ኢህአዴግ ከወትሮው በበለጠ አስመራ ላይና አስመራን ተገን ያደረጉ ተቃዋሚዎች አስመልክቶ የተንጠለጠሉ ጉዳዮችን አንድም በሰላማዊ መንገድ፣ አለያም በሃይል ለመቋጨት ፍላጎት እንዳለው ከተለያዩ ምንጮች ይሰማል። ይህንኑ መረጃ የሚያጠናክሩ መግለጫዎችና ዜናዎችም በቀጥታና በተዘዋሪ እየተደመጡ ነው። ድርድሩ የሚካሄደው ኦነግን ጨምሮ ከተለያዩ ድርጅት አመራሮች ጋር በተናጠል ስለመሆኑ ለስርዓቱ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ጠቁመዋል። ኦነግንና ኢህአዴግን ለማስማማት ከላይ ታች የሚሉት የአገር ሽማግሌዎች የሚባለውን ቁጥሩ በውል የማይታወቅ ኮሚቴ የሚመሩት ፕ/ር ኤፍሬም ይስሃቅን ጨምሮ የቀድሞው የኦነግ አመራር አባቢያ አባጆቢር፣ የኢትዮጵያ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት የነበሩት ቄስ ኢተፋ ጎበናና ከሳቸው ጋር የሚሰሩት ኮሚቴዎች፣ በአሜሪካ የወንጌላዊት ሉትራን ቤ/ክ የአፍሪካ ብሔራዊ … [Read more...] about ኢህአዴግ ኦነግን እያሰበ አስመራ ላይ አነጣጥሯል!
News
ዜና
የጎልጉል ቅምሻ
ስኳር ለስኳር በሽታ ያጋልጣል “ጣመኝ ድገመኝ” የምንላቸው ዓይነት ብስኩቶች፣ የቸኮሌት ውጤቶች፣ አይስክሬም፣ ብርታት ሰጪ መጠጦች፣ … በከፍተኛ ሁኔታ ለስኳር በሽታ እንደሚያጋልጡ ሳይንስ ደርሼበታለሁ ይለናል፡፡ በእነዚህ የምግብ ውጤቶች ውስጥ የሚገኘው የበቆሎ ስኳር (fructose corn syrup - HFCS) ምግቦቹን ለማጣፈጥ የሚጨመር በመሆኑ ይህንን ተመጋቢ የሆኑ 20በመቶ ለስኳር በሽታ መጋለጣቸው የማይቀር ነው ይላል ውጤቱ፡፡ ከምዕራባውያን አገራት መካከል አሜሪካ በጣፋጩ አወሳሰድ ቀዳሚውን ስትይዝ በአማካይ አንድ ሰው በዓመት 24.78ኪሎ የበቆሎውን ስኳር በተለያዩ ምግቦች አማካኝነት ወደ ሆዱ ይጭናል፡፡ አንድ ካናዳዊ በዓመት 9.13ኪሎ ሲጭን አንድ ጣሊያናዊ ወይም እንግሊዛዊ ከግማሽ ኪሎ በታች እንደሆነ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ ግብጻዊያን 1.6ኪሎ በአማካይ እንደሚጭኑ ያስረዳው … [Read more...] about የጎልጉል ቅምሻ
ህወሓት ደብረጽዮንን ቀጣይ ጠ/ሚ/ር ያደርጋል!
ከአቶ መለስ መለየት በኋላ ወደ አደባባይ የወጡት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆኑ እንደሚችሉ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ግምታቸውን ሰጡ። አገር ቤት ተቀምጠው በኢህአዴግ ላይ የሰላ ትችት በማሰማት ቀዳሚውን ስፍራ የያዙት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምህርና እንደ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም የአደባባይ ምሁር በመባል የሚታወቁት ዶ/ር ዳኛቸው ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ይፋ እንዳደረጉት ለግምታቸው ምክንያት ሰጥተዋል። አቶ መለስ በህይወት እያሉ የስልጣን ክፍፍሉን በሶስት ለመመደብ መታሰቡን ሰምተው እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር ዳኛቸው፣ ሃሳቡ ከስምምነት ላይ ሊደረስ ባለመቻሉ ተግባራዊ ሊሆን እንዳልቻለ አመልክተዋል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማንም ይሁን ማን ከዚህ ቀደም እንደነበረው ስልጣኑ በአንድ ሰው ላይ ተጭኖ ሊቀጥል እንደማይችል … [Read more...] about ህወሓት ደብረጽዮንን ቀጣይ ጠ/ሚ/ር ያደርጋል!
ከእሁድ እስከ እሁድ
በዱባይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነጋዴ ወይስ ለወገን ደራሽ? በዱባይ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ፓስፖርታቸው በአሰሪዎቻቸው አማካይነት ለተመለሰላቸው ወገኖች የፓስፖርት እድሳት በሚል አንድ ሺህ አንድ መቶ ድራም እንደሚያስከፍል ተሰማ። ለጎልጉል በስልክ መረጃ የሰጠች አንድ የዱባይ ነዋሪ ኤምባሲው አገልግሎቱን መጀመሩ እንደሚያስመሰግነው ጠቁማ፣ ክፍያው ግን የተጋነነ ንግድ እንደሚመስል አስታውቃለች። ዘጠና ከመቶ የዱባይ ነዋሪዎች ፓስፖርታቸው ጊዜው ያለፈበትና በአሰሪዎቻቸው በመያዣነት የተያዘ እንደሆነ የጠቀሰችው ይህች ወጣት “በችግር ላይ ካሉ ዜጎች ላይ ከስድሰት ሺህ በላይ የኢትዮጵያ ብር መቀበል አግባብ አይደለም። ኤምባሲው ፓስፖርታቸው ለተወሰደባቸውም መላ ይፈልግ” ስትል ጠይቃለች። አሰሪዎቻቸው በሚያደርሱባቸው በደል ተማረው የሚጠፋ ወገኖች ፓስፖርታቸው በመያዣነት አሰሪዎቻቸው ዘንድ ስለሚቀር የጉዞ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
የጁነዲን መጨረሻ አልታወቀም
ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም የኢትዮጵያን ታላቅ የሥልጣን መቀመጫ ሲረከቡ “ለተደረገልን ምደባ አመሰግናለሁ” ማለታቸውን ተከትሎ የከፍተኛ ባለሥልጣናት ሹመት “ምደባ” የሚል ስያሜ አግኝቷል። ትላንት ለተወካዮች ምክር ቤት በቀረበ የሽግሽግ ምደባ አቶ ጁነዲን ሳዶ ከምደባ ተዘለው ከሃላፊነታቸው መነሳታቸው ይፋ ሆኗል። የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ጁነዲን ሳዶ ወንበራቸውን ለአቶ ሙክታር ከድር እንዲያስረክቡ ተደርጓል። ኦህዴዱ አቶ ሙክታር የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ታክሎላቸው አቶ ጁነዲን ሲመሩት የነበረውን የሲቪል ሰርቪስ ተቋም እንዲመሩ ሲደረግ አቶ ሃይለማርያም ስለአዲሱ ተሿሚ አቶ ሙክታር ቁርጠኛነትና ብቃት ሲያብራሩ ስለ አቶ ጁነዲን ከሃላፊነት መነሳት ግን ያሉት ነገር የለም። ለዚህም ይመስላል የመድረክ አባል ብቸኛው ተቃዋሚ አቶ ግርማ ሰይፉ “ህዝብ … [Read more...] about የጁነዲን መጨረሻ አልታወቀም
ህወሃት አረጋግቶ አገገመ
ኢህአዴግ “አረጋግቶ አገገመ” ከተባለው አዲሱ “ምደባ” መካከል የንግድ ሚኒስትር ተብለው በተሰየሙት ላይ ብቸኛው የፓርላማ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ጠንካራ መከራከሪያ በማቅረብ ተቃወሙ። አቶ ግርማ የሚሾሙ ብቻ ሳይሆን የሚነሱ ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው የተነሱበት ምክንያትም ለህዝብ መቅረብ እንዳለበት አሳሰቡ። አቶ ሃይለማርያም ተቃውሞውን “መክረንና ገምግመን ያደረግነው ነው” ሲሉ ተከላከሉ። አቶ ግርማ ብሩ (አሁን አምባሳደር) ሲመሩት የነበረውን ሚኒስቴር መ/ቤት “ስያሜና ምልክት መለየት የማይችል” በማለት አንቋሸሹት። ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አገሪቱን በመሩበት ሶስት ወራት ካቢኒያቸውን በደንብ መገምገማቸውን በግምት በመግለጽ ተቃውሞ ያቀረቡት አቶ ግርማ ሰይፉ በምደባው በተወሰነ ደረጃ እንደሚስማሙ ተናግረዋል። የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔን ምደባ የተቃወሙት በማስረጃ … [Read more...] about ህወሃት አረጋግቶ አገገመ
የጎልጉል ቅምሻ
ለቢንላደን ቀብር ምስካሪ የባህር ኃይል የለም በሚያዚያ ወር 2003ዓም ድንገተኛ ወረራ ተካሂዶበት ቀብሩም ወዲው ተጠናቅቆዋል የተባለው ኦሳማ ቢንላደን ባህር ውስጥ ሲቀበር የተመለከተ አንድም የአሜሪካ የባህር ኃይል አባል እንደሌለ ተገለጸ፡፡ አሶሺየትድ ፕሬስ “የመረጃ ነጻነት ሕግን” ጠቅሶ በጠየቀውና ባገኘው መረጃ መሠረት “ባልታወቀ ባህር” ተቀበረ የተባለው ቢንላደን ሲቀበር ምስካሪ እንደሌለ የዘገበ ሲሆን ከፓኪስታን ወደ ካርል ቪንስ የአሜሪካ የጦር መርከብ በተጫነበት ወቅት የተነሳ ፎቶግራፍም ሆነ ቪዲዮ የመከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን) ማግኘት እንዳልቻለ ጨምሮ አስታውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የድህረሞት ምርመራ፣ የሞት ሠርቲፊኬት፣ የዲኤንኤ ምርመራ፣ … እንዳልተካሄደና ይህንኑ የሚያሳይ መረጃ የመከላከያ ሚ/ር ማቅረብ እንዳልተቻለ ተገልጾዋል፡፡ የቢንላደን ሬሣ ከታጠበና በነጭ ጨርቅ … [Read more...] about የጎልጉል ቅምሻ
ከእሁድ እስከ እሁድ
የእስክንድር ነጋ ጉዳይ ለመንግሥታቱ ድርጅት ቀረበ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያላግባብ የታሠሩ ሰዎችን ጉዳይ ለሚያጠናው ግብረኃይል መቅረቡን ለህሊና እስረኞች የሚሟገተው ፍሪደም ናው “Freedom Now” ስራ አስፈጻሚ ዋና ዳይሬክተር ማርዳ ተርነር ለአሜሪካ ሬዲዮ አስታውቀዋል። ዳይሬክተሯ እንዳሉት ድርጅታቸው የእስክንድር ነጋን ጉዳይ በጥልቀት ከመረመረ በኋላ የጋዜጠኛነት ስራውን ብቻ ሲያከናውን እንደነበር ሙሉ አረጋግጠዋል። የታሰረውም ያለ አግባብ እንደሆነ ታምኖበታል። በእስር ቤት ከአያያዝ ጀምሮ በርካታ ጥሰቶች እንደተፈጸሙበት አመልክተዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ለዓለም አቀፍ ህግጋት የገባውን ኪዳንና ግዴታ በመጣሱ የእስክንድር ጉዳይ በተባበሩት መንግስታት ያለ አግባብ የታሰሩ ሰዎችን ጉዳይ ለሚመረምረው አካል ባለፈው ሚያዚያ ቀርቧል። … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
“የኢሳያስ ልጅ አይከዳም! አናምንም”
ከኤርትራ ሰሞኑን የሚወጡ መረጃዎች ከጉዳዩ ባለቤቶች ማረጋገጫ ወይም ማስተባበያ ባይቀርብበትም ከኤርትራ ጋር በተያያዘ የተለያዩ አቋምና ተስፋ ባላቸው ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት የሳበ ጉዳይ ሆኗል። አንዳንድ በብሎግ ሂሳብ የሚጫወቱ የኤርትራ መንግሥት አገልጋዮች ለጉዳዩ ጆሮ ዳባ ቢሉም በዋና በተቃዋሚነት የሚታወቁት የኢሳያስ ባላንጣዎች ለወሬዎቹ ሽፋን በመስጠት ግንባር ቀደም ሆነዋል። የ1997 ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረው አለመረጋጋት “ህወሃት ሰራዊቴን በመያዝ ጓዜን ጠቅልዬ ወደ ትግራይ ምድር እገባለሁ” ማለቱን አስነብቦ የነበረው ኢንዲያን ኦሽን ኒውስ ሌተር ሰሞኑን የህወሃት ሊቀመንበርን ጠቅሶ ኤርትራ ላይ ጦርነት የማወጅ ፍላጎት እንዳለ ይፋ አድርጓል። ኢንዲያን ኦሽን ከውስጥ አዋቂዎች አገኘሁ በማለት ሌላ ያሰነበበው ዜና የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ አሊ አብዶ ካናዳ ጥገኝነት … [Read more...] about “የኢሳያስ ልጅ አይከዳም! አናምንም”
ኢህአዴግ ኢህአዴግን ማፈን ጀመረ!
የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ስም ሲነሳ አቶ በረከት ስምዖን በግንባር ቀደም ይጠቀሳሉ። የአቶ በረከት ንብረት ሆኖ የመለስን አመራር በታማኝነት ሲያገለግል የኖረው ይህ ተቋም ቆርጦ በመቀጠል፣ የዜጎችን ሃሳብ በማዛባት፣ ወሬን ባለማመጣጠንና የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በማስተላለፍ የሚታወቅ ነው። ስለሚጠየፉት የማይመለከቱት እንዳሉ አፍ አውጥተው የሚናገሩም አሉ። ለሙያው ቅርብ የሆኑ አስተያየት ሰጪዎች “ወገንተኛ እንኳን ቢኾን መሰረታዊ የሙያው ግዴታ ሳይጣስ ሊሆን ይገባል። አንድ መገናኛ ማመጣጠን ካልቻለ በራሱ ሙት ነው። እያደር ብቻውን ይቀራል” ሲሉ ኢቲቪን ይገልጹታል። እንደነሱ አባባል ኢቲቪ ከህዝብ ሳይሆን ከራሱ ጌቶችም ጋር ተነጥሎ የአንድ ወገን (ግለሰብ) ሎሌ የሆነ በድርጅት ቅርጽ የሚከላወስ ሱቅ በደረቴ አይነት ነው። ኢቲቪ ሃሳባቸውን፣ ንግግራቸውን፣ አቋማቸውን፣ ጥቆማቸውንና … [Read more...] about ኢህአዴግ ኢህአዴግን ማፈን ጀመረ!