• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጎልጉል ቅምሻ

February 6, 2013 05:53 am by Editor Leave a Comment

ሐላል ምግብ ውስጥ የአሳማ፤ በርገር ሥጋ ውስጥ ደግሞ የፈረስ ዲኤንኤ ተገኘ

በእንግሊዝ አገር ለእስረኞች ሐላል ምግቦችን የሚያቀርቡ ድርጅቶች (ቸርቻሪዎች) በሚያቀርቡት ሥጋም ሆነ የጣፋጭ ምግብ ውጤቶች ውስጥ የአሳማ ሥጋ (ዲኤንኤ) እንደሚገኝ ከታወቀ ወዲህ በርካታዎቹ ለእስርቤቶቹ ምግብ ማቅረባቸውን እንዲቋረጥ የፍትህ ሚ/ር አዝዟል፡፡

በበርካታ አገራት የፈጣን ምግብ አቅራቢ እንደሆነ የሚታወቅ በርገር ኪንግ በሚሸጠው የበርገር ሥጋ ውስጥ የፈረስ ዲኤንኤ እንደሚገኝ ባለፈው ሐሙስ አምኗል፡፡ የአሳማ ሥጋ መገኘቱ ከታወቀ ወዲህ በርካታ ሙስሊም እስረኞች ተቃውሟቸውን እየገለጹ ሲሆን የፍትህ ሚ/ር በአቅራቢዎቹ ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ቃል ሰጥቷል፡፡ በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ሐዘን የተሰማቸው ሙስሊም አስተያየት ሰጪዎች ጉዳዩ ሆን ተብሎ የተደረገ ጉዳይ በመሆኑ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በሙሉ በአንድ ድምጽ መነሳት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

$120ቢሊዮን ዶላር ወዳገርቤት

በቅርቡ በተጠናቀቀው የአውሮጳውያኑ ዓመት (2012) በአሜሪካ የሚገኙ ስደተኞች ወደየአገሮቻቸው የላኩት ገንዘብ ከ120 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደነበር ተገለጸ፡፡ ከዚህ ውስጥ ከ23ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚሆነው ወደ ሜክሲኮ፣ ከ13ቢሊዮን ዶላር በላይ ወደ ቻይና፣ 11ቢሊዮን ዶላር አካባቢ የሚሆነው ወደ ሕንድ፣ 10ቢሊዮን ወደ ፊሊፒንስ በመላክ ቀዳሚ አገራት ሆነዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ስኬት በማስመዝገብ ከቀዳሚ አገራቱ መካከል ለመሆን ያልቻለው ኢትዮጵያን የሚገዛው ኢህአዴግ ጉዳዩን በቸልታ ማለፍ እንደማይገባው ደጋፊዎቹና የጥቅም ተካፋዮቹ በጥብቅ የሚያነሱት ጉዳይ ነው፡፡ በሕዳሴውም ሆነ በአምስት ዓመቱ ታላላቅ የረጅም ጊዜ ዕቅዶችም ይሁን በሌሎች ጥቃቅንና አነስተኛ ዕቅዶች በጉዳዩ ላይ በጥብቅ መክሮበትና ያወጣቸውን ህጎች በመጠቀም የኤክስፖርት ንግዱን በማጧጧፍ ገቢ የሚጨምርበትን መንገድ ሊቀይስ እንደሚገባው ያሳስባሉ፡፡

“እጃችሁን ታጠቡ!” ለህጻናት ብቻ ሳይሆን ለወንዶችም ጭምር

ከዚህ ቀደም የተካሄዱ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የሕዝብ መጸዳጃዎችን ከተጠቀሙ በኋላ ከ90 በመቶ በላይ ሴቶች እጃቸውን የሚታጠቡ ሲሆን የወንዶች ቁጥር ግን 75በመቶ አካባቢ እንደሆነ ይመሰክራሉ፡፡

ሰሞኑን በኮሌጆችና በርካታ ወንዶች በሚጠቀሙባቸው የሕዝብ መጸዳጃዎች አካባቢ የተከናወነ ጥናት እንደጠቆመው እጅ መታጠብ አስፈላጊ መሆኑን የሚጠቁም ማስታወቂያና ማሳሰቢያ በመጸዳጃ ቤቶች ከተለጠፈ በኋላ እጃቸውን የሚታጠቡ ወንዶች ቁጥር በእጅጉ መጨመሩን ያስረዳል፡፡ በመሆኑም አዋቂ ወንዶች እንደ ህጻናት እጃቸውን መታጠብ እንዳለባቸው ሊነገራቸው ይገባል ወደሚል መደምደሚያ ደርሷል፡፡

በክርስቲያን ት/ቤት ህጻናት በወሲብ ተጠምደዋል

በካሊፎርኒያ ጠቅላይግዛት በሚገኝ የሉተራን መዋዕለህጻናት ውስጥ የሚገኙ የ4፣ 5 እና 6ዓመት ህጻናት እርስበርሳቸው በአፍ ወሲብ ድርጊት ተጠምደው እንደሚውሉ ይፋ ሆኗል፡፡

ጸያፍ ድርጊቱ የሚፈጸመው በዕረፍትና መኝታ ጊዜያቸው እንደሚሆን የተነገረ ሲሆን በድርጊቱ የተቆጡ ወላጆች ድምጻቸውን ካሰሙ በኋላ ት/ቤቱ ትምህርት መስጠቱን አቋርጧል፡፡ በሃይማኖት ድርጅቶች ልጆቻቸውን እንዲማሩ የሚልኩ ወላጆች ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ በት/ቤቱ ላይ ከማሳረፍ ይልቅ የራሳቸውን ልዩ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባቸው የሚናገሩ በርካታዎች ይናገራሉ፡፡ ሌሎች ግን ህጻናቱን እንደዚህ ዓይነት ጸያፍ ድርጊት እንዲፈጽሙ ማን ሊያሳያቸው ቻለ፤ ማንስ አስተማራቸው በማለት ምላሽ የሚሻ ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡ በዓለማችን ክፋትና ርኩሰት እየበዛ በመሄዱ ወላጆች ለራሳቸውም ሆነ ለልጆቻቸው ሃይማኖትንና ግብረገብነትን በትጋት ሊያስተምሩ ይገባል በማለትም ይመክራሉ፡፡

የጂፒኤስ መዘዝ

ወጣቶቹ የጓደኛቸውን ቤት ለማግኘት በጂፒኤስ እገዛ ጉዟቸውን አቅንተዋል፡፡ መንገድ ጠቋሚው መሣሪያም እነሆ ካሰባችሁበት ደርሳችኋል ሲላቸው ከደረሱበት ቤት የጠበቃቸው ግን ጓደኛቸው አልነበረም፡፡

በጆርጂያ ጠቅላይ ግዛት ነዋሪ የሆነውና የቪየትናም ጦርነት አርበኛ የ69ዓመቱ አዛውንት ግን ወደ ቤቱ የመጡት ወጣቶች ዘራፊዎች እንደሆኑ በመቁጠር ገና ከመኪና ሳይወርዱ ቪየትናምን አስታወሰባቸው፡፡ በተኩሱ የመኪናዋ አሽከርካሪ የ22 ዓመቱ ወጣት ሲገደል መኪናው ውስጥ የነበሩት ሁለት ወጣቶች ሁኔታውን ለፖሊስ አስረድተዋል፡፡ አዛውንቱ ያለዋስ በማረፊያ ቤት ሆኖ ፍርዱን እየተጠባበቀ ነው፡፡

ዕዳ በልጅ ሲከፈል

በቅርቡ በወጣ ዶክሜንታሪ ፊልም በአፍጋኒስታን የሚገኙ ገበሬዎች ብድራቸውን ለመክፈል ሲያቅታቸው የአደንዛዥ ዕጽ አዘዋዋሪ ጌቶቻቸው ልጆቻቸውን እንደክፍያ እንደሚወስዱባቸው ዘግቧል፡፡ ገበሬዎቹ ለዕዳቸው የሚከፍሉትን ሲያጡ ያሏቸውን ወንድም ሆነ ሴት ልጆቻቸውን እንዲሰጡ የሚገደዱ ሲሆን አስገባሪዎቻቸውም ልጆቹን (አንዳንዶቹ የ10ዓመት ህጻናት የሆኑ) ወደ ፓኪስታንና ኢራን ለወሲብ ባርነት እንደሚሸጧቸው ፊልሙ ጨምሮ ዘግቧል፡፡ ሴት ልጁን አልሰጥም ያለ አንድ አባት ለሌላው መቀጣጫ እንዲሆን አንገቱ ተቀንጥሷል፡፡

እስልምና ሃይማኖት ጥብቅ በሆነባት አፍጋኒስታን እንደዚህ ዓይነቱ አሰራር ሃይማኖቱን የሚያጎድፍ እንደሆነ አስተያየት ቢሰጥም ሌሎች ግን የሃይማኖቱ ጽንፈኝነት ያመጣው ጣጣ ነው በማለት ይኮንናሉ፡፡

ፕሬዚዳንታዊ ትጋት

በለውጥ መዓበል የምትታመሰው ሶሪያ ፕሬዚዳንት ባሽር አልአሳድ በመጪው መጋቢት ወር ልጅ ያገኛሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ ወሬውን ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ ባይቻልም ታማኝ ምንጮቻቸውን ጠቅሰው በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የዜና ወኪሎች የወሬውን እውነተኛነት እያረጋገጡ ይገኛል፡፡

ሶሪያ ያለችበትን ሁኔታ የሚከታተሉና ዜናው ያስገረማቸው አስተያየት ሰጪዎች በዚህ ሁሉ ደም መፋሰስ ውስጥ ፕሬዚዳንቱ በልጅ መውለድ (ማስወለድ) በኩል ያሳዩትን “ትጋት” በማድነቅ አላግጠዋል፡፡

የሳምንቱ ምርጥ ፎቶ

ሰሞኑን የፈረንሳይ ፓርላማ የግብረሰዶማውያንን ጋብቻ ለማጽደቅ በመከረበት ጊዜ ፕሬዚዳንቱ ፍራንሷ ኦላንድ የሚመሩት የሶሻሊስት ፓርቲ አባላት በሌላ ጉዳይ ላይ ተጠምደው ነበር፡፡ ሁለቱ የሶሻሊስት ፓርቲ የፓርላማ አባላት iPad ላይ ቃላትን የመደርደር ጨዋታ በመጫወት ሲፎካከሩ ታይተዋል፡፡

እነዚህ ሁለት የሕዝብ እንደራሴዎች ወደ ኢትዮጵያ ተልከው በአንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የታጀበውና 547 መቀመጫ ካለው ትጉህ የኢህአዴግ ፓርላማ አባላት ልምድ ይቀስሙ ዘንድ በቅጣት መልክ ወደዚያ እንዲላኩ እዚያው በአምባሳደርነት የሚገኙት የቀድሞው አፈጉባዔ ተሾመ ቶጋ የማያሳስቡ ከሆነ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽኑ ዕቅድ በፈረንሳይ ከሽፏል የሚያሰኝ ነው፡፡

ዘገባውን ለማጠናቀር በየጽሁፉ ከጠቀስናቸው ምንጮች በተጨማሪ ሌሎችንም የሚዲያ ውጤቶች መጠቀማችንን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ ከዜናዎቹ ማነስ አኳያ በየጸሁፉ ለመግለጽ ባለመቻላችን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule