• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሳሚ ዶላር አንዱ ነው፤ ሌሎቹስ ዶላር አጣቢዎች? ምነው ዝም ተባሉ?

October 28, 2022 04:04 am by Editor Leave a Comment

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኅብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማና ባደረገው ብርቱ ክትትል በህገ-ወጥ መንገድ ከ5.1 ቢሊዮን ብር (ከአምስት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር) በላይ ሲያንቀሳቅስ የነበረ ግለሰብ ከ25 ግብረ-አበሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራባቸው መሆኑን ገለፀ፡፡ ዜናውን የሰሙ “በነካ እጃችሁ ወኪሎቹ ጋር ጎራ በሉ” ሲሉ ተደምጠዋል።

በወንጀሉ የተጠረጠረው ሳሙኤል እጓለ አለሙ በቅፅል ስሙ ሳሚ ዶላር የሚባል ሲሆን ነዋሪነቱን በአዲስ አበባ ከተማ በማድረግ ወደ አሜሪካን ሀገር በተደጋጋሚ የሚመላለስ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች፣ የቤት እና የቢሮ እቃዎች
እንዲሁም ተዛማጅ መገልገያዎች የችርቻሮ ንግድ ፍቃድን ሽፋን በማድረግ ሕገ-ወጥ የውጭ ምንዛሬና በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ተጠርጥሮ በራሱና ዮዲት እጓለ አለሙ ከተባለች እህቱ ጋር በመሆን በስማቸው በተለያዩ ባንኮች በከፈቷቸው ሃያ አምስት የባንክ አካውንቶች በአንድ ዓመት ውስጥ ከ247 ሚሊየን ብር (ሁለት መቶ አርባ ሰባት ሚሊየን ብር) በላይ ማንቀሳቀሳቸውን ፖሊስ ደርሶባቸው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ግለሰቡ ከሃያ አምስቱ የወንጀል ግብረ-አበሮቹ ጋር በመሆን በህገ-ወጥ መንገድ ከ5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር (ከአምስት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር) በላይ ሲያንቀሳቅሱ እንደነበር በቅድመ ምርመራ ተደርሶባቸዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በሕገ-ወጥ የውጭ ሀገር የገንዘብ ዝውውር፣ በግብር ስወራ ወንጀል እና ከህወሃት የሽብር ቡድን ጋር የግንኙነት መረብ በመፍጠር ከፍተኛ ገንዘብ ሲያዘዋውሩ እንደነበር ተጠርጥረው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በአጠቃላይ በአንድ ዓመት ውስጥ 5,248,000,000 (ከ5 ነጥብ 1 ቢሊዮን) ብር በላይ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያንቀሳቅሱ እንደነበር ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ደርሶባቸዋል ሲል የዘገበው የፌዴራል ፖሊስ ነው።

በተያያዘ ይህን ዜና የሰሙ ራሳቸውን “ባለሃብት” የሚባሉትን፣ ሰው ግን በተለምዶ “ወኪል” እያለ የሚጠቋቆምባቸው በተመሳሳይ ስራ የተሰማሩ ስለመሆናቸው አስታውቀዋል። አቀባባዮቹም እነማ እንደሆኑ ስውር ባለመሆኑ መንግስት በነካ እጁ ጎራ ይበል ሲል ጥቆማ ሰጥተዋል። ዱባይ ላይ ሃብት የከመሩትና እግራቸው አዲስ አበባ የሆነውን፣ ለራሳቸው የውጭ ድርጅት በራሳቸው የአገር ቤት ድርጅት ኤል ሲል (LC) እየከፈቱ የሚመዘብሩት በደንብ ስለሚታወቁ መንግስት ዙሩን እንዲያከረው አሳስበዋል።

አሁን ላይ የውጭ ብር መንዛሪዎች አዲስ አበባ ዙሪያና ቅርብ በሆኑ ከተሞች የሚኖሩ እንድ ፍሬ ልጆችን በመቅጠር ነው የሚያሰሩት። በስማቸው ተያዥ አድርገው ገንዘብ በማስገባት በጥቁር ለሚመነዘርላቸው አካላት በአድራሽነትና አስተላላፊነት በወር እስከ 30 ሺህ ብር እንደሚከፈላቸው ብር ተልኮለት የተቀበል ዳያስፖራ ብሩን ከሰጥችው ልጅ መረጃ ማግኘቱን አመልካቶ ነው አሰራሩን ያስታወቀው።

አብዛኞቹ በስም የሚታወቁ የድርጅት ባለ ቤቶችና ሪል ስቴት ስር የሚንቀሳቀሱ በውጭ ምንዛሬ አጠባው ዋና ፊት አውራሪ መሆናቸውን ጥቆማ የሰጡት አመልክተዋል።

ሪልስቴ ዙሪያ ያሉ አብዛኞቹ ከመሬት ጋር በተያያዘ የሚያከማቹትን ሃብት ወደ ውጭ ስለሚያሸሹና በውክልና ድርጅቱን ላቆሙላቸው ዛሬ ላይ ሃብት የሚያስተላለፉትም በውጭ ምንዛሬ ብቻ በመሆኑ ዶላሩን እየለቀሙ ኑሮ እንዲግል፣ ህዝብ እንዲማረርና መንግስት ላይ እንዲነሳ ኢኮኖሚው ላይ ሚስማር የሚመቱት መሆናቸውን ጠቋሚዎቹ ስም ዘርዝረው ልከዋል። ሆኖም አዘግይተነዋል። ዶላር የሚዛወርባቸውን ቤቶችና እናውቃቸዋለን ያሉትን ተሽከርካሪዎች ሳይቀር ጠቁመዋል።

አብዛኞች እንደሚሉት በዚህ ሌብነት የተሰማሩት ቀደም ብለው ከትህነግ ጋር አብረው ሲነገዱና በውክልና “ምስለኔ ሃብታም” የሚባሉት ናቸው። ንብረት በተጋነነ ብር በመግዛት በቋሚ የወኪሎቻቸውን ብር የቻሉትን በውጭ ምንዛሬ፣ ያልቻሉትን በአገር ውስጥ በቋሚ ንብረት ላይ በማስቀመጥ ደሃው ቤት እንዳይገዛ፣ መሬት ወስዶ ጎጆ እንዳይቀይስ ዋጋውን እንዳናሩበት መረጃውን የላኩት አመልክተዋል። መንግስት ቆርጦና ወስኖ እነዚህ አካላት ላይ ከዘመተ የመሬትና የቤት ዋጋ በቅጽበት እንደሚሽቆለቆል በዕምነት ተናግረዋል።

መንግስት በአዲሱ ዓመት ሌብነት ላይ እንደሚዘምት፣ ዘመቻውንም ለመጀመር ዝግጅት ላይ እንዳለ ዳግም ወረራ መቀስቀሱ ይታወሳል። የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደአ “ሌባ ሊመነጠር ሲል ጦርነት መክፈት ምንን ለማሰናከል ታስቦ እንደሆነ ይታወቃል። ሁሉም ጎን ለጎን ይሄዳል” ማለታቸው ይታወሳል። (Ethio12)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: News, Politics, Right Column Tagged With: ethiopian terrorists, illegal money, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule