"ሀገሬን እጠብቃለሁ፤ መስዋዕትነት እከፍላለሁ" በሚል ከአዲስ አበባ ከተማ የተውጣጡ 363 አመራሮች ወደ ግንባር ሽኝት ተደርጎላቸዋል። በሽኝት መርሐግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ "አሸባሪው የህውሃት ጁንታ እና ተላላኪዎቹ እኛ እያለን መቼም ቢሆን ኢትዮጵያን አያፈርሷትም" ብለዋል። ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት እና ለህዝቦቿ አንድነት ሁላችንም እንታገላለን፤ ሞትም ቢመጣ ለኢትዮጵያ መሞት ክብር ነው ብለዋል ከንቲባዋ። ለኢትዮጵያ እና ለነፃነታችን እኛ ሁላችንም ዘማቾች ነን ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያለ መስዋእትነት ድል እንደማይገኝ ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ መሸነፍ የለም፤ አሁንም አንሸነፍም ነው ያሉት ወ/ሮ አዳነች። ጁንታው አይደለም ደሴ የትም ቢመጣ መጨረሻው መቃብር ነው ያሉት ከንቲባዋ በገባበት ሁሉ ገብተን እዚያው … [Read more...] about “ሀገሬን እጠብቃለሁ፤ መስዋዕትነት እከፍላለሁ” የአዲስ አበባ 363 አመራሮች
Right Column
ኃላፊነት የጎደላቸው የማኀበራዊ ሚዲያና አንቂዎችን ከእንግዲህ አንታገስም
ኃላፊነት የጎደላቸው የማህበራዊ ትስስር ገፆችን እና ማህበራዊ አንቂ ነን የሚሉ ግለሰቦችን እንደማይታገስ መንግስት አስታውቋል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጠው መግለጫ መንግስት ያቀረበውን ሀገርን የመታደግ ጥሪ ተከትሎ ህዝቡ እና የመንግስት ሰራተኛው በነቂስ ዘመቻውን እየተቀላቀለ መሆኑን ገልጿል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ የህብረተሰብን ሰላም እና ደህንነት የሚያውኩ ሆነው እስከተገኙ ድረስ መንግስት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚደረግ ማንኛውንም እንቅስቃሴ አይታገስም ብለዋል። (EBC) ከግለሰብ በማለፍ መንግሥት በሕጋዊ መልኩ የት ህነግን ዓላማ እየፈጸሙ ያሉና በዓለምአቀፍ ሚዲያ ተቋምነት እየሠሩ ያሉትንም በዚሁ መልኩ እንዲመለከታቸው ጥሪ እናሰተላልፋለን። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ኃላፊነት የጎደላቸው የማኀበራዊ ሚዲያና አንቂዎችን ከእንግዲህ አንታገስም
ለሸኔ ሊተላለፍ የነበረ የጦር መሳሪያ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋለ
በጋምቤላ ከተማ ለአሸባሪው ሸኔ ሊተላለፍ የነበረ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ከሁለት ተጠርጣሪ ግለሰቦች ጋር ትናንት በቁጥጥር ስር መዋሉን የጋምቤላ ክልል ሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ አቶ ቡን ዌው ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የጦር መሳሪያው የተገኘው በጋምቤላ ከተማ በባጃጅ ተሽከርካሪ ተጭኖ ለማስተላለፍ ሲሞከር ነው። ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋለው የጦር መሳሪያ መካከል አንድ ላውንቸር፣ አንድ ክላሽንኮቭ ከ705 ጥይት ጋር እንዲሁም 76 ዲሽቃ እንደሚገኝበት አመልክተዋል። ተጠርጣሪ ግለሰቦቹ በሰጡት ቃል ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ ለሸኔ የሽብር ቡድን ሊተላለፉ እንደነበር መናገራቸውን ኃላፊው አስረድተዋል። የክልሉ ፖሊስና የፌዴራል ፖሊስ በጋራ በመሆን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመከላከል ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ኃላፊው ገልጸዋል። … [Read more...] about ለሸኔ ሊተላለፍ የነበረ የጦር መሳሪያ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋለ
በባህርዳር ከተማ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ
በባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ሚኒሊክ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ማር ዘነብ ቀበሌ ሲቱ ዋርካ አካባቢ በአንድ ተጠርጣሪ ቤት ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማና ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 3 ሺህ 676 የክላሽ ጥይት፣ 1 ሺህ 288 የመትረየስ ጥይት፣ 3 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ እና 20 የተለያዩ ሽጉጦችን ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መያዙን የ9ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ቀለሙ ረታ አስታውቀዋል። እንደ ምክትል ኢንስፔክተር ቀለሙ ረታ ገለጻ በክፍለ ከተማው ብሎም በከተማዋ መሰል ወንጀሎች ከጊዜ ወደጊዜ ተደጋግመው ቢከሰቱም በፀጥታ ኀይሉ የጠነከረ ትጋትና በህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ይገኛሉ። አሸባሪው ህወሓት በየቦታው ህዝብን ለማጥፋት እሳት እያነደደ ባለበት በዚህ ጊዜ መላው ህዝብ ከፀጥታ ኀይሉ ጎን በመሆን … [Read more...] about በባህርዳር ከተማ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ
የአቮካዶ ምርት ወደ ውጭ በመላክ ምንዛሬ ለማግኘት እየተሰራ ነው
የጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ 45 ቶን የአቮካዶ ምርት ወደ ውጭ በመላክ ምንዛሬ ለማግኘት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። ምርቱን ወደ ስፔን፣ ፈረንሳይና የተባበሩት አረብ ኤሚሬት እንደሚልክ ነው የገለፀው። ወረዳው የተሻሻሉ የአቮካዶ ዝርያዎችን በ350 ሄክታር መሬት ላይ እያለማ እንደሚገኝም አስታውቋል። የመስቃን ወረዳ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መሀመድ ሳኒ÷ ወደውጭ ለመላክ ከታቀደው የአቮካዶ ምርት እስካሁን 20 ቶን መላኩን አስታውቀዋል። አቮካዶ በአመት ሁለት ጊዜ ምርት እንደሚሰጥ ያመለከቱት አቶ መሀመድ በአምናው የምርት ዘመን 26 ቶን የአቮካዶ ምርት ወደ ውጭ መላኩንም መናገራቸውን ከጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። በወረዳው የሚገኙ 2ሺህ 100 አርሶ አደሮች በ10 ክላስተር ተደራጅተው በአቮካዶ ልማቱ … [Read more...] about የአቮካዶ ምርት ወደ ውጭ በመላክ ምንዛሬ ለማግኘት እየተሰራ ነው
51 ትልቁ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥና የተለያዩ መሳሪያዎች ተተኳሽ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ
በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ 51 ትልቁ ቱርክ ሰራሽ ህገ-ወጥ ሽጉጥ፣ 2ሺ 1መቶ የብሬን ጥይት፣ 69 የክላሽ ጥይት እንዲሁም 222 የሽጉጥ ጥይቶች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቋል። ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያው በቁጥጥር ስር የዋለው የአማራ ክልል ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በትብብር መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ (ኢብኮ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about 51 ትልቁ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥና የተለያዩ መሳሪያዎች ተተኳሽ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ
ከ44.4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
ባለፈው ሳምንት ከ21/01/2014 ዓ.ም እስከ 27/01/2014 ዓ.ም ድረስ ከ44.4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ከሀገር ሊወጡ እና ወደ ሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆን፣ የገቢ ኮንትሮባንድ 43 ሚሊዮን 12ሺ 009 ብር፤ ወጪ ደግሞ 1ሚሊዮን 437ሺ 851ብር፣ በድምሩ የ44ሚሊዮን 449ሺ 860ብር ግምት አላቸው ተብሏል፡፡ አቃቂ ቃሊቲ እና ሞያሌ የጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች ላይ ከፍተኛ የኮንትሮባንድ እቃዎች ሊያዙ ችለዋል፡፡ ከኮንትሮባንድ ቁሶቹ መካከል የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የወርቅ ማውጫ ማሽን፣ ተሽከርካሪ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ሲጋራ፣ አደንዛዥ እጽ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ፣ የሰው መድሀኒትና … [Read more...] about ከ44.4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
34 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ
34 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር አዉሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። ተጠርጣሪው ግለሰብ በጥቁር ፌስታል የተጠቀለለ ነገር ይዞ ሲንቀሳቀስ መደበኛ የወንጀል መከላከል ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነስቷል፡፡ ፖሊሶቹ ባደረባቸው ጥርጣሬ ግለሰቡን ሲፈትሹት 34 ሺህ የአሜርካ ዶላር ይዞ በህገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ነው ተብሏል፡፡ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በአዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ሲሆን የኑሮ ውድነት እንዲባባስ እና መንግስት ማግኘት ያለበትን ገቢ እንዲያጣ እያደረገ ይገኛል፡፡ ወንጀል ፈፃሚዎች እና ህገ-ወጥ ተግባራት ላይ የሚሳተፉ አካላት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ህግን በጣሰ መልኩ እየተንቀሳቀሱ … [Read more...] about 34 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ
በአዲስ አበባ ሕገወጥ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ፍተሻ የተለያዩ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎች እና ሰነዶች በቁጥጥር ስር ዋሉ። በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው 32 ቀበሌ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውሰጥ ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት በተደረገ ፍተሻ የጦር መሳሪያዎች እና ሰነዶች መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። በግለሰቡ መኖሪያ ቤት ላይ ጥናት በማድረግና የፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት በተደረገ ብርበራ 85 የክላሽን-ኮቭ እና የሽጉጥ ጥይቶች፣ 3 ሽጉጦች ፣ 2 ሳንጃዎች እና 1 የእጅ ቦንብ መያዙን ነው ፖሊስ የገለፀው፡፡ በተጨማሪም 10 ሺህ የኢትዮጵያ ብር እና በርካታ ፓስፖርቶችን ጨምሮ የትምህርት ማስረጃዎች በግለሰቡ መኖሪያ ቤት ውስጥ መገኘታቸውን ከአዲስ ከተማ ክፍለ … [Read more...] about በአዲስ አበባ ሕገወጥ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ
ለኤርሚያስ ክስ ትህነግ ወጪውን ሊሸፍን ነው
ኤርሚያስ ቃል በቃል የተናገረው ይህንን ነው፤ “ቲዲኤፍን (ስሙን የቀየረውንና በሃሺሽ ያበደውን የትህነግ ጭፍራ ማለቱ ነው) ምሳሌ ውሰዱ፤ የትግራይ ቲዲኤፍ ሕዝባዊ ኃይል ነው፤ (እነርሱ) ሳይነጋገሩ አይወስኑም፤ እንደ ቤስት ፕራክቲስ ነው የሚወሰደው፤ እደግመዋለሁ ቤስት ፕራክቲስ ነው”። ለአማራ ህዝብ እንዲተገብረው የሰጠው “ምክር” ይህንን ነው። በሌላ አነጋገር ኤርሚያስ እያለ ያለው፤ አገኘሁ ተሻገር ደብረጽዮንን፤ ጄ/ል ተፈራ ማሞ ፃድቃንን፤ ጄ/ል አዳምነህ መንግሥቴ ታደሰ ወረደን ወይም ምዕግበን፤ ግዛቸው ሙሉነህ ደግሞ ጌታቸው ረዳን መሆን አለባቸው ነው። “የህወሃት አገልጋይ” በሚል ልዩ መለያው የሚታወቅው፣ በበረከት ስምዖን አስተምህሮ ተቀርጾ የተሠራ የሚባለውና ከዚሁ ፈጣሪው ጋር ጥብቅ ትሥሥር እንደነበረው በርካታ መረጃ የሚቀርብበት ኤርሚያስ ለገሠ፤ በአበበ ገላው … [Read more...] about ለኤርሚያስ ክስ ትህነግ ወጪውን ሊሸፍን ነው