መለስ የሚሌኒየም ንግሥ እለት ተገኝተው ዘፈን ምረጡ ሲባሉ “የሱዳን ዘፈን ይሁንልኝ” ብለው ከባለቤታቸው ጋር የተምነሸነሹበት የሚሌኒየም አዳራሽ በአቶ አሊ አብዶ የከንቲባነት ዘመን ለመስጊድ ማሰሪያ ተጠይቆ እንደነበር ፣ አቶ አሊም ቦታውን ለተጠየቀው ዓላማ እንዲውል መፍቀዳቸውንና ውሳኔው ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ኢህአዴግ ዘንድ መረጃው ደርሶ መታገዱን ውስጥ አዋቂዎች ያስታውሳሉ።
ከምርጫ 97 በኋላ ደግሞ መላ ሰውነታቸውን የተሸፋፈኑ ሙስሊሞች እየበዙ በመሆኑ ጉዳዩ ሥር ሳይሰድ፣ ከጀርባው እነማን እንዳሉበት ክትትል እንዲደረግ በታዘዘው መስረት የብሔራዊ የመረጃና የደህንነት አገልግሎት አስገራሚ ሪፖርት አቅርቦ እንደነበር እነዚሁ ክፍሎች ይናገራሉ። በክትትሉ የተገኘው መረጃና የመጨረሻ ድምዳሜ ተሸፋፍነው የሚለብሱት እህቶች አብዛኞቹ ሴተኛ አዳሪዎችና የገንዘብ ችግር ያለባቸው የሌላ ሃይማኖት ተከታዮች መሆናቸውን ነበር።
የገንዘቡም ምንጭ በሳዑዲ አረቢያ የሚገኝ አንድ የርዳታ ድርጅት ሲሆን፣ ይህንን ርዳታ ያደረገው የኢትዮጵያ ሙስሊም እህቶች አለባበሳቸው በሌላው ዓለም እንደሚዘወተረው ዓይነት ባለመሆኑ ገንዘብ በመክፈል የዕምነቱን ተከታዮች ለማደፋፈርና ተሸፋፍኖ መልበስ እንዲለመድ ለማድረግ በሚል እንደሆነ የሚጠቁሙት ክፍሎች የክትትሉ መጨረሻ ለገንዘብ ሲባል የሚደረግ የድህነት ውጤት እንጂ ወደ ሌላ አቅጣጫ ሊያመራ እንደማይችል የሚተነበይ መሆኑን ያስረዳሉ። በሌላ በኩል ግን ሳዑዲ የሚቀመጠው የርዳታ ድርጅት ከተወሰኑ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ሳይቀር ግንኙነት እንደነበረው፣ አቶ በድሩ አደምም በዚሁ በኩል አብረው እንደሚሰሩ ተጠቁሞ ማስተባበያ እንደሰጡበት ያስታውሳሉ።
ይህ ብቻ አይደለም በየመንደሩ የአካል ብቃት፣ የካራቴ፣ የቴኳንዶ፣ ጁዶና ተመሳሳይ ስልጠና ከሚወስዱ ወጣቶች ውስጥ ባብዛኛው ሙስሊም ታዳጊዎች እንደሆኑ መረጃ ተሰብስቦ ነበር። በአዲስ አበባ ወወክማ የሚገኝ የስፖርት ክፍል ጉዳዩ እናዳሳሰበው በመግለጽ ለፖሊስ ሪፖርት ማቅረቡም በዛው ሰሞን አጀንዳ ሆኖ ነበር። ከዚሁ ጋር የተነሳው ሌላው ቁም ነገር ገንዘብ መክፈል የማይችሉ የድሃ ቤተሰብ ልጆች ገንዘብ የሚከፍልላቸው አካል መኖሩ ነበር።
ከመጀመሪያው ግምት ስህተት በመነሳት ይሁን በሌላ መረጃ መነሻነት፣ በግልጽ ባልታወቀ መልኩ ኢህአዴግ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ እምነትን ማራመድ ወይም የዕምነት ስርዓትን ማከናወን የሚከለክል ህግ አወጣ። የማንኛውም ሃይማኖት ተከታዮች በትምህርት ተቋማት ውስጥ የእምነት ስርዓታቸውን እንዳያከናውኑ በተወሰነው መሰረት በትምርት ተቋማት ውስጥ ማሸብሸብ፣ መጸለይ፣ ተሰብስቦ ወንጌል መስማት፣ ሶላት ማድረግ … ቆመ ተባለ። ይህንን መረጃ ለሌላ ጽሁፍ ስናዘጋጀው የነበር ቢሆንም ዛሬ ቀንጨብ አድርገን ያቀረብነው። የምንሰማው በሙሉ ስህተት ነው። የምንመለከተው በሙሉ ትክክል ነው ከሚል የጅምላ ድምዳሜ እንዳንደርስ ለማመላከት ነው።
በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደሚነገረው ስርዓት ጠብቀው ሃይማኖታቸውን የሚያራምዱ አሉ። ስርዓትን በለቀቀ መልኩ የግል ምኞታቸውንና ፍላጎታቸውን በሌሎች ላይ ለመጫን የሚፈልጉ አሉ። ከሙስሊሙ፣ ከፕሮቴስታንቱ፣ ከካቶሊኩ፣ ጠንቋይቤት ከሚሰግዱት፣ ሃይማኖት የለንም ከሚሉና ከሌሎችም ዘንድ እንዲህ ያለው ያልተገባ ተግባር እንደሚፈጸም በርካታ መረጃዎች አሉ። በፖለቲካው ዘርፍም እንዲሁ ነው። “እኔ የምለው ብቻ ትክክል ነው፤ እኔን ብቻ ተከተል፤ የራስህን መንገድ መከተል አትችልም፤ እኔ ባትመርጠኝም አማራጭህ ነኝ፤ እኔን አለመደገፍ ነጻነትንና ዴሞክራሲን መቃወም ነው” በሚል አቶ መለስና ድርጅቶቻቸው የሚሰሩትን ዓይነት ጥፋት የሚደግሙ አሉ። የሚለያዩትና ለተመልካች የሚያሳስቱት ሁለቱም በተጻራሪዎች በመሆናቸው ብቻ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ “የኔ ሃሳብና እቅድ ይህ ነው ካመንክበት ተከተለኝ” በማለት በጨዋነት የራሳቸውን ስራና ተግባር የሚያከናውኑ መኖራቸው የሚዘነጋም አይደለም።
“እኔ ከሌለሁ አገሪቱ ሞቃዲሾ ትሆናለች” በሚል ሙሾ የሚያወርደው ኢህአዴግ ጨው እንደቀመሰ ሙክት ገንዘብና የስልጣን እድሜውን እያሰላ በሚፈጽማቸው አላስፈላጊ ተግባሮቹ አገሪቱ ለተለያዩ ማህበራዊ፣ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ቀውስ ተዳርጋለች። ህዝብም የሞራል ውድቀት ደርሶበታል። ከጥንስሱ ሊቋጭ የሚገባ ቀላል ጉዳይን እያነኮረ ግራ ሲገባው የድርሰትና የተወናይነት አኬልዳማዊ “ኩኩሉ” ውስጥ ተወትፎ ግራ መጋባቱን ህዝብ ላይ ያራግፋል። የሰሞኑ ድራማ የዚህ ውጤት ስለመሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ።
ጂሃዳዊ ሃረካት
አኬልዳማ የደም መሬት ማለት ነው። መቼም ኢህአዴግ የቃላትና የስም ማውጫ ማሽኑ አይደክምም “ጂሃዳዊ ሃረካት” ሲል የሰየመው ዶክመንታሪ ፊልም በራሱ ትርጉም “የጂሃድ ጦርነት” ማለት ነው።
አኬልዳማ ድርሰቱና ቅንብሩ ትኩስ በነበረበት ወቅት ሁሉም በመሰለው መልኩ አጉመተመተና የወቅቱ አዲስ ጉዳይ አረጀ፣ ተረሳ። አሁን ደግሞ የድምጻችን ይሰማ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ከአንድ ኣመት በኋላ አዲስ ተዘጋጀ በተባለው “ጂሃዳዊ ሃረካት” በኢህአዴግ ትርጉም “የጂሃድ ጦርነት” በተሰኘ ዶክመንታሪ ፊልም የጂሃድ ጦርነት ስሜትና እስክስታ “ሰለፊያ ጁስ ቤት” ተጠነሰሰ ተባለ። አሁን ለዛሬ እስኪረሳ ትኩስ ነው። ነገ ያረጃል። በሁሉም ጉዳዮች ውስጥ ግን የማያረጁ ጉዳዮች አሉ። ለተቃዋሚም፤ ለደጋፊዎችም፤ ለገዢውም፤ ለተገዢውም።
የመጅሊስ አመራሮች ይነሱ፣ የሙስሊሙን ህብረተሰብና ሃይማኖት ተከታዮች አይወክሉም፣ እኛ አልመረጥናቸውም በሚል የተነሳው የመብት ጥያቄ በጥበብ የሚይዘው ጠፋና እየተካረረ ሄዶ እዚህ ደረሰ። የመብት ጥያቄ ያቀረቡትን የሃይማኖቱ ተወካዮችን መንግስት አሰረ። ፍርድ ቤት ክስ መሰረተ። ጉዳዩ በፍርድ ቤት ተይዞ የመጨረሻው የፍርድ ሂደት እየተጠበቀ ባለበት ወቅት ኢህአዴግ በበላይነት በሚቆጣጠረው በፕሮፓጋንዳ ማሽኑ ኢቲቪ በኩል ባለፈው ማክሰኞ “ህገ መንግስት ይከበር ሲል፣ ህግን ሲጨፈላልቅ ታየ። ህግን ከምድሪቱ እንደ ጉም በማትነን አምባገነንነቱን አወጀ፡፡”
የጂሃድ ጦርነት ሲል ርዕስ ሰጥቶ ያቀረበው ፊልም ሲጀምር መነሻው “ድህነት” መሆኑ ከዜናው በላይ ገንዘብ እየተከፈላቸው በቀን የተወሰነ ሰዓት ተሸፋፍነው ጥቁር በመልበስ ለመኖር የሚታገሉትን ምስኪን የስርዓቱ ውጤቶች አስታወሰን። “ድህነት ለሽብር መፈጠርና መስፋፋት ዋና ምክንያት ነው” ሲል ትረካውን የጀመረው ዘጋቢ ፊልም መነሻውና መድረሻው “ኢትዮጵያን የሙስሊም አገር ለማድረግ፣ የሙስሊም መንግስት በኢትዮጵያ ለማቋቋም የተያዘ፣ በእምነት ሽፋን የሚካሄድ ነውጥ ነው” ሲል የደመደመበትን ሪፖርቱን “ሶማሊያ ድሃ አገር በመሆንዋ አልሸባብና አልቃይዳ ይህንኑ ድህነት ተጠቅመው አገሪቱን የሽብር መሬት አደረጓት” ይላል። እኛም ወደዚያ እንዳንሄድ በማስጠንቀቅ!!
“አለመታመን ታላቅ ውድቀት ነው” በሚል አስተያየት የሰጡ እንዳሉት አንድ መንግስት በብሔራዊ የአገሪቱ መገናኛ የሚሰጠው መረጃ ሁሌም ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ከሆነ እውነት ቢነገር እንኳን “እንደልማዱ እየዋሸ ነው፣ ውሸት ልማዱ ነው፣ እሱን ማን ያምናል” እየተባለ በህዝብና በመንግስት መካከል መተላለፍ ይፈጠራል። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ መንግስት መረጃ ስለማስተላለፉና ፕሮፓጋንዳ ስለመስራቱ እንጂ ስለታማኝነት ብዙም ደንታ እንደሌለው የሚገልጹት አስተያየት ሰጪ “በዚህ አካሄድ ኢህአዴግ ሳይሆን አገሪቱ አንድ ቀን ዋጋ መክፈሏ አይቀርም” ብለዋል። አስተያየት ሰጪው ጨምረው እንዳሉት ከሆነ ስሜታዊ ሚዲያዎች የማንም ሆኑ የማን “ስጋና ደምን ረግጠው ለእውነት ብቻ ካልሰሩ አይታመኑም። ከማይታመን ሚዲያና ተቋም ይልቅ የሚዲያ ረሃብ ይመረጣል” ሲሉ ሁሉም ወገኖች ስለመታመን ሊጨነቁ እንደሚገባ ይናገራሉ።
የሳይበር ጦርነት የተካሔደበት አዲሱ የኢቲቪ “ሙቪ” እንደሚለቀቅ ይፋ ከሆነበት እለት አንስቶ ፕሮፓጋንዳውና ማስታወቂያው በማህበራዊ ገጾችና የማክሸፊያ ሚሳይል ሲወርድበት ነበር የከረመው። ፊልሙ ይፋ መሆኑንን አስመልክቶ በማከታተል የመልስ ምት የሚሆኑ “የዩቲዩብ ምርቶች” በብዛትና በዓይነት ተሰራጭተዋል። ኢህአዴግ በህግ በተያዘ ጉዳይ ላይ መግባቱና ህግን አደባባይ ላይ እንደለመደው መስቀሉ በመጀመሪያ ደረጃ ተሸናፊ ያደርገዋል። በፍርድ ቤት እግድ እንደወጣና ፊልሙ እንዲተላለፍ አይደረግም በሚል በይፋ መግለጫ ከተሰጠ በኋላ እንዲህ ያለ ተግባር መፈጸም አቶ ጁሃር መሐመድ ለኢሳት እንዳሉት በፍርድ ቤት አልሳካ ያለውን ጉዳይ ህዝብ ዘንድ በመውሰድ ጥርጣሬን መፍጠር ነው። “ውዥንብር” ማካሄድ ነው።
አነጋጋሪው አምበሉ ወይም እስማኤል አሰፋ ማን ነው?
ሃደሬ ሰፈር ከዓመታት በፊት ተከፍታ የነበረችው የሰለፍያ ጁስ ቤት ባለቤት የተባለውና በራሱ አንደበት ናይሮቢ ገብቶ “ከዳሩ ቢላል ክበብ” አባላት ጋር መገናኘቱን የገለጸው ሰው የኢቲቪ ሪፖርት እንዳለው ማን ነው? ከሁሉም በላይ አመጽን በጦር መሳሪያ በማገዝ ረገድ አልሸባብ እንዳሰለጠነው ሲናገር ተሰምቷል። በወታደራዊ ስልጠናው ክላሽንኮቭ መገጣጠም፣ የውጊያ ቦታ አያያዝ፣ የከባድ መሳሪያ ተኩስ፣ ተመሳሳይ ስልጠና መውሰዱን አስታውቋል። የመንግስትን በህዝቡና ባገሪቱ ላይ ያለውን ቁጥጥር ማሳጣት፣ ጂሃዱ እየሰፋና መንግስት ከህዝብ ጋር ሲነጠል የራስን አስተዳደር መመስረት ብሎም በመላው አገሪቱ እስላማዊ መንግስት ማቋቋም ዋናው አጀንዳ እንደሆነ ተናግሯል። ይህ የቆየ እምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ኬንያ ገብቶ የዳሩ ቢላል ክበብን ተገናኝቶ ወደ ሶማሊያ “የሽብር” ትግበራ ተምሯል።
እንደ የአውሮጳውያኑ አቆጣጠር በ1999 እንደከሰመ በተጠቆመው የኳታር ሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ አባል በነበሩት ዶክተር ሳላህ ነቢሃ አማካይነት ህዝባዊ ዓመጽ ስለማቀጣጠል፣ በሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ አስተምህሮ የቀለም አብዮት ለማካሄድ የሚያስችል ስልጠና እንደወሰዱ ከገለጹት ጋር ተዳምሮ በኢትዮጵያ የጂሃድ ጦርነት ለማካሄድ ተደርሶባቸዋል የተባሉት ለ“ጦር ባለሙያው” አምበሉ አጃቢ ሆነው ቀርበዋል። ኢቲቪ “ስራዬን አስመልክቶ አስተያየት ሰጡኝ” ካላቸው መካከል አንድ አስተያየት ሰጪ በፊልሙ እውነትነት እንደማያምኑ አስታውቀው ለመሆኑ “አምበሉ ማን ነው?” ሲሉ ጠይቀዋል። አምበሉን የሚያውቁ ወደፊት ስለማንነቱ የሚሉትን ለመስማት የጓጉም አሉ።
ማንን እንመን?
በዚህ ዘገባ የቀረበውን ዶክመንታሪ ፊልም ውስጥ ምንም እውነት የለም ብለው የሚከራከሩ ያሉትን ያህል “ኢትዮጵያ በጽንፈኛ የሙስሊም አክራሪ አገሮችና ድርጅቶች ዒላማ ውስጥ ስለመሆኗ አንጠራጠርም” የሚሉ አሉ። ኢህአዴግ ለፖለቲካ ቁማር ሲል ሲፈልገው የሚለኩሰው፣ ሲፈልገው የለኮሰውን በማጥፋት ሃላፊነት የሚሰማው እየመሰለ የሚተውንበት መድረክ አድርገው የሚቆጥሩትም ጥቂት አይደሉም። አሁን ችግር የሆነው “ማንን እንመን” የሚለው ነው።
ህወሓት/ኢህአዴግንና አገርን ለይቶ የማየት ችግር በበርካታዎች ዘንድ አለ። ኢህአዴግም ጊዜያዊ የፖለቲካ ቁማርና ወደፊት የሚከተለውን መዘዝ ባለማመዛዘን የሚፈጽማቸው ስህተቶች ባንድነት ተዳምረው መጪው ትውልድ ላይ እየዛቱበት እንደሆነ የሚጠቁሙ ክፍሎች፣ ኢትዮጵያዊ ወንድማማቾች እርስ በርሳቸው ሳይሆን ከውጪ ሊገቡ በሚችሉ የተሳሳቱ ዓላማ ያላቸው “ጨዋታዎች” ውስጥ ላለመነከር መጠንቀቅ እንደሚያሻ ይመክራሉ። ወደ ልብ በመመለስ ሰክኖ መራመድ እንደሚገባ ይናገራሉ። ህወሓት/ኢህአዴግ ከህግና ከህገ መንግስት በላይ ሆኖ ስለሚፈጽመው ተግባሮቹ አብዝተው የሚኮንኑ ሁሉ “አገሪቱ ላይ የተረጨውን የብሄር ልዩነት መርዝ፣ የንቅዘት ጣጣ፣ የመበስበስ አደጋ፣ በድንገት መደርመስ አደጋ፣ በሃይማኖት ስም በየአቅጣጫው የተበተነውን ‘ጅኒ ተኮር’ ትምህርት በመለየት ሊሆን ይገባል” ይላሉ። ለጊዜያዊ ጥቅሙ እንጂ የአገራችን ዘለቄታዊ ሁኔታ ምንም የማያሳስበው ህወሃት/ኢህአዴግ በተለይ በሶማሊያ ገብቶ የፈጸመው አሰቃቂ ተግባር ኢትዮጵያን ወዳጅ እንዲበዛላት ያደረገ አይደለም፡፡ ይህንን የትላንት ድርጊት መዘንጋት እንደሌለበት የሚወተውቱ ወገኖች የሚሰጡት ማሳሰቢያ አሁን እየተካሄደ ያለውም ሆነ ወደፊት የሚደረገው ማንኛውም እንቅስቃሴ አገራችን ከገባችበት የዘርና የጎሣ አዘቅት አውጥቶ ወደሌላ ያልታሰበ አዙሪት ውስጥ የሚከታ እንዳይሆን በሰከነና በረጋ መንፈስ የወደፊቷን ኢትዮጵያን በማሰብ መሆን እንደሚገባው ነው፡፡
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Save-Ethiopia says
አክራሪነት (Extremism) በማንኛውም አካሄድና አይነት ለሙስሊሙም ለክርስቲያኑም ለይሁዲው ሆነ ለሌላው እምነት ለማንም አይጠቅምም፡፡እራሱ ፈጣሪ የሰጠውን ነፃ-ፍቃድ (Free-Will) ማንም ፈጣሪን አማኝ ነኝ የሚል በሃይማኖት ሽፋን ይህንን ነፃ-ፈቃድ ሊጋፋና ሊከለክል አይችልም፡፡ከራሱ ከፈጣሪ መለኮታዊ ስራ እንደምንማረው ፈጣሪ በአርአያው ለፈጠረው ሰው ለሚያምነውም ለማያምነውም ሕይወትን አየርን ፀሃይን ምግብን ወዘተ አልከለከለም፡፡ስለዚህ እኛ አማኝ ነን የምንል የእኔን እምነት ካልተከተልክ አንገትህን ነው የምቀላው የምንልበት ማን ሆነን ነው ፡፡ስለዚህም ይህ አክራሪነት (Extremism) በማንኛውም አካሄድና አይነት ምንም የእምነት መሰረት የለውም፡፡በእምነቱ የተነሳ ከራሱ ጋር ስለ እምነቱ ሰላም ያለው ግለሰብ ቀድሞውንም የሌሎችን ሰላም አይጋፋም፡፡ሰብዓዊነትን(Humanity) የማይወድ የማያከብርና የማያስቀድም ማንኛውም ሃይማኖት እውነተኛ ሃይማኖት ሊሆን አይችልም፡፡ሃይማኖት የጋራ ነው ሀገር የግል ነው እንደተባለው ሁሉም የየራሱን ሃይማኖት በስርዓትና በሰላማዊ መንገድ ለማራመድ የሚችለው ግን የጋራ ሃገር ሲኖረን ነው፡፡ኢትዮጵያ እንደ ሀገር በሂደት በአንፃራዊነት አለማዊ የሆነ መንግስት(Secular Government) የሚያስተዳድራት ሀገር ነው የምትሆነውም እንደዚሁም መሆን ያለባት፡፡እውነቱን ለመናገር ደግሞ አሁን ያለው አገዛዝ በእርግጥ ሃይማኖትን ለራሱ የፖለቲካ ጥቅምና የስልጣን መደላድል ለመጠቀም ቢፈልግም ቅሉ ግን ያን ያህል አይን ያወጣና የተጋነነ የሃይማኖት አድሎ አልፈፀመም፡፡ይህንን ማመን አለብን፡፡ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅፅበት የአንድ ሃይማኖት የበላይነት የነገሰበትን አገዛዝ የሚያራምድ ሃይል ስልጣን ላይ ድንገት እንዲወጣ መንቀሳቀስና መፈለግ ግን አጉል ቅዠት ነው እንደዚሁም ለማንም አይጠቅምም፡፡ማንኛውም ነገር የራሱ ጤናማ ተፈጥሯዊ ሂደት አለው፡፡ከዚህ ውጪ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ከመቅፅበት አንድ የሆነ የእስልምና መንግስት እንዲፈጠር የሚጠበቅ ሙስሊም ካላ ልክ ሳኡዲ አረብያ ሪያድ ውስጥ በተመሳሳይ መንገድ በተአምር የክርስትና መንግስት እንዲፈጠር የመፈለግ ያህል ነው፡፡ነገር ግን ይህ ማለት አንድ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ወይንም ግለሰብ ፕሬዝዳንት ወይንም ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን አይችልም ለማለት አይደለም፡፡እያወራሁኝ ያለሁት ስለ አጠቃላይ መንግስታዊ ሰርዓት ነው፡፡ሌላው ብዙ የታዘብኩት ነገር ኢትዮጵያዊነትን ሲመቸን የምንቀበለው ሳይመቸን የምናናንቀው መሆን የለበትም፡፡አንድ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ የእስልምናን ሃይማኖት ብቻ ተገን አድርጎ ሳኡድ አረቢያዊ ወይንም ኩዌታዊ ሊሆን አይችልም፡፡ፕሮቴስታንቱም ሆነ ሌላው አዳዲስ የያዘውን የሃይማኖቱን ትስስር ተከትሎ የዚያን ሃገር አዲስ ማንነት ሊሆን አይችልም፡፡ስለዚህም ሃይማኖታችን እንደ ግለሰብም ሆነ ቡድን በየራሳችን እይታና መንገድ እንድንሄድ እንዳደረገን ሁሉ የጋራ የሆነው ኢትዮጵያዊነታችን ደግሞ በጋራ እይታ አንድ ያደርገናል፡፡ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ የፈረደበት በቅጡ ያልገባን መከረኛ ዲሞክራሲ የሚባል ነገር ከመጣ ጀምሮ ሰዎች አንድ የሚያደርጉንና የሚለያዩንን ነገሮች በጥሞና ለመለየት እንዲከብደን ነው እየሆነ የመጣው፡፡በባህላችን ስለማህበራዊ ፍቅር ሲባል በጋራ በአንድ ገበታ ላይ እንቀርባለን ነገር ግን ሁላችንም ለየራሳችን ነው የምንጎርሰው፡፡እጃችን አንድ ሆኖ እንኳን ጣቶቻችን የተለያዩ ናቸው፡፡Here I want to assert and remind that we are very much confused to discern the difference between identity and universality.በሃይማኖታችን አንድ ሆነን በብሄራችን የተለያየን እንሆናለን በብሄራችን አንድ ሆነን በሃይማኖታችን እንለያያለን በብሄራችንና በሃይማኖታችን አንድ ሆነን በትምህርት ደረጃችንና በአስተሳሰባችን እንለያያለን ወዘተ ወዘተ ነገር ግን በሁሉም አንድ ሆነን በፆታችን ደግሞ እንለያያለን ነገር ግን ፈጣሪ በፆታችን በመለያየታችን የበለጠ አንድ እንድንሆንና ሌላ መሰል ዘራችንን እንድንተካ አላደረግንምን፡፡ከዚህ ሁሉ ለዩነታችን በዘለለ ግን ክቡር ሰው ሆነን በመፈጠራችን በፈጣሪ ረቂቅ መለኮታዊ ስራ ሰብዓዊነት አንድ ያደርገናል፡፡የሰው ልጅ ስጋዊና መንፈሳዊ ፍላጎቶች ሁሉ አንድ ናቸው፡፡መብላት መጠጣት መጋባት መራባት መደሰት ማዘን መወለድ መሞት ታላቅነት ውድቀት ፍቅር ጥላቻ ንዴት ትእግስት ወዘተ ወዘተ ይህ ሁሉ የሰው ልጅ የጋራ እሴት ነው፡፡ብዙ መናገር ይቻላል ነገር ግን ወደ ነጥቡ ስንመጣ አክራሪነት (Extremism) የጥቂት የስልጣንና የሀብት ሱስ ያለባቸው ልሂቃንና ተከታዮቻቸው ፍላጎትና አላማ ነው እንጂ የብዙሃኑ ህዝብ አይደለም፡፡
አክራሪነት (Extremism) የከፋፍለህ ግዛው መሰሪ ስልት ነው፡፡አክራሪነት (Extremism) ህዝብ የጋራ እሴቶቹ ላይ እንዳያተኩርና ህብረት እንዳይኖረውና በዚህም መሰሪ በሆኑትና ሰብዓዊነት በጎደላቸው ስግብግብ ጨቋኝና ዘራፊ ልሂቃንና አገዛዞች ላይ በጋራ እንዳይነሳ ዋነኛ ማዳከሚያ ስልት ነው፡፡
እውን አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ የሆነው ጭቆና ስደት ርሃብ እርዛት በሽታ ድንቁርና ድህነት ወዘተ እንደ አንድ ክቡር ሰብዓዊ ፍጡር ከማንኛውም የሃይማኖት የብሄር የፆታ ልዩነት በዘለለ አንድ ሊያደርገው አይገባምን፡፡እረ ጎበዝ እንዴት ነው ነገሩ እስከመቼ በድንቁርና አለም ውስጥ እንኖራለን በእነ ንግስት ኤልሳቤጥ የንግስና እና ሌላም ተያያዥ የንጉሳውያን ቤተሰቦች ሰርግና ፌስቲቫሎች ላይ እኮ ቅድሚያ የሚገኙት የእስላሙ አለም የአረብ ሀገራት ሀብታም ንጉሳውያን ቤተሰቦች ናቸው፡፡ኃብታሞቹን ሀብታቸውና ድሎታቸው አንድ ሲያደርጋቸው ምስኪኑ ድሃው ግን ድህነቱና ሰቆቃው አንድ ሊያደርገው ያልቻለበት ዋና ምስጢሩ እረ ምንድን ነው?ጥቂት ሃያላን ልሂቃኑ ከላይ ሆነው አክራሪነት አሸባሪነት እያሉ ምስኪኑን በስራቸው ያለውን የእኔ ብጤ ምስኪን እስላምና ክርስቲያን ድሃ ህዝብ እርስ በርስ ያናክሳሉ ያፋጃሉ እነሱ ግን ባማሩ ቅጥሮቻቸው ፌስታ ያደርጋሉ፡፡ይህንን እንቆቅልሽ የሚፈታልኝ ማነው?አክራሪነትና አሸባሪነት አለ የለምም፡፡This is our modern time paradoxical event we have to discern and unravel wisely to figure out the prevailing myth.ኢ-ሰብዓዊነት ባጎበጠውና ጤናማ ባልሆነ አክራሪ የእስልምና እምነት አገዛዝ ውስጥ ካላ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ይልቅ ጤናማና ሰብዓዊነት ባለው የክርስትና እምነት አገዛዝ ባለበት ውስጥ ያለ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ የተሻለ ነው፡፡ለክርስትናውም የሚበጀው እንደዚያው ነው፡፡ከዚህ ሁሉ ግን ኢትዮጵያ በሃይማኖት ውስጥ ብዙም ጣልቃ የማይገባና በተወሰነ ጤናማ አካሄድ ገለልተኛ የሆነ አለማዊ መንግስት(Secular Government) ቢያስተዳድራት የተሻለ ነው፡፡ብዙዎቹ የአረብ ሀገራት አገዛዞች ኢትዮጵያ ውስጥ ፈፅሞ የለየለት እስላማዊ መንግስት ስልጣን ላይ እንዲወጣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግፊት እንደሚያደርጉ ከጥንትም ጀምሮ የታወቀ ነው፡፡ይህንን መረዳትና ማመን አለብን፡፡ ይህ ደግሞ ፈፅሞ ሊሆን አይችልም፡፡እነዚህ የአረብ ሀገራት ሃብታም ንጉሳውያን አገዛዞችም ከምእራቡ አለም መንግስታትና አገዛዞች ጋር ያለቸው በመከባበረና በእከክልኝ ልከክልህ የጋራ የጥቅም ትስስር ላይ ያተኮረ ግንኙነት ምን እንደሆነም ከላይ በተወሰነ እንደጠቀስኩት የሚታወቅ ነው፡፡ታዲያ እውነታው ይህ ሆነ ሳለ ምስኪኑ የታችኛው ድሃ የህብረተሰብ ክፍልና ህዝብ አንተ እስላም አንተ ክርስቲያን እየተባባለ በአክራሪነትና በአሸባሪነት ሰበብ እርስ በርሱ እየተናከሰ የሚጠፋፋበትና ለሌሎች ልሂቃን የስልጣንና የሀብት መደላድል በከንቱ ጭዳ የሚሆንበት ምን ምክንያት አለ?ውድ ሙስሊም ኢትዮጵያውን ሆይ ኢትዮጵያ ውስጥ እስላማዊ መንግስት ስልጣን ላይ መውጣት አለበት ብለው ከበስተጀርባ የሚሰብኳችሁን ሃብታም የአረብ ሀገራት ልሂቃን አገዛዝችና ተላላኪዎቻቸውን መሰሪ ምክር አትቀበሉ፡፡ይህ ፈፅሞ ለእናንተም የማይጠቅም ነገር ነው፡፡ኢትዮጵያ ውስጥ ከዚህ በፊት ያሉት አገዛዞች የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ስለነበሩ ከዚህ በኋላ ደግሞ ተራው የእኛ ነው አይነት ጠባብ አስተሳሰብ ካለ ይህ የትም አያደርሰንም፡፡ይህንን የሚመክሩ የአረብ ሀገራት ሃብታም ንጉሳውያን አገዛዞችና ተላላኪዎቻቸው ሀገራቸው ባሉት የክርስትና እምነት ተከታይ ሴቶቻችን ላይ የሚያደርሱትን አስከፊ ግፍና መከራ ወደ ጎን ትተነው በሌላ እይታ ግን ኢትዮጵያውን ሙስሊሞች እንደ ፍልስጤማውያን ሀገር የለንም አስጠጉን ብለው ቢጠይቋቸው እንደ ሀገራቸው ዜጋ ሙሉ የዜግነት ፍቅርና ክብር እንደማይሰጡ የታወቀ ነው፡፡ስለዚህም ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያዊነትን ጥልቅና ሰፊ ትርጉምና ፋይዳ ተረድታችሁ ለኢትዮጵዊነታችሁ ተገቢውን ፍቅር ክብርና ታማኝነት አሳዩ ምክንያቱም ማናችንም ብንሆን የምናጭደው የምነዘራውን ነውና፡፡ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በእስልምናው ላይ ለክርስትናው አድልቶ የተለየ አድሎ አላደረገም ነገር ግን ሁለቱንም ለስልጣኑ መዳለድል በራሱ መንገድ መዘወር ይፈልጋል እንጂ፡፡ይህንን እውነታ ማመን አለብን፡፡በዋልድባ ገዳም የሆነውንና በኦርቶዶክሱም ውስጥ ያለውን የስልጣን ሽኩቻና የመንግስት ጣልቃ-ገብነት ማየት ተገቢ ነው፡፡ይህ ሁሉ እየታወቀ ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅፅበት የእስላም መንግስት ካልተመሰረተ የሚል የእስልምና ተከታይ ካለ ልክ በተመሳሳይ መንገድ ሳኡዲ አረብያ ውስጥ ለምን የክርስትያን መንግስት አልተመሰረተም አይነት ነገር ነውና ይህ እጅግ በጣም ሞኝነት ብቻ ሳይሆን አደገኛም ነገር ጭምር ነው የሚሆነው፡፡ከዚህ ሁሉ ይልቅ እንደ እናት በጋራ ያቀፈችንን የጋራ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነታችንን እያሰብን ወደፊት በሂደት እንዴት ለሁሉም ሃይማኖቶች ያልወገነ አለማዊ የሆነ መንግስት(Secular Government) በአስተማማኝ ለመመስረት እንደምንችል በማስተዋል ማሰብና መንቀሳቀሰ ነው የሚጠቅመን፡፡የእስልምና ተከታዮችም አንድ በቅጡ መረዳት ያለባችሁ ነገር እናንተ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በታማኝነት በፍቅርና በአክብሮት መከታ ሆናችሁ ለመቆም ስትችሉ ከላይ እንዳልኩት ሁላችንም የዘራነውን ነውና የምናጭደው በተመሳሳይ መንገድ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትም ለእናንተ አስተማማኝ መመኪያ መከታና መጠለያ ይሆንላችኋል፡፡ስለዚህም ስለሃይማኖታችሁ ብቻ ሳይሆን በታማኝነት በፍቅርና በአክብሮት በቀናኢነት መነሳትና መታገል ያለባችሁ ስለ ሀገራችሁ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ጭምር መሆን አለበት፡፡ምክንያቱም ሀገር የሌለው ዜጋና ህዝብ ስለሃይማኖቱ ነፃነትና ክብር አፉን ሞልቶ በልበ ሙሉነት መብቱ እንዲከበርለት የሚጠይቀው የእኔ የሚለው አገዛዝና አካል የለምና፡፡አዎ ሀገራዊ ግዴታችንን በተገቢው መንገድ ስንወጣ የዜግነትና የሰብዓዊነት ክብርና ነፃነታችንን የሚያጎናፅፈንን መብታችንን መጠየቅና ማግኘት እንችላለን፡፡
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!
the sudanese says
i was always wondering about meles and why he didn’t choose ethiopian song but a sudanese one ~ i think he was confused which song should he choose? Tigrean? Amharic? Oromiffa? በቆፈረው ጉድጉዋድ ተጠልፎ ሊገባ ሲል “የሱዳን ይሁንልኝ” አለ
Germame Neway says
Your title “Islamwi mengist be Ethiopia?” that is to say to set up an Islamic state in Ethiopia denotes a political power struggle not a religious right issue-which is now universally recognized as part of democratic and human rights of citizens. Governments does not give or take away these rights which ultimately leads to violence.. Who is doing the violence in Ethiopia against its own people? The answer is directly connected who is ruling the country and how it is ruled. Failure to grasp the essence and nature of the regime seldom leads to confused remarks even false consciousness of comparing or judging the victims and the victimizer in the same scale in the name of ” fair and balance” journalistic gymnastics . That is how woyane/TPLE LIKE TO SHAPE OR PORTRAY ITSELF AND DEFINE THE POLITCAL NARRTIVE AS THE GURDIAN OF THE SECULAR STATE AS OPPOSED THE BIG AND SENSTIONAL HEAD LINE “ISLAMIC STATE OF ETHIOPIA???” ..THAT IS AGAINST BACKDROP OF OF THE JUST demands of our people-in the present case our Ethiopian Muslims struggling to exercising their faith in accordance with the law of the secular state. As far as the vast majority of Ethiopian people is concerned- Muslims,Christians ,non believers etc..- do struggle for justice and democracy and equality before the law.The struggle has been going on for the last 40 yrs now.The main obstacle for justice and democratic state is despotic and dictatorial regimes including TPLF/EPRDF AS ITS PREDESSOSOR DERGUE/MENGISTU REGIME WAS .
The Woyane/TPLF apartheid regime is employing every available coercive and divisive instruments to maintain its hegemony of political,economical and social stranglehold by employing divide and conquer schemes. The vast majority of the Ethiopian people have resisted and continue to resist the last 21 yrs all these divisive attempts from succeeding and tear the country and the people apart. It is not a lack of effort,resources or will from Ethiopia’s enemies that spare our people and country from being totally disintegrated or the perennial “scarecrow” Somalia -like catastrophe. Ironically the reverse is happening like those who wish harm to Ethiopia -its enemies are dropping like flies one by one including by divine intervention of providence saving our faithful countrymen and women. RESPOSIBALE CITZENS INCLUDING JOUNALISTS SHOULD REFRAIN FROM INFLAMING the current situation by inadvertently being used by the leftover power grabbers and “GREAT PRETENDERS” scheme who continue to desperately harass and create havoc by manufacturing NO-WIN OR DANGEROUS ZERO SUM GAME situation.
The price the vast majority are paying for such resistance is immense. It saddens me when good people who are in the journalism world still expect justice from the unjust regime and speculate something good can come out of its so called courts which is other than “legalizing ” its “illegal” and criminal action. TPLF/EPLF IS USING THE MEDIA TO INFLAME AND JUSTIFY ITS REPRESSION BY DISEMINATING ISLAMOPHOBIA THAT HAD ENGULFED THE WESTERN BODY POLITICS IN THE AFTERMATH OF THE TERRORIST ATTACKS IN US AND EUROPE. THOUGH ITS COUNTER PRODUCTIVE SOME UTILITARIANS LIKE TPLF/EPRDF ARE ATTEMPTING TIME AND AGAIN EXPLOIT THE FEAR-MONGERING TO BOLESTER ITS LOYALITYAS ANTI -TERROROST REGIME BY IN FACT TERRORIZING ITS OWN POPULACE.A DANGROUS GAME OF A DESPARTE REGIME..
The whole exercise of this drama is the out come of a despotic regime run amok…out of control..relying on lies and deception. How one trusts this regime and its mouth piece ETV which told the world and the Ethiopian people for several days about the late Meles Zenawi’s returning to his PM alive and kicking to his post soon.Never happens. so are many, many things… Who is the gullible? Fool me once….you guessed it.
Extremists are those who can not tolerate of differences. TPLF/EPRDF REGIME IS RUN BY AN EXTERMIST ETHNO NATIONALIST GROUP WHICH BREEDS EXTERMIST ELEMENTS FROM WITHIN AND WITHOUT. IT IS SO VITAL AND IMPERTAVITE to radically transform the whole political system. You can not reform despotism and tyranny- you get rid of it. The longer authoritarian and despotic regimes stay in power the warning that those who neglected to learn from their past are doomed to repeat it will be self fulfilling prophecy. Remember that coward Colonel Mengistu …..and the aftermath!! ALAS GOD SAVE US ALL TO HELP OUSELVES!!!
INJUSTICE EVERYWHER IS INUSTICE ANYWHERE!!
Jobii says
Unique and an article that face truth. I remember i red an article titled ‘The Head of The Snake’ to express IRAN some ten years a go. In that article the writer used some references which predict that there will be Iranian led revolution, ….. Egypt, Libya and Ethiopia, from Africa will become major allay for Iran…… Lead to create ‘King of South’ to confront the Christian Europe. And three years a go the same magazine predicted the the soon revolution in Egypt and it said Ethiopia willbe the next potential ground for Iranian led Islamic movements. From the pamphlets EPRDF propagating a year and half a go to the Iranian government increased friendship with Ethiopia, we can ask ”who shall we trust” the dictator Ethiopian government …. Or our MUSLIM BROTHERS who claim the ”right to religious freedom”?
nwba says
ጽሁፉን በደንብ ለማንበብ ሞክሪያለው ግን ጸሃፊውም ሆነ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች አሁንም ሰለ እስልምና እና ስለኢትዮጵያ እንዲሁም ስለ ኦረቶዶክስ ክርስቲያን ያላቹህ አመለካከት መታረም አለበት፡፡ አትዮጵያዊነት በሃይማኖት የሚገኝ አይደለም!!! የትኛውም ሃይማኖት አትዮጵያ ውስጥ አልተወለደም ሁሉም የመጡትም በአረቦች ነው (ክርስትና ለአጼዎቹ ተሰበከ እስለምና ደግሞ ለጭቁኑ) ከዚህ ውጭ ሕገመንግስቱን ዞር ብሎ ማየት ያስፈልጋል አለዚያ ኢትዮጵያ የምትሏትን ሀገር በግልጽ ልታስቀምጧት ይገባል፡፡ ካልሆነ ኢትዮጵያ ማለት እያላቹህ ‘‘ሰሜንና ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ’’ እና ‘’ቀሪው ኢትዮጵያ’’ እያላቹህ ግለፁልን ምክንያቱም ከሰሜንና ሰሜን ምዕራብ ካለው ህዝብ በስተቀር ሌላው ህዝብ የሰሜኑ ጦረኞች ከማየላቸውና በጦር ከማስገደዳቸው በፊት የእስልምና (የኦሮሞ፤አፋር፤ሶማሊ፤አርጎባ፤ስልጢ፤ሃረሪ..መጥቀስ ይቻላል) እና ቀሪው ደግሞ ባህላዊ እምነት ተከታዮች (መካከለኛው ኦሮሚያና አሁን ደቡብ ኢትዮጵያ እየተባሉ በሚጠሩት አካባቢ ነዋሪዎች) እንደነበሩ ግልፅ ነው፡፡ ስለዚህ እስልምና በኢትዮጵያ ውስጥ የጭቁን ህዝቦች ሃይማኖት ሆኖ ነው የቆየው በዚህም ሁኔታ እራስን ከመከላከል በዘለለ ይህ ነው የሚባል ጥፋት በሃገራችን አላስከተለም፤ በተቃራኒው ግን ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ የእስልምና ስልጣኔዎችና መንግስታትን አሻራ እንኳን እንዳይኖር አድርጎ ነው አፄዎቹ ያጠፉት፡፡ በተቃራኒው ግን የኢማም አህመድ የጦርነት ክስተቶች ግን እስልምናን ለማስፋፋትና ክርስትናን ለማጥፋት እንደተደረገ ጦርነት የታሪክ ጸሀፊያን ተብዬዎች ሲደሰኩሩ ከርመዋል እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ ይህ አመለካከትም በተተኪው ትውልድም ላይ ሲረጭ ስላደገ አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያዊ ሙስሊምን ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ከአረብ ሃገራት ጋር ማያያዝ አሁንም አልተዋቸውም፡፡
ይህንንም ለማየት ጸሃፊው ያለውን እንመልከት (……..በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደሚነገረው ስርዓት ጠብቀው ሃይማኖታቸውን የሚያራምዱ አሉ። ስርዓትን በለቀቀ መልኩ የግል ምኞታቸውንና ፍላጎታቸውን በሌሎች ላይ ለመጫን የሚፈልጉ አሉ። ከሙስሊሙ፣ ከፕሮቴስታንቱ፣ ከካቶሊኩ፣ ጠንቋይቤት ከሚሰግዱት፣ ሃይማኖት የለንም ከሚሉና ከሌሎችም ዘንድ እንዲህ ያለው ያልተገባ ተግባር እንደሚፈጸም በርካታ መረጃዎች አሉ። ይህ አጋጣሚ አይደለም ሆን ተብሎ የተደረገ ነው፡፡) ከታች አስተያየት ከሰጡት ግለሰቦችም ማየት ይቻላል ……. ለምሳሌ እንዲህ/ ይህ ማለት…… (የተራ የጽንፈኞችና የአጼዎች ርዝራዥ ህልምና ፕሮፖጋንዳ ስለሆነ ስሙ ለመጥራት አልፈልግም) ሲጠቅሱ ያቀረቡት ደጋፊ ሃሳብ ስንመለከተው…. ሳኡዲ ውስጥ የክርስትና መንግስት ይቋቋም ወይም ቤተክርስትያን ይሰራ እንደማለት ነው እያሉ የሚሉትን ማመሳሰያ በጣም የሚገርምና ጠባብ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ የሳዑዲን ጉዳይ የሳዑዲ ዜጎች እንጂ እኛ ኢትዮጵያዊያን አይመለከተንም ክርስቲያኑ ስለ ግሪክ እንደማያገባው (ወይስ አፋርና ሶማሊ ለማለት ፈልጋቹህ ይሆን ይህንንም ለወንድማማችነት ሲባል አናደርገውም አላደረግነውምም)፡፡ ልብ ብላቹህ እንደሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም እንኳን ያን ሁሉ ጫና ቢኖርም በደምና በአጥንታቸው ታግለው እስልምናቸውን ሳይቀላቅሉ ይዘው የቆዩ ቤሄር ብሄረሰቦች ያሉባትና በሁሉም ቤሄረሰብ ውስጥም በርካታ ቁጥር ያለው ሙስሊም ያለባት ሃገር ናት; ‘‘ህዝቡን ጠልቶ መሬቱን መውድድ የለም’’፡፡ ስለዚህ በህዝቡ ኢትዮጵያዊነት የምትጠራጠሩት ነገር ካለ በቤሄር ብሄረሰበች ማንነትና ሉዓላዊነት መጠራጠር ነው አሊያም ቀደምት አያቶችህን ፤እናትህን፤ አባትህን ወይም ዘመዶችህን ማንነት መግፈፍ ነው (እስቲ ዞር ብላቹህ ዘመዶቻችሁን ቃኙ)፡፡ በመጨረሻም አየዲዮሎጂ ሃገርና ድንበር እንደልለውና የሰዉን አዕምሮና ልብ ሲገዛ እንደሚያርፍ ልብ እንድትሉ እጠይቃለሁ፤ ለማንኛውም በዚህ ክፍለዘመን ይህንን አታውቁም ብዬ ሳይሆን ላስታውሳቹህ በማለት ነው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ እስላማዊም ሆነ ክርስታኒያዊ መንግስት አይኖርም!!
ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያዊያን!!!!
Hilina Berhanu says
“ጂሃዳዊ ሃረካት” የተባለውን የመንግሥት የፕሮፓጋንዳ ፊልም፣ እንዳው የውሸት ናዳ ነው የሚሆነው ብዬ ሳልንቅ አንድ ባንድ ተመለከትኩ። ምርር የሚያደርግና ሃገራችን ናላቸው በተደፈነ፣ የስነልቦና አዋቂዎች ሲኮፓት/psychopaths; *** see below/በሚሏቸው ቡድኖች የሚተደደር መሆኑን ነው ያረጋገጠልኝ። ይህ ሲሆን ደግሞ ሁሌ ህሊናዬ ውስጥ ዘሎ የሚገባው ከነርሱ ጋር የሚያብሩት በዴሞክራሲ እንተዳደራለን የሚሉት የዓለም መንግሥታት ናቸው። በተጨማሪም፣ እንዲህ ዓይነቱን ሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸምን የመንግሥት ወንጀል የሚከለክል፥የሚፋረድ ህግ የለም ወይ የሚለው ነው። ግን ደግሞ ያሜሪካዊው ጉዋንታናሞም/Guantanamo/ አለ! የማን ልጅ ሆነሽ ትባራኪያለሽ እነደሚባለው ነው።
ዓላማው ማህበረሰባችንን ማለትም፣ ሃገራችን ኢትዮጵያን በሃይማኖት አክራሪነት በትልቁ ከፋፍሎ ሥልጣን ላይ ለመቆየት ባለው ግብ፣ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ እንደሆን፣ እንደማንም ሰው ስለሚገባኝ፣ የፈለገው ዓይነት እውነት በጀርባው ቢኖረው እንኳን፣ በኢሰብዓዊ መንገድ የተገኘ እውነት እንደሆነ ስለማውቅ፣ ከመጀመሪያው የይዘት ክርክር ውስጥ አልገባም። የይዘት ክርክር ውስጥ ከገባሁ ባጭሩ የሌባው ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ሆንኩ ማለት ነው። ይህ ነጻ ፍርድ ቤት ቢኖር የፍርድ ቤት ጉዳይ ነበር የሚሆነው። መንግሥትም በፕሮፓጋንዳው ኢላማ ያደረገው ይህንኑ ነው፤ ማህበረሰባችንን በአክራሪ ሃይማኖተኝነት መከፋፈል ውስጥ አስገብቶ ለማነታረክና አደንቁሮ ለመግዛት ነው። (በብሄረሰቡ የመከፋፈሉ የትላንትናው ናላ ማዞሪያ /indoctrination/ ቀስ በቀስ ምናልባት እየከሸፈብኝ እየመጣ የሄዳል በሎ በሆዱ ስለሚያስብ!)።
ይህን አደንቋሪ ፕሮፓጋንዳ ስመለከት፣ ይልቁንም፣ የመጀመሪያው ጥያቄዬ የሆነው፣ ወህኒ ቤት ውስጥ አስሯቸው የሚያሰቃያቸውን የፖለቲካ እስረኞች ገና ፍርድ ሳያገኙ ላደባባይ የሜድያ ፍጆታ አውጥቶ፣ እንዲህ ራሱ ሰብዓዊነትንና የሰው ልጅ ልኡላዊነትን የሚያዋርድ መንግሥት፣ ለመሆኑ በዛሬው ዓለም ውስጥ ሌላ አካባቢ አለ ወይ የሚል ነው?
በዶኩመንታሪ አተታዎች የማውቀው፣ ቢያንስ እኔ የተከታተልኩት፣ በናዚ ጀርመን ዘመን ተቃዋሚዎች ላይ ፍርድ ሲሰጥና እስረኞች ቃላቸውን እየሰጡ ለጥፋታቸው ባደባባይ በፊልም ተቀርጸው ሲቀርቡ ነው። በዛ የሰው በላ የናዚ አስተዳደር እንኳን ለሜድያ ፍጆታ የሚወጡት፣ ሲፈረድባቸው እንጂ ሲመረመሩ አልነበረም። በስታሊኑ የኮምኒዝም አስተዳደር ውስጥም ይኽው እንደነበር እገምታለሁ። ሌላው ከሁለተኛው ጦርነት በኋላ፣የድል አድራጊዎቹ የኑርንበርግ ትሪቡናል/The Nuremberg Tribunals/ ተብሎ የሚታወቀው ያደባባይ ፍርድ ቤት ነው።
በጨለማው ቤት የሚወርድባቸው ስቃዩና መዓቱ አነሰ ብሎ፣ ፍርዱን ያደባባይ ክንውን ማድረግ እንደሆን እንጂ፣ ምርመራውን ራሱን ባደባባይ ያወጣ ግን በዓለም ላይ ያለ አይመስለኝም። ሁለት ሶስት ጊዜ አንድን ሰው የመግደል የናላ በሽተኞች /psychopaths / ሱስ ነው።
ስለሆነም ፣ የሃገር ወዳዶች የፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው፣ ከሁሉም በፊት መሰረት የሚያደርገው ሰብዓዊነት እስከሆነ ድረስ፣ እውነትን ለማወቅ ሰብዓዊነትን መሰረት ያላደረገ እውነት ህሊናቸው ሊቀበል አይችልም። /”The End justifies the Means” /”ከየትም አምጪው ዱቄቱን ፍጪው” ፣ የሚባለው ነገር፣ ምን ጊዜም ቢሆን ሰብዓዊ ዘይቤ ሊሆን ስለማይችል፣ የአምባገነኖችን ፖሊስና የፍርድ ቤቶቹን ተረት ወደ ጎን መተው ብቻ ሳይሆን፣ ለህሊና ፍርድ የሚቀርብን ፋይልንም ወድያውኑ ዘግተን ለስቃይ ከተዳረገው ሰው ጋር መቆም አለብን፣ ነው የምለው።
የጠላቴ ጠላት ወዳጄ የሚባለው ተንኮል ለሰብዓዊነት ስለማይሰራ፣ ወይንም በሌላ አማርኛ፣ “ቀንድ ካወጣ ሰይጣን ጋር ተባብሮ ጠላቱን የሚታገል“ ራሱ ሰይጣን እንጂ ፣ ምንጊዜም ቢሆን መላክ ሊሆን ስለማይችል። ይህችን ዓለማችንን ዛሬ ከግጭት ወደ ግጭት እያሰጠማት ያመጣው ጣጣ የዚህ ዓይነቱ አመለካከት ነው። በኔ አስተያየት፣ የሞተው ቢን ላደን ከመቃብሩ ወጥቶ እንኳን በኢህአዴግ ናላቢስ ገራፊዎች/psychopaths/ ተገዶ መንግስት ልገለብጥ መጣሁ ቢል እንኳን፣ የቢን ላደን አክራሪነት ክርክር ውስጥ ሳይሆን፣ እንደ ክርስቲያን የምገባው የናላቢሱ መንግስት ኢሰብዓዊነት ጉዳይ ውስጥ ነው ።
ሌላው፤ ዛሬ ዓለም የገባችበት የሃይማኖት አክራሪነት፣ የሙዝሊምም ሆነ የክርስቲያን ወይንም ሌላ፣ እንደ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ ውስጥ፣ ሁለቱም ሃይማኖቶች በስፋት በቆዩበት ሃገር፣ ተከታይ ለማግኘት የማይገለብጡት ድንጋይ እንደማይኖር፣ እንኳን ለፖለቲካ ተዋናይ ቀርቶ፣ ለማንም ግልጽ ነው። ደግሞም፣ እነዚህን፣ በሁሉም በኩል ያሉትን አክራሪዎች በቀዳማዊነት በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ የሚመግቡት፣ እውነት ለመናገር ራሳቸው የሜሪካንና የሳውዲ ባለጸጎች መሆናቸው ደግሞ ግልጽ ነው። ያልካዒዳ መዋቅር ውስጥ የሚረጨው ሃብትም ከየት እንደመጣ ዊኪ ሊኪስ አንድ ሰሞን አዳባባይ እንዳወጣው፣ የሳውዲ ባለጸጎች ነው፤ የኢትዮጵያውንም እግዜር ይወቀው! የሳውዲ ባለጸጎች እራሱ ኢህአዲግ ጉያ ውስጥም አሉና።
ስለሆነም ፥ ይልቅ የኢህዴግን ተረት ትተን፣ ዛሬ በጀግንነትና ሳይከፋፈሉ በአንድነት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመብታቸው፣ ለመብታችን በመቆም የሚታገሉት የሙዝሊም ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን፣ አርአያነት በማስተዋል፣
“ድምጻችን ይሰማ !” መሪዎቻችን ይፈቱ፣
የሚሉትን ያህል፣ የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ ይፈቱ!
እውነት! እውነቱም ይሰማ ! እውነቱ ሃገራችንን ዛሬ የሚያስተዳድሩት የእጅ አዙር ቅኝ ገዥዎች ናቸው!
አንድ ህዝብ ነን ! አንድ ህዝብ ነን ! ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ !!!
ብለን እጅ ለእጅ ተያይዘን፣ ሃገር ወዳድ የሆን ሁሉ ድምጻችንን ከፍ አድርገን ለሰብዓዊነት ና ለነፃ ኢትዮጵያ እንጩህ ! ከተኛንበት በአእምሮም በተግባርም ከዳር እስከዳር እንነሳ !!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
———————————————————–
*** MORE
—————————-
This is Humiliating a Generation!
***
Humiliating and Demoralization is a disgusting political tool -an expression of inhumanity employed in a social evolution, indicating the primitiveness and inhumanity of the employer! A disaster for the social community, in all aspects, collective as well as individual!
The objective of the play is humiliation of the whole new generation and has nothing to do with “Rule of Law”. (It began way back in 2005 with the so-called pardon process of the incarcerated opposition leaders; followed by the October 2010 release-procedure of the opposition leader Birtukan Mideksa; and one year later a similar humiliating action on other political prisoners).
The very fact of publicizing such “processes” is the very testimony of the torture, (1 (a simple closer look of their body language tells all the facts) underlying the outcome. It is, as a matter of fact: the perpetuation of the torture even in the aftermath (cf. History is full of testimonies of the kind under Stalin and Hitler).
Humiliating a generation; -A crime against a generation!
-This is a concerted project of a bunch of psychopaths.
The Whole Ethiopian administration is sick and this is a mockery of “Rule of Law”.
And moreover SHAME to all those supporting the regime, specially the “United States”, the most important ally and protector, and gar-ant of the Melese Regime, looking and letting this farce happen in “political silence and hypocrisy”! – A double game! One can even speculate that the whole stuff is taking place under the Reggie OF THEIR own “INTELLIGENCE OFFICES”; given THE FACTS underlying the socio-historical process of the generation, beginning way back at the roots of the “Cold War”!
More see the link:
(1) http://samvak.tripod.com/torturepsychology.html
ዱባለ says
ከዚህ በፊት አንድ ምሁር እንዳሳሰቡን ራሳችንን መሆን እንዳዳገተን የሚያስገነዝበን ዋናው ተጨባጭ ማስረጃ የምንጠቀመው ቋንቋ ራሱ በአብዛኛው ከምዕራብያውያንና ከሶሻሊስት አራማጆች የተቀዳ ስለሆነ ቃሉ የሚሰጠን ትርጓሜ የተለየ ስለሆነ ለመግባባት አስቸጋሪ ሆኖብናል:: ለምሳሌም ጭቁንና ጨቋኝ የተባሉት ቃላቶች በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የመደብ ልዩነት የሚገልጽ ሆኖ ሳለ እኛ ግን በተለያዩ ህብረተሰብ ውስጥ በታሪክ አጋጣሚ ለሚከሰት የበላይነት ለሚያሳይ ግንኙነት ሁሉ ስለምንጠቀምበት እይታችንንና የታሪክ አመለካከታችንን በእጅጉ ብዥታ ውስጥ ከቶታል:: ለምሳሌም ጭቆናንና ጨቋኝነትን ብንመለከት የአንድ ህብረተሰብ ገዥ መደብ የራሱን ህብረተሰብ ተገዥ መደብ ምናልባትም ከውጭ ከሚመጡ ህብረተሰብ የበለጠ በአሰቃቂ ሁኔታ ይጨቁናል:: የኢትዮጵያን ጥንታዊ ታሪክ ያየን እንደሆነ ከላይ አንዱ እንደጠቀሰው በተለያየ ወቅት የእስላም ኤሜሬቶች አንዳንዴም እየጠነከሩ አንዳንዴም እየደከሙ ይከሰቱ ነበር:: ይሄም የራሱ ምክንያቶች ነበሩት:: ዝርዝር ውስጥ መግባት ተመለሶ የነገር አዙሪት ውስጥ መገባት ስለሆነ አያስፈልግም:: ከመሀል አገርም ይሁን ከስሜን ከሚገኙት መንግስታት ጋር አንዳንዴም የላላ አንዳንዴም የጠነከረ ግጭቶች ይደረጉ ነበር:: ሆኖም ግን ዞሮ ዞሮ (የላላ) የመገበርና የማስገበር በሁለቱ የገዥው መደብ በኩል ግኑኝነት ቢኖርም የሶሻሊስት ፍልስፍና የሚገልጸው አይነት የመጨቆን ግንኙነት አለ ማለት አያስችልም:: እንደውም ከመጨቆን ግንኙነት ይልቅ የላላ ፌዴራላዊ ግኑኝነት አለ ብንል የነበረውን ህብረተሰብ የማስተዳደር ስልተ የበለጠ ይገልጸዋል:: ነገር ግን ለኛ ለኛ ሲሆን ጥሩ ነገር ስለማይጥመን መጥፎ መጥፎውን እያጎላን መኮራኮም ይቀናናል:: ይሄው የራስን አለማወቅና መናቅ ነው እስከአሁን የሚያናቁረንን::
ታሪክ ጸሀፊዎቻችንም ቢሆኑ የጥንቱም ሆኑ ያሁኖቹ ከሌላው አገር የታሪክ ጸሀፊዎች የተለየ የታሪክ አጻጻፍ ስልት አለነበራቸውም:: የአውሮፓም ታሪክ ጸሀፊዎችም ቢሆኑ የገዥውንና የአሸናፊውን ታሪክ እንጂ የምስኪኑን ህብረተሰብ ታሪክ አይጽፉም:: የኛ የታሪክ ጸሀፊዎች የበለጠ ደረጃ (“higher standard”) የሚጠበቅባቸው ምክንያት የለም:: በአገኙት መረጃ የነበረውን ታሪክ ዘክረዋል:: መቼም ከቃል ከተወራረደ ታሪክ በጽሁፍ የተላለፈ የበለጠ ተአማኒነት ይኖረዋል:: ከፖለቲከኛ ከሚጽፈው ታሪክ ይልቅ ደካማ ባለሙያ ታሪክ ጸሀፊን ማመን ሳይበጅ አይቀርም::
ዋናው ቁም ነገር ግን ይህንን ሁሉ መከራከርያና ጦር አስመዝዞ እያዋጋ ከሀገራት ሁሉ ወደ ኋላ ያስቀረንን ነገር እርግፍ አርገን ትተን ከገባንበት ውርደት እንላቀቅ ነው:: አሁን ከኢትዮጵያ የሚባል ምድር የተገኘ በሙሉ በየተኛውም ክፍለ ዓለም ተዋርዶ ነው የሚገኘው:፡ የዓረብ አገሩማ አይወራ:: በአሁኑጊዜ ከሚገኙት ጥራዝ ነጠቅ ፖለትከኞች በሚንቁት ንጉሥ ጊዜ እነኳ ኢትዮጵያዊ በውጭው ዓለም የተከበረ እንደነበር ነው የሚነገረው:: ከዚህ ውርደት እንዴት እንውጣ ነው ጥያቄው:: መውጣት የሚቻለው ሁላችንም በኢትዮጵያዊነታችን ተባብረን አሁን ያለንበትን ችግር እንወጣ:: ይሄ የማያዋጣ የድሮ ታሪክ እየቃረሙ አባቶቼ እንዲህ ተጨቁነው ነበር እከሌ በድሎኝ ነበር የሚል ጭቅጭቅ አይበጀንም። የትም አልደረስንበትም ነው ጉዳዩ::
ስለዚህም የቃላት አጠቃቀማችን የተቀዳና ትክክለኛውን ትርጓሜ የማያንጸባርቅ ስለሆነ የታሪክና በህብረተሰብ ውስጥ ያለ አመለካከታችንን በማዛባቱ መግባባት አስቸግሮናል:: የራሳችንን ቃላቶች እንጠቀም:: ታሪክን ለፖለቲካ ጠቄሜታ ባናውለው ህብረት ለመፍጠር ይረዳናል::
snap says
eskahun kayehuachew yesdb 100% wshet, sdbasdboch ena ye metfo asteyayet nadawoch yeteshale hono aggnchewalehu
inkopa says
Thank you for telling it us it is Golgul !!
we have to have our beloved countries interest at heart,
before we say or act upon something.
one can not swim in every water insight,
some are poisonous.
God bless and give wisdom to my countrymen,
muslim or otherwise.
koster says
There is only state terrorism in Ethiopia lead by woyane ethnic fascists. The home grown fascists know how to use “fighting terrorism” like Pakistanis. They are using terrror and famine just to enrich themselves because both of them are lucrative businesses for those greedy individuals who cares less for the suffering of their people.
tigabu lema says
We don’t have to be cheated again and again with the same issue more frequently than any normal human being! Let alone in Ethiopia there is no religious Gov’t interest in Egypt or other Muslim dominant countries. History clearly tales us that “all the evil religious movements in the far/near past were the result of covert racial or political goals”. People use religion to mobilize community to accomplish their mission usually the goal is unrelated! Religion is always the pretext for covert racial, political or business mission!! the above post and some of the subsequent comments definitely have covert mission!! so we have to be aware that weyane is more evil than we expect! Extreme racism is more dangerous than any other group!
ethio muslim says
i am akrary (foundamentalist) and i am proud!!!!!
muslim or christians, please dont be deceived by satanic medias like etv…follow the foundamentals of ur religions.AKA be foundamentalist.
follow ur religions extremely.AKA be extremists.
muslims in ethiopia are fighting b/c they can not elect their religious leaders.
no.
this””እስላማዊ መንግሥት በኢትዮጵያ?””thing is one of the lies of weyane.