ካውያ እንደ ስልክ ባለቤቱን በርካታ ሥራዎችን በአንድ ጊዜ መሥራት እንደሚችል በማሳየት ለማስደሰት ቆርጦ የተነሳው ፖላንዳዊው ባል እንዳሰበው አልሆነለትም፡፡ ባለቤቱ ከሥራ ስትመጣ ማከናወን የሚገባውን ሥራዎች በተገቢው ሁኔታ ሳይፈጽም መቅረቱ ሁልጊዜ የሚያሳስበው ባል ቴሌቪዥኑን ለኩሶ ከጎኑ ቢራውን እየተጎነጨ ልብስ መተኮስ ጀመረ፡፡ በመካከል ስልኩ ሲያንቃጭል እጁ ላይ ያለው የጋለ ካውያ ስልክ የመሰለው አባወራ ካውያውን ጆሮው ላይ በመደገን ባደረሰው ጉዳት አሁን በአንድ ጊዜ በርካታ ሥራዎችን ማከናወን በተመለከተ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች እጅግ ደካማ እንደሆኑ አስመስክሯል፡፡ ከእንግዲህ ወደቤት ሥራ እንደማይመለስ የተናገረው ባል ጉዳዩ ሲያት ቀላል እንደሚመስል ከዚህ በኋላ ግን ለባለቤቱ ተገቢውን ክብር እየሰጠ አርፎ እንደሚቀመጥ ተናግሯል፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ አራት ጊዜ ቃለመሃላ … [Read more...] about የጎልጉል ቅምሻ
News
ዜና
“ከኢትዮጵያ ስለመጣችሁ ታሰራችሁ”
አገር ቤት ያሉትን ወገኖች ለጊዜው መታደግ ካልተቻለ ቢያንስ ከማንም ተጽዕኖ ወጪ በስደት የሚኖሩትን ኢትዮጵያዊያኖች ለመርዳት ለሚቀርብ ጥያቄ የሚሰጠው ምላሽ የሚያሳዝን እንደሆነ አቶ ሳሙኤል አለባቸው በእስራኤል የኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማህበር ሊቀመንበር ገለጹ። አቶ ኦባንግ ሜቶን ማህበሩ በተለይ መጋበዙን አስታወቁ። ከሚያሳዝን መከራ ተርፈው እስራኤል ከደረሱ በኋላ እስር ቤት እንዲቆዩ የተደረጉት ታዳጊዎች መፈታታቸውን አስመልክቶ መግለጫ ያሰራጩት አቶ ሳሙኤል በተለይ ለጎልጉል እንደተናገሩት “በተለያዩ አገራት መከራ እየተቀበሉ ያሉትን ወገኖች መታደግ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ተቋማትና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ጠቅሰው፣ በተግባር ግን ይህንን ማየት” እንዳልቻሉ ተናግረዋል። በእስራኤል እየደረሰ ያለውን የወገኖች ስቃይ አስመልክቶ ለቀረበ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት … [Read more...] about “ከኢትዮጵያ ስለመጣችሁ ታሰራችሁ”
ከእሁድ እስከ እሁድ
ገበያ የደራላት ጅቡቲ ታህሳስ 4 ቀን 2005 ዓም ከወደአገርቤት የተዘገበው ዜና መለስን በማስታወሻነት የሚዘክር ሆኗል። ዜናው እንዳለው ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በተገኙበት ጅቡቲ ታጁራ ላይ አዲስ ወደብ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነስርዓት አከናውናለች። የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ የወደቡ ግንባታ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ የምትፈልገውን የወደብ አገልግሎት በተሟላ ደረጃ እንድታገኝ ያስችላታል ሲሉ የ “ገበያው ደራ” ንግግር አድርገዋል። በስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት ሃይለማርያም ደሳለኝ ፥ አዲሱ የወደብ ግንባታ የኢትዮጵያና የጅቡቲ ህዝብ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑንን ጠቅሰው መናገራቸውን የገለጸው ፋና ብሮድካስቲንግ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት በየብስና በባቡር ትራንስፖርት ፣ በሃይል አቅርቦትና በወደብ አገልግሎት የተቆራኘው የሁለቱ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
ኢህአዴግ እያስታመመ ነው
የአቡነ መርቆርዮስ ወደ አገር ቤት መመለስ ከስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡ ልዩነት የተፈጠረው መንበራቸውን በመረከባቸው አብይ የቤ/ክርስቲያን ቀኖና ላይ ነው፡፡ ይህ የተገለጸው ከህዳር 26 እስከ ህዳር 30፤ 2005ዓም (December 5 – 9, 2012) በዳላስ ከተማ በቴክሳስ ጠቅላይ ግዛት በአገርቤቱ ሲኖዶስና በአሜሪካ ከሚገኘው ስደተኛ ሲኖዶስ ተወካዮች ድርድራቸው ካጠናቀቁ በኋላ ባወጡት የጋራ መግለጫ ነው፡፡ የጋራ መግለጫው ከመውጣቱ በፊት ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ አቡነ መርቆሪዮስ ከነሙሉ መንበራቸው አገር ቤት እንዲመለሱ የሚጠይቅና ማረጋገጫ የሚሰጥ ደብዳቤ ልከው ነበር፡፡ “የኔው የራሴ ደብዳቤ ነው” በማለት ለቪኦኤ የአማርኛ ክፍል በቃላቸው ጭምር ያረጋገጡት ፕሬዚዳንቱ ከአፍታ በኋላ “ያለሥልጣኔ ገብቼ የፈጸምኩት ነው” በማለት ደብዳቤውን መሰረዛቸውን አስታውቀው ነበር፡፡ … [Read more...] about ኢህአዴግ እያስታመመ ነው
ሱዛን ራይስ የቤንጋዚው መዘዝ ሰለባ ሆኑ!
በተባበሩት መንግሥታ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑትና በፕሬዚዳንት ኦባማ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መስሪያቤትን እንዲመሩ ሊታጩ ይችላሉ የተባሉት ቀዳሚ ተወዳዳሪ ሱዛን ራይስ ራሳቸውን ከእጩነት አግልለዋል፡፡ ጉዳዩ ለፕሬዚዳንቱ የፖለቲካ ክስረት፤ ምርጫውን ሲቃወሙ ለነበሩት የሪፓብሊካን ፓርቲ አመራሮች እና በአሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያውን ታላቅ ድል ሆኗል፡፡ በቅርቡ በተጠናቀቀው የአሜሪካ ምርጫ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለሁለተኛ ጊዜ መመረጣቸውን ካረጋገጡ በኋላ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሱዛን ራይስ ሂላሪ ክሊንተንን እንደሚተኩ በሰፊው መነገር ተጀመረ፡፡ የፕሬዚዳንቱ ቀዳሚ እጩ መሆናቸው ብዙ ቢነገርላቸውም ከተቃዋሚዎቹ የሪፓብሊካንና ሌሎች ጉዳየኞች የተቃውሞ ድምጽ ለመስማት ግን ብዙም ጊዜ አልወሰደም፡፡ መስከረም 1፤ 2005ዓም በሊቢያ ቤንጋዚ ከተማ የአሜሪካ … [Read more...] about ሱዛን ራይስ የቤንጋዚው መዘዝ ሰለባ ሆኑ!
አንድነት ስየን ሊሰርዝ ወይም ሊያስጠነቅቅ ይችላል
በነባር አመራሮች ሲንከባለል የኖረው “የቅንጅት ወራሽ” አንድነት ፓርቲ ኃላፊነቱንና አመራሩን ለተተኪ ሳያስረክብ መቆየቱ በአብዛኛው ትችት ሲያሰጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ በተለይም አቶ ስየ አብርሃ ፓርቲውን በተቀላቀሉ ማግስት በከፍተኛ ኃላፊነት መሰየማቸው አልተወደደለትም ነበር፡፡ በአንድነት ፓርቲ ውስጥም እስከመከፋፈል የዘለቀ ልዩነት መፍጠሩ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ አሁን የረገበ የሚመስለው የፓርቲው የውስጥ ልዩነት፤ በወቅቱ “ዝም አንልም፤ መርህ ይከበር” የሚሉት ኃይሎች የወሰዷቸውን ጽንፈኛ አቋሞች ብዙዎች የሚደግፉት ባይሆኑም ያነሱትን ጥያቄ አግባብነት ግን ይቀበላሉ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ይሁን በሌላ የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊመንበር የነበሩት ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም “እኛ የማማከር አገልግሎት መስጠት አለብን፤ አመራሩን መያዝ ያለበት አዲሱ ትውልድ ነው” በማለት ራሳቸውን … [Read more...] about አንድነት ስየን ሊሰርዝ ወይም ሊያስጠነቅቅ ይችላል
አልአሙዲ ያጠሩትን መሬት ተነጠቁ
የሼክ መሐመድ ሁሴን አልአሙዲ ኢንቨስትመንት ላይ ጥያቄ ያላቸው ጥቂት አይደሉም። የራሳቸውን ህንጻ ከመጨረስ ይልቅ በኪራይ አንድ ህንጻ የሚያሰራ ገንዘብ ለዓመታት ሲከፍሉ ማየትና መስማት የተለመደ ነው። የንግድ ሰዎች ይህንን ዝንባሌያቸውን ከነጋዴ የሚጠበቅ እንዳልሆነ ይናገራሉ። በዙሪያቸው ተሰባስበው ያሉትም ቢሆኑ አመቺ ቦታ ሲያገኙ በዚሁና በሌሎች ጉዳዮች ያሟቸዋል። ጊዮን ሆቴል አጠገብ የተሰራው የናኒ ህንጻ ሲጀመር የተወለደ ህጻን አስራ ሁለት ዓመት ሲሞላው ነው ያለቀው። ከጊዮን ሆቴል ፊትለፊት ለአስራ ሁለት ዓመት ለህንጻው መጋዘን ሆኖ ሲያገለግል የነበረው የአዲስ አበባ ስታዲየም የመኪና ማቆሚያ ተገቢው ክፍያ ሳያገኝ ቢኖርም የሳቸውን ፎቶ በስታዲየም ውስጥ ለመለጠፍ ቀዳሚ ነው። አሁን መለስ መጡና አሳነሷቸው እንጂ ስታዲየሙ የእርሳቸው የሚመስልበት አጋጣሚም … [Read more...] about አልአሙዲ ያጠሩትን መሬት ተነጠቁ
የጎልጉል ቅምሻ
ብልቴን ሰረቁት በምስራቅ ቻይና የዢያንግ አውራጃ የኒቂያዖ ፖሊስ የደረሰው ክስ ግራ የሚጋባ ሆኗል፡፡ የ41ዓመቱ ፌ ሊን “ተኝቼ ሳለ ሌቦች ክፍሌ በርግደው በመግባት ብልቴን ሰረቁት” በማለት ነበር ወንጀሉን ያብራራው፡፡ ሲቀጥልም ሌቦቹ ቤቱ እንደገቡ ጭንቅላቱ ላይ የሆነ ነገር አድርገው ሱሪውን ወደታች ካወረዱ በኋላ ሮጠው እንደጠፉ አስረድቷል፡፡ “በጣም ከመደንገጤ የተነሳ ምንም የተሰማኝ ነገር አልነበረም፤ በኋላ ግን እየደማሁ መሆኔን ሳስተውል ብልቴ ተበጥሶ መሄዱን አስተዋልኩ” ብሏል፡፡ ፖሊስ እንደሚለው ሌቦቹ ሊን በሚያዘወትራቸው በርካታ ሴቶች የቀኑ አፍቃሪዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምት በመስጠት ፍለጋውን ቀጥሏል፡፡ ሊን ግን ይህንን የፖሊስ መላምት ካለመቀበል በተጨማሪ የትም ሂያጅ ሳይሆን ታማኝ እንደሆነ ለራሱ ይመሰክራል፡፡ በስርቆቱ በርካታ አስተያየቶች እየተሰጡ ቢሆንም በርካታዎች … [Read more...] about የጎልጉል ቅምሻ
“በአገራችን የአሸባሪዎች ድር አለ”
ኢትዮጵያን መምራት ከጀመሩ ሶስት ወር ያስቆጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ኢትዮጵያ በአሸባሪዎች የተከበበች አገር መሆኗን አመለከቱ። ኦብነግ በመገንጠል ስም የፖለቲካ ንግድ የሚያካሂድ ድርጅት እንደሆነ ገለጹ። መንግስታቸው ለሚታማበት ጉዳይ ማስተባበያ አቀረቡ። ከአልጃዚራ ቴሌቪዥን እንግሊዝኛው ክፍለጊዜ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት አቶ ሃ/ማርያም ስለ አሸባሪዎች የተናገሩት በአገሪቱ የተነሳው የእስልምና ሃይማኖት ጥያቄና ተቃውሞ ስለቀረበበት የአህባሽን አስተምሮ ተከትሎ ከአያያዝ ጉድለት ጉዳዩ ወደ ቀጠናው እንዳይሸጋገር ስጋት ስለመኖሩ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ ነው። “ጥያቄው የጥቂቶች ነው” በሚል አቃለው በማቅረብ ማብራሪያቸውን ጀመሩ። መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ በማመልከት አብዛኞቹ ሙስሊሞች ጥያቄያቸው የአስተዳደርና የሲስተም መሆኑንን አመላክተው … [Read more...] about “በአገራችን የአሸባሪዎች ድር አለ”
ከእሁድ እስከ እሁድ
የጉራ ፈርዳ አማሮች መሬታቸው በሃራጅ ተሸጠ ቪኦኤ ሰለባዎችን በማነጋገር እንደዘገበው የጉራ ፈርዳ ነዋሪ አማሮች መሬታቸውን እንዳያርሱ ከተከለከሉ በኋላ መሬታቸው በሃራጅ እየተሸጠባቸው እንደሆነ ይፋ አድርጓል። መሬታቸውን በህጋዊ መንገድ የግላቸው እንዳደረጉና ግብር እየከፈሉ የሚኖሩት ተበዳዮች ርምጃው የተወሰደባቸው ቅንጅትን በመምረጣቸውና ለመኢአድ መረጃ ትሰጣላችሁ በሚል እንደሆነ ተናግረዋል። በተደጋጋሚ መታሰራቸውንና በከሰሳቸውን የተናገሩት የጉራ ፈርዳ ነዋሪ ከእስር ከተፈቱ በኋላ “መሬታችሁን የያዛችሁት በህጋዊ መንገድ ነው” በማለት ለመኢአድ መረጃ መስጠታቸው እንደ ጥፋት እንደተወሰደባቸው አመልክተዋል። በ1997 ምርጫ ወቅት በምስጢር የድምጽ መስጫ ክፍል ውስጥ የጤና ባለሙያዎችን በማስቀመጥ ማንን እንደመረጡ መሰለላቸውንም አመልክተዋል። የሚሸጠውን መሬት የወረዳ፣ የቀበሌ፣ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ