• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በጋምቤላ፤ አሜሪካ የዜጋዋን መቃብር ከፍታ መረመረች

March 16, 2013 05:36 pm by Editor 1 Comment

በጋምቤላ የመከላከያ ሰራዊት ከጨፈጨፋቸው ሰዎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው አቶ ኡሞት ኡዶል ግድያ ለማጣራት ከአሜሪካ መንግስት የተላኩት የፎረንሲክ (ለህዝብ ይፋ የሚያደርጉ) ባለሙያዎችን ጋምቤላ ገብተው የማጣራት ሥራ ጀምረዋል። “የጋምቤላ አኬልዳማ” እየተዘጋጀ እንደሆነም ተሰማ።

የጎልጉል የጋምቤላ መረጃ አቀባዮች እንዳሉት ጋምቤላ የደረሱት የአሜሪካ ዜጎች የሄዱበትን ጉዳይ ለማከናወን ከክልሉና ከመከላከያ ሰራዊት ባለስልጣናት ዘንድ እክል ገጥሟቸው ነበር።

(ፎቶው የማሳያ ነው)

የፎረንሲክ ባለሙያዎቹ የዜጋቸውን አሟሟት መንስኤና የጉዳት መጠን ለማጣራት ጋምቤላ እንደደረሱ አስከሬኑ በስውር የተቀበረበትን ቦታ ማወቅ እንደሚፈልጉ፣ አስከሬኑ ላይ የዲኤንኤ ምርመራ በማካሄድ የሟችን ትክክለኛ ማንነት ለማረጋገጥ፣ የጉዳቱን መጠንና በምን ያህል ጥይት እንደተደበደበ ለማጣራት፣ ከዚያም በላይ ለምርመራ ስራቸው ይረዳቸው ዘንድ የሚፈልጉትን መረጃ ለመሰብሰብ ድርጊቱ የተፈጸመበት ቦታ መሄድ እንደሚፈልጉ ጠይቀው እንደነበር ለክልሉ መንግስት ቅርብ የሆኑ ለጎልጉል ገልጸዋል።

ጥያቄውን መቀበል የተሳናቸው የመከላከያና የክልሉ ባለስልጣናት አስከሬኑ መመርመር የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን፣ ከተቀበረ የቆየ በመሆኑ ለማውጣት አስቸጋሪ እንደሆነና እንደማይቻል ለመርማሪዎቹ ገልጸው ነበር። “ስራው የኛ ነው” ያሉት መርማሪዎቹ አስከሬኑ በየትኛውም ደረጃ ላይ ቢገኝም ማየት እንደሚፈልጉ፣ ይህ አቋም እንደማይቀየር መሆኑን አመልክተው አስከሬኑ የተቀበረበት ቦታ ደርሰው የሚፈልጉትን ምርመራ ማድረጋቸው ታውቋል። አከራካሪ የነበረውና ግድያው የተፈጸመበት ቦታ የመጓዙ ጉዳይ እንደነበር የጠቆሙት የመረጃው ምንጭ፣ የቀረበው መልስ አስገራሚ እንደነበር ይገልጻሉ።

“ቦታው ላይ ደም የለም፣ ማንንም አታገኙም፣ ምን ያደርግላችኋል?” የሚሉ መከራከሪያዎችን ባለሥልጣናቱ  ቢያቀርቡም ተቀባይነት ማግኘት አልቻሉም። አጣሪዎቹ ወደ ስፍራው ከመሄዳቸው በፊት ካድሬዎች ሽማግሌዎችንና ያካባቢው ነዋሪዎችን በማባበል የቅስቀሳና ፊልም የማዘጋጀት ስራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆናቸውን የጎልጉል ምንጮች አመልክተዋል።

ምንጮቹ እንዳሉት የአካባቢውን ነዋሪዎች ለማባበል አሳ አስጋሪዎቹ ሲጨፈጨፉ የታሰሩት የቀበሌ ሊቀመንበር ከልጆቻቸው ጋር ከእስር እንዲፈቱ ተደርጓል። ከዚህም በተጨማሪ አንድ ወጣት ከእስር ነጻ እንዲሆን በተላለፈ ውሳኔ መሰረት ተለቅቋል። ይህ ሁሉ የሚደረገው የአካባቢውን ሽማግሌዎች ለማባበልና “የጋምቤላ አኬልዳማ” በማለት የሚሳለቁበት ዘጋቢ ፊልም በተሳካ ሁኔታ እንዲሰራ ለመቀስቀሻነት ነው።

በጊሎ ወንዝ ዳርቻ ወደምትገኘው አብሌን በማምራት የበጋውን ደረቅ ወቅት ከወንዝ አሳ በማስገርና ያገኙትን በማደን ቀን እየገፉ ሳለ የካቲት 21፤2005ዓም (28/2/13) በድንገት የመከላከያ ሰራዊት ከበባ አካሂዶ ተኩስ በመክፈት አስራ ሁለት የሚጠጉ ንጹሃንን መግደሉን መዘገባችን ይታወሳል። እዚህ ቦታ ደርሶ ማጣራት ማካሄድ የሚፈልጉት የፎረንሲክ ባለሙያዎች ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ ወደ ስፍራው አልተነቃነቁም።

አጣሪዎቹ አቶ ኡሞት ከአሜሪካ መቼ ወደ ጋምቤላ እንዳመሩ የሚያረጋግጥ መረጃ አላቸው። ጥርሳቸውን ሲታከሙ ከነበረበት ክሊኒክ የዲኤንኤ መለያቸውን አግኝተዋል። ተጨማሪ አስፈላጊ መረጃዎችም አሏቸው። ስማቸውን የማንጠቅሳቸው ዲፕሎማት እንዳሉት ኢህአዴግ ለመዋሸት የሚችልበት ዕድል የጠበበ ነው።

ሪፖርተር ማርች 6 ቀን 2013 “በጋምቤላ ክልል 29 ሰዎች ግድያ የሚጠረጠረው ግለሰብ ተገደለ” በሚል ርዕስ ባቀረበው ዜና የፍርድ ቤት ስራ መስራቱ ብዙዎችን እንዳስገረመ የጎልጉል የአሜሪካ ዘጋቢ አስታውቋል፡፡ ስለ ህግና የህግ የበላይነት እከራከራለሁ የሚለው ሪፖርተር ያለ አንዳች የፍርድ ሂደትና ማስረጃ አቶ ኡሞትን አሸባሪ ሰፈር ማሰለፉ የሟቾችን ቤተሰቦች ቅር እንዳሰኘም ታውቋል።

የአኙዋክ የፍትሕ ምክርቤት “Anuak Justice Council – AJC” በሚል ስያሜ የሚታወቀውና ከዘጠኝ ዓመት በፊት ለ424 የአኙዋክ ተወላጆች ጭፍጨፋ ተጠያቂ የሆኑትን የህወሃት/ኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ለፍርድ ለማቅረብ የሚሠራ ድርጅትና አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው የክልሉ ተወላጆችና ፍትህ ወዳዶች አሜሪካ ለዜጎቿ የምትሰጠውን ክብር ያለማዳላት ለአቶ ኡሞት እንድትሰጥ በ11 የአሜሪካ ጠቅላይግዛቶች ተወካይ የሆኑ የሕግ መወሰኛ ም/ቤት አባላትን (ሴናተሮችን) በማነጋገር ግፊታቸውን ቀጥለዋል። እነዚህ ክፍሎች አቶ ኡሞትን ብቻ ሳይሆን ደረቁን የበጋ ወቅት ለማሳለፍ ወደ ወንዝ የወረዱ ንጹሃን በግፍ የተጨፈጨፉበት ምክንያት እንዲጣራ እየጠየቁ እንደሆነም ዘጋቢያችን አመልክቷል።

የማጣራቱ ስራ ከተጠናቀቀ በኋላ ስለሚደረገው ቀጣይ ተግባርና ራሱ የምርመራው ውጤት ምን እንደሚሆን በቀጣይ ምንጮቻችን እንዳደረሱን እንዘግባለን።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. alem says

    March 18, 2013 03:55 am at 3:55 am

    Thank you for this report. We’re very proud of our brother. His blood will cry out from the grave until this evil regime is removed.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
Copyright © 2026 · Goolgule