የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በ440 የምርጫ ክልሎች የተከናወነውን አጠቃላይ ምርጫ ውጤት ሐምሌ 3 ቀን 2013 ዓም በስካይላይት ሆቴል በተከናወነ መርሐ ግብር ይፋ አደረገ፡፡ ቦርዱ እስካሁን በሒደት ካሳወቃቸው የተረጋገጡና ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶች በማስከተል ምርጫው በተከናወነ በ20 ቀናት ውስጥ የምርጫውን ውጤት ማሳወቅ እንደሚኖርበት በሕግ በተደነገገው መሠረት ቅዳሜ ሐምሌ 3 ቀን 2013 ዓ.ም. በስካይላይት ሆቴል በተከናወነ መርሃ ግብር አስታውቋል፡፡ ቦርዱ ይፋ ባደረገው ውጤት መሠረትም፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድምጽ ከተሰጠባቸው 425 የምርጫ ክልሎች መካከል ብልጽግና ፓርቲ 410 መቀመጫዎችን ያሸነፈ ሲሆን፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አምስት፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ አራት፣ በኦሮሚያ … [Read more...] about ምርጫ ቦርድ የስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ውጤት አሳወቀ
Left Column
የህወሓት ቀጣይ ዕቅድ
(የሚከተለው ፅሁፍ ከትግረኛ ወደ አማርኛ የተተረጎመ የዲጂታል_ወያኔ ምሥጢራዊ እቅድ ነው!) በተለያዩ ሚዲያዎች እየወጣችሁ አሸነፍን እያላችሁ ደስታ ማሳየት በፍጥነት አቁሙ። ገዳዮቻችን ጠላቶቻችን ለሌላ እንደተጠቁ አድርገው ሊጠቀሙበት ይችላሉ። በቀጣዩ ቅዳሜ ወደ ትግራይ የሚወስዱ መንገዶችን በመዝጋት ድልድዮችን በማፍረስ የትግራይን ህዝብ በረሀብና ጥማት አፍኖ ለመጨረስ እየተረባረቡ ይገኛሉ በሚል በመላው አለም የሚገኝ ትግራዋይ_ሰልፍ እንዲወጣ በቀጣይ ሳምንታት ደግሞ የተደረጉ ጭፍጨፋዎችን በመዘከር የሻማ ማብራት ስነሥርዓት በማካሔድ የተለያዩ ቦታ ሰምዕታትን መዘከሪያ ፕሮግራም እንዲዘጋጅ በዚህ መሠረት፣ የመጀመሪያው ሳምንት የማይካድራን ዳንሻንና ሁመራን ሰማዕታት በመዘከር ሁለተኛ ሳምንት የአክሱምን እና የደብረ አባይ ሰማእታትን በመዘከር ሶስተኛው ሳምንት … [Read more...] about የህወሓት ቀጣይ ዕቅድ
ጩኸት ያፈናት ከተማ
የድምጽ ብክለት መጨመር የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ለምሬት እየዳረገ ይገኛል፡፡ ከመጠን ያለፉት ረባሽ ድምጾች፡- ከንግድ ትርኢቶች፣ ከሐይማኖት ተቋማት፣ ከምጽዋት ጠያቂዎች፣ ከጎዳና ላይ ንግድ፣ ከምግብና መጠጥ ቤቶች፣ ጋራዥ፣ እንጨት ቤት እና ብረት ቤትን ከመሰሉ አገልግሎት ሰጪዎች፣ ከፊልምና ሙዚቃ መሸጫዎች፣ ከተሽከርካሪዎች እና ከመሳሰሉት ይመነጫሉ፡፡ ለመሆኑ የድምጽ ብክለት ማለት ምን ማለት ነው? ምን ጉዳት ያስከትላል? እንዴት መቆጣጠር ይቻላል? የሚለውን ጥያቄ አንስተናል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የባለሙያዎች አስተያየት እና የተጎጂዎች ሐሳብ ተካቷል፡፡ "የድምፅ ብክለት መደበኛውን የሕይወታችንን እንቅስቃሴ ይጎዳል፣ ያስተጓጉላል፣ እንቅልፍ ይነሳል፤ ውይይቶቻችንንና መደማመጣችንን ይቀንሣል፣ በአጠቃላይ የአኗኗራችን ሁኔታ የተረበሸ እንዲሆን ያደርጋል።” የሚሉት የቀድሞ የኢትዮጵያ … [Read more...] about ጩኸት ያፈናት ከተማ
መከላከያ ያገኘው የአሸባሪው ህወሃት ኮትተ
በተወሰደበት እርምጃ የጁንታው አፈ ቀላጤ ጌታቸው ረዳ ታጣቂ ኃይሉን ብቻ ሳይሆን የመዋጊያ ንብረቶቹንም ጭምር በየቦታው ማዝረክረኩን የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር አስታወቀ፡፡ የደቡብ ዕዝ 21ኛ ጉና ክፍለ ጦር የሠራዊት አባላት፣ የማይሰበር እልህና ወኔ ሰንቀው ጁንታው በዕብሪት ተወጥሮ በሀገራችን የጀመረውን ጦርነት በማክሸፍ የሀገራችንን ሉአላዊነት በማስከበር የህግ የበላይነትን እንዲረጋገጥ እያደረጉ እንደሚገኙ የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር ህብረት ዘመቻ ቡድን መሪ ሌ/ኮ ብርሃኑ ኃይሉ ተናግረዋል። ሌ/ኮ ብርሃኑ ኃይሉ ሰሞኑን በተደረገው በፈታኝ መሰናክል የታጀበ የአሰሳ ውጊያ ፣ የአካባቢውን አስቸጋሪ ተራራና አቀበት በመጋፈጥ ጠላትን ማፅዳት መቻሉን አረጋግጠዋል፡፡ በተለይም የጁንታው አፈቀላጤ የሆነው አቶ ጌታቸው ረዳ ሲፈረጥጥ አንጠባጥቧቸውና ደብቋቸው የነበሩትን ወታደራዊ ንብረቶች … [Read more...] about መከላከያ ያገኘው የአሸባሪው ህወሃት ኮትተ
“ችግኙ” ተተክሏል!
ሰኔ 14 ቀን 2013 ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ቀን ነው። በሀገራችን የመጀመሪያ ነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ድምፃቸውን ለማሰማት ወጥተዋል። ምስሎች አንድ ሺህ ቃላት ይናገራሉ እናም እነሱ በህዝባችን ያለውን ቅንነት፣ ለሰላም እና ለዴሞክራሲያዊ ሂደት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያሉ። ኢትዮጵያ ትናንት አሸነፈች። ኢትዮጵያ በአሸናፊነት ትቀጥላለች! - ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ June 21, 2021, is a historic day for Ethiopia. All sections of society have gone out to cast their voice in our nation’s first free and fair election. Pictures are worth a thousand words and they show the earnestness, commitment to peace, and the … [Read more...] about “ችግኙ” ተተክሏል!
በኦሮሚያ ክልል በ26 ታጣቂዎች ላይ ዕርምጃ ተወሰደ
በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን፣ በቦረናና ጉጂ ዞኖች አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የነበሩና የምርጫውን ሒደት ለማስተጓጎል በተንቀሳቀሱ 26 ታጣቂዎች ላይ ዕርምጃ መወሰዱ ታወቀ፡፡ ዕርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል 20ዎቹ ታጣቂዎች ከጅማ ዞን ናቸው፡፡ ጅማ ዞን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት በጎማ 2 የምርጫ ክልል ዕጩ ሆነው የቀረቡበት አካባቢ ነው፡፡ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ጥላሁን አመንቴ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢ ይንቀሳቀሱ የነበሩና በፓርላማ አሸባሪ ተብለው የተፈረጁ ታጣቂ ቡድኖች በምርጫው ሒደት ላይ መስተጓጎል ለመፍጠር በመሞከራቸው ዕርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ የክልሉ ፖሊስ ከተለያዩ የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በምርጫው ሒደት የሚከሰቱ የተለያዩ ችግሮችን ለመከላከል፣ … [Read more...] about በኦሮሚያ ክልል በ26 ታጣቂዎች ላይ ዕርምጃ ተወሰደ
የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ
በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም አቅደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ፡፡ የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች ሁከት፣ ሽብርና ትርምስ በመፍጠር ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳቸውን ለማሳካት በሚንቀሳቀሱ የውጭ እና የውስጥ ፀረ-ሰላም ኃይሎች የሚደገፉ የሸብርተኞቹ የህወሓትና የሸኔ ቡድን አባላት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ ሴራ ወጥነው ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት በዝግጅት ላይ እንዳሉ በጋራ ግብረ ኃይሉ በተደረገባቸው ጥብቅና የተቀናጀ ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል። ይህን እኩይ የጥፋት ሴራ ለመፈጸም ከውጭ በተለያዩ አካላት በሚደረግላቸው … [Read more...] about የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ
በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ዋለ
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በተደረገ ክትትል በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 1 መቶ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረው ዶላር የተያዘው ሚያዚያ 28 ለ29 አጥቢያ 2013 ዓ/ም በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ላምበረት መናኸሪያ ግቢ ውስጥ ከለሊቱ 10 ሰዓት ገደማ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ወደ ሃረር ሊጓዙ የተዘጋጁ ሁለት ተጠርጣሪዎች በያዙት ሻንጣ ላይ በተደረገ ፍተሻ በጥቁር ላስቲክ የተጠቀለለ 110 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መገኘቱን ፖሊስ ያስታወቀው፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ (ኢብኮ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ዋለ
ሸኔ የሚባል የፖለቲካ ፓርቲ የለም፣ ህወሃትና ሸኔ አሸባሪ መባላቸው ለውጥ አያመጣም፤ መረራ ጉዲና
ውሳኔ ከመዘግየቱ በስተቀር ተገቢ ነው፤ የህግ ባለሙያዎች የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ተቀዳሚ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ መንግስት “ሸኔ” እና “ህወሓት” ቡድንን በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ለማድረግ መዘጋጀቱ መሰረታዊ ለውጥ አያመጣም ብለዋል፡፡ እንዲህ አይነት ፍረጃ የቀድሞ መንግስትም ሲያደርገው የነበረ ነዉ የሚሉት ፕሮፌሰሩ፣ ይህ ዓይነቱ ፍረጃ መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ቢሆን እዚህ ደረጃ ላይ አንደርስም ነበር፤ ይህም ተግባር ቀድሞ ከነበረው መንግስት የተለየ ነው ብዬ አላስብም ብለዋል ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፡፡ “ሸኔ የሚባል የፖለቲካ ፓርቲ የለም፣ በኦሮሞ ስም የሚንቀሳቀሱ ሀይሎችን በተዘዋዋሪ መጥራት ይመስለኛል የሚሉት ፕሮፌሰር መረራ በዚህ ስም ራሱን የሚጠራ ድርጅት በሌለበት፣ መንግስት ግን በኦሮሚያ አካባቢ በኦሮሞ ስም የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችን ኢላማ … [Read more...] about ሸኔ የሚባል የፖለቲካ ፓርቲ የለም፣ ህወሃትና ሸኔ አሸባሪ መባላቸው ለውጥ አያመጣም፤ መረራ ጉዲና
በአስመጪ ዳዊት የማነ ሀሰተኛ ሰነድ ወደ ሀገር ዉስጥ ሊገባ የነበረ ገጀራ ተያዘ
ከፌደራል ፖሊስ ፈቃድ እንደተሰጠው በማስመሰል በተጭበረበረ ሰነድ ርክክብ ተፈጽሞ ባለቤት የተባለው ሰው ከተረከበ በኋላ በተደረገ ክትትል 186 ሺህ 240 ገጀራ በቁጥጥር ስር ዋለ። በጅምላ ጭፍጨፋ በተካሄደባቸው አገራት በተገኘ ልምድ ገጀራ ክልከላ የጣለበት የእጅ የጥፋት መሳሪያ ነው። ገጀራው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያዎች ህጋዊ ፈቃድ እንዳለው እየተገለጸ የሚሰራጨው ደብዳቤ ሃሰት መሆኑም ተመልክቷል። ከ15 ቀን በፊት በአስመጪ ዳዊት የማነ ስም ብዛቱ 186,240 የእጅ ገጀራ በአራት ባለ 20 ጫማ ኮንቴይነሮች ከቻይና ተጭኖ ሞጆ ጉምሩክ ይደርሳል። እቃው በዲክላራሲዮን ቁጥር 4-1919/21 ተመዝግቦ ወደ ሀገር ዉስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ የተፈቀደለት በማስመሰል እና ሐሰተኛ ሰነድ የተዘጋጀለት ነው። ይኸው ሃሰተኛ ሰነድ ለገቢ ዕቃ አወጣጥ የሰነድ መርማሪው … [Read more...] about በአስመጪ ዳዊት የማነ ሀሰተኛ ሰነድ ወደ ሀገር ዉስጥ ሊገባ የነበረ ገጀራ ተያዘ










