የአቶ በረከት ስምዖንና የአቶ ስብሃት ነጋ የደፈጣ ውጊያ ገሃድ መውጣቱን የሚያመላክት መረጃ ይፋ መሆኑን ተከትሎ በህወሃት መንደር ውስጥ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሯል። ጉዳዩን የሚከታተሉ እንደሚሉት ልዩነቱን ለማርገብ በከፍተኛ ደረጃ ጥረት ቢደረግም ሊሳካ አልቻለም።
ከፍተኛ ስልጣን የያዙትንና አቶ መለስ ለመተካካት ያዘጋጇቸውን አዳዲስ አመራሮች፣ በቅርቡ ደንብና ህግ በመጣስ ሹመት የሰጡዋቸውን ጨምሮ የሰራዊቱን አዛዦችና ደህንነቱን ከጎናቸው ያሳተፉት ክፍሎች የተፈጠረው ልዩነት እልባት ማግኘት ይገባዋል የሚል አቋም መያዛቸውን የሚጠቁሙ ክፍሎች እነማን ተለይተው እንደሚመቱ ለመገመት አስቸጋሪ መሆኑንን ይገልጻሉ።
“ፓርቲያችን ከእንጥሉ በስብሷል” በማለት ከዛሬ አስራአንድ ዓመት በፊት በአገር ክህደት ሊያስወግዷቸው የተነሱትን ጓዶቻቸውን የረቱት መለስ የተጠቀሙበት ዋንኛ ስልት አባይ ጸሃዬን “ከውህዳኑ” ጋር በማሰለፍ ነበር። ዛሬ ለህወሃትና ለትግራይ ህዝብ በትግርኛ ቋንቋ ተጽፎ ተሰራጨ የተባለውና ይህንኑ መረጃ ዋቢ በማድረግ ኢየሩሳሌም አርአያ በተለያዩ ድረገጾች ይፋ እንዳደረጉት አቶ አባይ ጸሐዬ የተመደቡት ወጥመዱ ከተጠመደባቸው ዘንድ ነው።
“ድርጅትህ ኢህአዴግ እስከዛሬ ታግሎ እዚህ አድርሶሃል። በተለይም የሁሉም ነገር አድራጊና ፈጣሪ የሆነው ባለ ራዕዩን መሪህን በቅርቡ አጥተሃል” የሚል የአምልኮ መሪ ቃል ያለበት የጥሪ ወረቀት “ተቆርቋሪ ለሆናችሁ የትግራይ ተወላጆች በሙሉ” በማለት ጥሪ አቅርቧል። ኢየሩሳሌም አርአያ ቃል በቃል በትምህርተ ጥቅስ አኑረው ባሰራጩት በዚህ ጉልህ ዜና “እነ አቶ በረከት፣ ወ/ሮ አዜብ፣ ቴዎድሮስ ሃጎስ” ወረቀቱን አዘጋጅተው እንዳሰራጩ ያስረዳል።
በኢየሩሳሌም አርአያ ዜና ላይ እንደተመለከተው እነ አቶ ስዩም መስፍን፣ አባይ ጸሐዬ፣ አለቃ ጸጋዬ ከነባለቤታቸው የትግራይን ህዝብ ለጠላት ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ያወሳል። “… የኔ የምትላቸው ጅቦች ተነስተውብህ ይገኛሉ” የተጠቀሱትንና ሌሎች ደጋፊዎቻቸውን “ጅቦች” ሲል የሚጠራው መልዕክት፣ “… ከእኛ ኋላ የተፈጠሩና ራሳችን ያሳደግናቸው ሲጠናከሩ ድርጅታችን ግን እየተዳከመ በመሄድ ላይ ነው” ሲል ያሳስባል። እነማን እንደሆኑ በግልጽ ሳይዘረዘር “የተወገዱ ግን በመጥፎ ጎዳና ያልተሰማሩን መልሰን ወደ ፓርቲው ማስገባት አለብን። ይህ ካልሆነ ግን የህዝብ ትግል አውላላ ሜዳ ላይ ጅብ በልቶት ሊቀር ነው ከጠላቶቻችን ጋር እንታረቅ እያሉን ነው” የሚል ማስጠንቀቂያ ያስቀምጣል። በስተመጨረሻ “ከጀርባ ሆኖ የዚህ አፍራሽ ዋና ቀያሽ መሃንዲስ ስብሃት ነጋ መሆኑን ደርሰንበታል” ይላል።
“የኢህአዴግ ስኬት የመስመር እንጂ የግለሰብ አይደለም” በማለት የመለስን አምልኮ ለመቃወም ቀዳሚ የሆኑት አቶ ስብሃት ኤፈርትን ለወ/ሮ አዜብ ካስረከቡ በኋላ ከድርጅቱ ጋር ያላቸው ግንኙነት የላላ መሆኑን ለማሳየት እንደ ሩቅ ተመልካች አስተያየት ሲሰጡ ባብዛኛው ባልተለመደ መልክ ይዛለፉ ነበር። በተለይም አቶ በረከትን የማኮሰስና ምናምንቴ አድርጎ የማሳየት ስልት ሲጠቀሙ ቆይተዋል። ይህ እንዳለ ሆኖ አለመግባባቱ ሊከሰት ግድ እንደሆነ አስቀድመው የተነበዩም ነበሩ።
“… መለስ ስለሌሉ የወንበር ቡቅሻው የማይቀር ነው። በድርጅቱ አመራሮች ዘንድ የሌባና ፖሊስ፣ የሃይል ሚዛንና ቅኝት፣ አሰላለፍን የማሳመር ሰልፍ እየታየ ነው፤ … የመለስ ማለፍ በድርጅቱ ውስጥ ታፍኖ የቆየውን ቁርሾ ማፈንዳቱ አይቀርም…” ሲሉ ኦክቶበር 25 ቀን 2012 ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ቃለ ምልልስ የሰጡት አሁን በትምህርት ላይ የሚገኙ የኢህአዴግ ሰው፣ የኢህአዴግ ድልድይ ተሰብሯል፤ የጋራ ነጥብም የለውም ብለው ነበር።
አውራምባ ታይምስ በበኩሉ ምንጩን አዲስ አበባ በማለት በተመሳሳይ የህወሃትን አደጋ ውስጥ መውደቅ ሲያበስር በስም ከዘረዘራቸው አመራሮች መካከል አቶ ስብሃት ነጋን አልጠቀሰም። ኢየሩሳሌም አርአያ አቶ በረከት የሚዘውሩትና የእነ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ወገን በዋናነት ለመምታት ያሰበው አቶ ስብሃት ነጋን እንደሆነ ለአባላት ተበተነ የተባለውን የማስጠንቀቂያ ወረቀት በመጥቀስ ይገልጻል።
አውራምባ ታይምስ “እያጣራሁ አቀርበዋለሁ” በማለት ያወጣው ትኩስ ዜና ለህወሃት አባላት ተሰራጨ የተባለውን ደብዳቤ “ማን እንደጻፈው አልታወቀም” በማለት ብዥታ የሚያጭር መልክት ሲያስተላልፍ፣ ኢየሩሳሌም አርአያ ከአውራምባ ድረገጽ ባለቤት አቶ ዳዊት ከበደ በተለየ መልኩ ዜናውን በትነው አስረድተዋል። በሁሉም በኩል እንደተጠቀሰው ህወሃት ቀውስ ውስጥ ተነክሯል።
በየካቲት ወር በሚደረግ ድርጅታዊ ግምገማ ጠራርገው እንደሚያስወግዷቸው እንደ ከባድ ሚዛን ቦክስ ቀጠሮ በመያዝ እነ አቶ ስብሃት፣ ስዩም፣ አባይና አለቃ ጸጋዬን በመጥቀስ የተሰራጨው ወረቀት በስተመጨረሻ ስብሃት ነጋ ላይ ክርኑን አስደቁሶ እንደሚያበቃ የህዋሃትን ጓዳ አስመልክቶ በተደጋጋሚ ለየት ያለ ዜና የሚያስነብቡት ኢየሩሳሌም አርአያ ያበቃሉ።
ከጎልጉል ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው የነበሩት የኢህአዴግ ሰው ይህንን ዜና አስመልክተው ምን አስተያየት እንዳላቸው ጠይቀናቸው ነበር። “በሌሎቹም አቻ ድርጅቶች ውስጥ በተመሳሳይ ይህ ሁኔታ ይከሰታል። የመበስበሱ በሽታ ሁሉም ዘንድ ነው” በማለት መልሳቸውን ይጀምራሉ። ለጊዜው ደኢህዴንና ብአዴን አንድ ላይ መሆናቸውን ያስታወቁት እኚሁ አስተያየት ሰጪ የኦህዴድ አቋም አለመጥራቱን ነው የሚናገሩት።
“የድጋፉ ጉዳይ የፎርሙላ ነው። ዶ/ር ደብረጽዮንና በረከት ስለላውን፣ ጦር ሃይሉን፣ የፖሊስና የልዩ ሃይሉን ሙሉ በሙሉ ስለተቆጣጠሩት በአሸናፊነት እንደሚወጡ ጥርጥር የለውም” ካሉ በኋላ አቶ ስብሃት ሰሞኑን “አማራውን ከሰደብኩ እኔ ታምሜያለሁ ማለት ነው ሆስፒታል መሔድ አለብኘኝ” በማለት የሰጡት መግለጫ ሲዘልፉትና ሲረግሙት የኖሩትን አማራና ብአዴንን ተለሳልሶ ለመቅረብ ያደረጉት እንደሆነ በተዋረድ ለብአዴን አባሎች መገለጹን እንደሚያውቁ አስረድተዋል።
“ምንም ተባለ ምን በመከላከያውና በደህንነቱ ሃይል ተጠቅመው የፈለጉትን መወሰንና የማስወሰን፣ ባላቸው በሚሰራው የፖለቲካ መዋቅር እስከታች መመሪያ በማውረድ የእነ በረከት ወገን ባለድል እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። ቀድሞ ታጋይ የነበሩ፣ የደህንነት ሃይሉን እየረዱ ብር የሚያመርቱ ግርግሩ ስለማይመቻቸው ሃይል ካለው ወገን ጋር በመሆናቸው እነ ስብሃትን ያቀላጥፏቸዋል። ይህ ሁሉ የሚሆነው ግለሂስ አድርገው አርፈው ለመቀመጥ ካልተስማሙ ብቻ ነው” በማለት አስተያየታቸውን ይደመድማሉ፡፡
ይህንን መረጃ በሚያጠናክር መልኩ ከዚህ በፊት ከጻፍናቸው ዜናዎች መካከል አቶ በረከትና አቶ ሃይለማርያም የመለስ የቅርብ ሰዎች መሆናቸውንና አቶ መለስ ወደ ውጪ ሲወጡ የሥልጣኑን ቁልፍ የሚሰጡት ለአቶ በረከት እንደሆነ፤ የአቶ ሃይለማርያም ሹመት መነሻውም በዚሁ ቀደም ሲል በተፈጠረ “የቤተሰብ መሰል” ግንኙነት መሆኑን በመናገር ስማቸው ሳይጠቀስ ቃላቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የሰጡ የኦህዴድ ሰው ጠቅሰን መጻፋችን የሚታወስ ነው፡፡ አቶ መለስ በሞቱ ማግስት ከኢህአዴግ ምክርቤት እና ከፓርላማው ውሳኔ በፊት አቶ ሃይለማርያም ጠ/ሚ/ር ሆነው እንደሚቀጥሉ በመናገር የተጠባባቂ ጠ/ሚ/ርነት ሥልጣን ይዘው እንደሚሠሩ አቶ በረከት በወቅቱ በሰጡት ቃለምልልስ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡ አቶ ሃይለማርያም ለፎርማሊቲ በፓርላማ ፊት ቀርበው ምህላ እንደሚፈጽሙ አቶ በረከት በግላቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መናገራቸው ይህንኑ ቤተሰባዊ ግንኙነት የሚያጠናክር መሆኑን መዘገባችን የሚጠቀስ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Meyisaw Thewodros says
ቸር ወሬ ያሰማን ጅምራቸውን ይፈጽመው
moged says
For ethiopian people both groups are enemies.
We wish both of them to kill eachother and l eave the power for the genuine ethiopians.
Freedom for ethiopians
Ewnetu says
“Keznjero konjo min yimeraretu” yilal Ethiopiawi siterit.
weye says
Kebesebese koytual derom bandsewu tekesha lay neber
ehadeg ecko miste yebelawu enchet newu yemigeftrewu aydelem midegefewu ateto newu enji
Legesse Meles Zenawi Asres says
Dear golguloch, Thank you for the wonderful job you’re doing. You are mentioning my name a lot less. Just because I died does not mean you have to stop talking about me. At least amet yemulagne. tirum hone metfo selene le zemenat tawesalachehu beye egemetalehu. Semu enjie, debleklekun awutechewu shel alku adelle? endeh newu yarada lij. ye chat merkana eko sent hassab yametal. ahun partiwochu hulu sewerachoo, Azebina ende lemadewa hulunem terarga zor telalech. ya sheme sebhat ahunem yankareral. gena sent tayeto. termesmesu yewetal. ezeh betam yemokal. lene seyoum ena younis be tshirt nu beluachewu. adera awukewalehu endaylu sedersu. ene getem adrege kejachewalehu. Hitler and Stalin are laughing at me all the time. You only murdered thousands only belewu seseku, I tell them, but I killed the hopes and aspirations of millions of Ethiopians. ene yemekochegne, leza jemala alamoudin agerun meshete newu. esun bello sheik. esu kene tach newu yemegebawu. degnetu, yenen ferd askeneselegne. yelekunu mekerut, ye ager meshetu ansot, setochun yemeshetewun yakum. anyway, ahun benante bekul bezu mesteroch lemawutat ready negne. ye internet geezeye aleke. kemehede befit annd neger lachawutachehu, tenant messa se’at lay, Aba Paulos lemen meskel awootetewu kaltesalemk aylugne messelachehoo. feker eske mekaber belewu tedeberuben. woyne eza behon noro, terrorist beye hulum yekerechemu neber. belu eshie golguloch, yekebere selamtayen le Adwa hizb akerbulegne. yemegermewu, i was sure be haya amet woost Ethiopiawineten gelalehu beye neber. Esu enkuan lemot South Africa endegena anserara. Stalin, enka selamtia….. belu ciao. Ke Stalin gara ledeber.
Kinfe Michael Abay says
እውነቱ መቼም እኚህ ከላይ በጽሁፋችሁ ውስጥ የተጠቀሱት ውስጥ አዋቂ እንዳሉት ነው:-
“የድጋፉ ጉዳይ የፎርሙላ ነው። ዶ/ር ደብረጽዮንና በረከት ስለላውን፣ ጦር ሃይሉን፣ የፖሊስና የልዩ ሃይሉን ሙሉ በሙሉ ስለተቆጣጠሩት በአሸናፊነት እንደሚወጡ ጥርጥር የለውም”
እንዳውም ይህ የመሰንጠቅ ተረት ሜዳ ላይ የተበተነው፣ ውነት በመሃከላቸው የረባ ልዩነት ኖሮ ሳይሆን፣ አንደኛ፣ ውነተኛ የተቃዋሚው መንደር የሚያኝከው ባዶ ዜና አግኝቶ፣ መንግሥት በውስጥ ድካምና በመሎኮታዊ ታምር ይወድቃል ብሎ በህልም እንጀራ ከትግሉ እንዲዘናጋ ለማድረግ፤
ሁለተኛ፣ ሲሆን በስምምነት፣ ካልሆነም እነ ስብሃት ነጋ በሆነ ባልሆነው አፋቸውን እንዳያሾሉና አንገታቸውን ደፋ እድርገው ሳጥናቸው ውስጥ እንዲገቡ /እውነተኛው ሳጥን መግቢያውም እየተቃረበ ሰለመጣ/ የተወረወረ የማደንቆሪያ ወሬ ሲሆን፣ ሌላው ዋናው ምክንያት ይህ ተረት የተነዛበት ምክንያት፣ ለህወሃት/TPLF ጭፍን ተከታይ የይስሙላ ጠላት ምስል አበርክቶ፣ እንደገና ለትግል እንዲፐወዝ /revitalizing the rank and file by giving them an enemy image / ለማድረግ ነው።
ከሁሉም ይበልጥ ይህን አጉልቶ የሚያሳየው፣ የነስብሃት ቡድን የሚባለው ለሜድያ ፍጆታ ብቻ የሚያገለግል እንጂ፣ (አልፎ ተርፎ “ጠላት መንደርም” እየገባ ቃለ መጠይቅ የሚያሰጥ “ድፍረት”) ምንም የማተርያል / የተጨባጭ ጉልበት መሰረት የሌለው ባዶ ዲስኩር መሆኑ ነው። ስለሆነም በንደዚህ ዓይነት የአያ ጅቦ ተረት ተውጦ ብዙ ድርሰት ባይጻፍና ትርጉም ባይሰጣቸው የሚሻል ይመስለኛል። በራቸውን ዘግተው መሳቂያ እንኳን እንዳያረጉን!
እዚህ ጨዋታቸው ውስጥ ገብቶ አሰላለፋቸውን እንኳን ትንሽ ጠጋ በለን ብንመለከተው፣ እንዳው ለምሳሌ ያህል፣ በረከትና አቶ ስዩም መስፍን፣ አባይ ጸሐዬ፣እንዲሁም እነ አቶ ስብሃት አንዳንድ አሉት ከሚባሉት የወታደር ባለሥልጣኖች ጋር ባንድ ዘርፍ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አነ አዜብና ደብረጽዮን ከነስለላ ጣቢያዎቹ ሆነው ተፋጠዋል ቢባልና፣ ብናዳንቅ፣ ይሄ ነገር ትንሽ ጉድ ይወጣው ይሆናል ብሎ ማሰብ ይቻል ነበር። ግን አይደለም፣
እነበረከትና ደብረጽዮን፣ ከአዜብ ጋር እስካፍጢማቸው ታጥቀው፣ ጠግበው፣ ባነድፊት፤ በሌላ ባኩል ደግሞ ባገኘው ሜዲያ ሁሉ፣ እራሱን ከፍ ከፍ ለማድረግ፣ እንዳው በመጦሪያው ጊዜ “እልሞትኩም ብዬ አልዋሽም” የሚለው የነስብሃት ትርጉም የለሽ ቡደን ነው።
ስለሆነም ሃገር ወዳዶች ከህወሃት የሜዲያ ሸፍጥ ጠንቀቅ እንዲሉ እያሳሰብኩ፣ ይሀን ያህል የትንተና ጉዳይ ባያደርጉት ይሻላል እላለሁ። ይህ የማወናበድ ዘይቤ የተለመደ፣ በተለይ ሰለጠንን የሚሉ ያምባገነኖች የአገዛዝ ዘይቤ ነው። በዚህ ፈንታ የጥቅም መሰረት ያለበት ልዩነትና ትንተና ላይ ማተኮር ይሻላል። አዎ ስነልቦናዊውንም ሳይዘነጉ እንደሆን ይገባኛል!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
ዱባለ says
ከላይ ሀሳባቸውን ካካፈሉን ወንድም ክንፈ ጋር በጣም እስማማለሁ:: ወረቀት ተበተነ ብሎ እንደ ዜና ማቅረብ ሌላ ጉዳይ ነው:: መተንተን ግን በፍጹም ጊዜ ማቃጠልና ማሳሳት ነው:: በተቃዋሚ ዘንድ ይህ የተከፋፍለዋል ምኞት ቢቀር ነው የሚሻለው:: ቢከፋፈሉስ ለተቃዋሚው ምን ጠብ የሚል አለ? እንደውም አዘንፎ የሚወጣው ይጠናከራል ማለትም ተላት የሚለውን ሁሉ የበለጠ ይደመሣል:: ምንም ያለተደራጀና ያልተዘጋጀ ተቃዋሚ በምንም አጋጠሚ ለራሱ የሚበጀውን ነገር ሊፈጽም አይችልም:: በኔ ግምገማ ግን ስብሀት የሚባለው አጁዛ ይህንን ማወናበጃ ለመዝራት ያዘጋጁት ሰው ነው እንጂ ምንም ሀይል ያለው አይመስለኝም:: ስራውን ግን በሚገባ የሚወጣ የኢትዮጵያ ጠላት ነው::
goytom says
Dialogue between God and the deceased meles:
The author apologizes, due to resource constraints that he is unable to cover all the longest ever confession and full of most horrific stories of the late crime minister meles ( legesse) .The stories said by meles ( legesse) during this confession that lasted 1 solid week are incredibly a lot. He has mentioned so many untold stories and conspiracies he committed against the Ethiopian public and the evil missions he was waiting until an opportune time and condition arise to accomplish. There had been a little bit of debate over his creature among the Angels attending his confession, some say he is not human, some argue he is, however, only partly whereas others argue he is an incarnate devil. Here goes the dialogue.
God: legesse, what have you done throughout your lifetime? Please confess?
legesse: I have been murdering my cronies, I have been conspiring against each one of them, most of them successfully avoided by premeditated death , by persecution and by an orchestrated prosecution which’s all conspired and masterminded by me ;I have committed ethnic cleansing against the Amahara people; I have done my level best to dismantle the Orthodox church and as a result it is now in the process of dismantling ; I have sold the land of Ethiopia to foreigners with the purpose of making the public ultimately landless and without a country which they claim is theirs ; I have rigged elections; I have divided the country along ethnic lines; I have siphoned millions of Euro off the country and kept in malasia, India and china banks, ‘’alas’’, I departed without having a good time with this easy money; I have gambled in the name of the tigray people, I have pinned them against the rest of the country’s ethnic groups …………………………………………………………………; suddenly interjected God, legesse, that is enough I have to hear others’ confession too, yours need special attention and time. As you know We have been in this session of hearing your confession since Monday and today is Friday , We cannot hear any confession on Saturday and Sunday because of Sabbath that We have to observe by resting from any engagement of the routine. You will carry on with the rest of your confession next Monday.
Legesse: ok, but I have a supplication God , please in the meantime allow me to stay out of the Hades where I am suffering day and night for my sin ever since I come here .
God: sorry legesse, the souls of your victims are all here pleading with Us to take a revenge on you on their behalf for having taken their life.
Legesse (menacingly): If you do not do this I will falsely accuse you as terrorist and you will all end up in prison!
Suddenly Arch Angel Micheal interjects: legesse, this is not like the rubber stamp Ethiopian parliament where you presided over, are you still same tyrant?!
Legesse: sorry, I thought I was still there.
2 days later , Monday
God: legesse, please carry on with………………..but cut a long story short or just say your plead and let us conclude your case.God goes on & asks: what is on your conscience now and what would you do if you are resuscitated?
Legesse with a bloody bitter resentment : I would straight go to the land of the Ethiopian, and resume in an intensified manner my systematic extermination mission of the so called Amahara people from the face of that land and beyond and make sure that all ethnic Amhara vanish off the face of the earth and also intensify my dismantling mission of the Orthodox church.The third thing I would do is , I shall get killed & amputated the body of the individual called Abebe Gellaw who scared me to death on my penultimate in the USA , he made me become as if I was struck by a thunder.This hard & horrible memory is still fresh.
Arch Angel Micheal interjects: why all of this evil …….. what a cursed creature! you are the devil incarnate! devil in human form!…………………………………..
Dear fellow Ethiopians, see how awfully & bitterly meles ( legesse) the notorious butcher, hates ethnic Amhara ?
I promise you, those of you who claim to implement meles’ evil legacy , you will end up in a similar terrible predicament before and after your death !
Peace