የዋቄፈታ እምነት ተከታዮች በማህበር ተደራጅተው እውቅና ጠየቁ! ባለአወልያዎችም ተደራጅተዋል በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የዋቄፈታ እምነት ተከታዮች በማህበር ተደራጅተው ህጋዊ ፈቃድና የህጋዊነት ማረጋገጫ የምሰክር ወረቀት የጠየቁት “ይበራል ይከንፋል፣ አይሞትም ያርጋል” እየተባለ ሲመለክ የነበረው ታምራት ገለታ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ ነበር። የእምነቱ መሪዎች በ2002 ዓ ም ወልመራ ከተማ ቆቦ በምትባል ቀበሌ መስራች ስብሰባ አካሂደው እንደነበረ ያስታውሳሉ። ከሁለት ዓመት በፊት የወልመራ ወረዳ ከተማ በሆነችው ሆለታ የተደራጁት የዋቄፈታ ስርዓተ አምልኮ ተከታዮች የህጋዊነት ጥያቄ ያቀረቡት ለኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ መሆኑን የሚጠቅሱት እነዚህ የእምነቱ ተከታዮች ለጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ እንደገለጹለት ከሆነ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቷል። መንግሥት በተደጋጋሚ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
News
ዜና
ኢህአዴግ በፖለቲካ ወለምታ ውስጥ!!
ኢህአዴግ በ“ፖለቲካ ወለምታ” ውስጥ እንደሚገኝ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የኢህአዴግ ዲፕሎማት ለጎልጉል ተናገሩ። በከፊል ኢህአዴግን የተለዩ የሚስሉት ዲፕሎማት በጎልጉል የቅርብ ሰው አማካይነት ድምጻቸው ሳይቀረጽ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት የተፈጠረው የፖለቲካ ወለምታ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል አመልክተዋል። የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በመካከለኛ አመራሩ ውስጥ የመጠራጠር ስሜት መፈጠሩን በፓርቲ ግምገማ ላይ በግልጽ መናገራቸው የዲፕሎማቱን አስተያየት የሚያጠናክር ሆኖ ተገኝቷል። የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የአቶ መለስን ሞት ደብቀው በመያዝና ማስተባበያ በመስጠት ጊዜ የወሰዱት ይኸው የተባለው የፖለቲካ ወለምታ እንዳይፈጠር ለማድረግ በማሰብ እንደነበር ዲፕሎማቱ ያስታውሳሉ። ይሁን እንጂ አቶ መለስ ሁሉንም ጉዳይና ሃላፊነት ብቻቸውን ይዘውት ስለነበር በድንገት ማለፋቸው … [Read more...] about ኢህአዴግ በፖለቲካ ወለምታ ውስጥ!!
ድህረ ምርጫ አሜሪካ
“ሊሆን የማይችል ነገር ነው” ባለፈው ማክሰኞ የተከናወነው የአሜሪካ የፕሬዚዳንት ምርጫ ተጠናቅቆ ባራክ ኦባማ ማሸነፋቸው ግልጽ በሆነበት ጊዜ የሚት ሮምኒ የምርጫ ዘመቻ ኃላፊዎች በተወሰኑ ግዛቶች የድጋሚ ቆጠራ እንዲካሄድ መፈለጋቸው ተገለጸ፡፡ በተለይ በኦሃዮ፣ ፍሎሪዳና ቨርጂኒያ ግዛቶች የተደረገውን የድምጽ ቆጠራ ለማስደገም አራት አውሮፕላኖች የሪፓብሊካን ፓርቲ ሰዎች ለመላክ በወሰኑበት ጊዜ ሚት ሮምኒ “ሊሆን የማይችል ነገር ነው” በማለት ጉዳዩ እንዲቆም ከልክለዋል፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት በተሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ መሠረት ኦባማ ሦስቱንም ግዛቶች በጠባብ ውጤት ማሸነፋቸው ይፋ ሆኗል፡፡ በሌላ በኩል ሮምኒ ምርጫውን ያሸንፋሉ በሚል እሳቤ ተዘጋጅቶ የነበረ የእጩ ፕሬዚዳንት ድረገጽ ለተወሰኑ ጊዜያት ተለቅቆ እንደነበር ሮል ኮል የተሰኘ የፖለቲካ ድረገጽ አስታውቆዋል፡፡ ይኸው … [Read more...] about ድህረ ምርጫ አሜሪካ
ከእሁድ እስከ እሁድ
ኢህአዴግ በ “ልማት ሠራዊት” ግንባታ ችግር ገጠመኝ አለ ኢህአዴግ በልማት ሠራዊት ግንባታ ችግር እንደገጠመው አስታወቀ። ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በብአዴን ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንዳስታወቁት አሁን የተፈጠረው ስሜት “መነቃቃት ነው” ካሉ በኋላ “መነቃቃት በመፈጠሩ የተሰራው ስራ የዘመቻ ነው” ብለዋል። አቶ ደመቀ “የአመለካከት ችግር አለ” በማለት የልማት ሰራዊት ግንባታው ችግር እንደተጋረጠበት አመልክተዋል። የብአዴንን ግምገማ ከፋፍሎ ካሳየው የአማራ ቴሌቪዥን ለመረዳት እንደተቻለው አቶ በረከት ስምኦንም አቶ ደመቀን አግዘዋል። ከ2003 ጋር ሲነጻጸር በተጠናቀቀው ዓመት የተሰራው ስራ የተሻለ መሆኑን ጠቁመው “የልማት ሰራዊት ግን አልፈጠርንም” ብለዋል። የክልሉ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊና ምክትል ር/መስተዳድር አቶ ጉዱ አንዳርጋቸው “የተጀመረው ልማት … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
“ኦባማ መጀን” ወይስ “በእውቀት” መደራጀት?
የአሜሪካ ምርጫ ሲጠናቀቅ ተሸናፊው ሚት ሮምኒ ደጋፊዎቻቸው በተሰበሰቡበት አዳራሽ ምስጋና ካቀረቡ በኋላ እንዲህ አሉ፡- “… ሁለታችንም ለምንወዳት አገራችን የምንመኘውን ለማድረግ በተለያየ አቅጣጫ ሞከርን፤ … ሕዝባችን ደግሞ የሚፈልገውን መሪ መረጠ፤ … ስለዚህ ፕሬዚዳንቱን ደውዬ አነጋሬያቸዋለሁ፤ ባገኙትም ድል እንኳን ደስ አለዎ ብያቸዋለሁ፤ … በተለይ ለእርሳቸው፣ ለቀዳማዊ እመቤት እና ለልጆቻቸው ሁሉ መልካሙን እመኛለሁ፤ … አገራችን ከባድ ፈተናዎች ተጋርጠውባታል፤ … ባለቤቴና እኔ ለፕሬዚዳንቱና ቤተሰባቸው ከልብ እንጸልያለን፤ በሥራቸው ስኬት እንዲያገኙና ታላቋን አገራችንን በመምራት የሚያከናውኑት ሁሉ የተሳካ እንዲሁን እመኛለሁ፡፡” ይህንን ካሉ በኋላ ወደተለመደው ህይወታቸው ሄዱ - የፖለቲካ ገዳም ገቡ፡፡ ይህ ንግግር ወደራሳችን እንድንመለከት የሚያደርግ ነው፡፡ የእኛስ ፖለቲከኞች … [Read more...] about “ኦባማ መጀን” ወይስ “በእውቀት” መደራጀት?
ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን ምስጢር ይፋ አደረጉ
“የሙስና መርከብ” በሚል ስያሜ የሚጠሩት አሉ። ከተቋቋመ ጀምሮ አንድም ቀን ስለንብረቱ መጠን ለህዝብ ተገልጾ አያውቅም። ከአገሪቱ ባንኮች ትልቁ ተበዳሪ ነው።የወጋጋን ባንክ ትልቁ ባለድርሻ ነው። በአንዳንድ ከፍተኛ የንግድ ተቋማት ውስጥ የንግድ ሽርክና እንዳለው ይታማል። የወርቅ ማዕድን ፍለጋው ሰምሮለታል። የግል አስመጪዎችን በመፈታተን አነካክቶ ጥሏቸዋል። አገሪቱ ላይ የገነባው የንግድ ኢምፓየር በበርካቶች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል። በሌሎች ክልሎች በተመሳሳይ የተቋቋሙትን የንግድ ተቋማት በመደፍጠጥ በፖለቲካው የበላይነቱ ሳቢያ ልዩ ተጠቃሚ በመሆኑ አይወደድም። ይህ ታላቅ የህወሃት የንግድ ግዛት ኤፈርት ነው። የትግራይ ህዝብ “ያንተ ነው” ስለሚባለው ታላቅ የንግድ ኢምፓየር የሚያውቀው ነገር እምብዛም የለም። አስራ ሶስት ሰፋፊና ስትራቴጂክ ኩባንያዎችን ያቀፈው ኤፈርት በቅርቡ የእህት … [Read more...] about ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን ምስጢር ይፋ አደረጉ
“በአገራችን ባይተዋር ከመሆን በላይ ውርደት የለም”
ይህንን ዘገባ ሳሰናዳ በ1997 ምርጫ ወቅት አዲሱ ገበያ አካባቢ አልሞ ተኳሾች የገደሉባቸውን ልጃቸውን ስም እየጠሩ “ምን አደረካቸው? ምን አጠፋህ? አንተኮ ትንሽ ነህ? ማንን ልጠይቅ? ማንን ላናግር? ልጄ … የኔ ባለተስፋ፣ እኔ ልደፋ፣ እኔ መንገድ ላይ ልዘረር፣ ምነው ለኔ ባደረገው? የማን ያለህ ይባላል…” የሚሉ ልብን ዘልቆ የሚገባ ሃረግ እየደጋገሙ እብደት የተቀላቀለው ለቅሶ አልቅሰው ያስለቀሱን እናት ታወሱኝ፤ ብዙዎች በተመሳሳይ አንብተዋል።ደረታቸውን ደቅተዋል። አሁን ድረስ የልጅ፣ የአባት፣ የወንድም፣ የእህት፣ የዘመድና ወዳጅ ብሎም የአገር ልጅ ሃዘን የሚያቃጥላቸውን ቤታቸው ይቁጠራቸው። “ኢትዮጵያ ለእኛ አስፈላጊ አገር ናት። ኢትዮጵያዊ በመሆናችን ለአገራችን ትልቅ ቦታ መስጠት አለብን። ምክንያቱም አስፈላጊ ናትና። እዚያ እስከተወለድን ድረስ /መሰረታችን ኢትዮጵያ እስከሆነች … [Read more...] about “በአገራችን ባይተዋር ከመሆን በላይ ውርደት የለም”
ከሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች
የአዲግራት ወህኒ ቤት ተደረመሰ በትግራይ ክልል ካሉት እስር ቤቶች መካከል ከ1‚300 በላይ የሚሆኑ የሕግ እስረኞችን የያዘው የአዲግራት ወህኒ ቤት ባለፈው ረቡዕ ተደርምሶ 14 እስረኞች ሲሞቱ፣ ከ35 በላይ ደግሞ በከባድ ሁኔታ መጎዳታቸውን ሪፖርተር ምንጮች እንደነገሩት ጠቅሶ አስታወቀ። እስር ቤቱ በምን ምክንያት እንደተደረመሰ ያልገለጸው ሪፖርተር እስረኞቹን ለማትረፍ ሦስት ሎደሮችና በርካታ ወታደሮች ሲረባረቡ ማየታቸውን አመልክቷል። አደጋው ቀን ረፋድ ላይ መድረሱ በጀ እንጂ አደጋው የከፋ ሊሆን እንደሚችል ተዘግቧል። ተረፉ የተባሉት 35 ሰዎች ክፉኛ በመጎዳታቸው አዲግራት ሆስፒታል ተኝተዋል። ህይወታቸው ያለፈው 14 እስረኞች ግን ከፍርስራሹ መቀበራቸውን የሪፖርተር ዘገባ ያስረዳል። የመከላከያ ሰራዊት አባላት ያደረጉት በዶዘር የተደገፈ ርብበርብ በህይወት የተረፉትን ነፍስ እንደታደገ … [Read more...] about ከሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች
“የአረብ ጸደይ” ለኢትዮጵያ “የቆላ ቁስል” ይሆን?
ሶርያን ጊዜያዊ ማረፊያው አድርጎ አገሪቱን እያዳሸቀ፣ ህዝቡን እየበላ፣ ያለው የ“አረብ ጸደይ” ብዙዎች እንደሚሉትና የመፈክር ያህል እንደሚስተጋባው መነሻው የቱኒዚያ ምድር ሳይሆን ቆመች ስትባል መልሳ በምትናጠው ጎረቤታችን ሶማሊያ ነው። ይኸው የለውጥ “ቀይ” ነፋስ በሊቢያ ጋዳፊን እንደምናምንቴ በውሻ አይነት አሟሟት እስከወዲያኛው አሰናብቷል። ጋዳፊ ላይ ከተፈጸመው ጋር በንጽጽር ላስተዋለው አሁን በሶሪያ እየተከናወነ ያለው የዚያ ግልባጭ መሆኑን ለመረዳት የሚያዳግት አይደለም፡፡ በአገራችን አባባል “የቆላ ቁስል” እንደምንለው! ዓለምአቀፍ የግንኙነት ቡድን ተፈላጊ የሆነው አገር ስም እየተሰጠው በዓለምአቀፉ ኅብረተሰብ (በምዕራባውያን ወኪልነት) የሚቋቋመው ዓለምአቀፍ የግንኙነት ቡድን (International Contact Group) እየተባለ የሚጠራው አካል ለሶማሊያ የተመሠረተው እኤአ … [Read more...] about “የአረብ ጸደይ” ለኢትዮጵያ “የቆላ ቁስል” ይሆን?
“ገበሬው ነጻ እስካልወጣ ችጋር ይቀጥላል”
“የዜግነትና የሰውነት መሰረታዊ መብቶች በተከበሩ ጊዜ ሌሎች መብቶች ሁሉ ይከበራሉ” የሚል ዋና መርህ ያለው በወጣት አመራሮች የተገነባው ሰማያዊ ፓርቲ ገበሬው ነጻ እስካልወጣ ድረስ ችጋር ከኢትዮጵያ ምድር ሊጠፋ እንደማይችል አሳሰበ። የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌታነህ በፓርቲያቸው ድረገጽ ላይ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፣ ኢህአዴግ ታላቅ ገድል አድርጎ የወሰደውን የጠቅላይ ሚኒስትር ሹመት አስመልክቶ “ላይመለስ የሄደ ሰው ነበር፤ ባዶ ቦታ ነበር። ምክትሉ ተተኩ” ሲሉ የስልጣን ሽግግር አለመካሄዱን ጠቁመዋል። የዛሬ መቶ ዓመት የተደረገውን የስልጣን ስያሜ የተሻለ ነበር ብለዋል። “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከመሰረቱ መነሳት ያለበት ከግለሰብ መብት ላይ መሆን እንዳለበት እናምናለን” በማለት ለግለሰብ መብት መከበር ያላቸውን ጽኑ እምነት ኢንጂነር ይልቃል ጌታነህ “ሰው … [Read more...] about “ገበሬው ነጻ እስካልወጣ ችጋር ይቀጥላል”