አቡነ ሉቃስ በተከሰሱበት የቅስቀሳ ወንጀል ጥፋተኛ በተባሉበት ድንጋጌ በሥድስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ። ከፈጸሙት ወንጀል አኳያ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላሉ። የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ሕገ-መንግሥታዊና በሕገ-መንግሥት ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮች የሚመለከተው ችሎት ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በአቡነ ሉቃስ ላይ ከሦስት ወራት በፊት÷ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 247 (ሐ) እና አንቀጽ 258 (ሀ) ሥር እና የወንጀል ሕግ አንቀጽ 251 (ሐ) የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚሉ ሁለት ክሶች ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ ተከሳሹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የምሥራቅ … [Read more...] about አቡነ ሉቃስ 6 ዓመት ተፈረደባቸው፤ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላል
Archives for May 2024
ትሕነግ ሕጋዊ ዕውቅና ተሰጥቶት ብልጽግናን ሊቀላቀል ይችላል ተባለ
ትሕነግ ሌላ ሕንፍሽፍሽ ይጠብቀዋል በጌታቸው አሰፋ የሚመራው ጽንፈኛ የክልል ፓርቲ ሆኖ ሊቀጥል ይችላል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህወሓት መልሶ ሕጋዊ እውቅና እንዲያገኝ የሚያስችል የአዋጅ ማሻሻያ ወደ ፓርላማ መራ። ውሳኔው ትሕነግን ሕጋዊ ዕውቅና ሰጥቶ ወደ ብልጽግና ለመቀላቀል የታሰበ ነው የሚል ግምት ሲሰጠው በትሕነግ ውስጥ አንጃ ፈጥረው ፓርቲውን ቀውስ ውስጥ የከተቱት እነ ጌታቸው አሰፋና ሞንጆሪኖ በክልል የተወሰነ ጽንፈኛ ፓርቲ ይዘው ሊቀሩ ይችላሉ እየተባለ ነው። የሚኒስትሮች ምክር ቤት “ከሕጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ” ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፖለቲካ ቡድኖች መልሰው እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ለመመዝገብ የሚያስችላቸውን ድንጋጌ የያዘ የአዋጅ ማሻሻያን ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መራ። የሕጉ ዋና ዓላማ ትሕነግን ወደ ሕይወት ለማምጣት … [Read more...] about ትሕነግ ሕጋዊ ዕውቅና ተሰጥቶት ብልጽግናን ሊቀላቀል ይችላል ተባለ
ድምጽ ዓልባ እና ናፍጣም ሆነ ቤንዚን የማይጠቀም ጄኔሬተር የሠራው ኢትዮጵያዊ ወጣት
ፈዴሳ ሹማ ይባላል። ተወልዶ ያደገው በቄለም ወለጋ ሲሆን በከተማው ውስጥ በኤሌክትሪክ ጥገና ሙያውም ብዙዎች ያውቁታል፡፡ ሥራው ጥገና እንደመሆኑ የመብራት መጥፋትና መቆራረጥ ሥራውን ብዙ ጊዜ ያስተጓጉልበታል። ችግር ብልሃትን ይወልዳል እንዲሉ ወጣቱ መላ በመዘየድ ከብዙ ጥረት በኋላ አንድ ግዜ ቻርጅ ተደርጎ እስከ አንድ ዓመት ድረስ አገልግሎት መስጠት የሚችል ቴክኖሎጂ እውን አደረገ። ቴክኖሎጂውንም ይበልጥ አዘምኖ መሥራት ችሏል። ቴክኖሎጂው የመብራት አገልግሎት ከመስጠቱ ባለፈ ሞባይል፣ ለቴሌቭዥን፣ ፍሪጅና የትኛውንም ዓይነት የኤሌክትሮኒክስ መጠቀሚያዎችን ቻርጅ የሚያደርግ፣ የሚያንቀሳቅስና በገመድና ገመድ ዓልባ ቴክኖሎጂ መጠቀም እንዲቻል ተደርጎ የተሠራ ነው። አንዴ የያዘውን ኃይል ሪሳይክል እያደረገ ራሱን ቻርጅ ከማድረግ አልፎ ለረዥም ጊዜ ኃይል ማመንጨት የሚችለው … [Read more...] about ድምጽ ዓልባ እና ናፍጣም ሆነ ቤንዚን የማይጠቀም ጄኔሬተር የሠራው ኢትዮጵያዊ ወጣት
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. እና ኢትዮጵያ
ወደ ግንቦት 20ቀን, 1983 ዓ.ም. ከመግባታችን በፊት ትንሽ ወደ ኋላ መለስ በማለት የደርግ ስርዓትን በትንሹ እንቃኘው:: ደርግ የካቲት ወር 1966 ዓ.ም. የዘውድ አገዛዙን ስርዓት በመቃወም በአርሶ አደሩ ፣ በተማሪው ፣ በአስተማሪው ፣ በመንግስት ሰራተኛው ፣ በወዛደሩ ፣ በነጋዴው እና በመለዮ ለባሹ ወዘተ ፣ ወዘተ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ጊዜ ሳይወስድበት በ6 ወራት ውስጥ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ ግቡን መታ:: ህዝባዊ አመጹን የሚመራው የተደረጀ ፓርቲ ባለመኖሩ በር የተከፈተለት መለዮ ለባሽ አመቺ ሁኔታ በማግኘቱ በፍጥነት ተደራጅቶ ከተራ ወታደር ጀምሮ የተለያዩ ማእረግ ያላቸው አባላቱን አስመርጦ ወደ 120 የሚጠጉ ተወካዮቹን አዲስ አበባ በሚገኘው አራተኛ ክፍለጦር አሰባሰበ:: ከጦር ሃይሎች ፣ ከክቡር ዘበኛ እና ከፖሊስ የተውጣጡት እንኚሁ መለዮ ለባሾች በሰኔ … [Read more...] about ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. እና ኢትዮጵያ
የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች! “ክፋት” – በሁሉም መስክ!!
የዛሬ ስድስት ዓመት የግንቦት 20 መርዛማ ፍሬዎች በሚል ርዕስ በአምስት ተከታታይ ጽሑፎች የግንቦት 20ን አስራ አምስት መርዛማ ፍሬዎች አስነብ በን ነበር። ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር በማለት የሚጠራውና አሁን ምንም ዓይነት ሕጋዊ ማንነት የሌለው የበረሃ ወንበዴዎች ስብስብ የተከለው መርዛማ ዛፍ ያበቀላቸው መርዛማ ፍሬዎች አሁን ላይ በገሃድ የሚታዩ መሆናቸው ተረስቶ ትርክቱ ሌላ በሆነበትና በወያኔ በርበሬ የታጠኑ አንዳንዶች ትሕነግ ናፈቀን እያሉ ሲሰሙ ባለበት ጊዜ ይህንን ጽሑፍ መልሶ መቃኘት አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት ድጋሚ ታትሟል። ይህ የመጨረሻው ጽሑፍ ሲሆን ከዚህ በፊት የታተሙትን አራት ተከታታይ ጽሑፎች አንባቢያን እንዲያነቡ እንጋብዛለን። የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች! (ክፍል 1)የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች – የመሬት ነጠቃና ስደት (ክፍል … [Read more...] about የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች! “ክፋት” – በሁሉም መስክ!!
“ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ
በሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት። ከአርቡ ዓለም፣ ከአውሮፓ፣ ከአፍሪቃ፣ ሩሲያና አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ አካላት የሚዳክሩበት በዚህ ጦርነት የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ መገኘቱ ይፋ መሆኑን ተከትሎ አማራ ክልል ውስጥ ያሉ ታጣቂዎችን ከፍፍሏል። ትህነግ በድርጅት ደረጃ በውስጡ አለመጋባባት እንዳለበት፣ ከጊዜያዊ አስተዳደሩም ጋር ስምምነት እንደሌለው ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ዳዊት ከበደ አቶ ጌታቸው ረዳ “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል” ሲል ሚስጢር ያለውን ይፋ አድርጓል። በመረጃው ለምን አቶ ጌታቸው ብቻ ተለይተው በዚህ ጉዳይ ግንባር ሊሆኑ እንደቻሉ ወይም እንደተፈልገ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። በተደጋጋሚ እንደሚባለው ከራያ ወገን መሆናቸው ለያዙት ስልጣን ችግር … [Read more...] about “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ
ፌዘኛው ትሕነግ አንድም ታጣቂ የለኝም አለ
በሱዳን የተለያዩ የሰደተኛ ካምፖች፣ እንዲሁም በከተሞችና በተለዩ ሥፍራዎች የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትሕነግ) ያደራጃቸውና "ሳምሪ" የሚባሉ ታጣቂዎች መስፈራቸው በተደጋጋሚ ተገልጿል። በማስረጃና በመረጃ ወደ ሱዳን ማቅናታቸው ሲገለጽ ጎን ለጎን እነዚሁ ታጣቂዎች በማይካድራ ጭፍጨፋ፣ ከግብጽና ሱዳን ሰፊ ድጋፍ አግኝተው ራሳቸውን ለጦርነት እያዘጋጁ መሆኑ በተለያዩ አውዶች ሲገለጽ ነበር። ትሕነግ "የትግራይን ሕዝብ ነጻ አወጣለሁ" ብሎ ሲነሳ ጀምሮ ከሱዳን ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው እንደሆነ አባላቱና አመራሩ በኩራትና በውለታ ቆጣሪነት መስክረዋል። "ከአማራ ይልቅ የሱዳን ህዝብ ይሻለናል" በሚል በግልጽ ንግግርም ተደርጎ እንደነበር ይህ ትውልድ ያስታውሳል። ግንቦት ሃያ መቀሌ ሲከበር የቀድሞው የሱዳን መሪ አልበሽር የትሕነግን መለያ ለብሰው በበዓሉ ላይ እንደ ቤተሰብ ይጋበዙ … [Read more...] about ፌዘኛው ትሕነግ አንድም ታጣቂ የለኝም አለ
ማንን እንመን ትህነግን? ወይስ ያየነውን፣ የሰማነውንን በዓይናችን የመሰከርነውን?
ኢንተርፖል፤ የህወሃት ሳምሪዎች የማይካድራ ጭፍጭፋ ከቦኮሃራም የከፋ ነው February 4, 2021 11:10 am by Editor 2 Comments (Edit) በማይካድራ ሳምሪ በተሰኙ የተደራጁ ወጣቶች የተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ ቦኮሀራም ናይጄሪያ ላይ በተመሳሳይ ወር ከፈፀመው ወንጀል የበለጠ እንደሆነ ኢንተርፖል አስታወቀ። ዓለም አቀፉ የፖሊስ ትብብር ተቋም ኢንተርፖል በፈረንጆቹ የዘመን አቆጣጠር በወርሃ ህዳር 2020 ዓ.ም በመላው ዓለም የተፈፀሙ 10 አስከፊ የሽብር ጥቃት አስመልክቶ ሪፖርቱን አውጥቷል። እንደዚህ ሪፖርት ከሆነ በህወሃት ቡድን አደራጅነት ማይካድራ ላይ የተፈፀመው የጅምላ ግድያ ቦኮሃራምና ሌሎች የሽብር ቡድኖች በተለዩ ሀገራት ከፈፀሟቸው አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች በመብለጥ በርካታ ንፁሃን ሰዎች ህይወታቸውን ያጡበት ኢሰብዓዊ ድርጊት … [Read more...] about ማንን እንመን ትህነግን? ወይስ ያየነውን፣ የሰማነውንን በዓይናችን የመሰከርነውን?
Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAF
Sudanese warring party Rapid Support Forces has officially accused the Tigray People’s Liberation Front Fighters of fighting in Sudan in support of the Sudanese Armed Forces (SAF). Civil war broke out in Sudan in April last year involving Rapid Support Forces (RSF) led by Hamdan Dagalo and Sudanese Armed Forces (SAF) led by military chief Abdul Fattah al Burhan. Several regional and international players are involved in Sudanese civil war. Around a month ago, Sudanese military lodged a formal … [Read more...] about Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAF