አባልን የሕግ ከለላ ስለማንሳት የቀረበ የውሳኔ ሐሳብን መርምሮ ማፅደቅ” የሚል ቢሆንም፣ የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ ይህንን በቀጣይ ስብሰባ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
“[ሻዕቢያ] በየቀኑ እየሞተ ነው”
ኤርትራ ከውጪና ከውስጥ ተዥጎርጉራለች። ከውጪ ደግሞ “በየቀኑ ትንሽ ትንሽ እየሞተች ነው፤ በቅርቡም የሚፈነዳ ነገር አለ” በሚል ግምት ከየአካባቢው እየተሰጠ ነው። ከውስጥ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የኢንቨስትመንት ጥያቄና ግብዣ ላይ ናቸው። የተበላሸባቸውን ዲፕሎማሲ ለማቃናት ላይ ታች እያሉ ነው። “ኤርትራን በተመለከተ የሚወጡት መረጃዎች የችግሮቿን መወሳሰብና የፕሬዚዳንት ኢሳያስ እጣ ፈንታ መገባደጃው ላይ ለመድረሱ አመላካች ነው” የሚሉ ያሉትን ያህል “ኢሳያስ በውጪ ግንኙነታቸው ላይ የሰሩትን ስህተት በማረም ከበፊት ይልቅ አሁን ወደ ተሻለ መረጋጋትና የኢኮኖሚ ተሃድሶ ተሸጋግራለች” በሚል የሚከራከሩም አሉ። እንደውም ከህወሃት/ኢህአዴግ ይልቅ ሻዕቢያ ከስጋት የራቀ እንደሆነ አድርገው የሚከራከሩ አሉ። በኤርትራ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ፣ መንግስት ከያዘው ሞኖፖሊ አስተሳሰብ እንደሚወጣና ቃል … [Read more...] about “[ሻዕቢያ] በየቀኑ እየሞተ ነው”
የህወሃት/ኢህአዴግ የስለላ መረብ እየተበረበረ ነው
“አዲሱ ቴሌ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ/ኢንሳ” በሚል ርዕስ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ያዘጋጀው ጥናታዊ ሪፖርት የታላላቅ አገር የስለላ ተቋማት፣ ለጉዳዩ አግባብ ያላቸው መምሪያዎችና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ትኩረት መሳቡ ታወቀ። ሪፖርቱን አገራቱ በራሳቸው ቋንቋ በመተርጎም የህወሃት/ኢህአዴግን የስለላ መረብ ከተለያየ አቅጣጫ እየመረመሩት ነው። የጎልጉል ምንጭ የሆኑ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንዳስታወቁት አኢጋን የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም አዲሱ ቴሌን (ኢትዮ ቴሌኮምን) ከዋንኛው የስለላ መ/ቤት ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል NISS (National Intelligence and Security Service) እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ወይም በእንግሊዝኛው … [Read more...] about የህወሃት/ኢህአዴግ የስለላ መረብ እየተበረበረ ነው
ኢህአዴግና ኢህአዴግ ተፈራርተዋል
ሙስና በኢትዮጵያ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን ኢህአዴግ አይክድም። ኢህአዴግ ባለስልጣኖቹ በሙስና ስለመዘፈቃቸው ማመኑን የገለጸው “የመንግስት ሌቦች አስቸገሩኝ” በሚል ነው። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ “በሙስና የተለከፉ ዋጋቸውን ያገኛሉ” ሲሉ ስልጣን በያዙ ማግስት መዛታቸውን የሚያስታውሱ በስተመጨረሻ “ኢህአዴግና ኢህአዴግ ተፈራርተዋል” የሚል ድምዳሜ ላይ ነው። “ትልቅ ጫካ ሰርታችሁ የኛንም የናንተንም ሌቦች መደበቅ በመቻላችሁ ሁሉንም መመንጠር ስላልቻልን እየተተራመስን ነው” በማለት ጣታቸውን ወደ ነጋዴው ህብረተሰብ በመቀሰር ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በአገሪቱ ያለውን ሙስና አስከፊነት በገለጹበት መድረክ “ስልጣን የመክበሪያ ብቸኛው መንገድ በሆነበት አገር ዘላቂ ሰላም ይኖራል ማለት ዘበት ነው። በኪራይ ሰብሳቢነት እንደ መንግስትም፣ እንደ ባለሃብትም መቀጠል አንችልም። እንደ … [Read more...] about ኢህአዴግና ኢህአዴግ ተፈራርተዋል
ከእሁድ እስከ እሁድ
ኢህአዴግን በኃይል ለማስወገድ ጥሪ ቀረበ በኢትዮጵያ ያለውን አገዛዝ ለመጣል ይቻል ዘንድ ለቀድሞው ሰራዊት፣ አሁን በስራ ላይ ላሉት የመከላከያ አባላትና በአገር ውስጥና በውጪ ስደት ላይ ላሉ ዜጎች ሁሉ የትግል ጥሪ ቀረበ። “የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” በሚል ስያሜ ጥሪውን ያስተላለፈው ክፍል ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከሚመሩት ድርጅት ጋር ግንኙነት እንዳለው ለማጣራት ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት ኢሳት ዘወትር እሁድ በሚያቀርበው የሳምንቱ ዜናዎች ላይ አስታውቋል። ኢሳት በሰበር ዜና ያቀረበው ይህ ዜና ከዋናው የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጋር ግንኙነት እንዳለውና እንደሌለው ለማጣራት ያደረገው ሙከራ ለጊዜው ባይሳካለትም፣ በቅርቡ ግን መረጃዎችን በማሰባሰብ በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ የሚያቀርብ መረጃ ለመስጠት እንደሚተጋ አስታውቋል። በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያለ ህዝብ ይሁንታ ላለፉት ሃያ አንድ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
ከሶሪያ መሪዎች ጋር የሚደረገው ንግግር ጊዜው አልፎበታል፤
የኮፊ አናን ተልዕኮ በሶሪያ ላለው ትርጉም ያለዉ ዉጤት ማስገኘቱ አያስተማምንም። ይህ፤ ግጭቱ በየትኛዉም መልኩ መመለስ የማይችልበት ጠርዝ ላይ በመድረሱ ብቻ ሣይሆን፤ ከጅምሩም ምናአልባት የሶሪያ ገዥዎች ከወዲሁም ቢሆን በሰላም ሽግግሩ እንዲከናወን ፈቃደኛ አይሆኑምና ነው። የበሺር አል አሳድ ገዢ ቡድን፤ ቅንጣት የለዉጥ ሙከራ ሳያደርግና ተቃዋሚዎችን ሳያግባባ፤ ለምን በኃይል እንቅስቃሴዉን ለማጥፋት የወሰነበትን፤ መረዳት ያስፈልጋል። ባለፈው ዓመት፤ የመካከለኛው ምሥራቅ አምባገነን ገዥዎችን፤ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች አናግተዋቸዋል። ሶስት ዓይነት ዉጤቶች ተከስተዋል። በቱኒሲያና በግብፅ፤ ያለ ብዙ ሕይወት ጥፋት ፈላጭ ቆራጮቻቸዉን አስወግደዋል። ዚን ኤል አቢዴን ቢን አሊ እና ሆዝኒ ሙባረክ፤ ያለ ሕዝባዊ የርስ በርስ ግጭት ከሥልጣናቸው ተባረዋል። በግብፅ፤ ሙባረክ የመጨቆኛ ክንዱ አድርጎ … [Read more...] about ከሶሪያ መሪዎች ጋር የሚደረገው ንግግር ጊዜው አልፎበታል፤
ከሶማሊያውያን የሚበልጡ ኢትዮጵያዊያን ተሰደዋል
የአራት ዓመት ማነጻጸሪያ የቀረበበትን የሪፖርቱ አንያንዳንዱ ክፍል ያስገርማል። የማነጻጸሪያው ማሳረጊያ አስደንጋጭ ነው። መረጃው በአሃዝ፣ በኩኔታ፣ በባህሪው ስደትን ይገልጻል። ትንታኔው በካርታ፣ በስደቱ መነሻና መድረሻ መካከል፣ እንዲሁም በስደት መዳረሻ ላይ የሚያጋጥመውን አፈና፣ ቶርቸር፣ አስገድዶ መደፈር፣ ስቃይ፣ የባህር ሲሳይ የሆኑ ወገኖችን ይጠቅሳል። በተለይ በምስራቅ አፍሪቃ በኤርትራ፣ በኢትዮጵያ በኬንያ፣ በጅቡቲ፣ በሶማሊያና፣ፑንት ላንድ፣ ሶማሊ ላንድ፣ ስደትና የስደትን አስከፊነት በሪፖርቱ ተዘርዝሯል። አገራችን ኢትዮጵያ በስደት የተለዩዋት ዜጎቿ ቁጥር አገር አልባ ከሆነችው ሶማሊያ የሚልቅበትን ሁኔታ ያመላክታል። የዓለም የስደተኞች ኮሚሽን ከፍተኛ ኮሚሽርን /UNHCR/ በመጥቀስ የኖቬምበር 2012 ሪፖርቱን ያቀረበው Regional Mixed Migration … [Read more...] about ከሶማሊያውያን የሚበልጡ ኢትዮጵያዊያን ተሰደዋል
ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ መገንባት ጀመረች
በጅቡቲ አዲስ የሚገነባው ወደብ ወጪ በኢትዮጵያ እንደሚሸፈን ተገለጸ። ወደቡ በቀጥታ ከትግራይ ከሚነሳው አዲሱ የባቡር መስመር ጋር እንደሚገናኝም ታውቋል። እያደር ይፋ በመሆን ላይ ያሉት ፕሮጀክቶች አቶ ሃይለማርያም አስመራ ድረስ ለመሄድ ያሳዩትን ፈቃደኛነት “ለኢሳያስ የቀረበ የፖለቲካ አይስክሬም” በማለት አስተያየት ሰጪዎች ተናገሩ፡፡ ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የመሰረት ድንጋይ ለማስቀመጥ ጅቡቲ መጓዛቸውን የዘገቡት ያገር ውስጥ መገናኛዎች ያድበሰበሱት ጉዳይ ይፋ የሆነው ዲሰምበር 18/2012 ለአሜሪካ ሬዲዮ መግለጫ የሰጡት በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የአፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝና የታሪክ ምሁር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር አየለ በከሬ ናቸው። ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋ እያደገ በመሄዱ ተጨማሪ ወደቦች እንደሚያስፈልጓት የጠቆሙት እኚሁ ምሁር በጅቡቲ የሚሰራው አዲሱ የታጁራ ወደብ … [Read more...] about ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ መገንባት ጀመረች
“እስክንድር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈታ”
አስራ ስድስት የአውሮፓ ፓርላማ አባላት የተፈራረሙበት የተላዘበ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ልከዋል። ደብዳቤው ጋዜጠኛ፣ አሳታሚና ጸሃፊ እስክንድር ነጋ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ እንዲፈታ የሚጠይቅም የሚያሳስብም ነው። ደብዳቤውን አስመልክቶ በዓለም ዙሪያ ላሉ የህሊና እስረኞች ጥብቅና የሚቆመው “የፍሪደም ናው” ነገረ ፈጅ ፓትሪክ ግሪፍተዝ ለቪኦኤ እንደተናገሩት እስክንድር ነጋ እንዲፈታ በመጠየቅ የተጀመረው ስራ እስክንድርን በማስፈታት እንደሚጠናቀቅ ገልጸዋል፡፡ እስክንድር ነጋ በየትኛውም መስፈርት ከሽብር ጋር የሚያገናኘው ጉዳይ እንደሌለ ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል። ህጉ የጋዜጠኞችን አፍ ለማዘጋት የተፈበረከ መሆኑንም አስታውቀዋል። አስራ ስድስቱ ፈራሚዎች በላኩት ደብዳቤ የእስክንድር ነጋን ቤት ለመውረስ ስለተጀመረው ሩጫ መረጃ እንዳላቸው አስታውሰው … [Read more...] about “እስክንድር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈታ”