ከሰሞኑን በእንግሊዙ የቴሌግራፍ ጋዜጣ የወጣው የምርመራ ሪፖርት መነጋገሪያ ሆኗል። ሪፖርቱ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ አከባቢ አጋምሳ ተብላ የምትጠራ ከአፋር ክልል የጥቂት ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ መንደር ሙሉ በሙሉ መውደሙን በሳተላይት ምስል በታገዘ ሁኔታ ቀርቧል። ሪፖርቱን ያዘጋጀው ጋዜጠኛ ዘካሪያስ ዘላለም፥ በተደረገው የምርመራ ስራና ከአከባቢው ወደ ደሴ የተፈናቀሉት ንጹሃኖች በማነጋገር የጦር ወንጀል የተፈጸመው በአከባቢው ይንቀሳቀሱ የነበሩት የ "ትግራይ ሃይሎች" መሆኑን ደርሰንበታል ብሏል። በተጠቃው አከባቢ ላይ አብዛኛው ነዋሪ በግብርና ስራ የሚተዳደሩ ሲሆኑ ከሳተላይት ምስሎችን በመመልከት ከ50 በላይ ጎጆ ቤቶች መቃጠላቸውንና ቃጠሎዉ ከሃምሌ 26 እለት ጀምሮ መፈጸሙንም ማረጋገጥ መቻሉን የጋዜጣው ሪፖርት ያስረዳል። ጋዜጠኛው፥ የሳተላይት ምስል … [Read more...] about ትህነግ በሰሜን ወሎ የፈጸመው ጭፍጨፋ የሳተላይት መረጃ