• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የኢህአዴግና የሻዕቢያ ድርድር ተበጠሰ

May 27, 2013 12:00 am by Editor 4 Comments

ኳታር በተናጠል የጀመረችው ኢትዮጵያንና ኤርትራን የማሸማገል ሂደት መበጠሱ ተሰምቷል። ከሽምግልናው ዙሪያ የግብጽ ሚና ስለመኖሩ አመላካች ጉዳዮች አሉ እየተባለ ነው። በድርድሩ ኢህአዴግ በዋናነት እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠው የትግራይ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደሚት/ ጉዳይ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።

አቶ መለስ የኢትዮጵያን ወደብ እንደተራ ጉዳይ አሳልፈው በመስጠት ኤርትራን እንደ አገር እውቅና በሰጡበት ወቅት ድጋፍ ለማሰማት ቀዳሚ የነረችው ኳታር ከበረሃው ትግል ጀምሮ የሻዕቢያ ወዳጅ አገር እንደሆነች ይታወቃል።

ከዚሁ የከረመ ወዳጅነት በመነሳት ኳታር በ2008 ከኢህአዴግ ጋር ተፈጥሮ የነበረውን የጸብ ግድግዳ አፍርሳ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው በዋናነት ሁለቱን አገሮች መልሶ ለማስታረቅ በተያዘ እቅድ ስለመሆኑ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ይናገራሉ። በተለይም አሁን ያለው የኤርትራ አስተዳደር እጣ ፈንታ አብዝቶ ያስጨነቃት ኳታር በኤርትራ ወደብ ሊዝ በማድረግ፣ ኢንቨስትመንት ላይ በመሳተፍና ልዩ ድጎማ በማድረግ ቀዳሚውን ስፍራ ስለምትይዝ ችግር ከመፈጠሩ በፊት ላይ ታች ማለቷ እንደማይደንቅ ስምምነት አለ።

የጎልጉል ምንጭ የሆኑ ዲፕሎማት እንዳሉት ኳታር አሁን እርቁን የፈለገችው በኤርትራ መረጋጋት እንዲፈጠርና የኤርትራ ኢኮኖሚ አንዲያገግም ለማድረግ በሚል ነው። በሌላ በኩል ህወሃት የዘወትር ስጋቱ የሆነውን ሻዕቢያን ለማስወገድ ሌት ከቀን እንደሚሰራና ይህም በድርጅት ደረጃ አቋም የተያዘበት ጉዳይ በመሆኑ የኤርትራ መንግስት መሰረታዊ የአቋም ለውጥ ሳያደርግ ከኢህአዴግ ጋር የድርድር ስምምነት ላይ መድረስ አስቸጋሪ እንደሚሆን ሁሉም ወገኖች የሚረዱት ጉዳይ ነው።

ከውስጥም ከውጪም ፖለቲከኞች ትኩረት ሰጥተው እየተከታተሉት ያለው የሁለቱ አገሮች  የሰላም ድርድር ዲፕሎማቱ እንዳሉት ሁለት አብይ ጉዳዮች አሉበት። ሁለቱ አብይ ጉዳዮች ደግሞ ሊነጣጠሉ አይችሉም። በኤርትራ እለት እለት እየሰለለ የሄደው የአገሪቱ ኢኮኖሚና የኑሮ ውድነቱ የኢሳያስን አስተዳደር አናግቶታል። በተጨማሪ ሆን ተብሎ ይሁን በሌላ ምክንያት ከሃያላኑ አገራት ጋር የገጠሙት የረዥም ጊዜ ፍትጊያ የኢሣያስን ትከሻ አዝሎታል። ከዚህም በላይ እድሜ ለመለስ የፍቅር ጊዜያቸው ሲሻግት “አሸባሪ” አድርገዋቸው።

ከዓለምና ከአህጉር መድረኮች ሙሉ በሙሉ ተገልሎ የከረመው የኢሳያስ አስተዳደር በተለያዩ ደረጃዎች የደረሰበትን እግድና ቅጣት ለመቋቋም የዲፕሎማሲ ዘመቻ የጀመረው ከውጪ ያለውን ችግር ተከትሎ በአገር ውስጥ የገጠመውን ፈተና ለመቋቋም እንደሆነ ተንታኞች ያስታውሳሉ። በውስጥ የፖለቲካና የኢኮኖሚ አጣብቂኝ ውስጥ ያለው ሻዕቢያ ወንበሩ እየወላለቀ ስለሆነ ከቀድሞው ወዳጁ ህወሓት ጋር ለመወዳጀት ይፈልጋል።

ኤርትራ ኢኮኖሚዋ እንዲነቃቃ ኢትዮጵያን የንግድ ሸሪኳ ማድረግ የመጀመሪያው ስራ ነው።  ያለ ስራ “ሙት” ሆኖ የተቀመጠውን የአሰብን ወደብ ኢትዮጵያ ከጅቡቲ ባነሰ ዋጋ እንድትጠቀምበት ማድረግና ወደቡ ላይ ህይወት መዝራት ዛሬ ላይ ግድ እየሆነ የመጣ ጉዳይ ነው። በተለይም ኢትዮጵያ ጅቡቲ ላይ የራስዋን ወደብ ለመገንባት የጀመረችው እንቅስቃሴና ለጅቡቲ የወደብ ኪራይ የምትገፈግፈው እጅግ ከፍተኛ ወጪ ግማሹ እንኳን ኤርትራ ቋት ውስጥ ቢገባ አሁን የተፈጠረውን የኑሮ ግለት ጋብ እንደሚያደርገው በርካቶች ይስማሙበታል።

በዚሁ መነሻ የኢሳያስ መንግሰት ከገባበት የመኖርና አለመኖር ስጋት ለመገላገል እቅድ ተነድፎለት የተጀመረውን ድርድር ኢህአዴግ የህልውና ጥያቄ በመጠየቁ ሳቢያ ብዙም ሳይራመድ በእንጭጩ ተኮላሽቷል። ኢህአዴግ በድርድሩ መሰረታዊ ሃሳብም ሆነ በሌሎች ዝርዝር የኢኮኖሚ ነጥቦች የተፈለገው ርቀት ድረስ ለመጓዝ ፈቃደኝነቱን ለመግለጽ ጊዜ አልወሰደም ነበር። የለበጣም ቢመስልም አቶ ሃይለማርያም አስመራ ድረስ ለመሄድ ዝግጁ መሆኑንን ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

የሆነ ሆኖ ኢሳያስ አሁን ባላቸው የፖለቲካ አቋም ከሳቸው ጋር መነገድ የዛለውን ክንዳቸውን ማፈርጠም በመሆኑ ኢህአዴግ እንዳልተዋጠለት የሚጠቁሙት ዲፕሎማቱ “ፖለቲካዊ ይዘቱ ኢኮኖሚያዊ ሽርክናውን ዋጋ ቢስ አድርጎታል” በማለት ስለማይነጣጠሉት ሁለት ተያያዥ ጉዳዮች አስረድተዋል።

ኳታር ሶማሊያ ላይ በነበራት አቋምና የገንዘብ ተሳትፎ ከኢትዮጵያ ጋር የነበራት የዲፕሎማሲ መስመር ከመቋረጡም በላይ “ለሶማሊያ ጉዳይ አባቱ ነኝ” ይሉ በነበሩት አቶ መለስ ክፉኛ ተዘልዝላ ነበር። ያ ሁሉ አልፎ ዛሬ በኢንቨስትመንት ስም እርቅ አውርዳ የገባቸው ኳታር በጀመረችው ድርድር ኢህአዴግ ያነሳው መሰረታዊ የህልውና ጥያቄ አላላውስ ብሏታል።

ተቀማጭነታቸው ሎንደን የሆነ የጎልጉል ምንጭ እንዳሉት የኢህአዴግ ለመደራደሪያ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠው አጀንዳ ኤርትራ ውስጥ የሚንቀሳቀሰውን የትግራይ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደሚት/ ታጣቂ ሃይሎች ተላልፈው እንዲሰጡት ወይም ወደ ትግራይ ድንበር እንዲገፉለት ነው።

ቀደም ሲል የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት ህወሃት አካል የነበሩት እነዚህ ክፍሎች “ኤርትራ ውስጥ ታግተው የተቀመጡ”  ሃይሎች ስለመሆናቸውና ከ30 እስከ 40 ሺህ የሚደርስ ወታደር እንዳላቸው ለህወሃት ቅርበት ባላቸው የተለያዩ መገናኛዎች መዘገቡ ይታወሳል። በገለልተኛነታቸው የሚታወቁ መገኛዎችም ቢሆኑ የደሚት ሃይል ከአርበኞች፣ ከቤንሻንጉል፣ ከጋምቤላ፣ ከአማራ፣ ወዘተ ብረት አንጋቢዎች ጋር በጥምረት ለመሥራት መዘጋጀቱንና ይህም ሁኔታ ለህወሃት ስጋት እንደሚሆን አመልከተው ነበር።

ከኢህአዴግ የሚወጡ የምርመራ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ህወሃት ደሚትን እየፈራ ነው። ደሚት “በኤርትራ የታገተ ሃይል ነው” በማለት የድርጅቱን ሃይል ለማጣጣል ቢሞከርም፣ የደሚት ሃይል እንደሚባለው አለመሆኑንን የሚያረጋግጡ መረጃዎች አቶ መለስ በህይወት እያሉ ቀርቦላቸዋል። ከዚያ በኋላ ነበር ደሚት ጥንካሬው እንዳይጎለብት ህወሃቶች መስራት የጀመሩት።

በወቅቱ ከኢህአዴግ ጓዳ ያፈተለኩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ኢትዮጵያ አሰብን ለመጠቀም የሚያስችላት ድርድር ተጀምሮ ነበር። በስዊድን የሚኖሩ የጎልጉል ምንጭ የሆኑ የኤርትራ ተወላጅ ከዓመት ከስድስት ወር በፊት የአሰብ ወደብ እንዲታደስና ስራ እንዲጀምር ተወስኖ እንደነበርና ስራው ሲጀመር ስራ አቁመው የነበሩ ሰራተኞችና አገልግሎት አቋርጠው የነበሩ ድርጅቶች ስራቸውን እንዲጀምሩ መመሪያ ተሰጥቶ እንደነበር ያስታውሳሉ። ስራው አሁን በምን ደረጃ እንደሚገኝ ለጊዜው መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል።

በተለያየ ወቅት አቶ መለስን ከቀድሞው ወዳጃቸው አቶ ኢሳያስ ጋር መልሶ ለማሻረክ ግብጽን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች እንደተሳተፉ የሚገልጹ አሉ። የግብጽን የሸምጋይነት ሚና ጥርጥር ውስጥ በማስገባት አስተያየት የሚሰጡት ዲፕሎማት አሁን ኳታር ከጀመረችው ድርድር ጋርም ግብጽን ያያይዛሉ። ከኳታር ካዝና በሚወጣ ገንዘብ ሻዕቢያ የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች እንዲያደራጅ አጥብቃ የምትሰራውና የምትደጉመው ግብጽ አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያና ኤርትራ አስተማማኝ ሰላም አውርደው በሰላም በጉርብትና እንዲኖሩ አትመኝም።

ኳታር ግን በቀድሞው አቋም መቀጠሉ አግባብ እንዳልሆነና በ2008 ከኢትዮጵያ ላይ እጇን እንድታነሳ ተጠይቃ ባለመቀበሏ የተሰበረው የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለማቃናት መስራት የጀመረችው ከሊቢያው መሪ ጋዳፊ ሞት በኋላ እንደሆነ የሚገልጹ ክፍሎች ኳታር አሁን በጀመረችው “የትልቅ አገር ነኝ” ስሜትና በአፍሪካ ቀንድ ጂኦ ፖለቲካ ላይ ያላት ሚና መጎልበት ኢትዮጵያን መወዳጀት ብቸኛው አማራጯ እንደሆነ ይናገራሉ።

ሻዕቢያ እየከሰመ ሲሄድ ኢህአዴግ በሌላ በኩል በአፍሪካም ሆነ በዓለም ደረጃ ማደጉ ለንግድና ለፖለቲካ ዝናዋ ኢህአዴግን መወዳጀት አማራጭ የሌለው ጉዳይ የሆነባት ኳታር ሩጫዋ በጊዜ የተኮላሸው ከኢህአዴግ ወገን በተነሳ “የማይታሰብ” በተባለ ጥያቄ ነው። የደሚት የጦር ሃይል ተላልፎ እንዲሰጠው ወይም ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እንዲገፋለት የተየቀው ኢህአዴግ ይህ እስካልሆነ ድረስ ከሻዕቢያ ጋር አንድ መቀመጫ ላይ ተቀምጦ ለመነጋገር አለመቻሉ ለኳታር ሽምግልና የመጀመሪያውና ሊመለስ ያልቻለ ፈተና ሆኗል።

ከድሮ ጀምሮ አድብታ የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች በመርዳት የምትታወቀው ግብጽ ኢህአዴግ በፈለገው መልኩ ድርድሩ ሊካሄድ እንደማይችል አቋም ይዛ እየሰራች እንደሆነ፣ ለዚህም ሲባል ከአንዳንድ የተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ለመነጋገርና በሻዕቢያ አማካይነት ድጋፍ ለመስጠት ፍላጎት ማሳየቷን የጎልጉል ምንጭ የሆኑት ዲፕሎማት አስረድተዋል። ዲፕሎማቱ በደፈናው ከመናገር ውጪ ግብጽን ያነጋገረቻቸውን የተቃዋሚ ሃይሎች አልዘረዘሩም።

ኳታር የምጽዋን ወደብ በሊዝ ከመያዟ በተጨማሪ ለአሰብ ወደብ የነዳጅ ማጣሪያ ማደሻና ለወደቡ ስራ ማስቀጠያ ድጋፍ ማድረጓ አይዘነጋም። ያለ ስራ ተቀምጦ የነበረው ወደብ ለስራ እንዲዘጋጅ የታሰበው ለማን ተብሎና ማን እንዲጠቀምበት ታስቦ ነው ሚለው ጉዳይ ፖለቲካዊ ውሳኔ የሚጠይቅ አብይ ጉዳይ ከሆነ ዓመት ከስድስት ወር አስቆጥሯል። ኢህአዴግ የሚደጉመው የኤርትራ የሽግግር መንግስት አዲስ አበባ መቋቃሙም የሚታወስ ነው።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. ፍሬሠናይ ከበደ says

    May 27, 2013 09:02 am at 9:02 am

    ስለ አሰብ ወደብ ሲነሳ፡ እውነታውም መወሳት እንዳለበት የግድ ነው። ከፋሽስት ወያኔ አባልነት አፈንግጠው የወጡት ሳይቀር ምንም የማያውቁ የቀደምት የበረሃ ሽፍቶች እንደመሆናቸው፡ አሰብን በተመለከተ ድንቁርናቸውን ሲገልጹ፡ ኢትዮጵያ ወደብ ያስፈልጋታል የሚል ቃል ይደጋግማሉ። ሃቁ ግን ከሊግ ኦፍ ኔሽን አባልነት እስከተባበሩት መንግሥታት፡ የኢትዮጵያ ድንበር በግልጽ የሚታወቅ ነው። ኤርትራን ቅኝ፡የገዛው ጣሊያን ሳይቀር የተለያዩ ካርታ በመሥራት ቢያወናብድም፡ እንደአውሮፓ አቆጣጠር በ1961 በተባበሩት መንግሥታት ኤርትራ በፌዴሬሽን ወደ እናት ሃገሯ ኢትዮጵያ ስትቀላቀል፡ ከፌዴሬሽኑ ዕቅድ በተጨማሪ ሁለቱ በማስረጃ የጸደቁት፦ 2ኛው ” ቆላማው ክፍል ከምጽዋ ጋር ለሱዳን እንዲሰጥ። 3ኛው-” ደጋማው ክፍል ሃማሴን፤ ሠራዬ አካለጉዛይና ደንከል አውራጃ(አሰብ) ወደተቀረው ኢትዮጵያ ክልል እንዲከለልና፡ የመጨረሻው ኤርትራ እራሷን ችላ የምትገነጠል ከሆነ ደንከል አውራጃ(አሰብ) ቀሪነቱ የኢትዮጵያ ነው የሚለው ማስረጃ፡፡በተባበሩት መንግሥታት ጽ/ ቤት አለ። ይህንን ወያኔዎች ሊያነሱ አይፈልጉም ይኸውም በቀድሞው የሕወሃት ጠ/ሚንስትር ሟች መለስ ዘናዊ የታገተ ሊነሳ አይገባም ወደብ ሸቀጥ ነው የሚል የሕወሃትን የገበሬ ሽፍታ ማደናቆሪያ ወይም የማታለያ አቋም ነበር። ጎልጉሎች አሰብ ወደብን በተመለከተ ዜና ስትዘግቡ፡ አሰብ ወደብ የኢትዮጵያ መሆኑን ለኢትዮጵያ ሕዝብ መናገር ግዴታችሁ ነው። በቀጥታ የሻቢያና ወያኔዎችን ዜና እንዲህ ተደራድረው ነበር የሚል ዓረፍተ ነገር ስትዘግቡ፡ ስለ አሰብ ወደባችን የማያውቀው ሕብረተሰብ ትኩረቱ፡ አሰብ ወደብ ሻቢያ የሚሸቅልበት የሻቢያ ንብረት አድርጎ ስለሚገነዘብ ይምታታበታልና እባካችሁ አስተውሉ?????

    Reply
  2. ናሆም says

    June 7, 2013 06:09 pm at 6:09 pm

    ከዚህ በሃላ የአሰብ ጉዳይ ያለቀለትና የኤርትራ ሲሆን ለእልቂት ካልሆነ በስተቀር ትርፍ የሌለዉ በመሆኑ ባትደክሙ ይሻላል.እኛ ለአገራችን አስር ሞት እንደምንሞት ይግባችሁ.እንደ እንስሳ ማሰቡ አቁሙ ማሰብ ያቆማችሁ መሰለኝ.
    ኤርትራዊዉ ጀግና
    ናሆም

    Reply
  3. አበራ ጌታሁን says

    June 7, 2013 06:18 pm at 6:18 pm

    ወንድሜ እንቅጩን ለንገርህ እንደ እናንተ የመጨረሻ ደካማና አዙሮ ማሰብ የማይችል በአለም አልታየም.ጭንቅላታችሁን ሻቢያ በልቶታል.

    Reply
  4. Musie says

    June 9, 2013 03:32 pm at 3:32 pm

    hhmmmm Ahunim Ethiopiawyan rasachihun matalel aqumu , Asseb lay menzelazel waga yelewum bayhon agerachihun ayebetatene yalew weyanen adeb asgezut alebeleziya eyandandachu nege megbiya gojo aynorachihum , benga bekul kenante tegelaglenal bi ribenim bitemanim ager , bet , gojo yenga yeminillew be andinet yeminafeqrat, ende enante ye, 3000 amet qererto sayhon sile ewnet 10 gize bichal yeminimotilat ager alechin , lezihem kenante yewishet tarik lemegelagelin ye wushet ethiopiawinet kaba lemegelagel , 120 000 yekefelnachewin semaetat hiyaw misikirochachin nachew , ebakachihu atalazinu betat yemiqoteru donqoro weyanewoch eyechefechefuwachihu new, yetale alenn yemitilut jegninet, yetale anigezam yemitilut fukera , ager lesetochina hixanat titachihu shishit meretachihu yigermal , Eritrea only for Eritreans werq hizb sillehone !!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule