እለተ እሁድ 04/09/05 ከምሽቱ ሁለት ሰዓት በባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር እንዲሁም የብአዴን ዋና ፅ/ቤት ከሚገኝበት “የሰማእታት ሀውልት” ተብሎ ከሚጠራው ቦታ አቅራቢያ አንድ የፌደራል ፖሊስ በንፁሐን ዜጐች ላይ በከፈተው የሩምታ ተኩስ 16 ሰዎችን ሲገድል በርካቶችን አቁስሏል ከሆስፒታል ምንጮች እንደሰማሁት የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ ይችላል ገዳዩ የፌደራል ፖሊሱ ከግድያው በኋላ ምንም እንኳን ቦታው ብዙ ወታደሮች የሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ቢሆንም ከቦታው ሊያመልጥ ችሏል።አገዛዙን የተቃወመ ንፁሐን ዜጋ ሁሉ የሽብር ሴራ አከሸፍኩ እያለ የአሸባሪነት ታርጋ እየለጠፈ ወደ እስር የሚያወርደው የወያኔ መንግስት ጉያው ውስጥ ደብቆ ያቆየው የአገዛዙ የመንፈስ ልጅ አሸባሪ ሕዝብን ጨርሶ ሲያመልጥ “ስንት የሽብር ጥንስስ አከሸፈ” የተባለለት ፀረሽብር ግብረ ሀይል … [Read more...] about ባህርዳር አነባች!! ባህርዳር አነባች!!
News
ዜና
ሙስናን በስንጥር! ከዚያስ?
በቀረጥ፣ በሙስናና ባለስልጣናትን የንግድ ሸሪክ በማድረግ ኢትዮጵያን እየጋለቡዋት ያሉ “ባለሃብቶችና አሽከሮቻቸው” እስካልተነኩ ድረስ ኢህአዴግ በሙስና ላይ የጀመረውን ትግል ሙሉ ሊያደርገው እንደማይችል ተገለጸ። ጅማሮው የችግሩ ቁልፍና እምብርት በሆነው ተቋም ላይ መሆኑ የሚደነቅ እንደሆነ የሚገልጹ ክፍሎች ደግሞ ድሩ ያልተበተበው የለምና የመጨረሻው አካሄድ ወዴት እንደሚያመራ ለመገመት ቢቻልም ጅምሩ ይገፋል የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው አስታውቀዋል። የባለስልጣናት ሚስቶችን፣ ዘመዶችና ወዳጆችን በተቋሞቻቸው ውስጥ በማይመጥኑት ሃላፊነት በመመደብ፣ ከተለያዩ የማማለያ ሽልማቶች ጋር ከፍተኛ ደሞዝ በመክፈል፣ አንዳንዴም ውጪ አገር ድረስ የህክምና ወጪ በመሸፈን ሰበብ የአገሪቱን የአመራር በትር ጨብጠው አገሪቱን እያለቡ ያሉት ወገኖች በይፋ እንደሚታወቁ የሚገልጹ ክፍሎች “አሁን ተጀመረ የተባለውና … [Read more...] about ሙስናን በስንጥር! ከዚያስ?
የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት አንዷለም አራጌን እንዳይጠይቁ በልዩ ሀይል ተባረሩ
የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ወጣቱን ፖለቲከኛና የፓርቲው አመራር አንዷለም አራጌን እንዲሁም ሌሎችን የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ለመጠየቅ ቅዳሜ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ቃሊቲ ቢሄዱም ለመጠየቅ እንዳይችሉ መደረጋቸውንና እስካፍንጫቸው በታጠቁ ልዩ ሃይሎች በግድ ከአካባቢው እንዲርቁ መደረጋቸውን የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ አስታወቀ፡፡ እንደፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ገለፃ ከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ወጣቱን ፖለቲከኛና ከፍተኛ አመራር አንዱአለም አራጌና ናትናኤል መኮንን ሽብርተኞች እንደሆኑና በሰላማዊ ትግል ሽፋን ሽብርተኝነትን እንደሚያራምዱ ተደርጎ የቀረበው ሀተታና ውሳኔ እጅግ ያሳዘናቸው በርካታ አመራሮችና አባላቱ በከፍተኛ መነሳሳትና ቁጭት ከ 20 በላይ የሚሆኑ የፓርቲው ሰዎች ከ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እንኳን አደረሳችሁ … [Read more...] about የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት አንዷለም አራጌን እንዳይጠይቁ በልዩ ሀይል ተባረሩ
ከእሁድ እስከ እሁድ
አሜሪካ የሽብር ህጉ አሰጋኝ አለች በሳምንቱ አጋማሽ በእነ አንዷለም አራጌና እስክንድር ነጋ ላይ የበታች ፍርድ ቤት የወሰነው ውሳኔ መጽናቱን ተከትሎ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቃውሞ አሰምቷል። ቪኦኤ ድምጻቸውን ያሰማቸው የሚኒስቴሩ ተጠባባቂ ቃል አቀባይ ፓትሪክ ቬንትል "ውሳኔው በጸረ ሽብር ህጉ ላይ ያለንን ስጋት ያጠናክረዋል" ሲሉ ተደምጠዋል። "በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና በእነ እንዷለም አራጌ ላይ የተላለፈው ፍርድ በመጽናቱ አሜሪካ በጥልቅ ቅር ተሰኝታለች" ያሉት ቃል አቀባዩ ውሳኔው መንግስት የሚተቹትን ሁሉ ለፍርድ እንደሚያቀርብ አመላካች ነው ብለዋል። ሰዎች በነጻነት የመናገርና የማሰብ መብት እንዳላቸው የጠቆሙት ቃል አቀባዩ ኢትዮጵያ በህገ መንግስቷ ያሰፈረችውን የሰብአዊ መብቶችንና የዲሞክራሲ መብቶችን ማክበር የወደፊቱ ግቧ እንደሆነ አመልክተው "ኢትዮጵያ እነዚህን … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
ኦባንግ የኢህአዴግ ደጋፊ ስደተኞችን አስጠነቀቁ
“ክፉን በክፉ መመከት ባያስደስትም ወቅቱ ያስገድደናል” ሲሉ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል ተናገሩ። አገዛዙን ሸሽተው በተለያዩ አገራት ከለላ አግኝተው በስደት የሚኖሩም ሆኑ ጉዳያቸው እየታየ ያሉ ወገኖች አካሄዳቸውን እንዲያስተካክሉ አስጠንቅቀዋል። የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ህግ አውጪዎች፣ የጀርመን የኢሚግሬሽን ሃላፊዎችና ከፍተኛ የፖለቲካ ሰዎች፣ ከኖርዌይ የኢሚግሬሽን ጉዳይ ሃላፊዎችና ተዛማጅ ሃላፊነት ካላቸው የህግ ክፍሎች፣ በካናዳ በተለያዩ ደረጃ ካሉ ባለስልጣናትና ወትዋቾች (አክቲቪስቶች)፣ በስዊድን አንዲሁም በእንግሊዝ በተመሳሳይ ግንኙነት ፈጥረው እየሰሩ መሆኑንን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አገራቱ የስደት ፈቃድ ካገኙ በኋላ ለስደት ዳረገን ከሚሉት መንግሥት ጋር በቅርብ እየሰሩ ስላሉ አስመሳይ ስደተኞች አስገራሚ መረጃዎች … [Read more...] about ኦባንግ የኢህአዴግ ደጋፊ ስደተኞችን አስጠነቀቁ
ከእሁድ እስከ እሁድ
ኢትዮጵያ በቻይና ብድር እየተንበሸበሸች ነው በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ታላላቅ ስምምነቶች ይጠበቃሉ ከአፍሪካ ጋር መሳ ለመሳ የገባችው ቻይና በሳምንት ጊዜ ውስጥ ለኢትዮጵያ 4.5 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ ለማበደር ወስናለች። ከአባይን ግድብ የሚመነጨውን ሃይል የማስተላለፍና የማከፋፈል ጣቢያ ለመገንባት ከሚፈለገው 1.2 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 85 በመቶውን ለመስጠት መዋሰኗን የመንግስት ሚዲያዎች ዘገበዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዘወትር እንደሚደረገው የቻይና የኤሌክትሪክ ፓወር ኢኪውፕመንት ቴክኖሎጂ ኩባንያ ግንባታውን በሰላሳ ቀን ውስጥ ለመጀመርና በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማስረከብ ተስማምቷል። ስለዚህ ብድሩ ከቻይና ኪስ ወጪ ተደርጎ ወደ ቻይና ኪስ ይዛወራል። በሌላ ተመሳሳይ ወሬ ለአትዮጵያና ለጅቡቲ የባቡር መስመር ግንባታ የሚውል 3.3 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት የቻይና መንግስት መወሰኑን … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
ኢህአዴግ በኖርዌይ ገንዘብ ማሰባሰብ ተሳነው
በስደት አገራቸውን ለቀው የወጡ ሰዎች ያለመሰለል መብት አላቸው። በህግም የተደነገገ ነው። ከለላ የሰጣቸውም አገር ይህንን የመከላከልና የመቃወም ግዳጅም አለበት። ከለላ ያገኙ ስደተኞችም ሆኑ ከለላ እንዲሰጣቸው ያመለከቱ ወገኖች ስለመሰለላቸው ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ ከቻሉ ህጉን ጠቅሰው የመከራከር መብት አለቸው። ለመብታቸው ሲከራከሩ በመደራጀት ቢሆን ይበልጥ ውጤታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ አውሮፓ በስደት ያሉ ቀድሞ የውጪ ጉዳይ የዲያስፖራ ኢንጌጅመንት ዳይሬክቶሬት ዲፓርትመንት ኤክስፐርት ይናገራሉ። እኚሁ ሰው እንደሚሉት ከ1997 ዓ ም ምርጫ በኋላ በአቶ መለስ ቀጥተኛ ትዕዛዝ የተቋቋመው ይህ ዲፓርትመንት ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለወቅቱ የውጪጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍን ሪፖርት ያቀርብ ነበር። በጁላይ 2003 ስድስት አባላትን በመያዝ የተቋቋመው ዲፓርትመንት “ብዙሃን አድፋጭ” ዲያስፖራ … [Read more...] about ኢህአዴግ በኖርዌይ ገንዘብ ማሰባሰብ ተሳነው
ኦባማ አርፍደው ወደ ኢትዮጵያ?
በአፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ከሚገኙት የተለያዩ እንግዶችና ባለስልጣናት በተጨማሪ አራት ታላላቅ መሪዎች እንደሚገኙ እየተነገረ ነው። በዋናነት የሚጠቀሱት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ኦባማ ሲሆኑ፣ የቻይና አቻቸውም ዋናውና ታላቁ እንግዳ እንደሚሆኑ ይጠበቃል። የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ባለፈው ረቡዕ ለአሜሪካ ኮንግረንስ ኮሚቴ የተናገሩትን በመጥቀስ ዜናውን የላኩልን ክፍሎች እንዳሉት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ሊያመሩ ይችላሉ። ውጪ ጉዳይ ሚ/ሩ ኦባማ ኢትዮጵያ ስለመሄዳቸው ፍንጭ ቢሰጡም ስለጉዞው ዝርዝር አለመናገራቸው ታውቋል። የቻይና በአፍሪካ ሚና መጉላት ውሎ አድሮ የጠዘጠዛት አሜሪካ፣ በመጪው ወር በሚካሔደው የአህጉሩ 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ በፕሬዚዳንቷ ለመወከል መወሰኗ "ጉባኤ አድማቂ" አሰኝቷታል። "በአፍሪካ ብዙ የምንሰራው ስራ አለን" ሲሉ የተናገሩት ኬሪ … [Read more...] about ኦባማ አርፍደው ወደ ኢትዮጵያ?
ከእሁድ እስከ እሁድ
በሲዳማ ህዝብ እያመጸ ነው ሚያዚያ 6 ቀን 2005 ዓ ም ኢህአዴግ ብቻውን ሊያካሂደው የነበረውን ምርጫ አንቀበልም በማለት ከተለያዩ ወረዳ በትስስር የተቃወሙ የሲዳማ ብሔረሰብ አባላት መታሰራቸውን የጎልጉል ምንጮች አስታውቀዋል። ምንጮቹ እንዳሉት በአካባቢው ከፍተኛ ድጋፍ ያለው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ከምርጫው ራሱን ማግለሉ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንዳገኘም አመልክተዋል። በቀበሌ የመሰብሰቢያ አዳራሾች የታጎሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው የብሔረሰቡ አባላት እንዲፈቱ በሚጠይቁና በታጣቂ ሃይሎች መላከል የተካረረ ግጭት ይነሳል የሚል ፍርሃቻ እንደነበር ያመለከቱት ምንጮች የሲዳማ ተወላጆች የታጠቁ ስለሆነ ኢህአዴግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ አንጋቾችን ማሰማራቱን አመልክተዋል። ለምርጫው አንድ ቀን ሲቀረው እጩዎቼ፣ ታዛቢዎቼና አባላቶቼ በእስር፣ በድብደባና ከሥራ በመባረር እየተንገላቱ ነው … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
“ማፈናቀሉ የሚካሄደው በመንግሥት ትዕዛዝ ነው፤ ወደ ክስ እናመራለን”
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከ2000 ሺህ በላይ ትግሬዎች ባለይዞታ መሆናቸውንና ማንም ሳይነካቸው በሰላም እንደሚኖሩ፣ በቶጎ ወረዳ ከስልሳ በላይ ነባር የህወሃት ታጋዮች ሰፋፊ የእርሻ መሬት ወስደው በባለሃብት ደረጃ እንደሚገኙ የመኢአድ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አስታወቁ። ከሌሎች ብሔረሰቦች ተለይቶ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመበት ያለውን የአማራ ብሔረሰብ በድጋሚ ለማስወጣት መታቀዱንም በመረጃ ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል። በቦታው በመገኘት አስፈላጊውን መረጃ እንደሰበሰቡ ለአሜሪካ ሬዲዮ የገለጹት የመኢአድ ስራ አስፈጻሚ በክልሉ ከሚኖሩት የተለያዩ ብሔረሰቦች ተለይቶ የአማራ ብሔረሰብ እንዲፈናቀልና እንዲሰቃይ የሚደረገው በማዕከላዊ መንግስት ትዕዛዝ እንደሆነም አመልክተዋል። መኢአድ ያሰራጨውን መግለጫ ተከትሎ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ማብራሪያ የሰጡት አቶ ሃይሉ ሻወል፣ ድርጊቱ በበታች … [Read more...] about “ማፈናቀሉ የሚካሄደው በመንግሥት ትዕዛዝ ነው፤ ወደ ክስ እናመራለን”