
“ኢትዮጵያን ቀስ ብለን ስሟን እንቀይራለን”
Ethio Muslims Interfaith Dialogue for Justice በሚል ስያሜ በሚታወቀው የፓልቶክ ክፍል ውስጥ “አቡ ሃይደር” በሚል ቅጽል ስም የሚታወቁት ተናጋሪን በመጥቀስና ንግግራቸውን በቀጥታ በማሰማት የሙስሊሞች እንቅሰቃሴ የመጨረሻ ዓላማ ኢትዮጵያን የሙስሊም መንግስት ማድግ እንደሆነ በEthio Christians and Muslims discussion 4 solution የፓልቶክ ክፍል “ዘ ቤስት ሶሉሺን” በሚል የቅጽል መጠሪያ የሚታወቁት ተናጋሪ አስታወቁ።
የአቡሃይደርን ንግግር በተደጋጋሚ በድምጽ ማስረጃነት ሲቀርብ ኢትዮጵያን የእስላማዊ መንግስት ከማድረግ ባሻገር አስፈላጊ ከሆነ መጠሪያ ስሟን እንደሚቀይሩ ሲናገሩ ተደምጧል። “አገሪቱ የእኛ ናት። ካፊሮች አገሪቱ የኛ ናት የሚል የታሪክ ምስክር ያላቸውም” ሲሉ የተናገሩትን በማሰማት “ዘ ቤስት ሶሉሺን” የተባሉት ሰው በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የመብት ጥያቄ ስም ከጀርባው አለ የሚሉትን አመልክተዋል።
የግለሰቦችን እምነትና “ገና ያሰቡትን እናውቃለን” በሚል የሙስሊሞችን መሰረታዊ የመብት ጥያቄ ማጣመም አግባብ እንደማይሆን፣ የፓልቶክ ንግግርን በማስረጃነት በማቅረብ ሰዎችን መወንጀልና የግለሰብ አቋምን የሙስሊሙ ኅብረተሰብ አጠቃላይ አቋም አድርጎ መውሰድ ትክክል እንዳልሆነ አስተያየት በመስጠት የተቃወሙም አሉ። “ዘ ቤስት ሶሉሺን” ግን ላለፉት አራት ዓመታት የተመዘገቡ የድምጽ መረጃ እንዳላቸው፣ ጉዳዩ እዚህ ከመድረሱ በፊት ለመንግስትና ለሚመለከታቸው ማሳወቃቸውን፣ በቅርቡም ለሚዲያዎች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤና ፒቴሽን በማሰባሰብ ማቅረባቸው ተጠቁሟል።
አንድነት የማተሚያ ማሽን ሊገዛ ነው
አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) በማተሚያ ቤት ዕጦት ምክንያት ለተቋረጠው የፓርቲው ልሳን ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት የተለያዩ የገቢ ማስገኛ ዝግጅቶች እና እርዳታዎችን አሰባስቦ የማተሚያ ማሽን ለመግዛት ማቀዱን አስታወቀ፡፡ ፓርቲው እንዳስታወቀው፤ ለአንድ ዓመት ከሁለት ወር ያህል የመንግሥት በሆነው ብርሀንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት እየታተመ በየሣምንቱ ማክሰኞ ለገበያ ይቀርብ የነበረውን “ፍኖተ ነፃነት” ጋዜጣ ወደ አንባቢው ለመመለስ በውጭ እና በአገር ውስጥ ከሚገኙ ደጋፊዎቹ በአራት ወር ጊዜ ውስጥ ገንዘብ በማሰባሰብ አንድ ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የማተሚያ ማሽን ለመግዛት አቅዷል፡፡
የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እንደተናገሩት፤ በሕጋዊ መንገድ የተቋቋመ ማንኛውም ፓርቲ የራሱን ልሣን የማሳተም መብት እንዳለው ሕጉ ቢደነግግም፤ መንግሥት ማተሚያ ቤቶች ላይ በሚያደርገው የተለያዩ ጫናዎች ምክንያት በተፈጠረ ፍርሀት ጋዜጣ ብቻ ሳይሆን ደረሰኝ ማሳተም እንደተቸገሩ ተናግረዋል፡፡ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮጀክት ለማከናወን ሦስት ኮሚቴዎች መቋቋማቸውን የገለፀው ‹‹የፍኖተ ነፃነት›› ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነብዩ ኃይሉ ስለ ገቢ ማሰባሰቢያ እቅዱ እንዳብራሩት፤ መጽሐፍትን በመሸጥ፣ ከ30 ብር እስከ 1ሺሕ ብር ለሚለግሱ ኩፖን፣ ከተጠቀሰው ገንዘብ በላይ መለገስ ለሚፈልጉ የቃል ኪዳን ሰነድ መዘጋጀቱን እና ዓላማውን የሚደግፍ ማንኛውም ሰው በባንክ ሂሳብ ቁጥራቸው ገቢ ማድረግ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በኢንተርኔት ኦን ላይን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሚቀጥሉት አራት ወራት የገቢ ማሰባሰቡን ሥራ እንደሚቀጥሉ ጠቁሟል፡፡
አዲስ አበባ በጎጥ፣ ቀጣናና ብሎክ ልትቸረቸር ነው
ኢህአዴግ አዲስ አበባን በጎጥ፣ በቀጣና፣ በሰፈር ከፋፍሎ ለማስተዳደር ያመች ዘንድ ሶስት አዳዲስ መዋቅሮች ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑንን ሪፖርተር ምንጮቹን ጠቅሶ አስታወቀ። “ቀጣና” የሚለው አደረጃጀት በደርግ ጊዜ

የተጠላ፣ የተወገዘና ትርጉሙም “ረሃብ” ማለት ነው በሚል ስሙ እንዲቀየር በርካቶች ጠይቀው እንደነበር አይዘነጋም።
ሪፖርተር ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳለው “ቀጣና” በሚሰኘው መዋቅርና “ሠፈር” በተሰኘው መዋቅር የተወከሉ ሰዎች ምክር ቤት ያቋቁማሉ፡፡ ምክር ቤቱ የራሱ ሥራ አስፈጻሚ፣ ብሎም ዋና ሥራ አስኪያጅና ረዳት ሥራ አስኪያጅ ይኖሩታል፡፡ “ሠፈር” ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ወጣቶችና ጎልማሶች ምክር ቤት አቋቁመው መንደራቸውን ለማልማት ይሠራሉ፡፡ “ብሎክ” ወይም “ጎጥ” ተመሳሳይ ሥራ የሚሠሩበት ይሆናል ተብሏል፡፡ሪፖርተር ሰምቶ ከዘገበው በተቃራኒ መዋቅሮቹ የልማትና የእድገት ታፔላ ያነገቡ የአፈና መዋቅሮች ናቸው። ኢህአዴግ የስለላ መዋቅሩ መኖሪያ ቤት ድረስ የዘለቀ ትብትብ አንዳለው መገለጹ ይታወቃል። አዲስ አበባ አስር ክፍለ ከተሞችና 116 ወረዳዎች አሏት።
በሳውዲ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ታሰሩ
ኢትዮጵያውያኑ ዘወትር አርብ እየተሰባሰቡ የሚያደርጉትን የአምልኮ መርሀግብር ሲጀምሩ የሳውዲ የጸጥታ ሀይሎች ወደ አምልኮ ስፍራው በመሄድ አፍሰው ወስደዋቸዋል። 43 ሴቶች እና 6 ወንዶች መታሰራቸውን በሳውዲ ነዋሪ የሆኑት የእምነቱ ተከታይ አቶ በሪሁን አሰፋ ገልጸዋል፤ ሶስቱ አገልጋዮች ለብቻ ተወስደው መታሰራቸውን አክለዋል።
የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ሰዎች ወደ አገራቸው ሊመልሱዋቸው እንደሚችሉ የገለጡት አቶ በሪሁን፣ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ግን ታስረው ሊቆዩ እንደሚችሉ ፍርሀታቸውን ገልጸዋል።
ከወራት በፊት 34 የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ታስረው፣ የተወሰኑት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ይታወሳል። ሳውዲ አረብያ የሀይማኖት ነጻነት የሌለባት አገር መሆኑዋ ይታወቃል። (ምንጭ: ኢሳት)
ለፓትሪያርክ ምርጫ ወደ ፈጣሪ ጸልዩ!!
ከሃይማኖት አባቶችና መሪዎች በማይጠበቅ መልኩ ለወንበርና ለንዋይ ሲወዛገቡና የነበሩት “አባቶች” አባ ጳውሎስ ካለፉ ከስድስት ወር በኋላ አዲስ ፓትሪያርክ ለመሰየም ቀን ቆረጡ። 6ኛውን ፓትሪያርክ ለማስመረጥ የተያዘው ቀን የካቲት 27/2005 ዓም ሲሆን የምርጫው ውጤት በእለቱ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ ይፋ ይሆናል።ምርጫው የሚከናወነው በቅድስት ስላሴ ቤ/ክርስቲያን ውስጥ ነው።
ታህሳስ 10 ቀን 2005 የተመረጡት የጅማ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባ እስጢፋኖስ “ለቤተ ክርስቲያን መሪ የሚሰጥ እግዚአብሔር አባታችን ነውና በምርጫው እሱ የፈቀደው በመንበሩ ላይ ይቀመጥ ዘንድ በጸሎት እንጠይቅ” ብለዋል። በዚሁ ጥሪ መሰረት ከየካቲት 21 ቀን ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ሱባኤ ታውጇል። በምርጫው ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠ/ቤ/ክ የመምሪያ ሃላፊዎች፣ ጥንታዊያን ገዳማትና አድባራት፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና ማህበረ ቅዱሳን አባላት በጥቅሉ 800 የሚጠጉ ድምጽ ይሰጣሉ። ጥቆማን በተመለከተ በወጣው ምርጫው መስፈርትና ደንብ መሰረት በስልክና በፋክስ ጥቆማ ማድረግ እንደሚቻልም ተገልጿል።
185 ሰዎች በቃጠሎ ቤት አልባ ሆኑ
ሶስት ሰዎች ካንድ ቤት ሞቱ

ፒያሳ ሰራተኛ ሰፈር ጥር 18 ቀን 2005 ዓ ም በደረሰ የእሳት ቃጠሎ 185 የቤተሰብ አባላት ቤትና ንብረት አልባ ሆኑ። አዲስ አድማስ ሰለባዎቹን በማነጋገር በስፋት ባወጣው ዘገባ የተቃጠለው ባለ አንድ ፎቅ አሮጌ ህንጻ 35 አባወራ ይኖሩበት ነበር። አሮጌው ዛኒጋባ ህንጻ እየኖሩ እሳት ንብረታቸውን የበላው ነዋሪዎች ቀደም ሲል እዛው ፒያሳ ቅቤ ህንጻ ሲኖሩ እሳት መኖሪያቸውን አውድሞባቸው በጊዜያዊነት ወደ አሁኑ ህንጻ የተዛወሩ ናቸው።
በቃጠሎው እጅግ አሳዛኝ የተባለው አንድ እናት ከገጠር ያመጧትን ልጅ ጨምሮ ሶስት ሰዎች መሞታቸው ነው። ከዛሬ አርባ ዓመት በፊት ከጋምቤላ እሳት ንብረታቸውን ያወደመባቸውና ወደ አዲስ አበባ መጡት አቶ አቡላ አቡኔ ቅቤ ሰፈር ሲኖሩ እሳት ንብረታቸውን በድጋሚ በላባቸው። አሁን ደግሞ ለጊዜያዊ መጠለያነት በተሰጣቸው ቤት እሳት ለሶስተኛ ጊዜ ንብረታቸውን አወደመው። አዲስ አድማስ እንደዘገበው እሳቸውን ጨምሮ ሁሉም ሙሉ በሙሉ አመድ በሆነው ህንጻቸው ላይ ሆነው ያነቡ ነበር። የተቃጠለው አሮጌ ዛኒጋባ ለመኖሪያ የማይሆን እንደነበር አስተያየት ተሰጥቷል።
በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነትና ስፖንሰር አድራጊነት
“መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ”- ዕውቅ ምሑራንን ሊያወያይ ነው
በቅርቡ ለንባብ የበቃውና የብዙዎችን ትኩረት በመሳብ አነጋጋሪ የሆነው የፕሮፈሰር መስፍን ወ/ማርያም “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” የተሰኘ መጽሐፍ፤ እሁድ ታዋቂ ምሑራን፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራርና ጋዜጠኞች በተገኙበት በብሔራዊ ትያትር አዳራሽ፤ በተለያዩ ሐሳቦች ዙሪያ ፊት ለፊት ተገናኝተው ውይይት እንደሚያደርጉበት ተገለፀ፡፡

በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነትና ስፖንሰር አድራጊነት በሚከናወነው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ፤ ቀደም ሲል በመጽሐፉ ዙሪያ ደግፈውም ተቃውመውም የጻፉ እንዲሁም የተነሳው ጉዳይ ‹‹ይመለከተናል›› ያሉ፤ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ሰለሞን ተሰማ (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት አምደኛ)፣ አስራት አብርሃም (ከመለስ በስተጀርባ መጽሐፍ ደራሲ)፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር ብርሃኑ ደቦጭ፣ በታሪክና በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከፕሮፌሰሩ ጋር በፍትሕ ጋዜጣ ላይ ሲሟገቱ የቆዩት የሕወሓቱ ስብሃት ነጋ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጋዜጠኛና ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ፤እንዲሁም ፕ/ር ገብሩ ታረቀ፣ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም፣ ዶ/ር ሽመልስ ተ/ፃዲቅ እና ፕ/ር እንድርያስ እሸቴ ተገኝተው በመጽሐፉ ዙሪያ ያላቸውን ሐሳብ እንደሚያቀርቡ የዝግጅቱ አስተባባሪ አቶ አርአያ ጌታቸው ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
በመጽሐፉ ዙሪያ ብቻ በሚደረገው በዚህ ውይይት ላይ የሚገኙት የመጽሐፉ ደራሲ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም በበኩላቸው፤ ስለ መጽሐፉ የሚቀርቡ ማንኛውም አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን እንደሚያስተናግዱና ምላሽ እንደሚሰጡ፤ አስተያየት ለመቀበልም ፈቃደኛ እንደሆኑ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ (ምንጭ አዲስ አድማስ)
“ያልተጋተ ስለ መብቱና ጥቅሙ …” ሙሼ ሰሙ
… መንግስት እጅግ ገዝፎ ከሕዝብና ከሃገር ሉዓላዊነት በላይ ሲሆን የዜጎች ሚና በዛው ልክ እየቀጨጨና እየኮሰመነ በመሄድ፤ የሃገር ባለቤትነታቸው ጉዳይ ወደ አጋፋሪነትና አስተናጋጅነት ይወርዳል፡፡ ራእይና ትልምን ለማሳካት የሚያስፈልገው የመንግስት የሕዝብ አንድነትና ምሉዕነት በሕግ፣ በስርዓትና በደንብ “እኔ አንተን ስለሆነኩ ሁሉን ነገር አውቅልሃለሁ” በሚል ይተካል፡፡ ቀጥሎም የፖሊሲ አቅጣጫህን፣ ራዕይህን፣ የፖለቲካ ፍልስፍናህንና ሃይማኖትህን በአዋጅና በመመርያ ካልጋትኩህ ይመጣል፡፡ ዘመኑ የአማራጭና የምርጫ በመሆኑ እንደዚህ አይነቱ “የልጋትህ ፖለቲካ” ለማንም ዜጋ ሊዋጥ የሚችል አይሆንም፡፡ መጽሐፉ “ያልተጠመቀ አይድንም” እንዲል፤ ያልተጋተ ስለ መብቱና ጥቅሙ ዘብ ስለሚቆምና አልፎ ተርፎም በኒዎ ሊብራሎቹ ፊት በማሳጣት ብድር፣ እርዳታና ስጦታ ስለሚያጓድል ወቅቱን የጠበቀ ምርጫ ማካሄድ የግድ ነው፡፡ ምርጫ ካለ ደግሞ አማራጭ የግድ ነው፡፡ ምርጫን ያለአማራጭ ማስተናገድ የሚቻለው ነጻና ገለልተኛ ምርጫን በማዛባት የህልውና ማስቀጠያ በማድረግ ብቻ ነው፡፡

“የልማታዊ መንግስታት” የግዙፍ መንግስት ፍላጎትና መንስኤ ከግለኝነትም ይመንጭ ከቡድናዊነት፤አብዛኛዎቹ ግራ ዘመም “ልማታዊ መንግስታት” በስልጣን ላይ ለመቆየት በምክንያትነት የሚያቀርቧቸው መከራከርያዎች አዲስ አይደሉም በሃይማኖት፣ በብሄር፣ በፖለቲካ ወይም በኢኮኖሚያዊ ምክንያት በቁጥር አናሳ የሚሏቸውን የሕብረተሰብ አካላት ጥያቄ ሚዛናኑን በሳተ መንገድ በማጋነንና መራራ ቀለም በመቀባት ከተበዳዮቹ በላይ ለበደሉ ዘብ በመቆም፣ ጀግኖች የተሰውለትን የሰማዕታት ጥሪ አናስደፍርም የሚል የጥገኝነት አቋም በማራመድ፣ “ከኔ በላይ በሃገሬ ጉዳይ ተጠሪ ላሳር” የሚል ጭፍንነት በመፈከር፣“ለእኔ ካልተመቸኝ ለማንም አይመቸው” በሚል ግለሰባዊነት ወይም የጥቂት ቡድናዊነት ስሜት የጋራ ሃገራዊ ጉዳይን መያዢያ በማድረግና “ትጥቁና ስንቁ የኔ ስለሆነ” የሚነቀንቀኝ የለም በሚሉ የግብዝነት አባዜዎች እድሜያቸውን ያራዝማሉ … “
Ethio Muslims Interfaith Dialogue for Justice በሚል ስያሜ በሚታወቀው የፓልቶክ ክፍል ውስጥ “አቡ ሃይደር” በሚል ቅጽል ስም የሚታወቁት ተናጋሪን በመጥቀስና ንግግራቸውን በቀጥታ በማሰማት የሙስሊሞች እንቅሰቃሴ የመጨረሻ ዓላማ ኢትዮጵያን የሙስሊም መንግስት ማድግ እንደሆነ በEthio Christians and Muslims discussion 4 solution የፓልቶክ ክፍል “ዘ ቤስት ሶሉሺን” በሚል የቅጽል መጠሪያ የሚታወቁት ተናጋሪ አስታወቁ።
Is it a news? This indicates the degree of idiocy of this webiste. He is an individual and people would say whatever they like on paltalk. Some of them vomite. So, do you publish as news? It just needs some common sense to know what is important or not.
We know that what you said in public is different than that of in private.we don’t expect.that you going to tell us that you want set an islamic state. Until you gets enough support you entertain different silly religious rights. In the history of this country you we never have such a freedom of religious right we enjoyed as a christian or a muslim. The government or the public at large concerned only about those fanatic muslim who tried to put their faith on us by force. We need to learn from other country before this of out of our control.
Ethio Muslims Interfaith Dialogue for Justice በሚል ስያሜ በሚታወቀው የፓልቶክ ክፍል ውስጥ “አቡ ሃይደር” በሚል ቅጽል ስም …….” Nonsense….., this is how you wanna deprive Muslims right in the country… how could a single person (or even let it be a group) talking in paltalk room be taken as a proof. Don’t be ignorant use your mind how can Muslims build an Islamic state where more than half of the people and all it needs for a power is belong to other religious group. Have you heard of a Muslim country even having 3/4th of the whole population and having Islamic or the other way and having christian state? NOT POSSIBLE. Please rethink before you speak or write!!