• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ማንን እንመን ትህነግን? ወይስ ያየነውን፣ የሰማነውንን በዓይናችን የመሰከርነውን?

May 14, 2024 01:47 am by Editor Leave a Comment

ኢንተርፖል፤ የህወሃት ሳምሪዎች የማይካድራ ጭፍጭፋ ከቦኮሃራም የከፋ ነው

February 4, 2021 11:10 am by Editor 2 Comments (Edit)

በማይካድራ ሳምሪ በተሰኙ የተደራጁ ወጣቶች የተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ ቦኮሀራም ናይጄሪያ ላይ በተመሳሳይ ወር ከፈፀመው ወንጀል የበለጠ እንደሆነ ኢንተርፖል አስታወቀ።

ዓለም አቀፉ የፖሊስ ትብብር ተቋም ኢንተርፖል በፈረንጆቹ የዘመን አቆጣጠር በወርሃ ህዳር 2020 ዓ.ም በመላው ዓለም የተፈፀሙ 10 አስከፊ  የሽብር ጥቃት አስመልክቶ ሪፖርቱን አውጥቷል።

እንደዚህ ሪፖርት ከሆነ በህወሃት ቡድን አደራጅነት ማይካድራ ላይ የተፈፀመው የጅምላ ግድያ ቦኮሃራምና ሌሎች የሽብር ቡድኖች በተለዩ ሀገራት ከፈፀሟቸው አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች በመብለጥ በርካታ ንፁሃን ሰዎች ህይወታቸውን ያጡበት ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው፡፡

የህወሃት ቡድን አስታጥቆ እንዳሰማራቸው በተገለጸው ሳምሪ የተሰኙ የወጣቶች የጥቃት ቡድን በማይካድራ በፈፀሙት ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ 600 ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን በኢንተርፖል የሽብር ወንጀል መከላከል ዳይሬክቶሬት ያወጣው መረጃ ያሳያል።

ከሶስት ወራት በፊት በህዳር ወር ላይ ብቻ በተፈፀሙ የሽብር ወንጀሎች አፍሪካ ቀዳሚ ስፍራ ላይ መቀመጧን የጠቀሰው የኢንተርፖል መረጃ ንፁሃን ላይ ባነጣጠሩ የጅምላ ግድያ ወንጀሎች በርካታ ህይወት መቀጠፉን አስገንዝቧል።

የሽብር ቡድኖቹ ከሰብዓዊ ፍጡር በማይጠበቅ መልኩ ጭካኔ የተሞላባቸውን የጅምላ ጭፍጨፋዎች መፈፃማቸው የተገለፀ ሲሆን ከአፍሪካ በመቀጠል ደቡባዊ የእስያ አካባቢና ምስራቃዊ የሜዲትራኒያን ቀጠና የዚህ ሽብር ወንጀል ሰለባ መሆናቸው ተጠቁሟል።

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ወርሃ ህዳር ላይ ብቻ በተፈፀሙና በርካቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸውን ባጡባቸው የሽብር ወንጀል ድርጊቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገው የኢንተርፖል መረጃ በኢትዮጵያ ማይካድራ ላይ የተፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋና ናይጄሪያ ውስጥ ሜይጉዱሩ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ቦኮሃራም ያካሄደው ግድያ በሰብዓዊነት ላይ ከተፈፀሙ ከባድ የሽብር ወንጀሎች ቀዳሚ ተርታ ላይ መሰለፋቸውን ያሳያል።

“የማይካድራ ጭፍጨፋ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰብዓዊ፣ ስነልቦናዊ ቀውስና ጥልቅ ሀዘን ያስከተለ ነው” – ዶ/ር ዳንኤል

የተለያዩ ኢሰብዓዊ ዓላማዎችን ይዘው የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖች በንፁሃን ላይ የሚፈፅሟቸው ግድያዎች አሳሳቢ መሆናቸው በመረጃው ተጠቅሷል።

ከሶስት ወራት በፊት የንፁሃንን ህይወት የቀጠፉ የሽብር ወንጀሎች ከተፈፀሙባቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን፣ ናይጄሪያን፣ ሞዛምቢክን፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን፣ ሶማሊያን፣ ቡርኪናፋሶንና ቻድን የያዘችውን አፍሪካን በቀዳሚነት ጠቅሷል።

ከሌሎች የአለም ክፍሎች ደግሞ ከደቡብ እስያ አፍጋኒስታን፣ ከምስራቅ ሜዲትራኒያን ሶሪያን እንዲሁም ኢንዶኔዥያንና ኦስትሪያን አካቷል።

የሽብር ቡድኖ ቹ በእነዚህ ሀገራት በፈፀሟቸው አሰቃቂ የጅምላ ግድያዎች እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በህዳር ወር 2020 ዓ.ም ብቻ አንድ ሺ የሚጠጉ ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን ኢንተርፖል ያወጣው መረጃ ይጠቁማል።

ኢንተርፖል ያሰባሰበው የመረጃው ግኝት እንደሚያሳየው መንግስታዊ ባልሆኑ ታጣቂ ቡድኖች ከተፈፀሙ ጥቃቶች አራቱና በከፍተኛ ሁኔታ የንፁሃንን ህይወት የቀጠፉ የሽብርተኝነት ወንጀሎች በአፍሪካ፣ በደቡብ እስያ (በዋናነት በአፍጋኒስታን) በባህረ ሰላጤ አካባቢ ሀገራት በዋነኝነት በየመንና በምስራቅ ሚዲትራኒያን (በሶሪያ) የተፈፀሙ መሆናቸውንም አመላክቷል።

በኢትዮጵያ ሳምሪ የተሰኙ የህወሃት ቡድን ያደራጃቸው ሃይሎች ማይካድራ ላይ የፈፀሙትና በናይጄሪያ ቦኮሀራም የተፈፀሙት ኢ-ሰብአዊ ጭፍጨፋዎች ከሁሉም የከፋ እልቂት የተመዘገበባቸው የሽብር ወንጀሎች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኢንተርፖል የላከለትን መረጃ ዋቢ አድርጎ አድርሶናል፡፡ (ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

የማይካድራ ዕልቂት

November 12, 2020 04:03 am by Editor 1 Comment (Edit)

በምዕራባዊ ትግራይ ሁመራ አቅራቢያ «ማይካድራ» በተባለው አካባቢ የትግራይ ልዩ ኃይል ባልታጠቁ የአማራ ተወላጆች ላይ በሌሊት አሰቃቂ ግድያ መፈፀሙን ከሞት ያመለጠ የዐይን እማኝ ገለፀ። ጥቃቱ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው ሲል ደግሞ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ዐስታውቋል።

በምዕራባዊ ትግራይ ሁመራ አቅራቢያ «ማይካድራ» በተባለው አካባቢ የትግራይ ልዩ ኃይል ባልታጠቁ የአማራ ተወላጆች ላይ በሌሊት አሰቃቂ ግድያ መፈፀሙን ከሞት ያመለጠ የዐይን እማኝ ገለፀ። ጥቃቱ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው ሲል ደግሞ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ዐስታውቋል። ድርጊቱ የተጀመረውን ሕግ የማስከበር ሂደት ህወሓት ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲቀየር የዘየደው መላ ነውም ብሎታል። አንዳንድ የአማራ ክልል ነዋሪዎች የህወሓት የተስፋ መቊረጥ ስሜት ነው፤ ኅብረተሰቡ ህወሓት በዘየደው የብቀላ ሂደት እንዳይገባ አሳስበዋል። 

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ሰሞኑን ሁመራን ከተቆጣጠረ በኋላ ግስጋሴውን ወደ ማይካድራ ባደረገበት ወቅት ህዳር 1 ቀን፣ 2013 ዓ.ም አነጋጉ ላይ የትግራይ ልዩ ኃይል አካባቢውን በኃይል ተገፍቶ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ከመልቀቁ በፊት በአካባቢው የነበሩ የአማራ ተወላጅ በሆኑ ነዋሪዎችንና የቀን ሠራተኞችን በእለቱ ከሌሊቱ 9 ሰዓት ጀምሮ በየቤታቸው እየገባ በግፍ መጨፍጨፉን ከጥቃቱ አምልጦ አሁን አብደራፊ በተባለ ቦታ የሚገኝ የዓይን እማኝ ለዶይቼ ቬለ (DW) በስልክ ተናግሯል፡፡ 

ጥቃቱን ተከትሎ «እየሞትንም ቢሆን እናሸንፋለ» በሚል መግለጫ ያወጣው የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ እንዳለው «በማይካድራ የተፈፀመው ጭፍጨፋ አማራን መሰረት ያደረገ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው» ብሎታል፡፡ 

ድርጊቱ አሁን በትግራይ ክልል ሕግ ለማስከበር የሚደረገውን ትግል የእርስ በርስ ለማስመሰል ያደረገው ስልት ነው ሲልም ከስሷል፡፡ ፓርቲው ለአማራ ክልል ህዝብ ባስተላለፈው መልዕክት «…በተለመደው አስተዋይ ባህሪህ ምስኪኑ የትግራይን ህዝብ እንደ ትላንቱ ሁሉ ዛሬም ከየትኛውም ጥቃት ጥላ ከለላ ሆነህ ይህን ጊዜ እንድታሳልፈው ይሁን» ብሏል፡፡ 

አንድ የደብረማርቆስ ነዋሪ እንዳሉት ህወሓት ድርጊቱን የፈፀመው በአማራ ክልል በሚኖሩ የትግራይ ወንድሞችና እህቶች ላይ በቀል እርምጃ እንዲወሰድ ያዘጋጀው «ወጥመድ» እንደሆነና የእርስበርስ ግጭት ለመፍጠር እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ 

የእንጅባራ ከተማ ነዋሪውም ቢሆኑ ጥቃቱ የህግ ማስከበሩን ተግባር ወደ የእርስ በርስ ግጭት ለመግፋት የተደረገ ሴራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡  የደሴ ከተማ ነዋሪ እንዳሉት ደግሞ ህብረተሰቡ ራሱን ከስሜት ነፃ አድርጎ ህግ የማስከበሩን ሂደት በጥንቃቄ መከታተል አንዳለበት ጠቁመው ከበቀልና ከጥላቻ እንዲቆጠብ ጠይቀዋል፡፡ 

ከወንበዴዎቹ ጥቂቶቹ – አስመላሽ፣ ስብሃት እና አዲስአለም

የደቡብ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጥላሁን ደጀኔ በስልክ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ህብረተሰቡን ወደ ብስጭት በማስገባት አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳ ለማድረግ ነው ብለዋል፡፡ 

«የአማራና የትግራ ህዝብ ታሪክ የሰራ የተዋለደና ተመሳሳይ ስነልቦና ያለው ህብረተሰብ ነው» ያሉት አቶ ጥላሁን «ትግሉ ህገወጥ ቡድን» ካሉት አካል ጋር እንደሆነ አሰተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በስፍራው የሚገኘው የአማራ ቴሌቪዝን ዘጋቢ ከ100 በላይ የተገደሉ ሰዎችን አስከሬን መመልከቱን ለቴሌቪዥን ጣቢያው ዘግቧል፡፡ (ዶይቼ ቬለ (DW) 

የትህነግ ሰው በላ ቡድን በማይካድራ በንጹኀን ሰዎች ላይ ጭፍጨፋ ፈጽሟል።

የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ከሃዲው የትህነግ ቡድን ጦርነት ባወጀባቸው አካባቢዎች አቅንቶ ህግ የማስከበሩን እርምጃ ተመልክቷል።

ጦርነቱ ህገመንግስታዊ ስርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ እና የሃገር ክህደት በፈፀመው የትህነግ ቡድን ላይ ያነጣጠረ እንደሆነም ከትህነግ ቡድን ነፃ የወጣው ማህበረሰብ አረጋግጧል።

ነገር ግን ማይካድራ በመከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ በቁጥጥ ስር ከመዋሏ በፊት ጥቅምት 30/2013 ዓም ሌሊት በማይካድራ ህገወጥ ቡድኑ የፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል የቡድኑን በአማራ ህዝብ ላይ የለየለትን ጠላትነትና የድርጊቱን አስከፊነት ያሳየ ነበር።

በነበረው የተጠናከረ ጥቃት ሌሎች ይዞታወችን ለቆ ወደ ማይካድራ የገባው የትህነግ ጦር ይደርስበት የነበረውን ከፍተኛ ጥቃት ባለመቋቋሙ መሽጎበት የነበረውን የማይካድራ ይዞታ እንዲለቅም ተገዷል። ማይካድራም ከህገወጥ ቡድኑ ነፃ ሆናለች።

ይሁንና ቡድኑ ከዚህ ቀደም በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ይፈፅመው የነበረውን የተቀነባበር የሴራ ግጭትና የዜጎች ጭፍጨፋ በማይካደራም ፈፅሞታል። ሰው በላነቱን በአማራ እና በኢትዮጵያዊያን ላይ በተግባር አሳይቷል።

የትህነግ ዘራፊ ቡድን ዓላማ ማስፈጸሚያ የሆኑት ልዩ ሃይል እና ሳምሪ የተባለው ገዳይ ቡድን በማይካድራ ከተማ የሚገኙ ንጹኀን ሰላማዊ ዜጎችን በጂምላ ጨፍጭፏል።

አብመድ በቦታው በመገኘትም በሰው በላው  ትህነግ በርካታ ንጹኀን አማራዎች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን አረጋግጧል። በጥቃቱ  የሌሎች ብሔር ተወላጆችም ሰለባ እንደሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች  ተናግረዋል። (አብመድ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, Politics Tagged With: ethiopian terrorists, mycadra massacre, operation dismantle tplf, samri, tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule