አቶ መለስ ከሞቱ ጀምሮ በተለያዩ መድረኮች ንግግርና መዕልክት የሚያስተላልፉት ወ/ሮ አዜብ መስፍን መረጋጋት እንደማይታይባቸው ተገለጠ። አሁንም በባለቤታቸው ስምና መንፈስ ሙግትና ማብራሪያ ከማቅረብ አልተላዘቡም። ይህን የሚያደርጉት ከጭንቀት የተነሳ እንደሆነ ተመልክቷል። ሰሞኑንን በተጠናቀቀው የኢህአዴግ ጉባኤ አቶ መለስን አስመልክቶ ወ/ሮዋ የተናገሩት ንግግር በጭንቀት ውስጥ ስለመሆናቸው ማሳያ እንደሆነ የተናገሩት አብረዋቸው ባህር ዳር ስብሰባ የተቀመጡ የድርጅታቸው ኢህአዴግ “ባልደረቦቻቸው” ናቸው። በጉባኤው ወቅት አቶ መለስ ዜናዊን በማወደስ የተዘጋጀው “ዝክረ – መውደስ” ታሪካዊ ሰነድ እንዲሆን ከመጽደቁ በፊት ወ/ሮ አዜብ በሰጡት አስተያየት “በፔሮል የሚከፈለው ብቸኛ መሪ መለስ ብቻ ነው” በማለት ራሳቸውን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በፔሮል በሚከፈላቸው ገንዘብ ብቻ እንደማይኖሩ … [Read more...] about ወ/ሮ አዜብ ተጨንቀዋል!
News
ዜና
ከእሁድ እስከ እሁድ
አንድ ላስቲክ ውሃ 10 ብር!! በአፋር የቡሬ ነዋሪዎች ለከፍተኛ የውሃ ችግር መዳረጋቸውን ውሃ የሚሸጥበትን ላስቲክ በፎቶ በማያያዝ የጎልጉል የአይን ምስክር ከስፍራው አስታውቋል። በክልሉ የጎልጉል ተከታታይ የሆኑ እንደገለጹት በመጠጥ ውሃ ችግር እየደረሰ ያለው ችግር ከፍተኛና ህይወትን የሚፈታተን ነው። አካባቢው የጦር ቀጠና ከመሆኑ አንጻርና የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር አሳሳቢ እንደሆነ ያስታወቀው የአይን ምስክር "እባካችሁ የሚሰማ ካለ ንገሩልን" ሲል ጥሪ አስተላልፏል። የውሃ ችግር ጊዜ የሚሰጥ ባለመሆኑ አንድ ላስቲክ ውሃ 10 ብር ለመግዛት መገዳዳቸውን፣ በዚህም ቢሆን እንደ ልብ ማግኘት እንደማይቻል አመልክቷል። በስፍራው ያለውን የውሃ ችግር አስመልክቶ ሎጊያ የሚገኝ ጎልጉል የአይን ሪፖርተር አስተያየቱን እንዲሰጠን ጠይቀነው የበኩሉን ማጣራት ካደረገ በኋላ ችግሩ መኖሩን … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
World Bank told to investigate links to Ethiopia ‘villagisation’ project
An independent panel has called for an investigation into a World Bank-funded project in Ethiopia following accusations from refugees that the bank is funding a programme that forced people off their land. In a report, seen by the Guardian, the inspection panel – the World Bank's independent accountability mechanism – calls for an investigation into complaints made by refugees from the Anuak indigenous group from Gambella, western Ethiopia, in relation to the bank's policies and … [Read more...] about World Bank told to investigate links to Ethiopia ‘villagisation’ project
“የህዳሴው ግድብ” ከግማሽ በላይ የኢትዮጵያ አይደለም
“በራሳችን መሐንዲስ፣ በራሳችን ገንዘብ፣ በራሳችን የተባበረ ክንድ እንገነባዋለን" በማለት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመስቀል አደባባይ ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍና "መዓበላዊ መነቃቃት" ፈጠሩበት የተባለለት የ"ህዳሴው" ግድብ 51 በመቶ ድርሻ የኢትዮጵያ እንዳልሆነ ነዋሪነታቸው በአውሮፓ የሆነ ዲፕሎማት በተለይ ለጎልጉል ገለጹ። ስማቸው ምስጢር እንዲሆን የጠየቁት ዲፕሎማት እንዳሉት 51 በመቶ ባለድርሻ የሆነችው አገር አውሮፓ የምትገኝ የኢትዮጵያ አጋር አገር ናት። ለጊዜው የባለድርሻዋን አገር ስም መግለጽና የውሉን ዝርዝር ይፋ ማድረግ ያልፈለጉት ዲፕሎማት ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ የፈለገችውን ውሳኔ በራስዋ ለማስተላለፍ እንደማትችል፤ ያላት ድርሻ 49 በመቶ ብቻ በመሆኑ ድምጽን በድምጽ በሚሽረው በአብላጫ ድምጽ ህግ መሰረት በግድቡ ላይ የሚወሰነው ውሳኔ 51 በመቶ ባለድርሻ በሆነችው … [Read more...] about “የህዳሴው ግድብ” ከግማሽ በላይ የኢትዮጵያ አይደለም
“የመለስ አስተምህሮት” ጉባኤ ታዳሚዎች
ኦህዴድ ዘግይቶ ምርጫውን ይፋ ያደረገበት ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኋላ ባህር ዳር ለሚካሄደው ዘጠነኛው የኢህአዴግ ጉባኤ የተሰየሙትን የየድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ስም ዝርዝር ኢህአዴግ ይፋ አድርጓል። ጉባኤው "በመለስ አስተምህሮዎች ጠንካራ ድርጅትና የልማት ሃይሎች ንቅናቄ ለህዳሴያችን" በሚል መሪ ቃል ከቅዳሜ ጀምሮ በባህር ዳር ከተማ ነው የሚካሄድ ሲሆን ጉባኤው አራት ቀናት እንደሚፈጅ ይፋ ተደርጓል። በጉባኤው ያለፉት ሁለት ዓመታት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸምና ቀጣይ እቅዶች ላይ ይወያያል፣ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። ምርጫን አስመልክቶ በከፍተኛ ደረጃ ለውጥ ይኖራል ተብሎ እንደማይጠበቅ ከወዲሁ ለማወቅ ተችሏል። ፋና ያወጣው የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፡፡ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት/ ማዕከላዊ ኮሚቴ … [Read more...] about “የመለስ አስተምህሮት” ጉባኤ ታዳሚዎች
የኦህዴድ ምርጫ ውጤት ተራዘመ
ድሮ “ላዩ ካኪ ውስጡ ውስኪ” እየተባለ በኢሰፓ አባላት ዩኒፎርም ይቀለድ ነበር። ዛሬ ደግሞ ኢህአዴግ ተመሳሳይ ልብስ አልብሶ በየክልሉ የሰየማቸውን ፓርቲዎችና አመራሮቻቸውን የተመለከቱ “ስቱኮ” እያሉ እንደሚቀልዱባቸው ተሰምቷል። “ስቱኮ” ግልብጥና ግጭት የበዛበት መኪና ተቀጥቅጦ አልስተካከል ሲል፣ የተገጣጠበና አልመሳሰል ያለ ግድግዳ “በግድ” ለማመሳሰል የሚያገለግል ቶሎ የሚፈረካከስ ጭቃ መሰል የቀለም አይነት ማጣበቂያ ነው። “ኮሚኒስቶች በችግርና በቅራኔ ውስጥ ሆነው በግድ ለመመሳሰል አንድ ዓይነት መለያ መልበስ ይወዳሉ። ኢህአዴግም በተመሳሳይ በችግር ውስጥ ተዘፍቆ ሳለ፣ ለተመልካችና ለካሜራ ተመሳሳይ ልብስ ለብሶ በግድ አንድ ነኝ ሲል ማየቱ ብዙም የሚገርም አይደለም” የሚለው አስተያየት በስፋት እየተሰጠ ነው። “በግድ አንድ” ሆነው በየክልሉ ስብሰባ የሚያካሂዱት እህት ፓርቲዎች … [Read more...] about የኦህዴድ ምርጫ ውጤት ተራዘመ
ህጻናት እየራባቸው መማር አቅቷቸዋል!
ህጻናት እየራባቸው ትምህርት መማር እንዳቃታቸው ሸገር አዲስ ኤፍ ኤም ያነጋገራቸው መምህራንና ተማሪዎች ተናገሩ። ሸገር ያነጋገራቸው ተማሪዎች በየተራ እንደተናገሩት በምግብ ችግር ትምህርታቸውን መከታተልና ክፍል ውስጥ ትኩረት ማድረግ ተስኗቸዋል። “ሌሎች ምሳ ያላቸው ምሳ ሲበሉ እኔ የቤት ስራ እሰራለሁ። ወይም ቤተክርስቲያን እሄዳለሁ” በማለት አንድ ተማሪ ሲናገር፣ ሌላኛው ምሳ የሚባል ነገር እንደማያውቅ ገልጿል። በርሃብ ምክንያት ትምህርታቸውን በወጉ መከታተል ያልቻሉ ተማሪዎች ጉዳይ እንዳሳሰባቸው መምህራኑ ሲናገሩ ሸገር አስደምጧል። በሰሙት ዜና ረፍት ያጡ በርካታ ወገኖች ስልክ በመደወል ተማሪዎቹ በትምህርት ቤታቸው ውስጥ የምሳ አገልግሎት እንዲያገኙ የበኩላቸውን ለማድረግ ሲነጋገሩና ቃል ሲገቡ ለመስማት ተችሏል። አዲስ አበባ በኑሮ ውድነት ሳቢያ የሚበሉ ያጡ፣ በክፍል ውስጥ ረሃብ … [Read more...] about ህጻናት እየራባቸው መማር አቅቷቸዋል!
ከእሁድ እስከ እሁድ
"ፀላእትና ክንከራታትሞም ኢና" "ህወሓትን እናስቀድም ... 'ጠላቶቻችንን እናውድም'!" ሦስት ቀናት የፈጀው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ ትናንት ተጠናቋል። ለጉባኤው የሚሆን ኣጀንዳ ለመለየትና ልዩነታቸው ለማጥበብ ህወሓቶች ሲነታረኩ ቆይተው ቀጣዩ 11ኛ የህወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ በሰላም ለማጠናቀቅ የተስማሙ ይመስላሉ ሲል ኢትዮ ሚዲያ መድረክ የመቀሌ ዘጋቢውን አብርሃም ደስታን ጠቅሶ ዘገበ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በሁለት ተከፍለው ዘለፋና የጠብ መንፈስ የተሞላበት ጭቅጭቅ ከተካሄደ በኋላ ሌላ ሦስተኛ ቡድን ተፈጥሮ “ህወሓትን እናስቀደም፣ ልዩነታችን ወደ ጎን ትተን የጋራ ጠላቶቻችንን እንታገል፣ ሁለታቹ (ቡድኖቹ) የህዝብ ድጋፍ የላችሁም፤ ስለዚህ በሁለት ከተከፈልን ህወሓት ህልውናው ያበቃል።” በሚል ተማጽኖ ማሰማታቸውን ድረገጹ አመልክቷል። በዶ/ር ቴድሮስ ኣድሓኖም የተመራ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
በጋምቤላ፤ አሜሪካ የዜጋዋን መቃብር ከፍታ መረመረች
በጋምቤላ የመከላከያ ሰራዊት ከጨፈጨፋቸው ሰዎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው አቶ ኡሞት ኡዶል ግድያ ለማጣራት ከአሜሪካ መንግስት የተላኩት የፎረንሲክ (ለህዝብ ይፋ የሚያደርጉ) ባለሙያዎችን ጋምቤላ ገብተው የማጣራት ሥራ ጀምረዋል። “የጋምቤላ አኬልዳማ” እየተዘጋጀ እንደሆነም ተሰማ። የጎልጉል የጋምቤላ መረጃ አቀባዮች እንዳሉት ጋምቤላ የደረሱት የአሜሪካ ዜጎች የሄዱበትን ጉዳይ ለማከናወን ከክልሉና ከመከላከያ ሰራዊት ባለስልጣናት ዘንድ እክል ገጥሟቸው ነበር። የፎረንሲክ ባለሙያዎቹ የዜጋቸውን አሟሟት መንስኤና የጉዳት መጠን ለማጣራት ጋምቤላ እንደደረሱ አስከሬኑ በስውር የተቀበረበትን ቦታ ማወቅ እንደሚፈልጉ፣ አስከሬኑ ላይ የዲኤንኤ ምርመራ በማካሄድ የሟችን ትክክለኛ ማንነት ለማረጋገጥ፣ የጉዳቱን መጠንና በምን ያህል ጥይት እንደተደበደበ ለማጣራት፣ ከዚያም በላይ ለምርመራ … [Read more...] about በጋምቤላ፤ አሜሪካ የዜጋዋን መቃብር ከፍታ መረመረች
በሚዲያ መረሳት ያስፈራል
“ከምድር በታች ጨለማ ቤት ውስጥ የታሰሩትን በቀን ለ10 ደቂቃ እናያቸዋልን። ልብ የሚነካ ነው። የብርሃን ማነስ አይናቸውን እንደጎዳቸው ያስታውቃሉ … ሴቶችን በተገኘው ሰበብ ያስሯቸዋል። ምክንያት ፈልገው እስር ቤት ይከቷቸዋል። ከዚያም ይደፍሯቸዋል። በርካታ የተደፈሩ እህቶች አሉ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና መንግሥት ያሰማራቸው ሚሊሻዎች ይህንን አሳዛኝ ድርጊት እንደፈጸሙ ተነግሮናል” ይህ ማዕከላዊ እስር ቤት ታስሮ፣ ችግሩ ባለበት ቦታ ተገኝቶ የነበረው ስዊድናዊ የፍሪላንሰር ጋዜጠኛ ማርቲን ካርል ሻቢዬ ቃል ነው። ስለ ማዕከላዊ እስር ቤት መስማት ይጨንቃል። ሰዎች በሲቃ የሚያሰሙት የጣር ድምጽ ለጆሮ የተለመደ ነው። ከመሬት በታች የጨለማ ክፍል አለ። በዚህ መታጎሪያ ውስጥ ሆነው ስቃይ የሚፈራረቅባቸው ወገኖች ጥቂት አይደሉም። ማዕከላዊ ብዙ ጉድ ያለበት ሲኦል ነው። የሰው ልጆች … [Read more...] about በሚዲያ መረሳት ያስፈራል