• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ማፈናቀሉ የሚካሄደው በመንግሥት ትዕዛዝ ነው፤ ወደ ክስ እናመራለን”

April 23, 2013 04:10 am by Editor 4 Comments

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከ2000 ሺህ በላይ ትግሬዎች ባለይዞታ መሆናቸውንና ማንም ሳይነካቸው በሰላም እንደሚኖሩ፣ በቶጎ ወረዳ ከስልሳ በላይ ነባር የህወሃት ታጋዮች ሰፋፊ የእርሻ መሬት ወስደው በባለሃብት ደረጃ እንደሚገኙ የመኢአድ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አስታወቁ። ከሌሎች ብሔረሰቦች ተለይቶ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመበት ያለውን የአማራ ብሔረሰብ በድጋሚ ለማስወጣት መታቀዱንም በመረጃ ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።

በቦታው በመገኘት አስፈላጊውን መረጃ እንደሰበሰቡ ለአሜሪካ ሬዲዮ የገለጹት የመኢአድ ስራ አስፈጻሚ በክልሉ ከሚኖሩት የተለያዩ ብሔረሰቦች ተለይቶ የአማራ ብሔረሰብ እንዲፈናቀልና እንዲሰቃይ የሚደረገው በማዕከላዊ መንግስት ትዕዛዝ እንደሆነም አመልክተዋል።

መኢአድ ያሰራጨውን መግለጫ ተከትሎ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ማብራሪያ የሰጡት አቶ ሃይሉ ሻወል፣ ድርጊቱ በበታች የቀበሌና ወረዳ አመራር አካላት ተፈጽሟል መባሉን ተቃውመዋል።”ሰዎቹ እንዲወጡ ሲታዘዝ ያ ሁሉ ወታደር ከየት መጣ?” በማለት የጠየቁት አቶ ሃይሉ ሻወል፣ በርካታ የወያኔ ሰዎች በቦታው እያሉ አማራው ተለይቶ እንዲፈናቀል የበታች ባለስልጣናት በራሳቸው ውሳኔ ይህን ሊያደርጉ እንደማይችሉ ተናግረዋል። በማያያዝም በርካታ ተጨባጭ ማስረጃ ስለተሰባሰበ ጉዳዩን ወደ ዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለመውሰድ በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ አመልክተዋል።

ባላቸው የተለያየ መስመር ፍርድ ቤቱ የሚቀበላቸውን ማስረጃዎች በማጣራት አስፈላጊ መረጃዎችን እንዳሰባሰቡ የገለጹት ኢንጂነር ሃይሉ ሻወል፣ “የሰውና የቪዲዮ መረጃ አለን። የመንግስት ወታደሮች ህዝብ ሲደበድቡ፣ መኪና ተገልብጦ ሰዎች ሜዳ ላይ ሲሰቃዩ፣ በግድ ሲፈናቀሉ … የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ አሰባስበናል። ወደ ክስ እናመራለን” በማለት መናገራቸውን የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ (ቪኦኤ) አመልክቷል።

የመኢአድ የስራ አስፈጻሚ አባል በበኩላቸው የመንግስት ባለስልጣኖችና ካድሬዎች በኩምሩክ ሕዝብ በመሰብሰብ ማነጋገራቸውን ይጠቅሳሉ። እሳቸው እንዳሉት ህዝቡ “ለምን በዘራችን ሳቢያ ይህ ሁሉ ስቃይ ይደርስንባል?” በማለት ጠይቆ ነበር። የሰበሰቧቸው ባለስልጣናት “ክልሉ የናንተ አይደለም ውጡ” ሲሉ  እንደመለሱላቸው የጠቀሱት የስራ አስፈጻሚ አባል፣ በሌላ በኩል የተፈጸመው ህገ ወጥ የዘር ማጥፋት ተግባር የመንግስት እጅ ያለበት እንዳይመስል ለክልሉ ነዋሪዎች “አማራን አታስጠጉ፣ ከአማራ ጋር አትብሉ፣ ከአማራ ጋር አትጠጡ፣ ቤት አታከራዩ፣ ይህን ማድረግ ወንጀል ነው” በማለት መንገራቸውንና በዚሁ መነሻ ህዝቡ በክልሉ ያሉ አማሮች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ጥያቄ እንዲያቀርቡ መመሪያ መሰጠቱን አመልክተዋል። ይህ የሚሆነውም ጥያቄው ከህዝብ የመጣ እንደሆነ ለማሳየት እንደሆነም አስታውቀዋል።

ahmed
የቤኒሻንጉል ፕሬዚዳንት አህመድ ናስር

በዘር፣ በሐይማኖትና በአመለካከት አንድን ማህበረሰብ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት መሞከር፣ ማሸማቀቅ፣ ሴቶችን መድፈር በዘር ማጥፋት እንደሚያስጠይቅ ያመለከቱት የመኢአድ የስራ አስፈጻሚ አባል፣ “ይህ ሁሉ ተፈጽሟል” በማለት ድርጅታቸው በዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክስ ለመመስረት ከድምዳሜ መድረሱን ገልጸዋል።

የቤኒሻንጉል ክልል ፕሬዚዳንት ለሪፖርተር በሰጡት መግለጫ ስህተት መሰራቱን ማመናቸውና ድርጊቱን የፈጸሙት ኪራይ ሰብሳቢ የወረዳና የበታች አመራሮች እንደሆኑ ማስታወቃቸው አይዘነጋም። በተመሳሳይ ለስራ ፈረንሳይ አገር በነበሩበት ወቅት ለጀርመን ሬዲዮ ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ፕሬዚዳንቱ ተፈጸመ ስላሉት ስህተት “የማውቀው ነገር የለም። አልሰማሁም። እኔ የማውቀው ደን ጨፍጭፈው በሃይል መሬት የያዙ መፈናቀላቸውን ነው” ብለዋል። ዶ/ር ያዕቆብ ሃይለማርያም ቀደም ባሉት ሳምንታት ከቤኒሻንጉል የተፈናቀሉትን ዜጎች አስመልክተው በሰጡት አስተያየት ወንጀሉ የዘር ማጥፋት ስለሆነ ክስ መመስረት እንደሚቻል አመልክተው ነበር።

መኢአድ በበደኖ፣ በአርባ ጉጉ፣ አረካ ቀደም ሲል የተፈጸሙትን የዘር ማጥፋት ወንጀሎች አያይዞ ለክስ እንደሚጠቀምበት አመልክቷል። በጥያቄና መልሱ ወቅት ከነበሩት ጋዜጠኞች መካከል “የተፈናቀሉት ተመልሰዋል። ለምን አትተውትም” በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ጋዜጠኞች እንደነበሩ የቪኦኤው የአዲስ አበባ ዘጋቢ ጠቆም አድርጎ አልፏል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. አልማዝ says

    April 23, 2013 06:15 am at 6:15 am

    ውድ ጎልጉል፣ ሰፋፊ እርሻ አላቸው ያልካቸውን የህወሃት ታጋዮችን ስም ዝርዝር ማውጣት ይኖርባችኋል። ሌላው ሕዝብ ወደ ሌላ ክልል እንዳይሄድ ተከልክሎ [በተለይም ወደ ትግራይ] የትግራይ ሕዝብ ግን ወደ ፈቀደው ሄዶ እንደ ፈቀደው ንግድ ማካሄድ መቻሉ አግባብ አይደለም።

    Reply
  2. Mario says

    April 24, 2013 08:04 pm at 8:04 pm

    Ethiopians have been subjected to killilism over shadowed by fake federalism. The fact is, it is woyanes and Al Almoudie and their beneficiaries who have the right to work, live and create wealth in any part of the country. Not because they are forced, but by their own free will and the exclusive right they they have. The rest of us are, “የበይ ተምልካች”. People are not even allowed to travel out of their killils. Over the years, killilism and fake federalism developed to a subtle and refined woyane style apartheid system. That is what it is.

    Our immediate job is to dismantle killilism, fake federalism and apartheid systems in Ethiopia. The earlier we do it, the better!!!

    Reply
  3. moged says

    April 24, 2013 09:29 pm at 9:29 pm

    Yizegiy enji hulum edawun yikefla! Ahun enkua bayhon, beliju hone belij liju yaleksal.
    Gid yelem bisot yitefaqem. Genzebim habitim halafi new, Tplf.eprdf yeethiopian tarikinina hizbuan aqoshishew ayqerum!!

    Reply
  4. በለው ! says

    April 25, 2013 05:54 pm at 5:54 pm

    “ማፈናቀሉ የሚካሄደው በመንግሥት ትዕዛዝ ነው፤ ወደ ክስ እናመራለን”በጠ/ሚ ኅይለመልስ የተሰጠው የፓርላማ መልስ በጣም ጠለቅ ያለ ሚስጥርን አውጥቷል መተርጎም ለሚችል ወንጀለኛን የሚከላከል ቃል ነው። ለማይገባው ግን ግለሰቡን ኃይለኛ የህዝብ ተቆርቋሪና ብስጩ የሆኑ ያስመስላል ግን ቤታቸው የበሰበሰና የበሸቀጠ እኛ የሞቱ ጠ/ሚ እንዳሉት ቆሻሻ ሌባ እደግመዋለሁ ቆሻሻ ሌባ በኢህአዴግ በዝቷል ሕገመንግስቱም ሆ ! ብለህ አስወጣ ይላል አቶ ኀይለመልስ በፓርላማ ንግግራቸውን “የአማራ ክልልና የአማራ ብሔር ተወላጆች? “ሲሉ ነበር የጀመሩት ግን እዚህ ጋ ነው የህገመንግስቱ ብሽቃጣምነት ማንነትህን በዘርህ እንጂ በኢትዮጵያዊ ዜግነትህ አያውቅህም ሀገሪቱም ሉዓላዊነት ሳይሆን ክልላዊ የግለሰብ ሉዓላዊነት ብሎ አስቀምጦታል አንድ በረት የታጎረ ከብት መለያው ቋንቋውና ዘሩ የሆነ !!… አፈናቃይ ተብዬዎች? ሕገምንግስቱ እንደተጻፈው “ለክልሉ መሰተዳደርና ለሕዝቡ ልማት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ማናቸውንም ሠፋሪ (ሞፈር ዘመት) ብሎ ማስለቀቅ መብቱ እንደሆነ ይደነግጋል”። አታጭበርብሩ!…የፌዴራል መንግስት ሥልጣንና ኀላፊነት ግን “የክልሉ መንግስት ማስተዳደር ያልቻለውንና ተከራይ ማፈላለግ ባልቻለበት ጊዜ ሙሉ ኀላፊነት ወስዶ ተከራይ ማፈላለግና መሬቱን ማከራየት መብት እንዳለው ይገልጻል”። ስለዚህ እጅና ጓንት ሆኖ የተሠራውን ውንብድና በጥቂት ግለሰቦች ላይ ለጥፎ ለህዝብ ተቆርቋሪነትን ለማሳየትና እራስን ከወንጀል ማፅዳት በሩሱ የማጭበርብር ወንጀል ነው። ለመሆኑ ችግሩ ከተፈጠረ ጀምሮ ጠ/ሚ ኅይሌ ጋዜጣዊ መግለጫ በቲቪ፣ በሬዲዮ፣ በጽሑፍም ይሁን ማስተካከያ ሠጥተዋልን? እንዴት በፓርላማ ለመፎከር በቁ? ? በራሳቸው አንደበት የሚያምኑት ግን በሁሉም ክልል “ኢህአዴግ በሌብነት የተጨማለቀ ኪራይ ሰብሳቢ ወሮባላ መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል!።” ለመሆኑ ይህ ደን የሚመነጥረው(ከሌላ አካባቢ የሚመጡ ሰዎች ያሏቸው!!?) የኦሮሞና የአማራ ገበሬዎች ወንጀል ነው። ሕንድና አረብ ሲያቃጥለው ልማት ነውን?
    ”ሰዎቹ እንዲወጡ ሲታዘዝ ያ ሁሉ ወታደር ከየት መጣ?”
    የአጭበርባሪ “ከቡድን” ወደ “ኀብረት አመራር” የተሸጋገረ የተወራረሰ የተተካካ ሌብነት…
    *የቤኒሻንጉል ክልል ፕሬዚዳንት አህመድ ናስር ለሪፖርተር በሰጡት መግለጫ ስህተት መሰራቱን ማመናቸውና ድርጊቱን የፈጸሙት ኪራይ ሰብሳቢ የወረዳና የበታች አመራሮች እንደሆኑ ማስታወቃቸው አይዘነጋም።
    **በተመሳሳይ ለስራ ፈረንሳይ አገር በነበሩበት ወቅት ለጀርመን ሬዲዮ ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ፕሬዚዳንቱ ተፈጸመ ስላሉት ስህተት “የማውቀው ነገር የለም። አልሰማሁም። እኔ የማውቀው ደን ጨፍጭፈው በሃይል መሬት የያዙ መፈናቀላቸውን ነው” ብለዋል።
    ***አቶ ኀይለመልስ ግን የማያውቁትን ህገመንግስት በማቆላመጥ ሕዝብ ከእነ ነፍሱ የሚሸጥ ኪራይ ሰብሳቢ በሁሉም ክልል ይዘው ሀገር እንደሚመሩ በድፍረት ይናገራሉ። ገንዘብ ያለው አማራና ኦሮሞ አይፈናቀልም ሲሉ… በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከ2000 ሺህ በላይ ትግሬዎች ባለይዞታ መሆናቸውንና ማንም ሳይነካቸው በሰላም እንደሚኖሩ፣ በቶጎ ወረዳ ከስልሳ በላይ ነባር የህወሃት ታጋዮች ሰፋፊ የእርሻ መሬት ወስደው በባለሃብት ደረጃ እንደሚገኙ አልተናገሩም ምክንያቱም የእንጀራ ገመዳቸው ይበጠሳል።ለማስመሰል ጥቂት ማንበብና መፃፍ የማይችሉ ድሆች ሲታሠሩና ሲሰቃዩ በፍርድ ሲጉላሉ የሚያሳይ ተከታታይ ድራማ እራሳቸው የወያኔ ባለሀብቶች ፊልም ይሠሩበታል። የብላ ተባላ የኀብረት አመራር… “አመራር በደቦ” ሸዋ ተወቃህ በለው አላልኩም ነበር ?የኅይለመለስ ደስአላለኝም ይህንን ጉዳይ እልባት የሚሠጠው በዓለም መንግስታት ሕግ ፊት ቀርቦ ለተደጋጋሚው ጥፋት ዕርማት ባለመስጠቱ ቅጣትና ትምህርት ሲያገኝ አለዚያም የሕገመንግስቱ አተረጓጎም በሁሉም የሀገሪተ ቋንቋና የህግ ባለሙያዎች ከሌሎች መመሪያ ደንቦችና አዋጆች ጋር ሲናነብና ሲጠና ብቻ ነው!!። ለ፻፮ የሕገመንግስት አንቀፅ ፻፮ አዋጅና መመሪያ ማውጣት ከጥፋት አያድንም “ልዩነታችን ውበታችን ማለትም” ሀገሪቱን ከመበታተን አያድናትም ። ለነገሩ ብትኖር ኖሮ ሠው በዘር፣በድህነቱ፣በቋንቋው ተለይቶ ይፈናቀል ነበር ? ?የቀጣፊ ፣ሆድአደር ፣አድርባይ ፣ጥቅመኛ፣ወኔ ቢስ፣ ዘመንና ትውልድ የፈጠረ የተማረ የገደለው ህዝብ።
    ” ኢትዮጵያ እጆቿን ዘርግታ ቅን አሳቢ ልጆቿን ትሠበስባለች እንደገና አንድ ትሆናለች በለው! በቸር ይግጠመን ከሀገረ ካናዳ

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule