• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከእሁድ እስከ እሁድ

February 25, 2013 08:39 am by Editor Leave a Comment

“ጁነዲን ሳዶ ሳዑዲ ገብተዋል”

የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩትና በቅርቡ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነታቸው የተነሱት አቶ ጁነዲን ሳዶ ወደ አረብ አገር ማምራታቸውን አውቃለሁ ሲሉ አንድ ጎልጉል ተከታታይ ተናግረዋል።

ነዋሪነታቸው ሳዑዲ አረቢያ የሆነው እኚሁ ሰው ላቀረቡት ጥቆማ ማረጋገጫ አላቀረቡም። የሆነ ሆኖ አቶ ጁነዲን ኬንያ የፖለቲካ መጠየቃቸውን ኢትዮቻናል የሚባለው የመንግስት አንደበት የሆነው ጋዜጣ ይፋ አድርጓል። ኢትዮቻናልን በመጥቀስ ዜናውን በርካታ ሚዲያዎች የዘገቡት ሲሆን እስካሁን ድረስ ማስተባበያ አልቀረበም። አቶ ጁነዲን በትክክል ኬንያ የሚገኙ ከሆነ ኢህአዴግ ሊይዛቸው ስለሚችል ወደ ሌላ አገር ባስቸኳይ እንደሚያመሩ ከግምት በላይ አስተያየት ተሰጥቷል። ወደ አውሮፓና አሜሪካ ለማምራት አስቸጋሪ ሁኔታ ስለሚገጥማቸው ምን አልባትም የደንበኛችን ጥቆማ ትክክል ሊሆን ይችላል ተብሎ ቢገመትም ጎልጉል በራሱ መስመር ሊያረጋግጥ አልቻለም። አቶ ጁነዲን የሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ የቅርብ ወዳጅ መሆናቸው ሲገለጽ የቆየ ጉዳይ ነው።

ኢህአዴግ ከዲያስፖራው ድጋፍ እንዳላገኘ ገለጸ
(ፎቶ: ከግድቡ ድረገጽ)

ዲያስፖራው ለአባይ ግድብ ቦንድ የሚፈለገውን ድጋፍ አለማድረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። የሚኒስቴሩ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያስረዳው፣ ከዳያስፖራው ለአገር ልማት ሊገኝ የሚችለውን የሀብት ፍሰትና የልማት ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችሉ ጥረቶች ቢደረጉም እየተገኘ ያለው ድጋፍ ግን ውስን ነው ሲል የተናገረው ሪፖርተር ነው።

በውጭ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች 43 የድጋፍ አሰባሳቢና የቦንድ ሽያጭ ምክር ቤቶች አማካይነት  የድጋፍ ማሰባሰብ ሥራው በስፋት ቢሠራም ባለፉት ስድስት ወራት ለህዳሴው ግድብ የተገኘው አጠቃላይ ገቢ ግን 3.04 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መሆኑን ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡ ከዚህ ውስጥ 2.7 ሚሊዮን ዶላር የተገኘው ከቦንድ ሽያጭ ሲሆን፣ የተቀረው 292 ሺሕ ዶላር ደግሞ በልገሳ የተገኘ ነው። ገንዘቡ እንደሚጠበቀው ባይሆንም ጠቃሚ መሆኑንና ወደፊት በስፋት መሠራት እንዳለበት የሚጠቁም ነው ሲል ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡ በዚህም መሠረት የዳያስፖራ ፖሊሲ በማዘጋጀትና ሌሎችንም አማራጮች በመጠቀም ዲያስፖራውን ለማነቃነቅ በስፋት ዝግጅት ላይ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ታዋቂው የቻይና ኩባንያ ክስ መሰረተ

ፔትሮትራንስ የተሰኘው የቻይና ኩባንያ የካሉብና የሂላላ የተፈጥሮ ጋዝ መሬቶችን የኢትዮጵያ መንግሥት አላግባብ ቀምቶኛል ሲል ቅሬታውን ጄኔቭ ለሚገኘው ዓለም አቀፍ ንግድ ምክር ቤት አቀረበ፡፡

ፔትሮትራንስ በሶማሌ ክልል በኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ ክምችቶች ለማልማት የሚያስችል ስምምነት ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር በሐምሌ ወር 2003 ዓ.ም. ተፈራርሞ ነበር፡፡ ማዕድን ሚኒስቴር ኩባንያው በገባው ውል መሠረት የመስክ ሥራ አልጀመረም በሚል የፔትሮሊየም ልማት ስምምነቱን በሐምሌ 2004 ዓ.ም. ማቋረጡን ይፋ አደርጎ ነበር። የኩባንያው ኃላፊዎች ከማዕድን ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ጋር ለመደራደር በተደጋጋሚ ያደረጉት ሙከራ ባለመሳካቱ፣ ጉዳዩን ለዓለም አቀፍ ንግድ ምክር ቤት ግልግል ተቋም በታኅሳስ ወር መጨረሻ አቅርበዋል ብሏል፡፡ የማዕድን ሚኒስቴር ኃላፊዎች ለድርድር ፈቃደኛ ከሆኑ ለግልግል ተቋሙ የቀረበው አቤቱታ ሊቋረጥ እንደሚችል ሪፖርተር ምንጮቹን ጠቅሶ አስታውቋል፡፡

“ኢትዮጵያን ከመቅጣት አብሮ መቆየት”

ኢትዮጵያን አስመልክቶ በርሊን በተካሄደ ስብሰባ ተናጋሪ የነበሩት የኢትዮጵያ ጉዳይ አጥኚ ፕሮፌሰር ሽቴፋን ብሩነ ኢህአዴግን አሁን ያሉት አመራሮች የቀድሞውን ታጋዮች አይወክሉም አሉ። ፕሮፌሰሩ ስለ ጀርመንና ኢትዮጵያ ግንኙነት ፍንጭ ሰጥተዋል።

በሐምቡርግ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ጉዳይ አጥኚ ፕሮፌሰር ሽቴፋን ብሩነ የኢትዮጵያን የወደፊት ሒደት ማወቅ የሚቻለዉ በገዢዉ ፓርቲ መሪዎች መሐል ያለዉ የሐይል አሰላለፍ በግልፅ ሲታወቅ መሆኑን፣ «ኢትዮጵያ ከመለስ በኋላ» በሚል ርዕሥ ስር መናገራቸውን የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ አመልክቷል።

አርሶ አደሮችን በማፈናቀል ለባዕድ ከበርቴዎች መሬት በመቸርቸር፣ በምርጫ ማጭበርበር፣ በሰብአዊ መብት ረገጣ፣ ፖለቲከኞችንና እስረኞችን በማሰር ግንባር ቀደም የሆነው ኢህአዴግ ይህንን ሁሉ ሲያደርግ ለምን አውሮፓውያኑና አሜሪካ ዝምታን መረጡ በሚል በስብሰባው ላይ ለተነሳው ጥያቄ፤ ዉይይት ላይ የተገኙት በጀርመን የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳይ ምክትል ሐላፊ ሆልገር ክሬመርን “ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር መደራደር ከባድ ነው” የሚል መልስ ሰጥተዋል። ፕሮፌሰሩ በበኩላቸው ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ ማዕቀብ አግዶ፣ ኢትዮጵያን ከማጣት ይልቅ አብረው መቆየትን መርጠው ሊሆን እንደሚችል መላምት መስጠታቸውን ከጀርመን ሬዲዮ ዘገባ ለመረዳት ተችሏል። በስብሰባው ላይ የመንግስት ተወካዮች አልተገኙም።

የፖሊስ አዛዡ በመንግስተ ሰማያት
(ፎቶ: stuffkit ድረገጽ)

የሳምንቱ አስገራሚ ዜና የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ነኝ ያሉ (ሳጅን ዘመድኩን) ከአሜሪካ ሬዲዮ የአማርኛ ክፍል ጋዜጠኛ ሰለሞን ክፍሌ ጋር ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ የሰጡት ምላሽ ነው። በአዲስ አበባ ሙስሊሞች ቤታቸው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መፈተሹንና በፍተሻው ሰበብ ወርቅ፣ ሞባይልና የተለያዩ ንብረት መዘረፋቸውን ካስታወቁ በኋላ ምላሽ እንዲሰጡ የተጋበዙት የቦሌ ክፍለከተማ ፖሊስ አዛዥ በመልሳቸው ዛቻ ሰንዝረዋል።

አዛዡ ለቀረቡላቸው ጥያቄ “አላውቅም” የሚል መልስ ከሰጡ በኋላ ጋዜጠኛ ሰለሞን የአቤቱታውን መነሻ አጠንክሮ ሲጠይቅ “ከአሁን በኋላ ቢደውሉ ያሉበት ቦታ ድረስ መጥቼ እወስድዎታለው” የሚል ዛቻ አስከተሉ። ጋዜጠኛውም “እኔ እኮ ዋሽንግተን ዲሲ ነው ያለሁት” ሲል “ለማሰር” እንዲችሉ ትክክለኛ አድራሻውን አመላከታቸው። አዛዡም “ዋሽንግተን አይደለም መንግስተ ሰማያት ቢኖሩ ምንም የሚያገባኝ የለም … ” በማለት በቁጥጥር ስር እንደሚያውሉት ነገሩት። ሰለሞን “ፍርዱን ለአድማጮች እሰጣለሁ” በማለት ግርምቱን በመግለጽ ተሰናብቷል።

በሳውዲ የታሰሩት ክርስቲያኖች አገራቸው ሊመለሱ ይችላሉ ተባለ

በሳውዲ አረቢያ በእስር ላይ የሚገኙት 53 የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን አሁንም በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የመኖሪያ ፈቃድ ካላቸው ሁለት ኢትዮጵያውያን በስተቀር ሁሉም ወደ አገራቸው ሊመለሱ እንደሚችሉ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ኢትዮጵያውያን ለኢሳት መግለጻቸው ታውቋል።

ኢትዮጵያውያኑ መቼ እንደሚመለሱ እስካሁን ባይታወቅም በቅርቡ ከሳውዲ ሊባረሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። ከእሰረኞቹ መካከል 46ቱ ሴቶች ሲሆኑ፣ ፖሊሶች ለስነልቦና ጉዳት እየዳረጓቸው መሆኑም ታውቋል።

የዓለምአቀፉ ማህበረሰብ የእስረኞችን ደህንነት በተመለከተ በቂ ትኩረት አለመስጠቱ እንዳሳዘናቸው ኢትዮጵያውያኑ ተናግረዋል ሲል ኢሳት ዘግቧል። በሳዑዲ አረቢያ የክርስትና እምነት መከተል የሚያስከትለው መዘዝ ወገኖቻችንን እየጎዳ መሆኑ በተዘገበበት ዜና ስር አስተያየት የሰጡ “የሰው አገር ለመኖር ያገሩን ህግ ማክበር ግድ ነው።”፤ “ማን ሂዱ አላቸው?”፤ “አገሪቱ የሙስሊም አገር ናት …” የሚሉ አስተያየቶች ተነበዋል።

በስምጥ ሸለቆ ነዳጅ ፍለጋ ሊጀመር ነው
ጋምቤላ ነዳጅ ተገኝቷል

አፍሪካ ኦይል ኮርፖሬሽን በመካከለኛው የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ አካባቢ የነዳጅ ልማትና ፍለጋ ሊያካሂድ መሆኑን ፋና ብሮድካስቲንግ አስታወቀ። የማዕድን ሚኒስቴርና ኩባንያው በፍለጋው  የስምምነት ሰነድ ተመፈራርመዋል።

በፊርማው ወቅትም የማዕድን ሚኒስትሯ ወይዘሮ ስንቅነሽ እጅጉ “ነዳጅ ፈላጊ ኩባንያው በሃገሪቱ ጥናቶችን ሲያደርግ እንደመቆየቱና በሌሎች ሃገራትም ስኬታማ ስራዎችን እንደመስራቱ፣ ፍለጋው ውጤታማ ይሆናል ብለን እናምናለን” ብለዋል። የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ጀምስ ፍሊፕስ  “በኢትዮዽያም ተስፋ ሰጪ ጥናቶችን አካሂደናል ወጤታማ እንደምንሆነም እምነታችን ነው” ማለታቸውን ፋና ገልጿል።

ቱሎው ኦይል የሚባለው የነዳጅ ፍለጋ ላይ የተሰማራው ድርጅት እያካሄደ ያለው ቁፋሮ ውጤታማ መሆኑንና ቁፋሮው በተሳካ መልኩ እየተካሄደ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ውጤቱን እንደሚያስታወቁ ሚኒስትሯ መናገራቸውን ተመልክቷል። በጋምቤላ ነዳጅ እየፈለገ ያለው የካናዳ ኩባንያ የተሳካ ውጤት እያስመዘገበ በመሆኑ ተጨማሪ ቦታ እንደተሰጠው ይፋ መደረጉ ይታወሳል። ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ነዳጅ እንዳለና ጥቅም ላይ መዋል እንደሚችል በመረጋገጡ ተጨማሪ ቦታ መከለል አስፈልጓል።

መልዕክት ከፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ

የህትመት መሳሪያ ለመግዛት መረዳጃ ገንዘብ አላላክ (የፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ዝግጅት አስተባባሪ ኮሚቴ በሰሜን አሜሪካ)
ቀደም ሲል ለፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ የህትመት መሳሪያ ማደራጃ ለመግዛት እንዲቻል ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል። በጥሪው መሰረት በርካታ ወገኖቻችን ተግባራዊ ምላሽ እየሰጡ መሆናቸው በወገኖቻችን እንድንኮራ አድርጎናል።

ይሁን እንጂ በርካታ ወገኖቻችን በገንዘብ አላላኩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ በመጠየቃቸው ይህን ማብራሪያ አቅርበናል።

(እዚህ ላይ ይጫኑ)

ገንዘቡ የሚገባው በቀጥታ በፍኖተ ነጻነት አካውንት ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule