ሰማያዊ ፓርቲ ከአንድ ወር በፊት በጠራውና ባለፈው እሑድ የተደረገውን ሰላማዊ ሠልፍ መንግሥት ሲያወግዝ፣ ሰላማዊ ፓርቲ ደግሞ የመንግሥት ውግዘት በተቃውሞ የተነሳውን ሕዝብ ከማሸማቀቅ ባለፈ የሕግ ድጋፍ እንደሌለው እየገለጸ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዝያ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. ባስተላለፈው የሰላማዊ ሠልፍ ጥሪ፣ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጐች ወጥተው ተሰተውለዋል፡፡ አራት ኪሎ ቀበና አካባቢ ከሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ ጽሕፈት ቤት መነሻውን ያደረገው ሰላማዊ ሠልፉ በአራት ኪሎ፣ በፒያሳና በቸርችል ጐዳና አድርጐ ኢትዮ ኩባ የወዳጅነት መናፈሻ ደርሶ፣ እስከ ቀኑ ስምንት ሰዓት ድረስ የተለያዩ መፈክሮችንና ተቃውሞዎችን በመንግሥት፣ በመንግሥት መገናኛ ብዙኅንና በአንዳንድ የግል መገናኛ ብዙኅን ላይ አሰምተዋል፡፡ ሠልፈኞቹ ለመንግሥት ካቀረቧቸው ጥያቄዎችና መፈክሮች … [Read more...] about በሰላማዊ ሠልፉ ሰማያዊ ፓርቲና መንግሥት እየተወዛገቡ ነው
News
ዜና
ምርመራው ወደ አቃብያነህጉ ተዛወረ!
* “አዲስ ነገር የለም” ጸረ ሙስና ኮሚሽን በተለያዩ ከፍተኛ ወንጀሎች በተጠረጠሩ ሰዎች ላይ የተከፈቱ ክሶችን በማፈንና በመመሪያ ፍትህ በማዛባትና በማቋረጥ ወንጀል የተጠረጠሩ አቃቤያነህግ ላይ ምርመራ መጀመሩ ከፍተኛ ድንጋጤ መፍጠሩ ተሰማ። በተለይም ከወንጀል ጋር ቁርኝት እንዳላቸው በህዝብ የሚታወቁ ክፍሎች ክፉኛ መደናገጣቸው ተሰምቷል። በሙስና የተጠረጠሩት የጉምሩክ ባለስልጣናት፣ ተባባሪ ነጋዴዎችና ደላሎች መታሰራቸውን ተከትሎ ከተፈጠረው ስሜት በላይ ከፍተኛ መደናገጥ የፈጠረው ዜና አዲስ አድማስ ጋዜጣ ቅዳሜ እለት ለንባብ ያበቃው ዜና ነው። በቅርቡ ከሃላፊነታቸው የተነሱት የፍትህ ሚኒስትር አቶ ብርሀነ ሃይሉና ከአስር በላይ አቃብያነህግ በተለያዩ ጉዳዮች የተመሰረቱ ክሶች እንዲቋረጡ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው መመርመራቸው በትክክል ከተሰራበት ዋንኛ የሚባሉትን የሙስና ወንጀል … [Read more...] about ምርመራው ወደ አቃብያነህጉ ተዛወረ!
ከእሁድ እስከ እሁድ
ከእስረኞች ጠበቆች ጋር የተደረገው ውይይት ታፈነ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ከአሜሪካ የህግ ባለሙያዎች ማህበር ጋር በመሆን በኢትዮጵያ እስር ቤት ለሚገኙ የህሊናና የፖለቲካ አስረኞች ጥብቅና ከቆሙ የህግ ባለሙያዎች ጋር ለመነጋገር ያደረገው ሙከራ ታፈነ። የጋራ ንቅናቄው ለጎልጉል እንዳስታወቀው ዓርብ ሰባት ከሚሆኑ ጠበቆች ጋር ለመያየትና መረጃ ለመለዋወጥ መስመር ተዘርግቶ ነበር። አቶ ኦባንግ ሜቶና የጋራ ንቅናቄው የሚዲያ ዴስክ፣ ከአሜሪካ የጠበቆች ማህበር አራት፣ ከአዲስ አበባ ሰባት ጠበቆች በመሆን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 11 ሰዓት ላይ የስካይፕ ውይይት ለመጀመር ተዘጋጅተው ነበር። የጋራ ንቅናቄው እንዳስታወቀው ውይይቱ ሲጀመር ድምጽ መስማት አልተቻለም። በዚሁ ሳቢያ ውይይቱ መቋረጡን ያስታወቀው አኢጋን ከአሜሪካ የጠበቆች ማህበር ጋር በመነጋገር ሰኞ ቀን … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
የአሜሪካ የህግ ባለሙያዎችና አኢጋን በኅብረት ስራ ጀመሩ!
በኢትዮጵያ በግፍ የታሰሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን በተመለከተ የአሜሪካን የህግ ባለሙያዎች ማህበር (ABA – American Bar Association) ሙሉ በሙሉ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ስራ አርብ እንደሚጀምር ተገለጸ። አዲስ አበባ ካሉ የፖለቲካና የሙስሊም ወገን እስረኞች ጠበቆች ጋር የመጀመሪያ ስብሰባ አርብ ግንቦት 23፤2005ዓም ያደርጋሉ። አቶ ኦባንግ ሜቶ የተረሱ እስረኞች ጉዳይም እንደሚካተት ጠቅሰው በፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ለታሰሩ ዜጎች ጥብቅና የቆሙ ካሉ የአዲሲቷን ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ በቀጥታ እንዲገናኙ ጥሪ አቅርበዋል። (ABA) በሚል ስያሜ የሚታወቀውና ከተቋቋመ 135ዓመታትን ያስቆጠረው የአሜሪካ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ከ400 ሺህ በላይ የህግ ባለሙያ አባላት አሉት። ይህ በአሜሪካ ትልቅ የተባለ ማህበር በግፍ ለሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች … [Read more...] about የአሜሪካ የህግ ባለሙያዎችና አኢጋን በኅብረት ስራ ጀመሩ!
የኢህአዴግና የሻዕቢያ ድርድር ተበጠሰ
ኳታር በተናጠል የጀመረችው ኢትዮጵያንና ኤርትራን የማሸማገል ሂደት መበጠሱ ተሰምቷል። ከሽምግልናው ዙሪያ የግብጽ ሚና ስለመኖሩ አመላካች ጉዳዮች አሉ እየተባለ ነው። በድርድሩ ኢህአዴግ በዋናነት እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠው የትግራይ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደሚት/ ጉዳይ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል። አቶ መለስ የኢትዮጵያን ወደብ እንደተራ ጉዳይ አሳልፈው በመስጠት ኤርትራን እንደ አገር እውቅና በሰጡበት ወቅት ድጋፍ ለማሰማት ቀዳሚ የነረችው ኳታር ከበረሃው ትግል ጀምሮ የሻዕቢያ ወዳጅ አገር እንደሆነች ይታወቃል። ከዚሁ የከረመ ወዳጅነት በመነሳት ኳታር በ2008 ከኢህአዴግ ጋር ተፈጥሮ የነበረውን የጸብ ግድግዳ አፍርሳ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው በዋናነት ሁለቱን አገሮች መልሶ ለማስታረቅ በተያዘ እቅድ ስለመሆኑ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ይናገራሉ። በተለይም አሁን ያለው የኤርትራ … [Read more...] about የኢህአዴግና የሻዕቢያ ድርድር ተበጠሰ
የደህንነት ሹሙ ስዊድን ይመጣሉ
በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል NISS (National Intelligence and Security Service) የብሔራዊ ደህንነትና የደኅንነት አገልግሎት ሁለተኛ ሰው የሆኑት አቶ ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ ስዊድን እንደሚመጡ ተሰማ። በስካንዲኔቪያ አገራትና በድፍን አውሮፓ በሚኖረው ዲያስፖራ ላይ የሚያተኩር "የግል" መሰል የሬዲዮ ስርጭት ለመጀመር መታሰቡም ተሰምቷል። የጎልጉል የመረጃ ምንጮች እንዳስታወቁት አቶ ኢሳያስ ስዊድን ይመጣሉ የተባለው በመጪው የሰኔ ወር ነው። የኤርትራዊ ዜግነት ያላቸውና አቶ መለስ በእጅጉ ይተማመኑባቸው እንደነበር የሚነገርላቸው አቶ ኢሳያስ ስዊድን ከደረሱ በኋላ ሊያከናውኑ ስላሰቡት ተግባር ዝርዝር ለመረዳት ጊዜው ገና እንደሆነ ምንጮቹ አመልክተዋል። "ሆኖም ግን" ይላሉ ምንጮቹ፣ " ሆኖም ግን አቶ ኢሳያስ ድርጅታቸው ኢህአዴግ በስካንዲኔቪያን አገሮች በተደጋጋሚ … [Read more...] about የደህንነት ሹሙ ስዊድን ይመጣሉ
ኦባንግ ለኬሪ የጥሪ ደብዳቤ ላኩ!
በቅርቡ በሚከበረው 50ኛው ዓመት የአፍሪካ ኅብረት ክብረበዓል ላይ በተጋባዥነት ለሚገኙት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ በፋክስ የሚደርስ ቀጥታ ደብዳቤ ላኩ፡፡ በደብዳቤው ላይ አቶ ኦባንግ ሰሞኑን በአፍሪካ ህብረት አካባቢ ለተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ድርጅታቸው ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡ በበርካታ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ለሚ/ር ኬሪ በደብዳቤያቸው ላይ ማሳሰቢያ የሰጡት ኦባንግ የአፍሪካ ኅብረት ሲቋቋም ቅኝ አገዛዝን መታገል፣ የህግ የበላይነትን ማስከበርና የዜጎችን መብት ማስጠበቅ ዋንኛ ዓላማው የነበረ ቢሆንም የያኔዎቹ መስራች መሪዎች አሁን በህይወት ቢኖሩና የዛሬዪቱን አፍሪካ ቢመለከቱ ምን ይሉ ይሆን በማለት ጠይቀዋል፡፡ በመላ አፍሪካ በዘመናችን ያለውን የሰብዓዊ መብት መጣስ፣ የሙስና መስፋፋት፣ … [Read more...] about ኦባንግ ለኬሪ የጥሪ ደብዳቤ ላኩ!
ወ/ሮ ትዕግስት ከታገቱበት ሲና ተለቀቁ!!
የሱዳን፣ የኤርትራና የግብጽ ዜግነት ባላቸው ራሻይዳዎች ታፍነው ወደ ሲና በረሃ የተወሰዱት ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ ካይሮ መግባታቸው ታወቀ። ወ/ሮ ትዕግስት ቅዳሜ ረፋዱ ላይ ካይሮ የገቡት አጋቾቹ እንዲሰጣቸው ከጠየቁት 25 ሺህ ዶላር በድርድር 15 ሺህ ዶላር ተከፍሏቸው ነው። ዜናውን በሰሙ ማግስት “የወ/ሮ ትግስት የርዳታ እጆች” በማለት ተሰባስበው የነፍስ አድን ዘመቻውን ከጀመሩት መካከል አንዷ የሆኑት ወ/ሮ ሰብለ ደምሴ በተለይ ለጎልጉል እንደተናገሩት ወ/ሮ ትዕግስት ከአሰቃቂው የሲና በረሃ ወጥተው ካይሮ የገቡት ከአራት ወራት በኋላ ነው። አጋቾቹ ወ/ሮ ትዕግስትን በ10 ሺህ ዶላር እንደገዙ በመግለጽ 25 ሺህ ብር ካልተከፈላቸው እንደማይለቁና የሰውነት ክፍላቸውን በመሸጥ ያወጡትን ወጪ እንደሚሸፍኑ ይደራደሩ እንደነበር የገለጹት ወ/ሮ ገነት “አስቀድመን 10 ሺህ ዶላር ከፈልን። … [Read more...] about ወ/ሮ ትዕግስት ከታገቱበት ሲና ተለቀቁ!!
የ“ቀዩ መስመር” ሰላባዎች?
መለስ ህይወታቸው እንዳለፈ ከተሰጡት አስተያየቶችና ትንቢቶች መካከል ቀዳሚው የመለስ ሞት ለህወሃት ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ ፈንጂ መሆኑ ነበር። በዚሁ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በስልጣን ላይ ያሉ የኢህአዴግ ዲፕሎማት "መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ" በሚል ርዕስ በሰጡት ቃለ ምልልስ ይህ እንደሚከሰት ቁልጭ አድርገው ተናግረው ነበር። መለስ አፍነው የያዟቸው የፖለቲካ ችግሮች ጊዜያቸውን እየጠበቁ የሚፈነዱና በመጨረሻም ፓርቲውን እንደሚፈረካክሰው የተገለጸው በየደረጃ የሚፈነዱት ችግሮች እየበረከቱ በመሄዳቸው ነበር። መለስ አፍነው የያዟቸው ችግሮች የእርስ በርስ መበላላት ደረጃ እንደሚያደርሱ በርካታ ወገኖችና መገናኛዎች ጎልጉልን ጨምሮ አመላክተዋል። አሁን አሁን ትንቢቱ የፍጻሜው ጅማሬ ላይ እንደሚገኝ የሚናገሩም አሉ። የፖለቲካ አቋም ልዩነት ሳይኖር የአስተሳሰብ ልዩነት ማራመድ በህወሃት ዘንድ … [Read more...] about የ“ቀዩ መስመር” ሰላባዎች?
አኢጋን ታሪካዊ ያለውን ሰነድ አተመ!
"በቦታው ላይ ሆናችሁ ለህይወታችሁ ሳትፈሩ ይህንን መረጃ የሰጣችሁ ሁሉ የአገር ጀግኖች ናችሁ፤ አሁን አትታወቁም። አሁን ልንገልጻችሁ አንችልም። ጊዜና ወቅት ጀግንነታችሁን እስኪገልጹት ግን አትረሱም። ልትረሱም አትችሉም። ብዙ ባይነገርላችሁና ባይዘመርላችሁም ታላቅ ስራ ሰርታችሁዋልና ክብር ይሁንላችሁ" በማለት አቶ ኦባንግ ሜቶ ምስጋና ያቀረቡለት ታሪካዊ ሰነድ ታተመ። የስርዓቱ ላንቃ ስር ሆነው የህይወት ዋጋ በመክፈል መረጃ የሰጡትን ወገኖች የአክብሮት ምስጋና በማቅረብ በሚመሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ስም ለጥናቱ ተባባሪዎች ሁሉ ክብር እንደሰጡ የዘገበው የጋራ ንቅናቄው ለሚዲያ ባሰራጨው የፕሬስ ሃተታ ላይ ነው። ንቅናቄው “በኢንቨስትመንት ስም የሚፈጸም የመሬት ነጠቃ፤ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ተተርጉሞ መታተሙን ይፋ ባደረገበት ዜናው ይህ ታሪካዊ ሰነድ ለመጪው ትውልድ … [Read more...] about አኢጋን ታሪካዊ ያለውን ሰነድ አተመ!