ሰሞኑንን ይፋ የሆነውን የአዲስ የሚኒስትሮችና የ”ከፍተኛ” ባለሥልጣናት ሹመት ተከትሎ ከውስጥም ከውጭም የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው። ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ሹመቱን ይፋ ከማድረጋቸው በፊት ሪፖርተር “ምንጮቼ ነገሩኝ” በማለት አቶ በረከት ስምዖንን የደህንነት አማካሪ ሚኒስትር የሚያደርጋቸው አዲስ ሹመት እንደሚሰጣቸው ዘግቦ ነበር። ይህንኑ ዜና ተከትሎ “ኢትዮጵያ በኦፊሴል በኤርትራ መመራት ጀመረች” በማለት ቅድመ አስተያየት የሰነዘሩ ጥቂት አልነበሩም።
ሚዲያውን መዳፋቸው ስር አኑረው የቆዩት አቶ በረከት ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትርነታቸው ተነስተው የጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም የፖሊሲና ጥናት አማካሪ ሚኒስትር ተደርገው መሾማቸው “በረከት አደጉ ወይስ ተገፉ?” የሚል ጥያቄ አስነስቷል።
ከመለስ ህልፈት በኋላ ኢህአዴግ ውስጥ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ያሳዩት አቶ በረከት ከድርጅታቸው ይሁንታ ውጪ “አቶ ሃይለማርያም ጠ/ሚኒስትር ይሆናሉ። የሚቀረው የስርዓት ማሟላት ጉዳይ ነው” ማለታቸው የህወሃትና የኦህዴድ ሰዎችን ክፉኛ አበሳጭቶ እንደነበር የሚያስታውሱ አስተያየት ሰጪዎች “አቶ በረከት አማካሪ ሆነው ወደ ጠ/ሚኒስትር ቢሮ መዛወራቸው ከኢህአዴግ ባህሪ አንጻር የመገፋት ወይም ስራ አልባ የማድረግና ከቀጥተኛ ተሳታፊነት የመታቀብ ያህል ነው” ባይ ናቸው።
“በዜግነታቸው ብቻ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የመሳተፍ መብት የሌላቸው አቶ በረከት ሲፈነጩበት ከነበረው የኢህአዴግ ሚዲያ መሰናበታቸው በራሱ በርካታ ጉዳዮችን የሚያመላክት ነው” የሚሉት ምንጮች “የፖሊሲና የጥናት ጉዳዮች ከፍተኛ የቀለም እውቀትና ልምድ የሚጠይቅ ሃላፊነት ነው። አቶ በረከትም ሆነ አቶ ኩማ ለዚህ አይመጥኑም። ውሳኔው ማቀዝቀዣ ውስጥ የማስገባት ያህል ነው” ሲሉ አቶ በረከት ያላቸው የአደባባይ ሚና ማክተሙን ያወሳሉ።
በሌላ በኩል የተለየ አስተያየት የሚሰነዝሩ ክፍሎች እንደሚሉት “አቶ በረከት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስራ እለት እለት ሥርስራቸው ሆነው እንዲሰሩ የተሰጣቸው ስልጣን ነው። ይህ የሚያሳየው እሳቸው አሁንም ፈላጭ ቆራጭ ሆነው መቀጠላቸውን ነው” በማለት የሃሳብ ልዩነታቸውን ያስቀምጣሉ።
አቶ በረከትና አቶ ሃይለማርያም የቀረበ ግንኙነት እንደነበራቸው፣ አቶ መለስ በህይወት እያሉም ቢሆን ሶስቱ እንደማይለያዩ ያመለከቱት ክፍሎች፣ የህወሃት የበላይ አመራርና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር መሪ የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን አዲስ በሚቋቋመው የደህንነት ሚኒስትር ውስጥ የሚሰይሙት ሚኒስትር፤ ሪፖርትር እንዳለው አቶ በረከት ካልሆኑና የህወሃት ሰው ከተሾመ “በትክክልም አቶ በረከት ወደ ማቀዝቀዣ ክፍል ገብተዋል ማለት ነው” ሲሉ ሁለት ጫፍ ያለው አስተያየት ሰንዝረዋል።
አቶ ኩማ አሁን ባለው ኦህዴድ ውስጥ አንጋፋና ታማኝ፣ በቅጣት ከሶስት ዓመት ማዕቀብ በኋላ ወደ መንግስት ሃላፊነት የተመለሱ፣ ኦህዴድን ማጥራት ሲፈለግ በትር የሚጨብጡ፣ በመሆናቸው ከንቲባነቱን ሲለቁ እንዳያፈገፍጉ አዲሱ ሃላፊነት እንደተሰጣቸው አብዛኞች ይስማማሉ። አቶ ኩማ ካላቸው ልምድና ዕውቀት አንጻር አቶ ሃይለማርያምን በፖሊሲ ጉዳዮችና በጥናት ረገድ ለማማከር የሚችሉ ሰው እንዳልሆኑ ስምምነት መኖሩን የሚጠቁሙ ጥቂት አይደሉም። ከዚህ አንጻር በዓለምቀፋዊ ዋና ከተማነት ከምትታወቀው አዲስአበባ ከንቲባነት ወደ አማካሪነት ኩማ ደመቅሳ “ሲሾሙ” እንደ ሥልጣን ሽረት ከተቆጠረ፤ የበረከት ስምዖን በተመሳሳይ መልኩ መታየት የማይችልበት ምክንያት ሊኖር እንደማይችል የሚከራከሩ አሉ፡፡ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሥልጣን በምክትል ጠ/ሚ/ርነት ሲያድግና ኢህአዴግ በምርጫ የመሸነፍ ቅንጣት ችግር ሳይኖረው ኩማን ከከንቲባነት ሥልጣን ማንሳቱ የብቃት ማነስና አለመፈለግ እንደሆነ ተጨማሪ አስተያየቶች አሉ፡፡
ለሶስትና አራት ዓመት ህጻን “ከክልላችን ስለተባረርክ የትምህርት ገበታህ ላይ መቀመጥ አትችልም” የሚል ደብዳቤ የሚጽፉና በሙስና በከፍተኛ ደረጃ የሚታሙት የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ሽፈራው ሽጉጤ ወደ ትምህርት ሚኒስትርነት የተሻገሩት አቶ ሃይለማርያም ደቡብ ክልል ላይ ያለውን ሰንሰለት ለመበጣጠስ እንዲያመቻቸው እንደሆነ ይገመታል። ሃዋሳ ነዋሪ የሆኑ ለጎልጉል እንደገለጹት አቶ ሽፈራው የዘረጉት ድር መበጣጠስ እንዳለበት የታመነው አሁን አይደለም። በሚሊዮን የሚቆጠር የክልል በጀት እንደፈለጉ ከሚያስኬዱበትና ያለገደብ ሥልጣናቸውን ከሚያከናውኑበት የክልል ፕሬዚዳንትነት ወደ ሚኒስትርነት “መሾም”፤ የሥልጣን ሽረት ተብሎ ከመጠራት ውጪ ምንም ሊባል እንደማይችል በሽፈራው ሽጉጤ አመራር የተማረሩ ብቻ ሳይሆኑ ደጋፊዎቻቸውም ያመኑበት ጉዳይ ነው፡፡
የትምህርት ሚኒስቴርን መምራት ያቃታቸው አቶ ደመቀ በስራ ብዛት ሰበብ የምክትል ጠ/ሚኒስትርነታቸውን ወንበር ብቻ እንዲይዙ መደረጉን ያመለከቱት ክፍሎች “አቶ ሽፈራው በሹመቱ ደስተኛ እንዳልሆኑ ከሚቀርቧቸው ሰምተናል። ሃዋሳ በክልሉ መስተዳድር ውስጥ እሳቸው የሰገሰጓቸውም ስጋት ላይ ናቸው” ብለዋል፡፡ በቀጣይ ሃይለማርያም “ታማኛቸውን” በመሾም (“በማስመረጥ”) እውነተኛ የደኢህዴን ሊቀመንበርነታቸውን እንደሚያረጋግጡም ይጠበቃል፡፡
ደመቀ መኮንን በምክትል ጠ/ሚኒስትርነታቸው ብቻ እንዲቀጥሉ የተደረጉት ምን አልባትም አዲስ በሚቋቋመው የደህንነት ሚኒስቴር ውስጥ በአማራ ክልል ከነበራቸው “ልምድ” አኳያ ለኮታ ማሟያ ታስበው ነው በሚል ካድሬው በስፋት እንደሚያወራ እየተሰማ ነው። አቶ ደመቀ በአማራ ክልል የደህንነቱ መሪ እንደነበሩና በዚሁ በተግባራቸው “የተመሰገኑ ታማኝ” ለመሆን መብቃታቸውን የሚቀርቧቸው ይናገራሉ።
ወደ አዲስ አበባ የተዛወሩት ልጆቻቸውን በትምህርት ቤት እየሰደቧቸው በመቸገራቸው እንደነበር የሚያስታውሱት እኒህ ክፍሎች “አቶ ደመቀ የአማራው ክልል መሬት ተላልፎ ሲሰጥ አቶ አያሌው ጎበዜ አልፈርምም ሲሉ፣ እሳቸው መፈረማቸው ይፋ ከሆነ በኋላ ‘ከሃዲ’ የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል። ህጻናት ልጆቻቸውም ትምህርት ቤት መማር ያልቻሉት ለአባታቸው በተሰጠ ስም ትምህርት ቤት ውስጥ ጓደኞቻቸው ስለሚያበሽቋቸው ነው” በማለት አቶ ደመቀ ቀደም ሲል ጀምሮ ከደህንነቱ ጋር ያላቸው የሥራ ግንኙነት ታማኝ እንዳሰኛቸው አስታውቀዋል። ከዚሁ ውለታቸውና ልምዳቸው አንጻር በደህንነት መ/ቤት ውስጥ ይካተታሉ የሚል ግምት እንዳላቸው ተናግረዋል።
ሰኔ 27 ቀን ለተሰየመው ፓርላማ በቀረበው ሹመት መነጋገሪያ ከሆኑት መካካል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው፣ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በተለያዩ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ መድረኮች ችግር እንደተጣባው የተመሰከረለትን የትምህርት ሚኒስቴርን እንዲመሩ መመደባቸው፣ አንዲሁም የአቶ ደመቀ በ”ስልጣን በዛባቸው” ሰበብ የሚኒስትርነት ቦታቸውን መነጠቃቸው በቅድሚያ የሚጠቀሱ ናቸው።
የወርቅነህ ገበየሁ “ነገዎ” ሹመት
የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስትር ስለመደረጋቸው ከሚቀርቡት ምክንያቶች መካከል ቀደም ሲል ለረዥም ዓመታት ከደህንነቱና ከሽብር መከላለከል ግብረ ሃይል ጋር የነበራቸው ቁርኝት ከፍተኛ መሆኑ በግንባር ቀደም ይገለጻል። ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ እንደሚሉት ኢህአዴግ የትራንስፖርቱን ዘርፍ በቅርብ መቆጣጠር ይፈልጋል።
በምርጫ 97 ወቅት ለታየው ህዝባዊ መነቃቃት የትራንስፖርቱ ዘርፍ፣ በተለይም የታክሲና የግል ማመላለሻዎች የነበራቸው ሚና ከፍተኛ እንደነበር አስተያየት ሰጪዎቹ ያስታውሳሉ። ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች እስከወዲያኛው እንዳይታሰቡ ለማድረግ ዘርፉን ከደህንነቱ ጋር በቅርብ ማጠላለፍ፣ ኢህአዴግ በከፍተኛ ደረጃ እየገነባሁ ነው የሚላቸውን መንገዶች፣ የስልክና የብሮድ ባንድ መስመሮች፣ የባቡር ትራንስፖርት በቅርብ ለመቆጣጠርና የቁጥጥሩ ሰንሰለት ውስጥ ለማስገባት አቶ ወርቅነህ ሁነኛ ሰው ሆነው መገኘታቸውን እነዚሁ ክፍሎች ይናገራሉ።
አዲሱ ቴሌን ጨምሮ የትራንስፖርት ዘርፉን ከደህንነቱ መዋቅር ጋር በቀላሉ ለማያያዝ ልምዳቸውና የመረቡ አባል ሆነው መቆየታቸው የትራንስፖርት ሚኒስትር ያደረጋቸው አቶ ወርቅነህ፣ የጄኔራልነት ማዕረጋቸው ከሳቸው ጋር ይቆይ ወይም ይነሳ የተገለጸ ነገር እንደሌለ የጠቆሙት ክፍሎች፣ በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ የህወሃት አመራሮች አቶ ወርቅነህን በታማኝነት መድበው የተቀበሏቸው ሰው ስለመሆናቸው ጥርጥር የላቸውም።
አቶ ወርቅነህ ታማኝ ስለመሆናቸው፣ በዚሁ ታማኝነታቸው ስልጣናቸውን ሳይጠቀሙ በፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተርነት ለረዥም ጊዜ መቆታቸውን የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው አቶ ወርቅነህ በአገር አቀፍ ደረጃ ከሰባት ሚኒስትር መስሪያቤቶች ተውጣጥቶ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመራው የ”ደህንነት ኮር” ውስጥ አባል እንደነበሩ ይናገራሉ። ይህንን ኮር በአዲስ እየተዋቀረ ስለሆነ አቶ ወርቅነህ ወደ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት የተዛወሩት ከደህንነቱ የኮር መዋቅር ውስጥ እንዲወጡ ስለተፈለገ መሆኑን ይገልጻሉ።
ዝርዝር ጉዳዩን ለማብራራት እንደሚቸገሩ የሚናገሩት እነዚህ ክፍሎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ደረጃ እንዲዋቀር አዋጅ የታወጀለት የደህንነት መ/ቤት ሚኒስትርና የበላይ ሃላፊዎች ይፋ ሲሆኑ ነገሮች ይበልጥ እንደሚጠሩ ተናግረዋል። በኢህአዴግ ውስጥ ተፈጥሮ በነበረውና አሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ እንዳልጠራ የሚነገርለትን ልዩነት ተከትሎ የተሸናፊውን ወገኖች የማጥራት ስራ በተለያዩ ስልቶች እንደሚሰሩ የጠቆሙት እነዚህ ክፍሎች፣ የደህንነት ሚኒስትር ሲቋቋም የሚሾሙት ባለስልጣን ከቀድሞዎቹ መካከል እንደማይሆን ምልክት ማየታቸውን ጨምረው ገልጸዋል።
የኢህአዴግ ንብረትና የንግድ ተቋም የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ ከዚህ የሚከተለውን የአዲስ ሹመትና ተሿሚዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሃሙስ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሰላኝ የቀረቡ እጩዎችን ሹመት በአንድ ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።በዚህም መሰረት
አቶ ደመቀ መኮንን – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ወላሳ – የትምህርት ሚኒስትር
አቶ ሬድዋን ሁሴን ራህመቶ – የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር
አቶ አህመድ አብተው አስፋው – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ነገዎ – የትራንስፖርት ሚኒስትር
ወይዘሮ ሮማን ገብረስላሴ መሸሻ – በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር
ወይዘሮ ደሚቱ ሃንቢሳ ቦንሳ – የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
አቶ ጌታቸው አምባዬ በለው – የፍትህ ሚኒስትር
አቶ በከር ሻሌ ዱሌ – የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር
አቶ በለጠ ታፈረ ደስታ – የአካባቢ ጥበቃና የደን ሚኒስትር
አቶ መኮንን ማንያዘዋል እንደሻው – የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር
ሆነው የተሾሙ ሲሆን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ አማካኝነት ቃለ መሃላቸውን ፈጽመዋል።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
koster says
hodam Demeke Mekonnen has no grandfather why is it not mentioned?
Rule of Law says
he’s a muslim
koster says
Demeke Mekonnen Hassen
benjo says
I wouid like to say something about getachewu ambay he is appointed a justice minster , he was a justice minster in amhara region he is a dictator and also a criminal once upon a time when he was drive the office car he had an accident and kill somebody but as that time he call his driver the driver took the accident as he did after some day the driver become innocent and released from prison the crime was comitted by him not by a driver so how could be the crimnal became a justice minster.He is one of the corrupted one.
በለው ! says
**በደብረጺዮን ገብረሚካኤል እና በበረከት ስምኦን የሚዘወረው የኅበረት አመራር… በስብሃት ነጋ ቃል አቀባይነት! የህወአት ቢሮ ጠባቂ ሬድዋን መሀመድ! የህወአት አፈቀላጤ ዲና ሙፍቲ! የብሔር ብሄረሰቦች ተጠሪ በጠ/ሚ ማዕረግ ኀይለመልስ ከፋኝ !በህወአት፣ በወልቃይት ጠገዴ፣በሱዳን ልዩ ተጠሪ አዜብ ጎላ መስፍን፣ በሱዳንና ኬንያ ጠረፍ ጠባቂ አቶ ሼፈራሁ ሽጉጤ፣በጉራጌና ጨቦ መካከለኛ ደረጃ ተወካይ ሽመልስ ከማል!በወሎና አገው በም/ል ጠ/ሚኒ ማዕረግ የትምህርት ሥርዓትና ታሪክ አጥፊ ድንብሹ አቶ ደመቀ መኮንን ከዚያም እንደአስፈላጊነቱ የመከላከያ ሚ/ኒ የውሃና መብራትን የአዲስ አባባ ከንቲባ ስለ ኦሎፐምፒክ ረጅም ሩጫ ሲቀባጥር መስማት የተለመደ ሆኗል! በለው! ያ የፈረደበት ራዕየይና ለጋሲ (ከቡድን) አፈትልኮ በኅብረት እየተፈተለ የቆማጣ ልቃቂት ሆኗል በለው!።***
፩) *”“በረከት አደጉ ወይስ ተገፉ?
==ወቅቱ የሽፍፍን መሆኑ ያበቃል! የደቦ አመራር ችግር አለው!፤ የሻቢያ የበላይነትበኢትኦጳያ ፖለቲካና ሥልጣን መያዝ ለአካባቢው ሠላምና ሠጥቶ በመቀበል ለ፳፪ዓመቱ የማጭበርበርና የሀገር ማራቆት ሥርዓት፣ እጅግ ጠቃሚ ሆኖ ሠርቷል።አዲሱን ትውልድ አምክኗል፣ ታሪክ አውድሟል፣የራሱን ዓላማ፣ ራዕይና ለጋሲ አልብሶ የነበረውን ገፎ አስበርዶታል። አዲሱ ትውልድ ወኔው ጠፍቷል፣ማንነቱን ዘንግቷል፣ ሞራሉ ላሽቋል፣አሁን ዘንግተውት የነበረ አይደርስም ያሉት ድንበር ዘለል ጥያቄ ሲነሳ ሀገሪቱ ሉዓላዊ እንዳልሆነች ይህ የሕገ መንገስት ጽሑፍ እንደማያድናት ቤቱ ባዶ እንደሆነ ተረዱት ስለዚህም…በደቡብ ሲጨቆኑ የኖሩት ተረስተው የነበረው ማንነታቸው ያልተረጋገጠ አሁን የተረገጠ የሚለው ቱልቱላ የትም አያደርስም! እኔ ኢትዮጵያዊ የሚል ሳይሆን ክልሌ ፈርስት ትልቅ ችግርን ወለደ… ማጣፊያው ሲያጥር የሀገሪቱ የበላይ አካል ማወቅና ማሳወቅ ይጠቅማል።አለበለዚያ “ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ላይ ለመኖር የተስማሙ ብሔሮች የሚለው የግብጥ ፍሬ አላስተማመነም(ይጎመዝዛል) ። ስለዚህ አቶ በረከት ስምአን አላደጉምም ! አልተገፉምም ! ግን ተገለጡ በለው!! ሊያጠቁ ሲሮጡ ንፋስ እንዳይበዛባቸው አንድ የኦረሞ ተከላካይና አልባሽ ተጨመረላቸው። ( አሁን ‘የቡድንና’ የኅብረት(የደቦ) አመራርን…ልብ ብላችሁ አስተውሉ።
፪) *አቶ ኩማ ደመቅሳ አሁን ባለው ኦህዴድ ውስጥ አንጋፋና ታማኝ፣ በቅጣት ከሶስት ዓመት ማዕቀብ በኋላ ወደ መንግስት ሃላፊነት ኦህዴድን ማጥራት ሲፈለግ በትር የሚጨብጡና የሚጨበጡ፣ በመሆናቸው ከንቲባነቱን ሲለቁ እንዳያፈገፍጉ አዲሱ ሃላፊነት እንደተሰጣቸው አብዛኞች ይስማማሉ።
==”እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው ለማለት አደለም!” ኅብረት አመራር አስፈላጊነቱ እዚህ ላይ ነው፡፤ ከንባታን አስቀምጠህ ኤርትራን ማቆም! ትግራይን አሹረህ ኦሮሞን ማዳወር! አማራን ዘውረህ ሱማሌን መፍተል! የብሔር ብሄረሰቦች… ልዩነታችን ድምቀታችን ይሉሃል ይህ ነው በለው!ህዝቦች ስትላቸው ህንድ ዓረብ ቻይና ቱርክ ይሆናል።ገና የፋውንዴሽኑ ወታቦ እውን ሆኖ ታማኝ ካድሬ እስኪፈለፈል…በቻይና የሚሰለጥኑት አስኪያድጉ ታመኝ አገልጋይን መንከባከብ የሚለው መርሆና ለጥፋቱም የከንባታው አማካሪ ኦሮሞና ኤርትራ ነው ለሚለው ማሟያ ኩማ ጥሩ ቦታ ይዘዋል ግን ይህ ቦታ የወታደር አማካሪ ለምን አስፈለገ ኢትጵያም ግብጥ አማራት ወይስ የደብረሲናና የደብረብርሃን ቁንዲፍቲ?
፫) *በከፍተኛ ደረጃ የሚታሙት የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ሽፈራው ሽጉጤ ወደ ትምህርት ሚኒስትርነት የተሻገሩት አቶ ሃይለማርያም ደቡብ ክልል ላይ ያለውን ሰንሰለት ለመበጣጠስ እንዲያመቻቸው እንደሆነ ይገመታል።
== ይህ በእርግጥ አቶ ኅያለማርያም “ኪራይ ሰብሳቢዎች፣ ጸረ-ሕዝቦች፣ የፈፀሙት ወንጀል ነው ያሉት የአማርኛውን ተናጋሪ ህዝብ ማፈናቀል ጉዳይ ባይቃወሙም ማፈናቀሉ በስልትና በጥበብ የተሞላ መሆን እንደነበረበት ያስተምራሉ… ሽፈራሁ ሽጉጤ አቶ ሓይላመርያም ጉያ ተሸጎጡ (ሀ) እንዲከላከሏቸው (ለ) እንዲምሯቸው (ሐ) እንዲያስተምሯቸው (መ) መልሱ አልተሰጠም።
***መልሱ እንዳያመልጧቸው !? (ሀ) የተወከሉበትን ሥራ በአግባቡ አለመፈፀም ( ለ)የደበቋቸውን ፀረ-ሕዝቦች ለመግለጥ (ሐ) የደበቁትን የኪራይ ሂሳብ ሀገር ውስጥ ለማስቀረት (መ) በገንዘብም በብሔርም ሲያደሯጇቸው የነበሩትን እንደ ጁነዲን ሳዶ… ሰዶ ማሳደድን ለማስቀረት (ሠ) ሠፊው ሕዝብ ወዷቸዋል? አልወደዷቸውም? በትምህርት ተቛማት ብጥብጥ፣ ሰልፍ፣ ተቃውሞ፣ ይነሳል ወይስ ይተኛል? ከሥራ መባረሪያ ወይም ቃሊቲን ለመጎብኛ ቀረቡ? ?
፬)*አቶ ደመቀ መኮንን ወደ አዲስ አበባ የተዛወሩት ልጆቻቸውን በትምህርት ቤት እየሰደቧቸው በመቸገራቸው እንደነበር ‘ከሃዲ’ የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል። ህጻናት ልጆቻቸውም ትምህርት ቤት መማር ያልቻሉት ለአባታቸው በተሰጠ ስም ትምህርት ቤት ውስጥ ጓደኞቻቸው ስለሚያበሽቋቸው ነው” ትውልድ ተሻጋሪ ሥርዓት የዱላ ቅብብል ብቻ ሳይሆን ስድብ ቅብብልም ነው በለው!
==*ለመሆኑ የትምህርት ውርዓቱ ኮብል እስቶን ላይ ሲደርስ የእድገታችን ውጤት ሲሆን አቶ ሽፈራሁ ሽጉጤ ወይ የበሃ ድንጋይ ወይ ጥቁር ድንጋይ ያስፈልጣሉ። እሪ በይ ቀበና!
፭) *የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስትር ስለመደረጋቸው …ያልተጀመረው የባቡር ትራንስፖርት ጥንቃቄ ጥበቃ ይፈልጋል። ከክልል ፕሬዘዳንት የቀበሌ ሊቀመንበር… ከፖሊስ የአውቶቡስ የቀጠና ስምሪት ኅላፊ ይቺ ናት ራዕይ! ‘ ኮር ‘ትባልና ትኮረኮራለህ ‘ክላስተር’ ስትሆን ግን መጥፊያህ ቦንብ እግርህ ላይ ተጠመደልህ ማለት ነው።የጄነራልነቱንማዕረግ ትተህ የዕለት እንጀራህን ያዝ በለው!
****በኢትዮጵያ የኤርትራ የውሰጥ መሪ ሹም ዶ/ር ገብረጺዮን ገብረሚካዔል በምክትላቸው በኢፌዴሪ በጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የራዕይ አሰፈጻሚና የለጋሲው አስቀጣይ በአቶ ሃይለማርያም ደሰላኝ አማካኝነት እንዲያደርሱ የተላከውን የዕጩዎችን ሹመት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአንድ ድምፀ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል!!። እልል… ልል በለው!! አንድንሳቀቅ ወይስ እንድንስቅ? ?ሸዋ ተጠየቅ!በቸር ይግጠመን ከሀገረ ከናዳ!
አለም says
ጎልጉል፣ የሚንስትሮቹን ብቃት ለምን አልገለጻችሁም። ሽፈራው ሽጉጤ የትምህርት ሚንስትር ሆኑ ማለት ብቻውን ምን ይጠቅማል? የትምህርት ደረጃቸው? የትና መቸ እንዳጠናቀቁ? ዜናችሁን የሚከታተል ይህን የመሰለ መረጃ ይኖረዋል ማለት አይደለም እኮ።
Mesfin says
How on earth Shiferaw Shigutie, became a Minster of the Ministry of Education and Fine Arts? This man should have been demoted rather than being promoted. He should have been brought to justice, if there is justice in the country at all, for his crime committed against the Amhara people in Gura Ferda. This shows how Haile Mariam Desalegn hates the Amhara people and supports what the racist Shiferaw has done. In fact, it is obvious, if HD was not a narrow nationalist and anti Amhara, he would have not reached where he reached now.
The other major point is also his educational background. Is qualified enough to run Ministry of Education and Fine Arts? Does he have the experience to run this big institution? My heart is bleeding when I release how my country, Ethiopia, is going down from time to time.
May the Almighty God save mother Ethiopia and the Ethiopians.
andnet berhane says
የወያነ ፈሊጥ መተካካት እሚል ሃረግ በመበጀት አዲሱ የሕዝቡንና የደጓሚዎችን ለመሳብ የሕዝብን ልቦና ለመስረቅ ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለሙሉ ስልጣን ለማስመሰል የበረከት ውሸት በመሟጠጡ ረድዋን ሁሴን በአዲስ ለመተካት አዲስ የውሸት ንድፍ በማዘጋጀት ከኢኃዴግ ጽሕፈት ቤት ለማራቅ ሲሆን፡ ኩማ ደመቅሳ፡ ወርቅነህ ገበየሁ፡ ሽፈራው ሸንቁጤ፡ የስራአቱ ዋነና አቀንቃኞች በመሆን ያገለገሉ በሰብብ ከነበሩበ የስልጣን እርካን በማስለወጥ በተጀመረው የሙስና ማጋለጥ ተጠያቂዎች በመሆናቸው ውደ ቀረበ ማለት ለመጥፋት የማያመች ቁጥጥር ለማድረግ የታቀደ ይመስኛል
በርከት ከነበረበት ሹመት የበለጠ ከሩቅ ሆኖ ከመቆጣጠር ካዚያው ከቤተመንግስት የኃይለማርያምን እንቅስቃሴ ለመቆጣተር ሆን ብሎ በወያኔዎች የታለመ ሴራ በመሆኑ አሁንም በረከት ተጫዋች ቁልፍነቱ የበለጠ ሆኖ ይሰማኛል ነውም፡ ደመቀ መኮንን ሻጭና የራሱ ኃሳብ የሌለው ያሉትን የሚያስፈጽም በመሆኑ እንድ ተላላኪና ካማራ ም/ጠቅላይ አለ እንዲባል የተቀመጠ በመሆኑ ብዙም አያስደንቅም። ወያነ ሁልግዜ የተለያየ ስልት ለማታለል የሚያደርገው ጥረት ሊያስደንቅና ሊያነጋግር አይችልም
Shere says
Yaw yaw new.glesebawi lewt…teb yemayl
oliyad says
gulicha bikeyayer………….ale yagere sew